Major Prophets Jeremiah

Jeremiah 1-2

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ New Covenant Jeremiah 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 602 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ነቢዩ ኤርምያስ የትንቢተ ኤርምያስ መፅሀፍት ፀሀፊ ነበር የተፃፈዉም ከክርስቶስ ልደት 627 -580 በፊት ነበር ፤ በተጨማሪም ኤርምያስ የሰቆቃዉ ኤርምያስ ፀሀፊ ነበር ፤ ከአምስቱ ታላላቅ ነቢያቶች አንዱ ነበር ፡፡

ኢሳይያስ ኤርምያስ ከያዘዉ ተስፋ በጥቂቱ የሚበልጥን ይይዛል ፡፡ ማክአርቱር ከሌሎቹ ነቢያቶች በይበልጥ ኤርምያስ ስለራሱ ህይወት እንደመዘገበ ተመልክቷል ፤ አገልግሎቱን፣ የተቃዋሚዎችን ምላሾች እና የግል ስሜቱን የገለፀ ነው ፡፡ የስሙም ትርጉም በእግዚአብሄር ላይ የተጣለ መሰረትን እንዳለው “ ጆሆቫ መወርወር “ ማለት ነው ፤ በተጨማሪም “ ጆሆቫ ይመሰርታል፣ ያፀድቃል እንዲሁም ይልካል “ ማለትም ነው ፡፡ ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን ኤርምያስን ሰባት ጊዜ ተጠቅሷል ፤ ለምሳሌ ዳን (9፡ 2) ኤርምያስን ጠቅሷል፡ “ በነገሰ በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል የኢየሩሳሌም መፍረስ የሚፈጸምበትን ሰባውን ዓመት እግዚአብሄር በቃሉ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረውን የዓመቱን ቁጥር በመጽሐፍ አስተዋልሁ “ ፤ ማቴ (2፡ 18) ኤርምያስን ጠቅሷል፡ “ ድምፅ በራማ ተሰማ ልቅሶና ብዙ ዋይታ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች መጽናናትም አልወደደችም የሉምና የተባለው ተፈጸመ “ ፡፡

ኢየሱስ የብሉይ ኪዳን መፈፀም ነበር፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ (ማቴ 5፡ 17) ፡፡ ብሉይ ኪዳንን የሚጠቅሱ የአዲስ ኪዳን ፀኃፊዎች ለኢየሱስ ተገቢነት ማረጋገጫን ይጨምራሉ ፤ ይህ ከኤርምያስ ቃላችን ጋር ይጣጣማል፡ አዲስ ኪዳን፡ “ እነሆ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባባት ወራት ይመጣል ይላል እግዚአብሄር ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸዉን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸዉ ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም ፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸ ኑምና እኔም ቸል አልኋቸው ይላል እግዚአብሄር ፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል እግዚአብሄር ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ በልባቸዉም እጽፈዋለሁ ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል “ (ኤር 31፡ 31-33) ፡፡ የዕብራዊያን ፀኀፊ “ አዲስ በማለቱ ፊተኛዉን አስረጅቶአል አሮጌዉና ዉራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል “ አለ (ዕብ 8፡ 13) ፡፡ ኤርምያስ አዲሱ ኪዳን በእግዚአብሄር ሕዝቦች ልብ ዉስጥ እንደሚሆን አወጀ ፡፡ በኤፌሶን ጳዉሎስ “ ክርስቶስ በልባቸዉ በእምነት እንዲኖር “ ፀለዬ (ኤፌ 3፡ 17) ፡፡

ኤርምያስ የካህኑ ኬልቅያስ ልጅ ነበር ፡፡ ይህ ልክ በ 2ነገ (22፡ 8) የሕጉን መፅሀፍት እንዳጠናው እን ኬልቅያስ አልነበረም ፤ ለቢኒያም በደረሰው እጣ ግዛት ዉስጥ ከኢየሩሳሌም ሰሜን ምስራቅ ሰዎስት ማይል ርቀት ላይ ከምትገኘው ከዓናቶት ነበር ፡፡ ባሮክ በሚባለዉ ፀሀፊም ተረድቷል፣ ኤርምያስ መልዕክቱየኤርምያስን ፅሁፎች በፃፈዉና በኃላፊነት በያዘው በባሮክ እንዲፃፍ አሳልፎ ሰጠ (ኤር 36፡ 4) ፡፡

ኤርምያስ “ አልቃሱ ኒቢይ “ በመባል ይታወቃል፡ “ ተወግተዉ ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ዉኃ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ ! “ (ኤር 9፡ 1) ፡፡ በዚህ መንገድ ኮንስታብል የኤርምያስ አገልግሎት ከኢየሱስ ጋር ትይዩ እንደ ሆነ ፅፏል ፡፡ በኢየሱስ ዘመን ሰዎች ኢየሱስ ኤርምያስ ሊሆን እንደሚችል አስበዋል፡ “ እርሱም ፡- አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው አሉ “ (ማቴ 16፡ 14) ፡፡ በቅርብ ስለሚሆነዉ የባቢሎን ወረራ የኤርምያስ ትንቢቶች እርሱን በደቡቡ መንግስት ዉስጥ መካከል ካሉት ሕዝቦች ዉስጥ ማንንም ወዳጅ አላሸነፉም ፡፡ ማክአርቱር “ የተዛተበት እንደ ነበር፣ ለህይወቱ እንደሞከረ፣ በማከማቻዎች/ባዶ ቤቶች ዉስጥ እንደተቀመጠ፣ ከንጉስ ኢዮአቄም እንዲሸሽ እንደተገደደ፣ በአደባባይ በኃሰተኛ ነቢያት እንደተዋረደ እና ወደ ጉድጓድ ዉስጥ እንደተወረወረ “ ፅፏል ፡፡

ኤርምያስ ከአምስት አስር አመታት በላይ ተንብዮአል ፤ አገልግሎቱ በንጉስ ኢዮስያስ በአስራ ሰዎስተኛዉ አመት (ከክርስቶስ ልደት 627 በፊት) በባቢሎን እስከመዉደቅ (ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት) በሁሉም መንገድ ይጀምራል፡፡ ማክአርቱር ኢየሩሳሌም በባቢሎን ከወደቀች በኋላ ኤርምያስ ከቅሬቶቹ ጋር ወደ ግብፅ እንደሸሸ ፅፏል ፡፡ ምንም እንኳን ወደ ግብፅ የሸሸ ቢሆንም በመጨረሻም/በኋላም ባቢሎናዊያን ግብፅንም ያዙአት ፡፡ አንድ ራቢኒክ ፅሁፍ ኤርምያስ ከክርስቶስ ልደት 561 በፊት የመፅሀፉን መዝጊያ ወደሚፅፍበት ስፍራ ወደ ባቢሎን በምርኮ ተወስዶ እንደ ነበር ያቀርባል ፡፡

ማክአርቱር በኤርምያስ ትንቢቶች ዉስጥ አራት ዋና ስዕሎችን ነገርችን አቅርቧል፡ “ 1) የሕዝቡን ኃጢዓት፣ 2) እግዚአብሄር የሚልካቸዉን ወራሪዎች፣ 3) የከበባዉ ዘመቻን እና 4) የጥፋት መቅሰፍቶችን “ ፡፡ ፍርድ የኤርምያስ (1-29) ዋና ጭብጥ ሲሆን ኤርምያስ (30-33) ደግሞ የመሲሁን የወደፊት መንግስትን ያሳያል ፡፡ አብዛኛዉን ኤርምያስ ስለ ፍርድ ቢያወራም “ ሁለተኛዉ ጭብጥ ግን ሕዝቡ ንስኃ የሚገባ ከሆነ ለማዳን እና ለመባረክ ስለ እግዚአብሄር ፍቃደኝነት ነው “ ፡፡

ትምህርት

ኤርምያስ (1፡ 1-3)፡ የመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ጥቅሶች ለኤርምያስ መግቢያን ይሰጣሉ ፡፡ አገልግሎቱ በኢዮስያስ የአገዛዝ ዘመን ጊዜ ጀመረ ፤ ኤርምያስ እና ኢዮስያስ የሆነ አይነት ግንኙነት ነበራቸዉ ምክንያቱም ኤርምያስ በኢዮስያስ የቀብር ስነ ስርዓት/ሞት ላይ “ ኤርምያስም ለኢዮስያስ የለቅሶ ግጥም ገጠመለት ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር “ ( 2ዜና 35፡ 25) ፡፡

ኤርምያስ (1፡ 4-10)፡ እነዚህ ጥቅሶች የኤርምያስን ምርጫን ይገልፃሉ ፡፡ እግዚአብሄር ኤርምያስን በእናቱ ማህፀን ከመቀመጡ/ከመፈጠሩ በፊት እንደ ነቢይ መረጠው(ቁጥር 5) ፤ “ አቤቱ አንተ ኩላሊቴን ፈጥረኃልና በእናቴም ሆድ ሰዉረኸኛል ፡፡ ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንኃለሁ ፤ ስራህ ድንቅ ነው ነፍሴም እጅግ ታዉቀዋለች ፡፡ እኔ በስዉር በተሰራሁ ጊዜ አካላሜ በምድር ታች በተሰራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም” (መዝ 139፡ 13-15)፡፡

እግዚአብሄር ኤርምያስን “ ለአሕዛብ ነቢይ “ እንዲሆን ለየው (ቁጥር 5) ነገር ግን ኤርምያስ በጣም ልጅ ነኝ በማለት ተቃወመ ፡፡ በዚህ ጊዜ ኤርምያስ ከ20-25 አመት አካባቢ ይሆን ነበር ፡፡ እግዚአብሄርም ኤርምያስ በእርግጠኝት ነቢዩ እንደሚሆን እና በኃላፊነቱ የፈራ እንዳይሆን አረጋገጠለት ፤ ማክአርቱር “ የኤርምያስን አገልግሎት የመለሰዉ ኃይል የእግዚአብሄር መገኘት እና ስጦታ እንደነበር “ አመልክቷል ፡፡

ኤርምያስ (1፡ 11-19)፡ እነዚህ ጥቅሶች የኤርምያስን ኃላፊነት ይይዛሉ ፡፡ የለዉዝ ዛፍ “ እንደ ንቁ ዛፍ ይታወቃል “ ምክንያቱም ከሌሎች ዛፎች በበለጠ ቀድሞ በጥር ስለሚፈካ /ስለሚያብብ ፡፡ እዚህ ጋር የእግዚአብሄር የቀደመ ፍርድ ምልክቶች ነበሩ ፡፡ በተጨማሪም ኤርምያስ የባቢሎንን ዛቻ/ማስፈራራትን የሚወክለዉን የሚፈላ አፍላል አዬ፡፡

መደምደሚያ

እግዚአብሄር ለይሁዳ እንዲናገር አዝዞት የነበረዉን ማስጠንቀቂያ በኤርምያስ በኩል ላከ ፡፡ እግዚአብሄር ፍርዱን እንዲናገር ለኤርምያስ ቃል እና ኃይልን እንደሚሰጠው ቃል ገባለት ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 844.

  2. MacArthur, p. 844.

  3. MacArthur, p. 844.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Study Notes: Jeremiah, p. 5; available from https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/jeremiah.pdf.

  5. MacArthur, p. 844.

  6. MacArthur, p. 84-845.

  7. MacArthur, p. 845.

  8. MacArthur, p. 847.

  9. MacArthur, p. 847.

  10. MacArthur, p. 848.

  11. MacArthur, p. 848.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር በኤር (1፡ 5) ስላለዉ ነገር በደንብ እስባችሁ ታውቃላችሁ ? ሳይሰራችሁ በፊት ያውቃችኋል ! ጥቂት ጊዜ በመዉሰድ ስለዚህ ጥቅስ አስቡ ፤ ለዚያ ተዓምራቱ የአለም ሁሉ አምላክ ይመስገን ፡፡
  2. በኤር (2፡ 13) ጌታ ምን እንዳለ አጥኑ ፤ ይህን ጥቅስ ለአንድ ለማያምን እንዴት ትገልፁለታላችሁ ? ጌታን ለመግለፅ በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ የሚወርድ የህይወት ዉሀ ጥቅም ላይ ዉሏል ? (ኤር 17፡ 13, ዘካ 14፡ 8-9)
  3. ጣዖትን ማምለክ በኤር (2፡ 14-37) ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል ፤ እስራኤልም እንዳልታመነች ሚስት ጋር ተነፃፅራ ነበር፡፡ በግል አስተያየታችሁ ይህ እና ሌሎች ታሪኮች ልክ እንደዚህኛው በታሪኩ ዉስጥ ደግመዉ ደግመዉ ለምንድን ነው የተደጋገሙት ?
  4. በኤርምያስ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Jeremiah 1:4–5

“The word of the LORD came to me: I chose you before I formed you in the womb; I set you apart before you were born. I appointed you a prophet to the nations.”

እግዚአብሔር ኤርምያስን ለአይሁድ ነቢይ ይሆን ዘንድ ጠራው ፡፡ ኤርምያስ ሁሉንም ምክንያት ለእግዚአብሔር አቀረበ ፤ ሆኖም ግን እግዚአብሔር እርሱን መረጠው ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ከኤርምያስ ጋር ይሆናል ፣ ይረዳዋል ደግሞም ፈጽሞ አይተወውም ፡፡ የሚናገረውንም ቃል እንደሚሰጠው ቃል ገባለት ፡፡

እንተስ እንደ ኤርምያስ አታደርግምን ? መንፈስ ቅዱስ ሲናገርህ ለምሳሌ ፡- ሂድና ያንን ሰው አናግረው ፣ ስራ ልቀቅ ወይም ስራ ቀይር ፣ በትህትና ተራመድ ደግሞም ይቅርታ ጠይቅ ሲልህ ፣ ይህንን ላለማድረግ ምክንያት ታቀርባለህ ታንገራግራለህን ? አረ ጌታ ሆይ አይሆንም ፣ እኔኮ ልጅ ነኝ ፡፡ አረ አይሆንም ጌታ ሆይ ፣ እኔኮ ልምድ የለኝም ፡፡ አረ አይሆንም ጌታ ሆይ ፣ ይህን ማድረግ የሚችሉ ብዙዎች አሉ ፡፡ አረ አይሆንም ጌታ ሆይ ፣ አኔኮ ብዙ ጊዜ ወደቄለሁ አጥፍቻለሁ ፡፡ ሆኖም ግን አውነቱ እግዚአብሔር ለሆነ ነገር ሲጠራህ ፣ ትልቅ የህይወት ክስተት ወይም የሁልጊዜም ለውጥ ተግባር ቢሆን እንኳ ይሁን ፣ ይህ ለእግዚአብሔር ፣ ለእርሱ እቅድ እናም ለእርሱ ህዝብ አስፈላጊ ነው ፡፡ አስታውስ እርሱ መርጦሃል ፡፡ እርሱ ሾሞሃል ፡፡ እርሱ እንደዚህ ላለ ጊዜ ለይቶሃል ፡፡ ስለዚህም እርሱን ታዘዝ ፡፡ ከአንተ ጋርም እንደሚሆን እመን ፡፡ መንፈስ ቅዱስም እንድትናገር ቃልን በአፍህ ያስቀምጣል ፡፡ መልካም ይሆናል ፤ ለእርሱ ክብርን ስጠው ፡፡ በእግዚአብሔር ታመን ፡፡

“ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ ። በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ ። “

  • ኤርምያስ 1፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 139:13–16 — “ አቤቱ ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና ፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ፤ ሥራህ ድንቅ ነው ፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች ። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ። ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ ። “

ኤርምያስ 1:6–9 — “ እኔም ። ወዮ ጌታ እግዚአብሔር ፥ እነሆ ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ ። እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ ። ወደምሰድድህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና ፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና ። ብላቴና ነኝ አትበል ። እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና ከፊታቸው አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር ፦ እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ ፥ እግዚአብሔርም ፦ እነሆ ፥ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ ፡፡ “

ሉቃስ 12:12 – “ መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና ። “