Major Prophets Isaiah

The Established People

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 65-66 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 601 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኢሳይያስ የመጨረሻዉ ግብ ለእኛ ተስፋን መስጠት ነው ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ ሁልጊዜ ልጁን አማኑኤልን መላክ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ ስለ እስራኤል በአሶራዊያን እና በባቢሎናዊያን ስለ መማረካቸው ትንቢትን ሲናገር በመጨረሻ ነገሮች ለእግዚአብሄር ሰዎች የተሸሉ እንዲሚሆኑ እዉነታዉን አመለከተ ፡፡ ይህ በዚህ በምድር ላይ አይሆንም በሰማይ ላይ እንጂ ፡፡

የኢሳይያስ የመጀመሪያዎቹ 39 ምዕራፎች በፍርድ የተሞሉ ናቸው ፤ የመጨረሶቹ 27 ምዕራፎች ደግሞ በበረከት፣ በቤዛነት፣ በመፅናናት እና በነፃ መዉጣት የሚገለፁ ናቸው ፡፡ በዚህ መንገድ ኢሳይያስ የአጠቃላይ የመፅሀፍ ቅዱስ ትንሽ ማሳያ /መወከያ ነው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ 39 ምዕራፎች ብሉይ ኪዳንን ሲወክሉ የመጨረሻዎቹ 27 ምዕራፎች አዲስ ኪዳንን ይወክላሉ ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (65፡ 1-16)፡ እግዚአብሄር እርሱን ለማግኘት ለሚጓጉት ሰዎች ራሱን የሚገኝ አደረገ ፡፡

ኢሳይያስ (65፡ 17-25)፡ እግዚአብሄር አዲስ ሰማይን እና አዲስ ምድርን በመፍጠር ሁሉንም ነገር እንደሚያደስ ተስፋን ገባ ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ያድሳል ፡፡ ኮንስታብል ከእነዚህ ለዉጦች ጥቂቶቹ በሺሁ አመት ዉስጥ እንደሚከሰቱ ያመለክታል ፤ ሚሊኒየሙ/ሺሁ አመት ከሰባት አመቱ መከራ በኋላ የኢየሱስን የ1000 አመት ዘመን ነው ፡፡

ኢሳይያስ (66፡ 1-6)፡ እግዚአብሄር ትሁት፣ መንፈሱም ወደ ተሰበረ እና በቃሉ ወደ ሚንቀጠቀጡ ሰዎች እንደሚመለከት ቃልን ይገባል (ቁጥር 2) ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ልክ እንደ ጣዖት አምልኮ አይነት ከሚሰራ ሰዉ ጋር የተነፃፀረ ነው (ቁጥር 3) ፡፡ ማክአርቱር “ ለእግዚአብሄር መስዋዕትን በግብዝነት የሚያቀርቡ ነገር ግን ልጆቻቸዉን ከሚገድሉ፣ ዉሻን ከሚሰዉ፣ የእሪያ ደም ከሚያፈሱ፣ ጣዖትን ከሚባርኩ እና ጥላቻን ከሚወዱ ጣዖት አምላኪዎች ይበልጥ ልባሰዉ ያልሰተሰበረዉን ፤ እግዚአብሄር እንደዚህ አይነቶቹ ላይ እንደሚፈርድ “ አግልቶ ያሳያል ፡፡ ከሚቀርብ መስዋዕት ይል በእግዚአብሄር ፊት መዋረድ አስፈላጊ/ጠቃሚ ነው ፡፡ እንደ ገና ማክአርቱር “ እግዚአብሄር ቃሉን በሚገባ በሚሰሙት ልብ ዉስጥ ለማደር እንደሚመለከት “ ይፅፋል ፡፡

በሺኅ አመቱም እንኳን ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል ያለማክበር መምረጠ ነፃ ፍቃድ ይኖራቸዋል ፤ ቁጥር 5 በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ በሚያፌዙ ሞኞችይገልፃል ነገር ግን እግዚአብሄር በመጨረሻ ላይ እነዚህ ሞኞች የሚገባቸዉን እንደሚያገኙ ተናገረ (ቁጥር 6) ፡፡

ኢሳይያስ (66፡ 7-9)፡ ቁጥር 7 ከማማጥ በፊት ህፃን የወለደችዉን ፂዎን የሆነችዉን ኢየሩሳሌምን ይገልፃል ፡፡ ኮንስታብል ይህን ከመከራዉ በፊት የመሲሁ መልክ ሊሆን እንደሚችል ያቀርባል ፤ ማክአርቱር በቁጥር 7 ከመዉለድ ምሳሌዎች ዉስጥ ሊለቀሙ የቻሉ ሁለት ትምህርቶችን ይፅፋል፡ “ 1) የምጥ ህመም ሳይሰማ መዉለድ ሊመጣ አይችልም (ቁጥር 7-8) እና 2) ምጥ በሚሆን ጊዜ መዉልድ በእርግጠኝነት ይከተላል (ቁጥር 9) “ ፡፡ ከምጥ በፊት የመዉለድ ምስል የእግዚአብሄር ድርጊት በድንገት እንደሚመጣ ያመለክታል ፡፡

ዳን (11፡ 40-45) የአርማጌድዮን ጦርነትን ይስላል “ በፍጻሜዉ ዘመን የደቡብ ንጉስ ከእርሱ ጋር ይዋጋል ፤ የሰሜንም ንጉስ ከሰረገሎችና ከፈረሰኞች ከብዙም መርከቦች ጋር እንደ ዐዉሎ ነፋስ ይመጣበታል ፤ ወደ አገሮችም ይገባል ይጎርፍማል ያልፍማል ፡፡ ወደ መልካሚቱም ምድር ይገባል ብዙ አገሮችም ይወድቃሉ ፤ ነገር ግን ኤዶምያስና ሞዓብ ከአሞንም ልጆች የበለጡት ከእጁ ይድናሉ ፡፡ እጁን በአገሮች ላይ ይዘረጋል የግብፅም ምድር አታመልጥም ፡፡ በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ በከበረችም በግብፅ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሰለጥናል ፤ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል ፡፡ ከምስራቅ እና ከሰሜን ግን ወሬ ያዉከዋል ፤ ብዙ ሰዎችንም ይገድል ዘንድና ፈጽሞ ያጠፋ ዘንድ በታላቅ ቁጣ ይወጣል ፡፡ ንጉሳዊ ድንኳንኑም በባሕርና በከበረው በቅዱሱ ተራራ መካከል ይተክላል ፤ ወደ ፍጻሜዉ ግን ይመጣል ማንም አይረዳዉም “ ፡፡

ኢሳይያስ (66፡ 10-13)፡ እግዚአብሄር ለኢየሩሳሌም እንደ ምንትከባከብ ሞግዚት እና ለአዲስ ህፃን እንደምትጠነቀቅ እና መፅናናትን እንደሚሆንላት ተስፋን ሰጣት ፡፡

ኢሳይያስ (66፡ 14-16)፡ ማክአርቱር “ ብልፅግና ለታመኑት ቅሬቶች እንደሚሆን እግዚአብሄርን ለሚቃወሙት ደግሞ መዓት እንደሚሆንባቸው “ ያቀርባል ፡፡ መንግስቱን ሊመሰርት በመጣ ጊዜ ብዙዎች ከጌታ ጋር ይዋጋሉ ፡፡

ኢሳይያስ (66፡ 17-24)፡ የአይሁድ የቀሩት ቡድኖች በአሕዛብ መካከል ወንጌልን ይሰብካሉ (ቁጥር 19) ፡፡ ከተመለሱት ቅሬታዎች ዉስጥ አንዳንዶቹ በአዲሱ ቤተ መቅደስ ዉስጥ እንደ ካህናት እና ሌዋዊያን ያገለግላሉ (ቁጥር 21) ፡፡ የአማኑኤልን መልዕክት አለመያዝን ለመረጡት ሰዎች “ ትላቸዉ በፍፁም አይሞትም “ (ቁጥር 24) ፡፡ ማክአርቱር “ የማያቆም ዘላለማዊ ስቃይን የሚሸከሙት ሙታኖች ለፅኑ/ለኃይለኛ ተፈጥሮ እና በእግዚአብሄር ላይ ለሆነ አደገኛ አመፅ ዉጤት እንደ ግልፅ ማስታወሻ ማሳያ ያገለግላሉ “ በማለት ያመለክታል ፡፡ ይህ በመልካም ፅሁፍ አያበቃም !

መደምደሚያ

አሁን፣ በአርማጌድዮን ጊዜ ወይም በሺህ አመቱ ጊዜም ቢሆን ከእግዚአብሄር ዉጪ እንዳትሄዱ (ማን እንደሆናችሁ መንፈሳችሁም ) ዘላለማዊ እሳት እና መከራ ለዘላለም እስከ ዘላለም ትሆናላችሁ ፡፡ እርሱን ማምለክ በምንችለበት በኩል መሆን እንፈልጋለን እንጂ በመከራዉ /በስቃዩ መሆን አንፈልግም ፡፡ ይህ ከአንዲ ነቢይ ብቻ ሲሆን ነገ በሌላ ነቢይ እንጀምራለን !

.

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 452; available from http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 842.

  3. MacArthur, p. 842.

    MacArthur, p. 842.

  4. Constable, p. 461.

  5. MacArthur, p. 842.

  6. MacArthur, p. 843.

ጥያቄዎች

  1. በኢሳ (65፡ 1) እግዚአብሄር ለማን አመለከተ (ሮሜ 9፡ 24-26, 30, 10፡ 20) ? አሕዛቦች (እኛ) በአጠቃላይ የእግዚአብሄር እቅድ ድርሻ አለን ፤ ያ እንዴት ያበረታታችኋል ?
  2. ኢሳይያስ የእግዚአብሄርን አገልጋዮች እግዚአብሄር በጠራቸዉ ጊዜ ከማይመልሱት ጋር እንዴት አነፃፀረ ? (ኢሳ 65፡ 12-15)
  3. ኢሳ (65፡ 17-19) አዲስ ሰማይን እና አዲስ ምድርን ያመለክታል ፤ 2ጴጥ (3፡ 13) እና ራዕ (21፡ 1-4) አንብቡ ፡፡ እግዚአብሄር በባቢሎን ምርኮ ለነበሩት ሕዝቦቹ ይህ መረጃ ለምን እንደገለጠላቸው ምን ታስባላችሁ ? (ኢሳ 66፡ 22)
  4. በኢሳ (66፡ 2) እግዚአብሄር ትሁት መንፈሱ ወደ ተሰበረ እና በቃሉ ወደሚንቀጠቀጥ ሰዉ እንደሚመለከት ይናገራል (መዝ 51፡ 17) ፤ ይህ እናንተን እንደሚገልፃችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  5. ኢሳ (66፡ 24) አንብቡ ፤ ይህ ጥቅስ ምን ይገልፃል (ማር 9፡ 45-48) ? ይህ ግልፅ ስፍራ ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ? አዎ ከሆነ ያ እንዴት ተፅዕኖ ያደርግባችኋል ?
  6. በኢሳይያስ (65-66) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 66:18–19

“Knowing their works and their thoughts, I have come to gather all nations and languages; they will come and see My glory. I will establish a sign among them, and I will send survivors from them to the nations—to Tarshish, Put, Lud (who are archers), Tubal, Javan, and the islands far away—who have not heard of My fame or seen My glory. And they will proclaim My glory among the nations.”

ኢሳይያስ ለህዝቡ የሚናገረውን ትንቢት ከእግዚአብሔር ወደፊት ስለ ሚሆነው ነገር አዋጅን በመናገር ፈጸመ ፡፡ አዎን ፣ የእግዚአብሔር እጅ በኢየሩሳሌም ላይ ነበረች ፡፡ አዎን ፣ እግዚአብሔር በአህዛብ ላይ ይፈርዳል ከእርሱም ጋር ያልተራመዱትን ይቀጣል ፡፡ ሆኖም ግን በመጨረሻ ፣ የእግዚአብሔር ልብ ስለ ክብሩ ሲል ለአህዛብ ተስፋን ይሰጣል ፤ ስለዚህም ሁሉም ስሙን ያውቃሉ ፡፡ እግዚአብሔር በትህትና የሚራመዱትን ደግሞም በመንፈሳቸው የሚታዘዙትንና ቃሉንም የሚፈሩትን እነዚህን ይሻል ፡፡ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የተመለሰን ልብ ደግሞም የእግዚአብሔርን ክብር በትውልድ መካከል የሚናገርን ሰው ያደምጣሉ ፡፡

ዛሬ ራሳችሁን ሶስት ጥያቄዎች ጠይቁ ፡-

  • እግዚአብሔርን በትህትና እፈልጋለሁን ? ( የትህትና ታቃራኒው ትዕቢት ነው )
  • ለእግዚአብሔር ድምጽ እታዘዛለሁን ? ( ወይስ የባህልን ፣ የዓለምን ወይም የጠላትን ድምጽ ነው የምሰማው ? )
  • የእግዚአብሔርን ቃል እፈራለሁን ?

በጌታ ለማደግ ፣ ቃሉን አንብቡ ከዚያም ለቃሉ ታዘዙ ፡፡ እግዚአብሔር ትህትናን ፣ ለእርሱ መታዘዝንና ቃሉን መፍራትን ይወዳል ፡፡ እናንተም ክብርን ትሰጡታላችሁ ደግሞም ዓለም ሁሉ የእርሱን ታላቅ ስም ያውቃል ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል ፡፡

“ ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና አሕዛብንና ልሳናትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል ፥ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ ። በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ ፥ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ ። “

ኢሳይያስ 66፡18-19

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘፍጥረት 15:5–6 — “ ወደ ሜዳም አወጣውና ፦ ወደ ሰማይ ተመልከት ፥ ከዋክብትንም ልትቈጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ቍጠር አለው ። ዘርህም እንደዚሁ ይሆናል አለው ። አብራምም በእግዚአብሔር አመነ ፥ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ። “

መዝሙር 96:1–3 — “ ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ ። ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ ፡፡ “

ኢሳይያስ 66:2 — “እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ ። “