Major Prophets Isaiah

Zion's Restoration

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 62-64 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 600 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኢሳይያስ 60 ኢሳይያስ ወደ ፍሬ አማነት መጥተዉ ስለ ነበሩ ነገሮች እያወራ እንደ ነበር ይመስላል ፤ ከትርምስ/ከአደጋ በኋላ - ለዉጥ እና ተስፋን ስለሚያዩ በፂዎን መልካም ነገር እንደሚሆን አወራ ፡፡ በመቀጠልም በምዕራፍ 61 ኢሳይያስ በዚያ ማና እንደሚረዳ ለይቷል ፡፡ ቶም ኮንስታብል በምዕራፍ 62 እስራኤል ከባቢሎን ግዞት በወጣ ጊዜ ሕዝቡ እግዚአብሄር ተስፋ ገብቶላቸዉ የነበረዉን ሁሉንም ነገር እንደሚፈፅምላቸዉ እርግጠኞች መሆን እንደሚችሉ ያመለክታል ፤ ኢሳይያስ 62 እግዚአብሄር ይህን እንደሚያደርግ ማረጋገጫ ነው ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (62፡ 1-5)፡ በእነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሄር እየተናገረ ነው ፡፡ ለፂዎን/ለኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ግብ/አላማ ፅድቋ እንደ ፀዳል በመብራት (ቁጥር 1) አሕዛቦች የእግዚአብሄር እጅ በእርሷ ላይ እንደ ነበር እንዲያዉቁ ነበር (ቁጥር 2) ፡፡ ኢሳይያስ (13-23) በአሕዛብ ላይ የፍርድን ሸክሞች መናገሩን እናስታዉሳለን ፤ አሁን አግዚአብሄር እነዚህ ሕዝቦች በፂዎን ላይ እየሆነ የነበረዉን ነገር ማየታቸዉን እርግጠኛ መሆን ፈለገ ፡፡ ኢየሩሳሌም የእስራኤልን ሁኔታ የሚገልፅ አዲስ ስም ይኖራታል (ቁጥር 2) ፡፡ ፂዎን ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት ባቢሎን ይዛቸዉ ስለ ነበር ምድረበዳ እና ባድማ ተብላ ተጠርታ ነበር (ቀጥር ) ፡፡ አንዱ አዲስ ስም “ ደስታዬ በአንቺ ነው “ ሲሆን ሌለኛዉ ደግሞ “ ያገባች “ የሚለዉ ነው ፤ ይህ የሚያምር/ሚስጥራዊ የሆነ መልክ ነው ፡፡ ኢሳ (61፡ 10) እግዚአብሄር ለፂዎን “ የማዳንን ልብስ “ እና “ የጽድቅን መጎናፀፊያን “ አዲስን ልብስ እንደሚሰጣት ይገልፃል ፡፡ በዘፍ (17፡ 5) የአብራም ስም ወደ አብርሐም በመቀየር የማንም አባት ካልሆነዉ አብራም ወደ ብዙ አብት ወደ ሆነዉ አብርሐም ሄደ ፤ በዘፍ (32፡ 28) የያዕቆብ ስም ወደ እስራኤል ተቀይሯል ፡፡ አሁን የእስራኤል ስም ከምድረበዳ እና ከባድማ በእርሷ ያስደሰተች እና ያገባች የተቀየረ ይሆናል ፡፡ ቁጥር 12 ቅዱስ ሕዝብ፣ የተቤዣቸው፣ የተፈለገ እና ባድማ ያልሆች የሚሉትን ስሞች ይጨምራል ፡፡

የእግዚአብሄር እጅ በእስራኤል ላይ ይሆናል ምክንያቱም በእርሷ ስለተደሰተ (ቁጥር 4) ፡፡ የገባ የሚለዉ ስዕል ፍቺ እንደ ነበር አያመለክትም ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር እና አሕዛቦች እንደታረቁና አንድ እንደሆኑ ያመለክታል ፡፡ እስራኤል በእግዚአብሄር እጂ “ የክብር አክሊል “ ትሆናለች (ቁጥር 3) ፤ እስራኤል የክብርን አክሊል አትቀበልም የክብር አክሊል ትሆናለች እንጂ ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢየሩሳሌም ባድማ /ምድረበዳ አትሆንም - ያ ማለት ቃሉ የተረሳች አትሆንም ማለት ነው - ነገር ግን እግዚአብሄር በእነርሱ ደስ ይለዋል (ቁጥር 5) ፡፡ ባድማ እና የተረሱ እንደሆነ ቢሰማቸዉም እግዚአብሄር ግን በፍፁም አልተዋቸዉም ነበር ፤ ዕብ (13፡ 5) የኢሳይያስ 62 መልክ ነው ምክንያቱም እግዚአብሄር ሕዝቡን እንዳልረሳ የሚያጠቃልል ስለሆነ ፡፡ ይልቁንም እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ ይወዳቸዋል - እንዲሁም ሙሉ ለሙሉ ይወደናል ፡፡

ኢሳይያስ (62፡ 6-9)፡ እስከዚህ ስፍራ ድረስ በእስራኤል በጎቹን ያልጠበቁ ኃሻባቸዉ ያልተቀየረ ጎበኞች ነበሩ ፤ ነገር ግን አሁን እግዚአብሄር ተጨማሪ ብዙ ጉበኞችን እና ነቢያቶችን እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ያለማቋረጥ እንዲያዉጁ እንደሰጣቸዉ ይነግራቸዋል (ቁጥር 6) ፡፡ በእንግዶች፣ በክፉዎች እና በእንስሳትም እንኳን ያሉ ድሎች ሁሉ አሁን የተፈፅመዋል ፤ ያ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ የገዙ አገዛዞች ተፈፅመዋል (ቁጥር 8) ፡፡ በዚያ ፋንታም የሰበሰቡትን እህል ይበላሉ ከወይን ፍሬዉም ይጠጣሉ (ቁጥር 9) ፤ ዮሐንስ ማክአርቱር “ ቅዱስ ፍርዴ “ በሚለዉ ሀረግ ዉስጥ ያለዉ ቤተ መቅደስ እንደ ሺህ ዘመኑ ቤተ መቅደስ ጋር ያስተካክላል ፡፡

እስከዚህ ስፍራ ድረስ የእግዚአብሄር ግብ ለሁሉም ሕዝብ በኢየሩሳሌም ስራ ላይ እእዚአብሄርን እንዲያዩ ነበር ፡፡ በዚህ ሂደት ዉስጥ በኢሳይያስ 56 አሕዛቦች ጌታን ሲያመልኩት አይተናል ፤ አይሁዶች እና አሕዛቦች ሁለቱም በቤተ መቅደሱ ወይም በቤተ መቅደሱ አደባባይ ዙሪያ የማምለክ እድል ይኖራቸዋል ፡፡ ኢሳይያስ ይህን በፃፈበት ጊዜ የሰለሞን ቤተ መቅደስ ነበር ፤ ያ ቤተ መቅደስ እስራኤላዊያን ወደ ምርኮ በተወሰዱ ጊዜ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በባቢሎናዊያን ጠፋ ፡፡ ስለዚህ ሰዎች በእግዚአብሄር ቅዱስ አደባባይ ወይን መቼ ይጠጣሉ ? ከክርስቶስ ልደት 539 በፊት ንጉስ ቂሮስ ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ እንዲገነቡ እስራኤላዊያንን እንደሰደዳቸዉ እናዉቃለን ፡፡ ኢሳይያስ ሁለተኛዉ ቤተ መቅደስ በሚኖርበት ጊዜ ማዉራት ችሏል ፤ ይህ ቤተ መቅደስ አንዳንድ ጊዜ ከክርስቶስ ሞት 70 በኋላ በሮማዊያን የጠፋው የዘሩባቤል ቤተ መቅደስ በመባል ይጠራል ፡፡ አሁንም በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የለም ፡፡ ኢየሱስ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መጥፋትን በማቴ (24፡ 1-2) ተንብዮታል ፤ በማቴ (24፡ 15) ኢየሱስ “ እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለዉን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችዉ ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢዉ ያስተዉል “ በማለት አስጠንቅቋል ፤ ይህ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ በቅዱሱ ስፍራ ማለትም አሁን በሌለዉ በሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ የሚቆምበትን ጊዜ ያመለክታል ፤ ስለዚህ ሰዎስተኛ ቤተ መቅደስ እንደሚኖር እናዉቃለን ፡፡ ራዕ (11፡ 1-2) በሆነ ጊዜ ስለሚሆነዉ ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ ያወራል ፤ በአሁኑ ጊዜ በእስራኤል ለሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ መልሶ ግንባታ የሚጣሩ ፖለቲከኞች አሉ ፡፡ የቤተ መቅደሱ ተቋም እቃዎች እና በሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ ዉስጥ ለመቀመጥ የተዘጋጁ እቃዎች አሉ ፤ በእስራኤል የእስራኤል ሽማግሌዎች መልሶ የተቋቋመ ሲሆን አንዱ አላማዉ ቤተ መቅደሱን መልሶ መገንባት ነው ፡፡ ክርስቲያኖች ለዚህ ለምንድን ነዉ ማሰብ/ማገዝ ያለባቸው ? መጀመሪያዉ በራዕይ ዉስጥ ስለሆነ ፤ ሁለተኛው ክርስቶስ ተመልሶ ስለሚመጣ ፤ ሰዎስተኛዉ በዚያ የማምለክ ድርሻ ስላለን ፡፡ ስለዚህም ይህ “ በቅዱስ ስፍራዬ “ የሚለዉ ትንሽ ሀረግ የመጨረሻዉ መልክ ነዉ በተጨማሪም ሰዎች በአንድ ላይ በቅዱሱ ቤተ መቅደስ በአንድ ላይ ያመልካሉ ፡፡

ኢሳይያስ (62፡ 10-12)፡ በተግባር የሚናገረው ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም መልሶ መገንባት እንደሚያስፈልዉ ነው ፡፡ ብዙ ሰዎች ቤተ መቅደሱ በአሁኑ ስዓት የአለት ዶም ወይም የአላስካ መስጊድ በሚገኝበት ስፍራ ላይ መቀመጥ ያስፈልገዋል ይላሉ ፡፡ ቁጥር 10 እስራኤል እና አሕዛቦች ለክርስቶስ መመለስ የተዘጋጁ እንዲሆኑ እንዳስብ ያደርገኛል ፤ መንገዱ ግልፅ ወይም ስዕላዊ ቢሆንም ግባችን ለኢየሱስ ተመልሶ መምጣት መንገዶን ማዘጋጀት ነው ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ ገለፃ “ መንገዱን ማዘጋጀት ማለት ለማምለክ ሰዎች ወደ ቤተ መቅደሱ እንዲመጡ ማበረታታት ማለት ነው….ሰንደቀ አላማን ማንሳት እግዚአብሄርን እንዲያመልኩ ለሁሉም ሕዝቦች ማበረታቻ ነው “ ፡፡

በቁጥር 11 የሚባልበት የዕብራዊያን ቃል በትክክል ብዙሀነት ነው ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ መሰረት ብዙኃነት ከመሆኑ የተነሳ “ ብዙ ሰዎች ይህን የድነት መግለጫ ለኢየሩሳሌም እንደሚያዉጁት ያመለክታል “ ፤ በመጨረሻም ኢየሱስ መንገድ ነዉ የሚሉ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ቅሬታ ስለሆኑ የኢየሱስን መምጣት ያውጃሉ ፡፡ ይህን ጥቅስ በማቴ (21፡ 9) በኢየሩሳሌም ሕዝቡ “ ሆስዓና ለዳዊት ልጅ ! “ በማለት መጮህ ከጀመሩት መልዕክት ጋር አወዳድሩት ፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ይጠብቁት እንደ ነበረዉ ልክ እንደመሲህ ስላልመጣ እንደ ጌታ እና አዳኝ አልተቀበሉትም ፡፡ ዘካ (9፡ 9) የእስራኤል ድነት በአንድ አህያ ላይ ጋልቦ በሚመጣ ፃድቅ ንጉስ ይስለዋል ፤ ይህ ጥቅስ ስለ መጀመሪያዉ መምጣት የሚናገር ከሆነ አይሁዶች ደግሞ ኢየሱስን ስላልተቀበሉት አሁን ሁለተኛ እድል ያስፈልጋቸዋል ፤ ስለሆነም ኢሳይያስ ስለመጀመሪያዉ መምጣት እና ስለ ሁለተኛዉ መምጣት ተናግሯል ፡፡ ሰዎችን እርሱን ለማምለክ የሚጋብዙ ቅሬታዎች አሁንም እንዳሉ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡

መደምደሚያ

የመጣዉን ድነት ከያዝን የተቤዣችሁ እንደሆነ መረዳት ስለምትችሉ በቅድስና ትላለሳላችሁ ፡፡ ሰዎችን ክርስቶስን እንዲያመልኩ “ አይሆንም ” በማለት በሚመልሱ ጊዜ ሰንደቅን በመያዝ መፅናት አስቸጋሪ ነገር ነው ፡፡

የኢሳይያስ መፅኀፍት በስደት/በግዞት ሄደዉ ለነበሩት እና ነፃ ለሚወጡት ተናግሯል ፡፡ በግዞት ለመጀመሪያ ጊዜ ኢየሱስ እንደ መጣ መመልከት ያስፈልጋቸዋል ፤ ያ በሆነ ጊዜ ከእነርሱ ዉስጥ ሁሉም እርሱን አይዙትም (ዮሐ 1፡ 10) ፡፡ አሁን ኢየሱስን ለያዙት ሁለተኛ መምጣቱን እንጠብቃለን ፤ ያ ሲሆን አይሁዶች እና አሕዛቦች በአንድ ላይ በመሆን ትኩረታቸዉ በተቀባዉ በአማኑኤል እግዚአብሄር ከኛ ጋር ነዉ በሚለዉ ላይ ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ የአምልኮ በዓል ይኖራል ፡፡

  1. Thomas Constable, “Dr. Constable’s Notes on Isaiah,” p. 432; available from http://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  2. John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 838.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 871.

  4. Nelson’s Commentary, p. 871.

ጥያቄዎች

  1. ኢሳ (62፡ 1-2) ስለ ፂዎን እና ኢየሩሳሌም ፅድቅ ሲያወራ መዝ (14፡ 1, 3) “ ማንም መልካም አያደርግም “ ይላል ፤ ማንኛዉንም ሰዉ እንዴት እንደ ፃድቅ ሊታይ ይችላል ? (ኢሳ 61፡ 10-11, ፊል 1፡ 11, 3፡ 9)
  2. በኢሳ (62፡ 4) ኢሳይያስ ይህን መልዕክት ለማን አቀረበ ? ለሌላ ይህ ለማን ደርሷል ?
  3. ኢሳይያስ በኢሳ (63፡ 1-3) ልብሱ ለምን ቀይ እንደ ነበር ከጠየቁት ጋር ቃለ ምልልስ አለው ፤ ምላሹ ምን ነበር ? ራዕ (19፡ 13, 15) አንብቡ ፤ ይህ በኢሳ (63፡ 3) ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ተሳሳይ ነዉ ብላችሁ ታምናላችሁ ?
  4. ኢሳ (63፡ 9) “ በሁሉም በእስራኤል መከራ መከራን እንደተቀበለ “ ይነግረናል ፤ ይህ ጥቅስ ስለ ጌታ ምን እንደሚነግረን አስላስሉ ፡፡ ይህ እዉነት በሁሉም ለዉጥ ላይ ነዉ እንዴትስ እርሱን ታዩታላችሁ ?
  5. ኢሳ (64፡ 6) ሁሉም የፅድቅ ተግባራችን እንደ ቆሻሻ ወይም እንደ ተበከለ ልብስ ነዉ ይላል ፤ ስለዚህ “ ድርጊታችንን ከማንፃት “ ወይም ነገሮችን በራሳችን ለማድረግ ከመሞከር ለምን እንደሚጠብቀን ምን ታስባላችሁ ?
  6. በኢሳይያስ (62-64) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 62:1–2

“I will not keep silent because of Zion, and I will not keep still because of Jerusalem, until her righteousness shines like a bright light and her salvation, like a flaming torch. Nations will see your righteousness and all kings, your glory. You will be called by a new name that the LORD’s mouth will announce.”

ይሆናል ብላችሁ የማትጠብቁት ነገር መሆኑን የሚያበስር የሚያስገርም ወሬ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? ምናልባት የሆነ መካን ሰው ልጅ ሊያገኝ እንደሆነ ወይም እግዚአብሔር ጓደኛችሁን እንደፈወሰው ወይም ደግሞ ታምራዊ በሆነ መንገድ እንደረዳው ? ኢሳይያስ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ስለደረገው ሁሉ ዝም ማለት እንደማይችል ተናገረ ፡፡ የእግዚአብሔር ጽድቅ እንደ ጸዳል እንደሚያበራ ፋናም ይወጣል ፡፡ አስኪ የኦሎምፒክ መብራትን አስቡት ፡፡ እንደዚያ ያለ ጸዳል ብርሃንን መደበቅ አይቻልም !

እግዚአብሔር በህይወታችሁ ውስጥ ሲሰራ የእርሱ ብርሃን ልክ እንደ ትልቅ ፋና መብራት በውስጣችሁ ያበራል ፡፡ ምናልባት ትንስ መቀረጽ መስተካከል ፣ በእሳት ውስጥ መሄድ መፈተን ምናልባትም ደግሞ ህይወታችሁ ወደ አመድነት ወደ ስብርባሪነትም ሊቀየር ይችላል ፡፡ እግዚአብሔር ህይወታችሁን ሲቀርጽና በህይወታችሁ ሲሰራ ፤ እርሱ ሊታደጋችሁ ፣ ሊገነባችሁ ፣ ስማችሁን ሊቀይርና ሊያድሳችሁ ቃል ይገባል ፤ ከዚህ ቦታ ነው ፣ ከሚያቃጥለው እሳት ውስጥ ነው የእርሱ ብርሃን የሚያበራው ፡፡ ሁሉም የእርሱን ታላቅ ፍቅርና ጽድቅ ያዩት ዘንድ ፍቅሩ በኃይል ያበራል ያንጸባርቃልም ፡፡ ለሁሉም ሰዎች የእርሱን መልካምነት አውጁ ! ብርሃናችሁን አብሩ ፡፡ እግዚአብሔር አዲስ ስም ፣ አዲስ ልብ ፣ አዲስ ጽድቅ እንድሁም አዲስ ፍቅር ሰጥቷችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በእናንተ ደስ ይለዋል ፡፡ በእናንተ ሀሴት ያደርጋል ፡፡ ዛሬ ዝም አትበሉ !

“ ስለ ጽዮን ዝም አልልም ፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ ። አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ ። “

  • ኢሳይያስ 62፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 63:7–8 — “ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ ። እግዚአብሔር ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም ፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም ፡፡ “

ኢሳይያስ 64:8 — “ አሁን ግን ፥ አቤቱ ፥ አንተ አባታችን ነህ ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን ። “

ማቴዎስ 5:15–16 — “ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል ። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ ። “