Major Prophets Isaiah

Messiah's Jubilee

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 59-61 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 599 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ነቢዩ ኢሳይያስ ለእስራኤል የባቢሎናዊያን ምርኮኝነት በገጠማቸዉ እና ነፃ በሚሆኑበት ጊዜ ትንቢታዊ ቃልን አቀረበ ፤ በተጨማሪም የኢሳይያስ ትንቢት በኢየሩሳሌም የመምጫ ጊዜአቸዉን ይደርሳል በመጨረሻም ክርስቶስ እንደ ንጉስ በሚገዛ ጊዜ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም እንዴት እንደምታምር መልኳን ይስላል ፡፡

በዚህ ጥቂት ምዕራፎችን እንደ ኃጢዓት እና ቤዛነት ስርዓት ሊገለፁ እንደሚችሉ የሚታይ ነው ነገር ግን በሰዎቹ ድርሻ ላይ ከፍተኛ ግብዝነትን ይገልፃል ፡፡ ይህ ግብዝነት ይህ ግብዝነት በእስራኤል ሰዎች እና በእግዚአብሄር መካከል መሰናክል ሆነ ፡፡ ምዕራፍ 59 የቀደመ መልክን ሲያገለግል ምዕራፍ 60 በቃል እና በመንፈስ ከመልኩ በኋላ ስለ ሽግግሩ ያገለግላል ፡፡ ጌታ ለእስራኤል ሕዝቦች ከጌታ ጋር ግንኙነታቸዉን ለተቀበሉት እንደ ብርኃን ተስሏል ፤ እግዚአብሄር ባቀረበዉ ድነት እስራኤልን እና ሌሎች ሕዝቦችን ያካትታል ፡፡ በምዕራፍ 60 በቁጥር (10-14) እስራኤል እና ሕዝቦች እስራኤልን በማገልገል እና ኢየሩሳሌምን እንደ ገና ለመገንባት በአንድ ላይ ይመጣሉ ፤ ሕዝቦች በዚህ ንግግር አሕዛቦች ናቸው ፡፡ በቁጥር (15-18) ለዉጥ አለ፣ በቁጥር (19-22) እንደ ብርኃናችን የጌታ መልክ የተሰጠ ነው ፡፡ ኢሳይያስ 59 ከባቢሎን ምርኮ በፊት ለሕዝቦች እና ለእስራኤል እንደ ቀደመ መግለጫ የተፃፈ ነበር፣ ምዕራፍ 60 ደግሞ ቤዛነት ከሆነ በኋላ ኢየሩሳሌምን እና አሕዛቦችን ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (61፡ 1-11)፡ ምዕራፍ 61 በኃይለኛው እንደ ጉልህ ትንቢታዊ ምዕራፍ ሊታይ ይችላል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ያለዉ ቋንቋ የተቀባዉን ያመለክታል ፡፡ ኢሳይያስ በአካል መልዕክቱን ለሰሙት ሕዝቦች እየተናገረ ነበር ነገር ግን በዚህ ምዕራፍ በኢሳይያስ በኩል በዚህ ምዕራፍ እየተናገ የነበረው ጌታ ነበር ፡፡ ከእኛ አንፃር አማኑኤል “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ ኃጢዓታችንን ከእኛ የወሰደ የመከራ አገልጋይ ስለሆነ ወደ እግዚአብሄር የመግባት እድል አለን ፡፡ አማኑኤል ወደ እግዚአብሄር እንደ ድልድይ አገለገለን ፡፡ ምዕራፍ (40-66) የመፅናናት፣ የመዳንን እና ነሰዎችን ነፃ የማዉጣትን ቋንቋ ይጠቀማሉ ፤ እነዚህ ምዕራፎች “ ስለ አገልጋዬ “ የሚቀጥሉ መልዕክቶችን ይይዛሉ - የተመረጠ ነበር፣ መከራን ተቀብሏል እንዲሁም የተቀባ ሆነ የሚሉትን ያካትታሉ ፡፡ በኢሳይያስ 41 የጌታ አገልጋይን የሚጠቅሱ የመፅናናት ቃላቶች አሉ ፤ በኢሳይያስ 53 ለአሕዛቦች ፍትህን የሚያመጣዉ አገልጋይ አሁን የመከራ አገልጋይ ይሆናል ፡፡ በኢሳይያስ 61 ይህ የመከራ አገልጋይ አሁን የተቀባ ይሆናል ፤ በእነዚህ በእያንዳንዱ የትርጉም ክፍል ላይ የተለዬ ተግባርን መግለፅ እንችላለን ፡፡ ምናልባት የተነሳዉ ጥያቄ በባቢሎናዊያን ምርኮ ያሉ ሰዎች ይህን እንዴት ያደርጋሉ የሚል ነው ፡፡ ኮንስታብል “ እስራኤላዊያንን ከባቢሎና ምርኮ ነፃ ለማዉጣት ቂሮስ በጌታ የተቀባ እንደ ነበረው አገልጋዩ መሲህ ከኃጢዓት ምርኮኝነት ነፃ ሊያወጣቸዉ በእርሱ የተቀባ እንደሆነ ፤ እግዚአብሄር ቃል ገብቶት የነበረዉን ለእስራኤል የፈፀመ ከዚህ ክፍል ኋላ ያለ ታላቅ ተዋጊ ነው ፡፡ ክብር የሚለዉ ቃል በአንድ ወይም በሌላ ቅርፅ በምዕራፍ (60-66) ቢያንስ 23 ጊዜ ተከስቷል/አለ “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በዚያን ጊዜ የኢሳይያስን ትንቢት ለሚሰሙት ይህ የመከራ አገልጋይ ቂሮስን ሊያመለክት ይችላል ፤ ነገር ግን መፅሀፍትን ከመገምገም በተለይም በተለዬ መከራ በሚናገረዉ ምዕራፍ 53 ላይ ለመከራ አገልጋዩ የሚበልጥ እንደነበር ይደመድማል ፤ ቂሮስም የተጠቀሰ የመከራ አገልጋይ አልነበረም ፡፡

ቁጥር 1 ስላሴን እና ክርስቶስ በምኩራብ አንብቦት ስለነበረዉ ፅሁፍ ያብራራል (ሉቃ 4፡ 18) ፤ ክርስቶስ ቁጥር 1 እና የቁጥር 2 የመጀመሪያዉን ክፍል ካነበበ በኋላ በማቆም ተቀመጠ ፡፡ በመቀጠልም ኢየሱስ እነዚህ ቃሎች በእርሱ ላይ ይፈፀሙበት ስለ ነበረው ቀን ገለፀ ፡፡ ኢሳይያስ ስለሚመጣው መሲህ ትንቢትን ተናገረ - ክርስቶስ ያን ትንቢት ፈፀመው ፡፡ የቁጥር 2 ማስታወሻነት የእግዚአብሄር የበቀል ቀን ገና የሚመጣዉን ሁለተኛዉን የክርስቶስ መምጣትን ይደርሳል ፡፡ ኢሳ (34፡ 8, 35፡ 4 እና 63፡ 4) የመሲሁ መመለስ እስኪመጣ ድረስ ቅሬቶችን ያመለክታል ፡፡ ኮንስታብል “ በናዝሬት ምኩራብ ክርስቶስ ይህን ፅሁፍ በማንበብ ተፈፀመ በማለት ባወጄ ጊዜ ከአምላክ የሞገስ አመታት በኋላ ማንበቡን በማቆም የአምላካችንን የበቀል ቀን አላነበበም (ሉቃ 4፡ 18-19) ፤ ኢሳይያስ እንደተናገረው የተቀባ እንደሆነና ድነትን ለማምጣት የመጣ እንደ ነበር እየተናገረው ፡፡ የድነት ቀን ጀምሮ ነበር (ኢሳ 49፡ 8፣ 2ቆሮ 6፡ 2) “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ክርስቶስ “ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ! “ እስከምንል ድረስ እንደማናየዉ በተናገረ ጊዜ ማቴ (23፡ 39) የመጨረሻዉ ጊዜ ተመላክቷል ፡፡ ነቢዩ ዘካሪያስ ሰዎች እንደሚያዝኑና እንደሚያለቅሱ ትንቢትን ተናግሯል (ዘካ 12፡ 10) ፤ ከኢሳይያስ 61 ጋር ያለዉ ትስስር በማዘን ወደ ጌታ የሚያለቅሱትን የተቀባዉን የሚያመለክት ነው ፡፡ ክርስቶስ ላዘኑት በጺዎን ያዘኑትን ሁሉ በማደስ እና በመባረክ ያፅናናቸዋል ፡፡

በተጨማሪም ኮንስታብል “ እስከ ብዙቆይታ ጊዜ ድረስ የበቀል ቀን ባይጀምርም በሚመለስበት ጊዜ በተለይም የመከራዊ ጊዜ መጨረሻ ላይ ይመጣል (ኢሳ 34፡ 8, 35፡ 4, 63፡ 4፣ ዳን 7፡ 21, 24-27፣ ሚክ 5፡ 15፣ 1ጴጥ 1፡ 11, ራዕ 12፡ 13-17, 19፡ 15-20)…. መልካሙን ዜና ማሳወቅ ማለት ኃጢዓታቸዉ እንዳደበዘዛቸዉ/እንዳጠፋቸዉ በማመን ያዘኑትን የተቀባዉ ያፅናናቸዋል ማለት ነው (ኢሳይያስ 12, 40፡ 1-2, 49፡ 13, ማቴ 5፡ 3-4) ፡፡ እግዚአብሄር ኃጢዓተኞች ቢሆኑም ከአገልጋዩ ስራ የተነሳ ይቀበላቸዋል “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ሕዝቡ የእግዚአብሄርን የሞገስ አመት ያውጃሉ ፤ በሚቤዠዉ የሚገለገሉት የእግዚአብሄርን የሞገስን ቀን የሚያዉጁት የተዘረዘሩት ድሆች፣ በምርኮ ያሉት፣ እዉሮች እና የተጨቆኑት ናቸው ፡፡ የመሲሁ መመለስ አላማ ለድሆች መልካም ዜናን፣ ለታሰሩት ነፃነትን፣ ለእዉራን ማየትን እና ለተጨቆኑትም ነፃነትን ማምጣት ነበር ፤ አላማዉ ሁሉም እዳዎች የተሰረዙበትን የእግዚአብሄር የተወደደ አመት ኢዩቤልዩን መመስረት እና ማወጅ ነበር ፡፡ ትርጓሜዉም ለአሕዛቦች አዲስ ጅማሬ ማለት ነበር ፡፡

መደምደሚያ

እነዚህ ጥቅሶች “ አሁን በሚሆን ያሉ ይሁን እንጂ ትንቢቶች ካልሆኑ “ ምድቦች ጋር ይጣጣማሉ ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ከእኛ ጋር ከተሳሰሩ ለእነዚህ አድማጮች ማለትም ለድሆች፣ ለእዉሮች፣ ለታሰሩ እና ለተጨቆኑ በማድረግ/በማስኬድ - መሲሁ እንደሚመጣ መናገር ስራችን ይሆናል ፡፡ የእነዚህ ጥቅሶች መልዕክት ህይወት ቀያሪ ነው ፡፡

  1. Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 421; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  2. Constable, p. 429.

  3. Constable, pp. 429-430.

ጥያቄዎች

  1. በኢሳ (59፡ 2) እኛን ከእግዚአብሄር ምን ይለየናል ? በእግዚአብሄር እና በሰዉ መካከል ለእኛ እንደ መካከለኛ ምን ቆመን (ኢሳ 59፡ 16-17) ? ይህ ከኢየሱስ ሞት በፊት ካለዉ ህይወት በይበልጥ የተለዬ ነው ? (ዘጸ 32፡ 30, 1ጢሞ 2፡ 5, ዕብ 8፡ 6, 9፡ 15)
  2. ኢሳ (60፡ 19-22) ስለ ምንድን ነዉ የሚያወራው (ራዕ 21፡ 23-24, 22፡ 5) ? እነዚህን ቃላቶች ከኢሳይያስ እንደምሰመ ራሳችሁን አስቡ ፤ ይህን ስትሰሙ በራሳችሁ ላይ ምን ይሄዳል/ያልፋል ?
  3. ኢሳ (61፡ 1) ማን ያመለክታል? (ሉቃ 4፡ 18-19) እንዴት እና መቼ ይህ ትንቢት የተፈፀመ ነበር ? የኢሳ (61፡ 2) ሁለተኛዉ ክፍን “ የአምላካችንን የእግዚአብሄር የበቀል ቀን “ ከማለት በአጭሩ ኢየሱስ ለምን እንዳቆመ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በኢሳይያስ (59-61) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 61:1

“The Spirit of the Lord GOD is on Me, because the LORD has anointed Me to bring good news to the poor. He has sent Me to heal the broken hearted, to proclaim liberty to the captives and freedom to the prisoners.”

ኢሳይያስ ስለ ተቦሳቆለው አገልጋይ ፣ ስለ መሲሁ በኢሳይያስ 61 ላይ የተናገረው የመሲሁ የድል በዓል በመባል ይታወቃል ፡፡ ኢሳይያስም መሲሁ ለድሆች ወንገልን እንደሚሰብክ ፣ ልባቸው የተሰበሩትን እንደሚጠግን እንድሁም ለምርኮኞች ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እንደሚናገር ተናገረ ፡፡ በሉቃስ 4፡18 ኢየሱስ በምኩራብ የኢሳይያስን ትንቢት በመግለጥ ይህን ቃል ጠቀሰ ፡- “ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ፤ የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት ልኮኛል ። ” የነቢዩ ኢሳይያስንም ትንቢት ከጠቀሰ በኋላ ፣ ኢየሱስ ፡- “ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ “ አላቸው ፡፡

እንደ አማኝ ፣ እንደተቀባ በጣምም እንደተወደደ በእግዚአብሔር መንፈስ ተራመዱ ፡፡ ኢየሱስ እንድትሄዱና የእርሱን እውነት ለሌሎች እንድታካፍሉ ያዛችኋል ፡፡ እርሱ ወደ ድሆች ፣ በግዞት ወዳሉት ፣ ማየት ወደ ማይችሉት ደግሞም ወደ ተጨቆኑት እንድትሄዱ ያዛችኋል ፡፡ በኢየሱስ ዘንድ ባለው ጸጋና ምህረት ስላገኘኸው ቤዛነትና መመለስ መስክር ፡፡ በጌታ ላይ በመታመን ከትቢያ ወደ ክብር ፤ ከሀዘን ከለቅሶም ወደ ደስታ ዘይት ፤ ከተስፋ መቁረጥ ከማቅ ልብስም ወደ አማረ ልብስ ስለተቀየረው ታሪካችሁ ተናገሩ ፡፡ ቀንና ማታ በጌታ ላይ ስትታመኑ ፣ የእርሱ ህያው ምንጭ ህይወታችሁን ለሌሎች የሚነገር የሚወራ ያደርገዋል ፡፡

“ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል ። “

  • ኢሳይያስ 61፡1

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 1:2–3 — “ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል ፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል ። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች ፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል ፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል ። “

ኢሳይያስ 61:2–3 — “ የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ፤ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት ፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል ። “

ሉቃስ 4:18–21 — “ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው ፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና ፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር ። እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር ። “