Major Prophets Isaiah

A House Of Prayer For All

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 56-58 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 598 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢሳይያስ 54 የእስራኤልን መታደስ እና መመለስ ይናገራል ፤ ይህ አዎንታዊ፣ ተስፋ ያለዉ እና የሚያበረታታ ለዉጥ ነበር ፤ ምዕራፍ 55 ለአሕዛቦች ግብዣን ያካትታል ፡፡ ቁጥር (1-5) “ ስለማይቀረዉ/እርግጥ ስለሆነው የጌታ ድል አድራጊነት አካል ለመሆን “ ወደ እግዚአብሄር ለመምጣት የተደረጉ ግብዣዎች ናቸው ፡፡ ኢሳ (55፡ 6-13) የምዕራፍ 56 የመጀመሪያዎቹ ቁጥሮች ለአምልኮ የተደረገ ግብዣን ሲያካትቱ የመፈለግ ጭብጥ አላቸው ፤ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ሰዎስት እጥፍ ግብዣን ለአሕዛቦች እንደሰጠ፡ ኑ (ኢሳ 55፡ 1-5)፣ ፈልጉ (ኢሳ 55፡ 6-13) እና አምልኩ (ስገዱ) (ኢሳ 56፡ 1-8) “ በማለት ይገልፃል ፡፡

በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ ዋናዉ ፍሬ ነገር/ጭብጥ መዘጋጀት የሚል ነው ፤ ሁሉም ወደ ፊት ስለሚመጣዉ ነገር እንዲዘጋጁ ተጠርተዋል ፡፡ ኮንስታብል “ ኢሳይያስ እግዚአብሄር ተቤዥቷቸዉ እንደ ነበር ……. በራሳቸዉ ፅድቅን ማድረግ የማይቻል እንደ ነበር በማሳየት ገለፀ (ኢሳይያስ 1-39) ፡፡ እንደ ተቤዠ ሕዝብ ፀጋዉን ለመያዝ አስፈልጓቸዋል ….ከምርኮ ይቤዣቸዋል (ኢሳ 40-48) እና ከኃጢዓት ይቤዣቸዋል (ኢሳ 49-55) - እግዚአብሄር እንዲሆኑ የሚፈልገዉን የእግዚአብሄር አገልጋይ ይሆናሉ ፡፡ ምዕራፍ 56 በእግዚአብሄር የማዳን እይታ የስነ ምግባር ማበረታታዎችን እንደሚይዝ “ ይናገራል ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (56፡ 1-12)፡ ኢሳይያስ ድነት በመከራዉ አገልጋይ በኩል በቅርብ እየመጣ እንደ ነበር አለ ፤ በድነት ፅድቅ ይመጣል ፤ የእስራኤል ሰዎች እነዚህን ቃሎች ቢሰሙም እንኳን ማስጠንቀቂያዎችን አልተከተሉም ወይም አልያዙም፡፡ ቁጥር 2 ግለሰቦችን ሰንበትን እንዲጠብቁ እና ክፉን እንዳያደርጉ ታዘዙ ፤ የሰንበት አምልኮ ከግብፅ ነፃ ከወጡ በኋላ የተመሰረተ ነበር ፤ ለእግዚአብሄር በመታዘዝ የነበረ እና እግዚአብሄር ከሙሴ ጋር ያደረገዉ ኪዳን እንደ ምልክት ነበር ፡፡ ዋይርስቤ “ ይህ ትዕዛዝ በአይሁድ እና በእግዚአብሄር መካከል የተለዬ ምልክት ነበር (ዘጸ 31፡ 12-18, ነህ 9፡ 13-14)፣ ለአሕዛቦች በፍፁም የተሰጠ አልነበረም ፡፡ አይሁዶች በምድረበዳ በሚንከራተቱ ጊዜ እና በምድሪቱ በሚኖሩ ጊዜ (ኤር 17፡ 19-27) ሰንበትን በቸልታ በተመለከቱበት ነገር ተገስፀው ነበር (ሕዝ 20፡ 10-26)፡፡ ከምርኮ ከተመሱም በኋላ አይሁዶች ሰንበትን መጣስን ቀጥሏል (ነህ 13፡ 15-22) “ በማለት ይናገራል ፤ ይህ ያሳስባል ምክንያቱም እግዚአብሄር ይህን ስርዓት ወይም ኪዳንን ከሌላ ከማንም ሕዝብ ጋር አላደረገም ፡፡ ዋይርስቤ “ የሰንበት ቀን የሳምንንቱ ሰባተኛ ቀን እንደሆነ፣ እግዚአብሄር ፍጥረቱን በመጨረስ ያረፈበት ቀን እንደሆነ (ዘፍ 2፡ 1-3) ፤ እሁድ የሳምንንቱ የመጀመሪያ ቀን የእግዚአብሄር ቀን እንደሆነ እና ከሞት የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መታሰቢያ እንደሆነ አስታዉሉ ፡፡ ሰንበት የአይሁዶች ምልክት እና የህጉ አባል ነበር “ በማለት ይናገራል ፡፡ በቁጥር 3 እና በሚከተሉት ማንም እንግዳ ወይም አሕዛብ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ሰንበትን እንዲጠብቁ የተጠሩ አልነበሩም፡ “ እግዚአብሄር ሰንበትን በመጠበቅ አሕዛቦች ከአይሁዶች ጋር እንዲቀላቀሉ ቀድሞ በፍፁም አልጠየቃቸዉም ነገር ግን እዚህ ጋር እርሱ ያደርገዋል “ ፡፡ እግዚአብሄር እንግዶች በመምጣት ከአይሁዶች ጋር ማምለክ እንደሚችሉ እየገለፀ ነበር ፡፡ ይህ ለወደፊቱ ትንቢት የነበረና በጊዜዎም አስፈላገ ነበር ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ በዚህ ፅሁፍ ላይ የነበሩት ጃንደረቦች “ የተኮለሱ ምናልባትም በግዞት የነበሩ ስለነበሩ በባቢሎናዊያን እና በፋሪሳዊያን ፍርድ ላይ ማገልገል እንደቻሉ (ኢሳ 39፡ 7, ዳን 1፡ 3) “ ይገልፃል ፡፡ በተጨማሪም አሁን በቤተ መቅደስ ዉስጥ በአይሁድ እንዲያገለግሉ ተፈቅዶላቸዋል ፡፡

ማክአርቱር ስለ እስራኤል የወደፊቱ መንግስት የኢሳይያስ አስራ ሰባት መግለጫዎችን አስቀምጧል/መዝግቧል፡ እግዚአብሄር የእስራኤልን የታመኑ ቅሬቶችን እንደሚመልስ፣ እግዚአብሄር ጠላቶቻቸዉንም በማሸነፍም ለሕዝቡ ጥበቃን ያደርጋል፣ የተመለሰችዉ እስራኤል የእግዚአብሄርን ታላቅ በረከት ታገኛለች፣ አንድ ቀን ኢየሩሳሌም ከአለም ሁሉ ከፍ በማለት ትልቃለች፣ እስራኤል ጌታን የማክበር ተልዕኮ ይሰጣታል እንዲሁም “ በመንግስቱ ዉስጥ አሕዛቦች በታመኑት እስራኤላዊያን በኩል በረከትን ይቀበላሉ “ የሚሉትን ያካትታል ፡፡ ለአይሁዶች የማይመች የነበረ ከአሕዛቦች ጋር የሚለወጥ የእግዚአብሄር ግንኙነት ነበር ፤ ማክአርቱር “ በመሲሁ መንግስት አስተሳሰብ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ከሁሉ ዘር በተነሱ ሕዝቦች ጌታ የሚመለክበት ማዕከላዊ ስፍራ ይሆናል “ በማለት ይቀጥላል ፡፡ ኢየሱስ ገንዘብ ለዋጮችን ከቤተ መቅደስ ባስወጣ ጊዜ ይህን ጠቅሶታል ፤ “ የአይሁድ መሪዎች ቤተ መቅደሱን የንግድ ስፍራ አድርገዉት ነበር (ማቴ 21፡ 13, ማር 11፡ 17, ሉቃ 19፡ 46) ፡፡

የኢሳይያስ መልዕክት አላማው በቤተ መቅደስ ዉስጥ የሚሆነዉ አምልኮ ለሁሉም ሕዝብ እንደሆነ አይሁዶች እንዲያዉቁ ለመፍቀድ ነበር ፤ ቤተ መቅደሱ ለአይሁዶች ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብ ሁሉ የፀሎት ቤት ይሆናል ፡፡ አጠቃላይ ተልዕኮዉ/ተግባር በቤተ መቅደስ ዉስጥ እግዚአብሄርን ለማክበር ይሆናል፡ “ የእስራኤልን ምርኮኞች ወደ መንግስቱ ከመሰብሰብ በተጨማሪ ጌታ አይሁዳዊ ባልሆኑም ያመጣል (ኢሳ 49፡ 6) “ ፡፡

ቁጥር (9-12) ሕዝቡን በማስጠንቀቅ ስራቸዉን ሰርተዉ ያልነበሩትን የእስራኤል ነቢያት እረኞችን በመጥቀስ ዞር ይላሉ ፡፡ ኮንስታብል “ ራሳቸዉን ሳይወዱ ለበጎች ከመጨነቅ ይልቅ እነዚህ እረኞች በተደጋጋሚ በመጥፋት ሰከሩ ፤ በተግባራቸዉ ወጪ ላይ ራሳቸዉን አዝናኑ በሂደቱም ኃላፊነታቸዉን ለመፈፀም የማይችሉ እና ባሪያዎች እንደሆኑ “ ይናገራል ፡፡

መደምደሚያ

ኢሳይያስ 57 እግዚአብሄር መፅናኛ ስለሚሆናቸዉ ቅልቅል ሕዝቦች ሰላም ያወራል ፤ ለክፉዎች ሰላም እንደማይሆና ማሳሰቢያዎችንም ያካትታል ፡፡ ምዕራፍ 58 የሕዝቦችን ፆም ይደርሳል ፤ ትኩረቱ ፆሙ ግብዝነት እንደነበር ነበር ፡፡ ፆም በራስ ፅድቅ ላይ ማተኮር ሳይሆን በሌሎች ፍትህ ላይ ማተኮር ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe. The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 65.

  2. Thomas Constable, Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 395; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isiah.pdf

  3. Wiersbe, p. 65.

  4. Wiersbe, p. 65.

  5. Wiersbe, p. 65.

  6. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, p.865.

  7. MacArthur, John. The MacArthur Bible Commentary (Nashville, Thomas Nelson, 2002), p. 831.

  8. MacArthur, p. 832.

  9. MacArthur, p. 832.

  10. MacArthur, p. 832.

  11. Constable, p. 399.

ጥያቄዎች

  1. በኢሳ (56፡ 2) በኢሳይያስ በኩል እግዚአብሄር “ ሰንበትን ሳያረክስ የሚጠብቅ ሰዉ ብፁዕ ሰዉ ነው …..” አለ ፤ እግዚአብሄር በዚህ ምን እያለ ነው ? ሰንበት ለምን ነበር በጣም አስፈላጊ የነበረው (ዘጸ 31፡ 13-17) ? በአሁኑ ጊዜ ሰንበትን እንደ ቅዱስ እንደጠበቁት ማህበረሰብ መጠበቅ ይሰማችኋል ? በግላችሁ የሰንበትን ቀን ታከብራላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታከብሩም ?
  2. በኢሳይያስ 56 መሰረት በእግዚአብሄር በረከት ያልተካተተ አለ ? እነዚህን በረከቶች ለመቀበል ጥቂት መስፈርቶቹ ምንድን ናቸው ? (ኢሳ 56፡ 6)
  3. በኢሳይያስ 56 እግዚአብሄር ቤቱን በምን ጠራ ? ይህን ሌላ በመፅሀፍ ላይ የት ታገኙታላችሁ (ማር 11፡ 17)? በአጠቃላይ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በዚህ እንደምትሰራ ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ በአለም ዙሪያ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው ?
  4. በኢሳይያስ 57 መሰረት የእስራኤል ሕዝቦች ያደርጉት የነበሩት አንዳንድ ክፉ ነገሮች ምን ነበሩ ? በአሁኑ ጊዜ በተመሳሳይ የተሸልን፣ ከፋና እንደሆንን ታስባላችሁ ? ለክፉዎች የሚሆን ሰላም አለ ?
  5. የእግዚአብሄር መንፈስ የት ያድራል (ኢሳ 57፡ 15) ? የዳናችሁ ከሆናችሁ በዉስጣችሁ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አላችሁ ፤ መንፈስ ቅዱስ/የእግዚአብሄር መንፈስ በዉስጣችሁ እያለ አሁንም ኃጢዓት ለማድረግ ለምን ይቀላል ? (ሮሜ 6፡ 12-14, ገላ 6፡ 7-8)
  6. ኢሳይያስ 58 ስለ ፆም ያወራል ፤ ሁሉም ፆም እግዚአብሄርን የሚያስደስት ነው ? የመፅሀፍ ቅዱሳዊ ፆም አላማዉ ምንድን ነው (ኢሳ 6-9) ? በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ መጀመሪያ ፆም የተጠቀሰዉ የት ነው (ዘጸ 34፡ 28) ? ማነዉ የጠቀሰው ?
  7. በኢሳይያስ (56-58) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 56:8

“This is the declaration of the LORD God, who gathers the dispersed of Israel: ‘I will gather to them still others besides those already gathered.’”

ኢሳይያስ እግዚአብሔር ህዝቡን መልሶ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሰበስብ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር ፣ ታላቁ እረኛ እርሱ ለበጎቹ ሁሉ ያስባል ደግሞም ሁሉም በአንድ ላይ እስከሚሆኑ ይሰበስባቸዋል ፣ ቅጣትና ትምህርት የሚገባቸውንም ጭምር ፡፡ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል ፡፡

እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ፤ ልክ እግዚአብሔር እንደሚወድ ከወደዳችሁ ሌሎች የኢየሱስን ፍቅር ማወቅ ይችላሉ ፡፡ አንድኛው ኢየሱስ ፍቅሩን ያሳየበት መንገድ ሰብሳቢ በመሆን ነበር ፡፡ ሰብሳቢ ሰዎችን ወደ አንድ ማህበር ቡድን ይሰበስባል ፤ ልክ ኢየሱስ ሰዎችን ወደ አንድ እንደሰበሰበው ሁሉ እርሱም ይሰበስባል ፡፡ ሰዎችን ወደ ቤታችሁ ጋብዙ ሰብስቡ ፡፡ ሰዎችን ፓርክ ላይ ሰብስቡ ፡፡ ሰዎችን ካፌ ውስጥ አግኙ ፡፡ ወደ ውጪ ወጥታችሁ ሰዎችን አግኙ ውደዷቸውም ፡፡ ሰዎችንም በአንድነት ስትሰበስቡ ፣ የእግዚአብሔርን መንፈስ ይመራችሁ ዘንድ ጋብዙት ፡፡ በአንድ ላይ ስትሰባሰቡ ቡና ፣ አይስ ክሬም ወይም ደግሞ እግር ኳስ መጫወት በደንብ ለመተዋወቅ ለመግባባት ይረዳችኋል ፡፡ ሆኖም ግን ወዳጅነታችሁ በደንብ እንድጠነክር ስር እንድሰድድ ጌታ እንድረዳችሁ ጸልዩ ፡፡ አብሮ ከመብላትና ከሌሎች ድርጊቶች በዘለለ ልባችሁ ከክርስቶስ ልብ ጋር ደግሞም ከታላቅ ፍቅሩ ጋር ይገናኝ ይተሳሰር ዘንድ ጸልዩ ፡፡ ፍቅሩ የብዙዎችን ህይወት ለዘላለም ይለውጣል ፣ ይህም የሁሉም የመጨረሻ መሰባሰብ ነው !

“ ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር ፦ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ ይላል ። “

  • ኢሳይያስ 56፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ኤርምያስ 23:3 — “ የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ ፤ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል ። “

ዘካርያስ 10:8 — “ ተቤዥቼአቸዋለሁና በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ ፤ ቀድሞም በዝተው እንደ ነበሩ ይበዛሉ ። “

ማቴዎስ 23:37 — “ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም ። “