Major Prophets Isaiah

The Fourth Servant's Song

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 53-55 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 597 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢሳይያስ በአጠቃላይ ከመፅኀፍ ቅዱስ መፅሀፍት ጋር ተመሳሳይ ቁጥር 66 ምዕራፎች አሉት ፡፡ ኢሳይያስ 53 የኢሳይያስ ትንቢት አጠቃላይ መፅኀፍት እና ምናልባትም የመላዉ መጽኃፍ ቅዱስ እንደ ዋና/ዓቢይ ሊታይ የሚችል ነው ፡፡ በመጀመሪያም በኢሳ (52፡ 13-15) ላይ እንመለከታለን ምክንያቱም እነዚህ ጥቅሶች ከኢሳይያስ ጋር 53 የተሳሰሩ ናቸው ፡፡ የኢሳይያስን መፅሀፍትን የመጨረሻዉን እና የደበዘዘዉን ብርሃን ማጥናት ኃይለኛ ነው ነገር ግን መፅኀፉ በእዉነት የተስፋ፣ የነፃ መዉጣት እና በመሲሁ መወለድ የድነት ጥላ መጽሀፍት ነው ፡፡ ሕዝቡ አንድ ቀን ከባቢሎን ምርኮ ነፃ ይወጣሉ እዉነቱም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከኃጢዓት ባርነት ነፃ እንደሚወጡ ነው ፡፡ የኢሳይያስ 53 መልክ እግዚአብሄር በሰዉ ማንነት በመምጣት ከህዝቡ ጋር - አማኑኤል በመምጣት እንደሚሆን ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹ አይሁዶች በኢሳይያስ 53 ላይ በመመልከት ስለመሲሁ ከማመልከት ይልቅ ወደ እስራኤል ህዝብ በማመልከት ይተረጉሙታል ፤ ያ ትርጓሜ በሀሳቡ ትክክል ከሆነ - ትንቢቱ ለእስራኤል ሕዝቦች የባቢሎን ምርኮን መጨረሻን አመልክቷል - በተጨማሪም አለምን የሚቤዠዉን በሰዉ መልክ የመጣዉን ክርስቶስን እንደ ልጅ ለመጥቀስ አስፈላጊ ነው ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ብዙ አይሁዶች አሁንም ኢሳይያስ 53 አያነቡትም ፡፡ ማክአርቱር “ ዝርዝሩ ሰዉ በአጋጣሚ ሊገምተዉ የማይችለዉ እና አጭበርባሪዎች በብልጠት ሊያሳኳቸዉ የማይችሏቸዉ ጥቃቅን ነገሮች እንደሆኑ “ ይናገራል ፡፡ ኢሳይያስ 53 ከአራቱ ዜማዎች የመጨረሻዉ እና ከአራቱ በጣም የሚታወስ መዝሙር /ዜማ ነው ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (52፡ 13-15)፡ ይህን ፅሁፍ ማጥናት እኔን አስፈራርቶኛል ምክንያቱም ፅሁፉ ለአይሁድ ሰዎች መቀየረያ ነጥብ ስለሆነ ፤ አይሁዶች ይህን ፅሁፍ ከያዙ ነቢዩ ኢሳይያስ ኢየሱስ ማን እንደሆነ እንዲያዩ እና ተመልሶ እንደሚመጣ ስለ ሚመጣዉ መሲህ ፅፏል ፡፡ ቁጥር 13 “ በመጨረሻም ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል ፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል እጅግ ታላቅም ይሆናል “ በማለት ይገልፃል (ቆላ 2፡ 15) ፡፡ ቁጥር (14-15) አገልጋዩ “ ፊቱም ከሰዎች ሁሉ ይልቅ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጎሳቅሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁበት “ እንደሰዉ የሚታይ እንደማይሆን ይገልፃሉ ፤ “ ብዙ ሕዝቦችን መርጨት “ እስራኤልን እና የእስራኤልን ሕዝብ የማንፃት የአገልጋዩ/የካህኑን ስራ ያመለክታል ፤ የአለም ነገስታትም መሲሁን ያዉቁታል ፡፡

ኢሳይያስ (53፡ 1-3)፡ ኢሳይያስ 53 መሲሁ/አገልጋዩ የሚታገሰዉን መከራን ስዕል መልክን ይሰጣል ፡፡ በራሱ ወገኖች/ሕዝቦች የተናቀና የተገፋ ይሆናል (ቁጥር 1-3) ፤ “ እኛ “ እና “ የራሱ ህዝቦች “ ሁለቱም የአይሁድ ሕዝቦችን ያመለክታሉ ፤ (ማቴ 27፡ 1-2, ዮሐ 1፡ 10-11, 12፡ 37-38) ፡፡ በቁጥር 2 “ በፊት ያደገዉ ኢየሱስ የሂወቱን እያንዳንዷን ጥቃቅን ሁኔታ ያዘዘዉ እግዚአብሄር “ ያስቀምጣል ፤ በአይሁድ ሕዝቦች የሚያደርገዉን ብዙ ነገር የሚመስል “ ከደረቅ ምድር እንደወጣ ስር ያድጋል “ - ያልተቀበሉትን ህይወታቸዉን አምጥቶታል ፡፡ በአይሁድ ሕዝቦች ተቀባይነት አለማግኘቱ የሚፈፀም ይመስላል - ዋጋ አልሰጡትም (ቁጥር 3) ፡፡

ኢሳይያስ (53፡ 4-6)፡ በቁጥር ( 4-5) ዋጋ የሚከፍለዉ አገልጋይ ለራሱ ሳይሆን ለእኛ ኃጢዓት መከራ ደረሰበት (ሉቃ 13፡ 34) ፡፡ የእነዚህ ጥቅሶች መፈፀም በአዲስ ኪዳን የሚገኝ ነው፡ ማቴ (8፡ 17, ሮሜ 4፡ 25, 1ጴጥ 2፡ 24 ፡፡ ኢየሱስ ስለ እኛ አስቸጋሪ/ኃይለኛ መከራን ታገሰ ፤ ሁላችንም ከእርሱ ዞር ስላልን የመከራዉ አገልጋይ ስለ እኛ በመስቀል ላይ ተቀጣ (ቁጥር 6) ፡፡

ኢሳይያስ (53፡ 7-8)፡ ቁጥር 7 በመግለፅ ቶም ኮንስታብል “ ስለ ኃጢዓት የእግዚአብሄር ቅጣት ቢኖርም አገልጋዩ ራሱን ያለመከላከል ይሸከማል “ ይላል ፤ ዳዊት ክላይን “ አገልጋዩ… ሁሉም ነገር በእርሱ ላይ እንዲሆን ፈቀደ እንጂ ምንም ነገር አላደረገም አላለም “ በማለት ይናገራል (ማቴ 26፡ 62-64, 27፡ 12-14) ፡፡ ህይወቱ “ ተወገደ “ - በእግዚአብሄር ላይ ስለ ሰዎች ተገደለ (ቁጥር 8) ፤ “ አገልጋዩ በአይሁዶች ስፍራ ቅጣታቸዉን ለመቀበል በመተካት ህይወቱን አጣ “ (ዳን 9፡ 26) ፡፡

ኢሳይያስ (53፡ 9-10)፡ የመከራዉ አገልጋይ ከክፉዎች ጋር ይቀበራል ምክንያቱም በሁለት ወንበዴዎች ስለተሰቀለ ነገር ግን በባለጠጎች መቃብር ስፍራ ተቀበረ (ቁጥር 9) ፡፡ ማቴ (27፡ 57-60) ባለጠጋዉ ሰዉዬ የክርስቶስ ተከታይ የአርማቴዎሱ ዮሴፍ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ “ ጌታም በፍቃዱ በኃይለኛዉ እንዲያደቀዉ የፈቀደ ነበር “ (ቁጥር 10) ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ከባርነት ነፃ ለማዉጣት በመፈለግ በፍቃደኝነት ያ እንዲሆን ልጁን ሰጠ ፡፡ ኢየሱስ እንደ መስዋዕት በግ ለእኛ መለወጥ አንዴ ለመሰዋት መጣ ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ስቃይ ዉስጥ ማለፍ አልፈለገም ነገር ግን እስከሞቱ ድረስ እንኳን ለእግዚአብሄር ፍቃድ የታዘዘ ነበር (ማቴ 26፡ 39) ፡፡

ኢሳይያስ (53፡ 11-12)፡ እግዚአብሄር በልጁ ሞት ይደሰታል ምክንያቱም ሕዝቡን በእርሱ ፊት ፃድቃን ስለሚያደርጋቸው (ቁጥር 11) ፡፡ ኃጢዓት ጉዳይ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተወሰደ ነው ፤ ልጁም የተሰቀለ በመሆን ከወንበዴዎች ጋር ይቆጠራል (ከሌቦች) (ቁጥር 12) ፡፡

መደምደሚያ

በኢሳይያስ ትንቢት ምን ታደርጋላችሁ ? ኃጢዓታችሁን በራሱ ላይ ለመዉሰድ የተላከዉን የመከራዉ አገልጋይን ትንቢት በሚገባ ትወስዱታላችሁ ? ወይስ በአጠቃላይ ኢሳይያስ 53 አለመቀበልን ትመርጣላችሁ ? በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት፣ መቀበር እና መነሳት ብቻ ሊፈፀም የሚችለዉን የኢሳይያስን ትንቢት እንድትይዙ እሞግታችኋለሁ (ዮሐ 17፡ 3) ፡፡ አማኑኤል እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ማለት ነው ፤ ኢየሱስ ለእኛ እንዲሞት እና ከእኛ ጋር እንዲሞት በእግዚአብሄር የተላከ ነበር ፡፡

7 David J. A. Clines, “I, He, We and They: A Literary Approach to Isaiah 53,” Journal for the Study of the Old Testament, Supplementary Vol. 1 (Sheffield, Eng.: JSOT Press, 1976), pp. 64-65; quoted in Constable, p. 367.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 824.

  2. MacArthur, p. 824.

  3. MacArthur, p. 824.

  4. MacArthur, p. 824.

  5. MacArthur, p. 824.

  6. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes, p. 373; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  7. MacArthur, p. 826.

ጥያቄዎች

  1. የኢሳ (53፡ 1) ተስፋ በክርስቶስ መቼ እና እንዴት ተፈፀመ ? (ዮሐ 1፡ 9-11, 12፡ 37-38) ጳዉሎስ ይህን ተመሳሳይ ትንቢት ለአለም እንዴት ተገበረ ? (ሮሜ 10፡ 16)
  2. ኢሳይያስ አገልጋዩን ለመግለፅ ያለፈ ጊዜ ሰዋሰዉን ተጠቀመ ፤ ከኢሳይያስ ጊዜ ወደፊት የሚሆኑትን እንዴት ተነበዩ (ኢሳ 53፡ 4-5, 11-12) ? በአዲስ ኪዳን ስለ ኢየሱስ የእነዚህን ትንቢቶች መፈፀም ታገኛላችሁ ፤ (ማቴ 8፡ 16-17, 1ጴጥ 2፡ 24)
  3. በኢሳይያስ 53 ጥናት አድርጉ ፤ በምዕራፉ ዉስጥ በማለፍ ኢየሱስ የፈፀማቸዉን ቀጥተኛ ትንቢቶች ታገኛላችሁ ፡፡ ከዚህ በፊት ያላስተዋላችሁት ትንቢት አለ ?
  4. በኢሳይያስ 54 ኢሳይያስ የገለፃቸዉ እና እንድንሳተፍባቸው አንባቢዎቹን የጋበዛቸው በመከራ አገልጋይ የተገኙት ጥቂት ጥቅሞች ምንድን ናቸው ?
  5. ድነት፣ ፀጋና ምህረት በብሉይ ኪዳን ለነበሩት እንዴት የተገኘ/የቀረበ ነበር (ዘዳ 4፡ 29, 2ዜና 15፡ 4, ኢሳ 55፡ 6-7) ? እዉነተኛ እምነትን መፈለግ ምን ይይዛል ? (2ቆሮ 7፡ 10, 2ጴጥ 3፡ 9)
  6. በኢሳይያስ (53-55) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 53:5–6

“But He was pierced because of our transgressions, crushed because of our iniquities; punishment for our peace was on Him, and we are healed by His wounds. We all went astray like sheep; we all have turned to our own way; and the LORD has punished Him for the iniquity of us all.”

ማርያም ኢየሱስን ከመውለዷ ከትውልዶች በፊት ኢሳይያስ እግዚአብሔር አማኑኤልን እንደሚልክ ተነበየ ፡፡ ይህም አማኑኤል መከራን የሚቀበል ይሆናል ፡፡ አማኑኤል የሆነው ኢየሱስ ህመመችሁን ይቀበላል ስቃያችሁንም ይሸከማል ፡፡ ተመታ ፣ ተቸገረም ፤ ስለ መተላለፋችሁ ቆሰለ ስለ በደላችሁም ደቀቀ ፡፡ በቁስሉም ተፈወሳችሁ ፡፡ በጠቅላላው ኢየሱስ ስለ እናንተ ሊኖርና ሊሞት ወደ ምድር መጥቷል ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ መከራን ተቀበለ ፡፡

ኢየሱስ ራሱን እረኛ ብሎ ነው የጠራው እናንተን ደግሞ የማሰማርያ በጎቹ እንደሆናችሁ ነው ፡፡ አዎን እናንተ በየቦታው የተበታተናችሁ የእግዚአብሔር በጎች ናችሁ ፡፡ እናንተ የመተላለፋችሁን ህመምና ሞት መቀበል ስለማትችሉ ስለዚህ ሲል እግዚአብሔር ኢየሱስን መከራን እንድቀበልና ስለ እናንተ መስዋዕት እንድሆን ላከው ፡፡ እናንተ በእርሱ የዘላለምን ህይወት ታገኙ ዘንድ ኢየሱስ መጥቷል ፡፡ ዛሬ ይህን እውነት ተቀብላችሁ በዚህ የህይወት ስጦታ እረፉ ፣ በጌታም ደስ ይበላችሁ ፡፡ ከአንገታችሁ ቀና በማለት በእግራችሁ ቆማችሁ ለማመስገን ጊዜ ውሰዱ ፡፡ ስለ ፈለጋችሁና በፍቅሩ ውስጥ በሚገኘው በለመለመ መስክ ውስጥ ስላሰማራችሁ ፣ ስለ ምህረቱና ስለ ጸጋው እግዚአብሔርን አመስግኑ ፡፡ እርሱ መልካም እረኛ ነው ፍቅሩም ወረት የለበትም ፡፡ ዛሬ ወረት የሌለበት ፍቅሩን ተቀበሉ ፡፡

“ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን ። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ ። “

  • ኢሳይያስ 53፡5-6

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 53:11–12 — “ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል ። ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ ። “

ዮሐንስ 17:3–4 — “ እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት ። እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ ፡፡ “

1ኛ ጴጥሮስ 2:24–25 — “ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር ፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል ። “