Major Prophets Isaiah

Awake! Awake!

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 50-52 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 596 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለኢሳይያስ መፅሀፍት ቃላችን በሰዉ ስጋ የተገለጠዉ የእግዚአብሄር ልጅ የኢየሱስ ትንቢት የሆነው አማኑኤል ነው (ኢሳ 7፡ 14) ፡፡ ይህ ከክርስቶስ መወለድ 738 ዓመት በፊት ስለ ክርስቶስ የተፃፈ ነበር ማለት ከ700 አመታት በላይ አልተወለደም ፡፡ በኢሳይያስ መፅሀፍት ዉስጥ ሁልጊዜ ለአሁኖቹ አይሁዶች እና ስለ አይሁዶች ወደፊት መልዕክት ላይ እንመለከታለን ፤ በኢሳ (50፡ 4-11) ራይሞድ ኦርቱለንድ ታዛዥ አገልጋይን እንደ፡ “ ተማረ አገልጋይ (ቁጥር 4)፣ የመከራ አገልጋይ (ቁጥር 5-6)፣ 3) ልበ ሙሉ እንደ ሆነ አገልጋይ (ቁጥር 7-8) እና 4) ተረጋገጠ አገልጋይ (ቁጥር 9) “ ይገልፃል ፡፡ በመቀጠልም ቁጥር (10-11) ማን መከተልን እንደምንመርጥ ራሳችንን ወይም ክርስቶስን እንደ ሆነ ይጠይቃል ? ራሳችንን ለመከተል የምንመርጥ ከሆነ በፍርድ ስፍራ ላይ እንወድቃለን (ቁጥር 11) ፡፡

ኦርቱለንድ በኢሳ (51፡ 1-8) “ ልባም አድማጮች “ “ በእግዚአብሄር የተፅናኑ “ እንደሆኑና በማመልከት ምዕራፉን ፡ “ የእግዚአብሄር ማጽናናት ህይወት ሰጪ እንደሆነ (ኢሳ 51፡ 1-3)፣ 2) የእግዚአብሄር ኃይል አለምን ቀያሪ እንደሆነ (51፡ 4-6) እና 3) የእግዚአብሄር ጽድቅ የሚያነሳሳ አበርቺ እንደሆነ (51፡ 7, 8) “ አስቀምጧል ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ሕዝቡ ይጠነቀቃል ፡፡ ቁጥር 9 የእግዚአብሄርን መጽናናት እና በራስ ከመደገፍ ይልቅ የማይረታ ኃይሉን ለመቀበል የማንቃትን ጥሪ ያካትታል (ቁጥር 9-16) ፤ በቁጥር 17 በእግዚአብሄር ምህረት በኩል በቀድሞዉ ከእግዚአብሄር ቁጣ የማምለጥ ተስፋን በመያዝ ተመሳሳይ ቋንቋ የሚገኝ ነው (ቁጥር 17-23) ፡፡ ይህ ሁሉ እስካሁን ሆኖ ያልነበረዉን ነገር ግን ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት እንደሚሆን እና የእግዚአብሄር አዳኝን የመሲሁን የመምጣት ተመሳሳይ ጊዜ የተናገሩ ትንቢታዊ ቋንቋዎች ናቸው (ከክርስቶስ ልደት 3 በፊት) ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (52፡ 1-7)፡ ምዕራፍ 52 ለማንቃት በሰዎስተኛዉ ጥሪ ይጀምራል (ቁጥር 1) ፡፡ ኢሳይያስ ኢየሩሳሌምን (ፂዎንን) ነፃነታቸዉን እንዲያከብሩ ኃይላቸዉን እና ጌጠኛ ልብሳቸዉን እንዲለብሱ ጠራቸው ፡፡ ማክአርቱር “ ጥሪዉ ለፂዎን ከጨለማነት በመንቃት በእግዚአብሄር የተሰጣትን የክብርና የሞገስ ልብሷን እንድትለብስ ለማንቃት የተሰጠ ነው ፤ የዉጭ/ሌሎች ወራሪዎች በመጨረሻዋ የመታደስ ጊዜዋ ላይ ከተማዋን እንደማይቆጣጠሯት “ ይገልፃል ፡፡ “ የመጨረሻዉ ጊዜ ታድሶ “ ከባቢሎን ምርኮኝነት ወደ ኢየሩሳሌም መመለስን እና ወደ ኢየሩሳሌም የኢየሱስ ሁለተኛዉን መመለስ ሁለቱንም ያመለክታል ፡፡ ቁጥር 2 “ የራሷን ቆሻሻ ታራግፍ “ ይላል ትርጉሙም ወደ ቀድሞ ለመሄድ መፍቀድ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ግብፅ የእግዚአብሄርን ሕዝቦች በባርነት ገዝተዉ ነበር፣ አሶራዊያን አስጨንቀዋቸዉ ነበር እና ባቢሎን በምርኮኝነት ወስዳቸዉ ነበር ነገር ግን አሁን ያ አብቅቷል “ በማለት ይናገራል ፡፡

ቁጥር (3-5) ሕዝቡ ያለ ምንም ክፍያ ተሸጠዉ እንደ ነበርና ያለምንም ገንዘብ የተቤዢ እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ ማክአርቱር “ አይሁዶች ለእስራኤል ምንም ነገር ባልከፈሉ እንግዳ ሰዎች አገልጋዮች /ባሪያዎች ስለሆኑ እግዚአብሄር እስራኤልን ከኃጢዓት ያለክፍያ ይቤዣቸዋል (ኢሳ 45፡ 13, 55፡ 1) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር በመቀጠሉ ሕዝቦቹ ስሙን ያዉቁታል (ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄር ሕዝቡን አልታደጋቸዉም ምክንያቱም መልካም፣ ፃድቅ ወይም የሚገባቸወ ስለሆኑ ፤ ማን እንደሆነ ለማረጋገጥ ይታደጋቸዋል ፡፡ ማክአርቱር “ ከጌታ ቀን በኋላ / ከታላቁ መከራ በኋላ እስራኤል በአለም አቀፍ ከደረሰባት መከራ ነፃ በወጣች ጊዜ በኢሳይያስ በኩል እና በሌሎች የተነገረዉን ትንቢት መፈፀም በማስተዋል እግዚአብሄር ተናግሮ እንደ ነበርና ነፃ የማዉጣት ተስፋን እንደፈፀመ በሙሉ እርግጠኝነት ይደሰታሉ ፤ እነዚህ ክስተቶች ታላቅ ከሆነዉ ጋር እንደሚገናኙ “ ይገልፃል (ዘጸ 3፡ 13-15, 2ሳሙ 18፡ 26, ኢሳ 43፡ 11, ሮሜ 10፡ 15) ፡፡ ከተማዋ ስለመሲሁ መምጣት ዜና እየጠበቀች ነበር ፡፡

ኢሳይያስ (52፡ 8-15)፡ የኢየሩሳሌም ሰዎች በደስታ ይጮኃሉ ይዘምራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ መመለስ ለዉጥን ስለሚያዩ (ቁጥር 8) ፡፡ ኢየሩሳሌም የተቤዠች ትሆናለች ፤ ማክአርቱር “ የጠፋችዉ ከተማ ለደስታ መዝሙር ጥሪዉ ምላሽን ትሰጣለች ምክንያቱም እግዚአብሄር መጽናናትን እና ቤዛነትን ስለሰጠ “ (ቁጥር 9-10) ፡፡

ኢሳይያስ የእግዚአብሄርን የተቀደሱ እቃዎች የሚሸከሙትን እልፍ እንዲሉ፣ ርኩስ ነገርን እንዳይነኩ ነግሯቸዋል (ቁጥር 11) ፤ እግዚአብሄር ከፊታቸዉ እና ከኋላቸዉ ስለሚቀድም በችኮላ አይወጡም ከማንኛዉም ጠላት አይሸሹም (ቁጥር 12) ፡፡ ቁጥር (13-15) ስለሚመጣዉ አገልጋይ ስለ አማኑኤል ያስቀምጣል ፡፡

መደምደሚያ

ኃጢዓት ሁልጊዜ ወደ መስቀል ይመራል ፡፡ ከክርስቶስ ትንሳኤ የተነሳ በኃጢዓታችን ባርነት ስር አንኖርም ፤ የቤዛነት ስራዉ ባደረግነዉ ማንኛዉም ነገር ሳይሆን በእርሱ በራሱ ስለሆነ ፤ ይህ የኢየሱስ መልካም ዜና ነው ፡፡ በዙሪያችን ያሉት ሰዎች ያን ዜና ለመስማት እየጠበቁ ነው ፡፡ በማቴዎስ 28 ኢየሱስ በመሄድ መልካሙን ዜና እንድንናገር አዞናል ፤ አማራጭ አልተሰጠንም ፡፡

ዛሬ ልሞግታችሁ ፤ የመጀመሪያዉ ክርስቶስን የማታዉቁት ከሆነ አሁን ያዙት ፤ ሁለተኛው የምታዉቁት ከሆነ በዚህ ወንጌል መመላለስ ጀምሩ ፡፡ ቁጥር 7 በክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የሚመጣዉ ድል አድራጊነት ጥላ/ማሳያ ነው ፡፡ መጽናናት እና ቤዛነት ቀድሞዉኑ አንዴ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተዋል ፡፡ በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች አይሁድ ወይም አሕዛብ በአፋችን እና በእግሮቻችን መልካሙን ዜና የምንነግራቸዉ ያስፈልጉናል ፡፡ መልካሙ ዜና ጌታ አማኑኤል ከእኛ ጋር ለመሆን ይመጣል (ቁጥር 10) ፡፡

  1. Raymond C. Ortlund, Jr., Isaiah: God Saves Sinners, Preaching the Word (Wheaton, IL: Crossway, 2005), p. 334.

  2. Ortlund, p. 334.

  3. Ortlund, p. 332.

  4. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 823.

  5. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 57.

  6. MacArthur, p. 823.

  7. MacArthur, p. 823.

  8. MacArthur, p. 824.

ጥያቄዎች

  1. በኢሳ (50፡ 1) ይሁዳ ለምን መከራ እንደደረሰበት እግዚአብሄር ምን ምክንያትን ሰጠ ? ይህ ከማይቀየረዉ ከዳዊት ኪዳን ጋር እንዴት ይተሳሰራል ? (2ሳሙኤል 7)
  2. በኢሳ (50፡ 2) እርሱን ሳያምኑ ወይም ሳይታዘዙ በቀሩ ጊዜ እግዚአብሄር ምን እንዲያስታዉሱ ጠየቃቸው ?
  3. ኢየሱስ ኢሳ (50፡ 6) እንዴት ፈፀመው ? (ማቴ 26፡ 67, 27፡ 26, 30, ማር 14፡ 65)
  4. በእስራኤልና በእግዚአብሄር መካከል መለያየትም የነበረ ቢኖርም ኢሳይያስ በኢሳይያስ 51 ሕዝቡን በማበርታት የእግዚአብሄርን ተስፋ እንደ ገና እንዴት ተናገረ ? (ዘፍ 12፡ 1-3)
  5. ኢሳ (52፡ 7) በእስራኤል አዉድ እንዴት የሚተገበር ነዉ ጳዉሎስስ በአሁኑ ጊዜ በእኛ ላይ እንዴት ተገበረው? (ኢሳ 40፡ 9, ሮሜ 10፡ 15, ኤፌ 6፡ 15)
  6. በኢሳይያስ (50-52) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 52:6–7

“Therefore My people will know My name; therefore they will know on that day that I am He who says: ‘Here I am.’ How beautiful on the mountains are the feet of the herald, who proclaims peace, who brings news of good things, who proclaims salvation, who says to Zion, ‘Your God reigns!’”

የእግዚአብሔር ህዝቦች ፊታቸውን ከእግዚአብሔር መለሱ ፤ ስለ ኃጢአታቸውም ቅጣትንና ፍርድን ተቀበሉ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር እንደገና መመለስ ሆነላቸው ፡፡ በጊዜም ውስጥ እግዚአብሔር ከባርነት ነጻ አወጣቸው ፡፡ እነርሱም በህይወታቸው ስለተገለጠው የሚታደግ የእግዚአብሔር ኋይል ፣ የእርሱን ስም አወጁ ፡፡ ሰዎችም ታላቅ ስለሆነው ፣ ንጉስ ስለሆነው ብቸኛ አምላክ ስለ እግዚአብሔር ሰሙ ፡፡ አዎን እርሱ ምርኮኞችን የሚፈታ ደግሞም ለዛሬ ሰላምን ለነገም ተስፋን የሚሰጥ አምላክ ነው ፡፡

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን ፡- እንድሄዱና ስሙን እንድያውጁ ደግሞም ስለሚያድን ኃይሉ በመመስከር እርሱን እንድያከብሩ አዘዛቸው ፡፡ ስሙን ስታውጁና የኢየሱስ ክርስቶስን የምስራች ስትመሰክሩ ፣ እግዚአብሔር እግሮቻችሁን ያማሩ ብሎ ይጠራቸዋል ! አለም ውበት በተለያዩ መዋቢያ እቃዎች ፣ በስፓርት እንድሁም በቀዶ ጥገና እንደሚገኝ ይናገራል ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ፡- “ ስሜን ስታውጁ ያኔ እናንተ ውብ ቆንጆ ናችሁ “ ይላል ፡፡ ዛሬ ስለ ኢየሱስ የምትሄዱበትን ጫማ አድርጉ ፡፡ ሞት ሳይሆን ህይወትን ፤ ጭንቀት ሳይሆን ሰላምን ፤ ባርነት ሳይሆን ነጻነት እንድሁም ለነገ ተስፋን የሚሰጠውን የኢየሱስ ክርስቶስን የምስራች አውጁ ፡፡ እናንተ የምታምሩ የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ ተነሱ ፣ ልትፈጽሙት የሚገባ ሩጫ አለ !

“ ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል ፥ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ ፤ እነሆ ፥ እኔ ነኝ ። የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር ፥ መድኃኒትንም የሚያወራ ፥ ጽዮንንም ፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው ። “

  • ኢሳይያስ 52፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 28:19–20 — “ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ። “

ሮሜ 10:15 — “ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ ? “

2ኛ ቆሮንቶስ 4:15 — “ በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና ። “