The Second Servant's Song
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 47-49 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ወደ ኢሳይያስ 49 ጥናት ቀጥለናል/ገብተናል ፤ ነገር ግን ወደዚያ ምዕራፍ ከመግባታችን በፊት የምናገኘዉ ብዙ ነገር አለ ፡፡ አሁንም በኢሳይያስ ሁለተኛዉ ግማሽ ላይ ወይም “ መፅናናት መፅሀፍት “ ላይ ነን (ኢሳ 40-66) ፡፡ በምዕራፍ 47 ኢሳይያስ አድማጮቹን በአስማታቸዉ እና በጣዖታቸዉ ስለታመኑ ባቢሎናዊያን እንዲያዝኑ እንዲጠሯቸዉ ይነግራቸዋል ፤ ቀጥሎም በምዕራፍ 48 እግዚአብሄር ሰዎቹን ከባቢሎን የመዉጣት ዘመቻቸዉን ስርዓት ይሰጣቸዋል ፡፡ በምእራፍ 48 ቁጥር 12 እግዚአብሄር ብሉይ ኪዳንንና አዲስ ኪዳን በማገናኘት ስሙን “ እኔ ነኝ ፤ እኔ ፊተኛዉ ነኝ እኔም ኋለኛዉ ነኝ “ በማለት ይሰጣል ፡፡
በኢሳይያስ 45 ጥናታችን ቂሮስ እንደተቀባ ሰምተናል ፤ በኢሳይያስ 48 በቁጥር (14-15) ላይ እግዚአብሄር የፋሪስን ንጉስ ቂሮስን እንደሚወደዉ እና መለኮታዊ አላማዉን ለመፈፀም እንደሚጠቀምበት አሳወቀ ፡፡ በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሄር የተወደደ እንደ ነበር የተገለፀዉ ብቸኛዉ ንጉስ አይሁዳዊዉ ሰለሞን ነበር ፡፡ ቂሮስ ፈሪሳዊ (አሕዛብ) ነበር እና ለእርሱ በእግዚአብሄር የተወደደ መሆን የሚያስደነግጥ ነገር ነበር ፤ በሚያስደንቅ ሁኔታ የእግዚአብሄር ቂሮስን መጠቀም በባቢሎን ላይ እንጂ በእስራኤል ላይ አልነበረም ፡፡ የኢሳይያስ ትንቢት ስለ ቂሮስ ቂሮስ ንጉስ ከመሆኑ ከ200 አመት በፊት የተፃፈ ነበር ፤ አንድ ቀን ቂሮስ ባቢሎንን በመያዝ የአይሁድ ቅሬታዎችን መልሶ ወደ ምድራቸዉ ይልካቸዋል ፤ በተጨማሪም ቂሮስ በኢየሩሳሌም ለቤተ መቅደሱ መልሶ ግንባታ ይከፍላል ፡፡ እግዚአብሄር የፋሪስን ንጉስ ያካተተ እቅድ ነበረው ፡፡ እግዚአብሄር በአጠገብ ያሉ ሁሉም እስራኤልን እንዲባርኩ ፈልጎ ነበር ነገር ግን እስራኤል የሚተባበር ባይሆንም ፤ ስለዚህም ኢሳይያስ እስራኤል የእግዚአብሄርን በረከት ለመቀበል አንድ የመጨረሻ እዳለዉ ትንቢትን ተናግሯል ፡፡
ይህ ወደ ኢሳይያስ 49 ይመራናል ፡፡ በኢሳይያስ 42 ጥናታችን ላይ የእግዚአብሄር አገልጋይ የመሲሁን የአገልግሎት፣ የመከራ እና ከፍ ከፍ የማለት “ አራት የአገልጋይ ዜማዎችን “ አዉርተናል ፡፡ በምዕራፍ 49 በቁጥር (1-13) በሁለተኛዉ የአገልጋይ ዜማ ላይ እንመለከታለን ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (49፡ 1-7)፡ የአገልጋዩ ሁለተኛዉ ዜማ የመሲሁን ስራ በአለም ላይ እና ስኬቱን ይናገራል ፡፡ አለን ራድፓዝ “ ይህ ምዕራፍ በሙሉ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነና የተጠቀሱት ቃላቶች በአዳኛችን በሌላ በማንኛዉም ማዳን ምናልባትም ሙሉ መፈፀም ሊኖራቸዉ አይችልም “ አለ ፡፡ በቁጥር 1 ኢሳይያስአገልጋዩ በእናቱ ማኅፀን ዉስጥ እንደ ነበር በእግዚአብሄር እንደተጠራ ይናገራል (ኤር 1፡ 5, ሚክ 5፡ 2) ፡፡ በቁጥር 2 አገልጋዩ እግዚአብሄር እንዴት አጠንክሮት እንደ ነበርና አፉን እንዴት እንደተሳለ ሰይፍ አንደተጠቀመበት ይገልፃል ፤ በተጨማሪም ኤፌ (6፡ 17), ዕብ (4፡ 12, ራዕ (1፡ 16, 2፡ 12, 16, 19፡ 15) የሰይፍን ትንቢታዊ ጥቅም ይገልፃሉ ፡፡
በቁጥር 3 “ አንተ እስራኤል አገልጋዬ ነህ “ የሚለዉ ንግግር እስራኤልን ለመሲሁ እንደማጣቀሻ የተሸለ መረዳት ነው ፤ ይህ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም መጀመሪያ መሲሁ ከእስራኤል ስለሚመጣ እና የአሕዛቦች ተወካይ ሲሆን ሁለተኛው “ በእግዚአብሄር የሚተዳደር “ የሚል ትርጉም ያለዉን የእስራኤልን ስም መሲሁ ያሟላል ፡፡ ቁጥር 4 አገልጋዩ ስለተሰማዉ መከራና ታላቅ እጦት በመግለፅ ይቀጥላል ፡፡ ኢሳይያስ ኢየሱስ በፈተናዉ ጊዜ ስለሚሰማዉ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት፣ ደቀ መዛሙርቱ በመሳሳት ትምህርቱን በስርዓት ባልተረዱ ጊዜ የተሰማዉን ተስፋ መቁረጥ እና በጌቴሰማኔ አትክልት ስፍራ በመቅረብ ለብቻዉ ትተዉት በነበረ ጊዜ የሚሰማዉን ተስፋ መቁረጥ ማየት ችሎ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ ምንም እንኳን መሲሁ በአስቸጋሪ እና ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ቢያገለግልም በፍፁም ለተስፋ መቁረጥ አልተሰጠም ፤ ሁልጊዜ እምነቱን በእግዚአብሄር ላይ አስቀመጠ ፤ በእግዚአብሄር አይንም የተከበረ ይሆናል፡፡
ቁጥር 5 የመሲሁ ተልዕኮ እስራኤልን መልሶ ወደ ጌታ ማምጣት እንደ ነበርና ከአስፈላጊነቱ አንፃር ያሳያል ፡፡ በእግዚአብሄር እቅድ ዉስጥ እስራኤል የመታገሻ ስፍራ እና እቅዱ ይፈፀምበታል ፤ ሮሜ (11፡ 26) “ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናልና ፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፡- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል “ ፡፡ መሲሁ የእግዚአብሄርን ሕዝብን ያድሳል አሕዛብንም እንዲቤዥ ተመርጧል (ቁጥር 6) ፡፡ ስምዖን ህፃኑን ኢየሱስን “ ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል እንደ ክብር “ አየው (ሉቃ 2፡ 32) ፡፡ የኢሳይያስ ትንቢት በእጁ እንደ ነበር ስምዖን ተረድቶ ነበር ? መሲሁ በቀላሉ ድነትን አያመጣም ነገር ግን ለምድር መጨረሻ ላይ የእርሱ ማን ይሆናል (ቁጥር 6) ፡፡
ቁጥር 7 በአለም አቀፍ/ከመላዉ አለም በህዝቡ ከተናቀ በኋላ መሲሁ የሚቀበለዉን እልልታ/ጭብጨባ ይገልፃል ፡፡ በእርግጠኝነት ከኢሳይያስ ይህን መልዕክት ከሰሙት ዉስጥ ማንም አንድ ቀን መሲሁ እንደሚናቅ እና የተገፋ እንደሚሆን አላመኑም ፤ ይህም እስካሁን አልሆነም ፡፡
ኢሳይያስ (49፡ 8-13)፡ የእግዚአብሄር አገልጋይ የምድሪቱን መታደስ እና የሰላም መንግስት መመስረትን ይመለከታል (ቁጥር 8-13) ፡፡ መሲሁ ለህዝቡ ኪዳን በመሆን የእስራኤልን ምድር ያድሳል (ቁጥር 8) ፤ የመሲሁ አገልግሎት ሰዎችን ከባርነት እና ከእስራት ነፃ ያወጣል (ቁጥር 9-10) ፡፡ በአንድ ፈጣን በሆነ ምልከታ ይህ በእግዚአብሄር ስዉር እጅ ከባቢሎን ግዞት የይሁዳ መመለስን መሰጠትን እና መቆየትን ያመለክታል ፡፡ በትልቅ ምልከታ ደግሞ በመጨረሻዉ ቀን ወደ እርሱ ሲመለሱ ለሰዎች ስለ እግዚአብሄር ምህረት እና ስጦታ ይናገራል ፡፡
ቁጥር 11 እግዚአብሄር ተራሮችን ሁሉ መንገዶች እንደሚያደርግ ይገልፃል ፤ ሁሉም ማለት ሁሉንም ማለት ነው ፤ ያም ማለት በህይወት ምንም ነገር የለም ማለት ነዉ ማለትም - መሰናክል የለም፣ ብቸኝነት የለም፣ መከራ የለም፣ ኃዘን የለም - ያ ወደ በለፀገዉ የእግዚአብሄር በረከት መንገድ የሚያደርስ ላይሆን ይችላል ፡፡ “ ተራሮቼ “ ማለት አሁንም በመንገዱ ላይ ያሉ የእግዚአብሄር ተራሮች ለአላማ በዚያ የሚሆኑ ይፈቅዳሉ ማለት ነው ፡፡ ክርስቶስ በተራሮቹ መካከል ላይ በዚያ ነው - በመከራዉ መካከል ላይ ነው ፡፡
እግዚአብሄር ሕዝቡን መልሶ ከአለም ከሩቅ ስፍራ እንደሚያመጣቸዉ ቃል ገባ (ቁጥር 12) ፡፡ ምናልባትም ሲኒም በግብፅ አስዋን ወይም በቻይና አካባቢ ያለ ስፍራ ሊሆን ይችላል ፡፡ አንድ ማብራሪያ ኢሳይያስ እግዚአብሄር ምርኮኞቹን በምድር ላይ ከሚታመኑ/ከሚታሰቡ ስፍራዎች መልሶ እንደሚያመጣቸዉ ለማሳየት የተሰራን ስፍራ በመጠቀም ሆን ብሎ ግልፅ አላደረገዉም ነበር ፡፡ መሲሁ ለህዝቡ የእግዚአብሄር መፅናናት እና ድነት ወኪል ይሆናል (ቁጥር 13) ፡፡
ጳዉሎስ እና በርናባስ በመጀመሪያ የአገልግሎት ጉዞአቸው በአንጾኪያ ለአሕዛብን ወንጌልን በመዉሰድ ኢሳ (49፡ 6) ጠቀሱ፡ “ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ “ (ሐዋ 13፡ 47) ፡፡ በአንጾኪያ የአሕዛቦች መልስ በፍፁም ደስታ ነበር፡ “ አሕዛብም ሰምተዉ ደስ አላቸው የእግዚአብሄርንም ቃል አከበሩ ለዘላለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተሳፋፋ “ (ሐዋ 13፡ 48-49) ፡፡ ኤፌ (2፡ 11-18) እንዴት አይሁዶች እና አሕዛቦች አንድ እንደተደረጉ ይገልፃል ፡፡
ኢሳይያስ (49፡ 14-26)፡ ጺዎን በኢየሩሳሌም ከፍ ያለዉን ተራራ እና የእግዚአብሄርን ሰዎች ስፍራ በማጣመር ያመለክታል ፡፡ በቁጥር 14 ጺዎን እየሆነ በነበረዉ ነገር እና እግዚአብሄር ረስቷት እንደ ነበር አይነት ሁኔታ ዉስጥ ነበረች ፡፡ የምዕራፍ 49 ቀሪዉ ጥያቄዉን ይመልሰዋል “ በእዉነት እግዚአብሄር ይጠነቀቅልናል/ያስብልናል ? “ እግዚአብሄር በመጠንቀቅ ጌታ ለጺዉን ፍቅሩንና መታመኑን ገለፀ ፡፡ ቁጥር 16 ከትንሳኤ በኋላ የመሲሁን እጆች ይገልፃል (ዮሐ 20፡ 27) ፡፡
መደምደሚያ
የኢየሱስን የሚስማር ጣባሳዎችን በእጆቹ ላይ በምናይ ጊዜ በእጆቹ መዳፎች ላይ እንዴት እንደቀረፀን እናያለን ፡፡ ፍቅሩ ይህን ያክል ከሆነ እንዴት ህዝቡን ይረሳል ፡፡
ጥያቄዎች
-
በኢሳይያስ 47 በባቢሎን ላይ ያለዉ ፍርድ በራዕይ 17 እና 18 ላይ የሚወርደዉ ትንቢት ጥላ/ማሳያ እንዴት ይሆናል ?
-
በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በእዉነት እና በጽድቅ ሳይሆን በእስራኤል አምላክ ተብሎ የተጠሩትን እስራኤላዊያንን እንዴት የሚመስሉ ናቸው ? (ኢሳ 48፡ 1, 2ጢሞ 3፡ 5, 4፡ 3-4)
-
በኢሳይያስ 48 መጨረሻ ላይ (ቁጥር 21) ሕዝቡ የቀደመዉን የእግዚአብሄርን ስጦታ አስታወሱ ፤ ለአሁን እና ለወደፊት እግዚአብሄርን ለመታመን በሚታገሉ/በምትታገሉ ጊዜ ራሳችሁን ወይም ሌሎችን ቀድሞ እግዚአብሄር የሰጣቸዉን/የሰጣችሁን እንዴት ታስታዉሳላችሁ ?
-
በኢሳይያስ 49 በመጀመሪያዉ ግማሽ ክፍል ላይ የተገለፀ የሆነዉ ማነው ? (ኢሳ 53፡ 3, ማር 10፡ 45, ሉቃ 1፡ 31, 2፡ 32, ፊል 2፡ 6-7, ራዕ 19፡ 16)
-
በኢሳይያስ (47-49) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 49:5
“And now, says the LORD, who formed me from the womb to be His Servant, to bring Jacob back to Him so that Israel might be gathered to Him; for I am honored in the sight of the LORD, and my God is my strength.”
ኢሳይያስ ስለሚመጣው አገልጋይ የአለም አዳኝ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ተነበየ ፡፡ እግዚአብሔር ኢየሱስን ገና በእናቱ ማህጸን የሰራው አለምን እንደ አገልጋይ እንድያገለግልና እስራኤልን ወደ እግዚአብሔር እንድመልስ ነው ፡፡ የሚመጣውም አዳኝ የተናቀ ይሆናል ፣ በሰዎችም ፊት ይጠላል ፣ ለመሳፍንትም አገልጋይ ይሆናል ፡፡ ሆኖም ግን በእግዚአብሔር ምክንያት ነገሥታት በፊቱ ይቆማሉ ንግሥቶችም ይሰግዳሉ ፡፡
ዛሬ ገና በእናታችሁ ማህጸን ሳላችሁ እንደተሰራችሁ አስቡ ፡፡ ተጠርታችኋል ፣ አለማ አላችሁ ደግሞም በህይወታችሁ መድረሻ አላችሁ ፡፡ ወደዚህ በአጋጣሚ አልመጣችሁም ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ከብራችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ብርታታችሁ ይሆናል ፡፡ ስለራሳችሁ ልጆች እየጸለያችሁ ሊሆን ይችላል ወይም እንደ ልጁ ሆናችሁ እግዚአብሔርን እየፈለጋችሁ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህን እውነት ተቀበሉ ፡- ውብና ድንቅ ሆናችሁ ተፈጥራችኋል ፡፡ በእናታችሁ ማህጸን ሳላችሁ የተሰራችሁት እንደዚህ ላለ ጊዜ ነው ፡፡ ጭንቀትና ግራ መጋባት ሊኖር ይችላል ነገር ግን አስታውሱ ፣ እግዚአብሔር እናንተንና የምትወዷቸውን በስም እንደጠራችሁ ፡፡ እግዚአብሔር ስለ ክብሩ ሲል ህይወታችሁን ይታደጋል ፡፡ እጁ በእናንተ ላይ ናት ፡፡ ስለዚህም ከጓዳችሁ ትከሻችሁን መለስ አድርጋችሁ አይኖቻችሁን ወደ ፊት በኢየሱስ ላይ በማድረግ ውጡ ፡፡ በጸሎት ጽኑ እንድሁም በእግዚአብሔር እውነት ተመላለሱ ምክንያቱም ዛሬ እርሱ ለእናንተ እቅድ ስላለው ! የተወለዳችሁት ከዓለማ ጋር ነው !
“ አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና ፥ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። “
- ኢሳይያስ 49፡5
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 139:13–16 — “ አቤቱ ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና ፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች ። እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም ። ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ ። “
ኢሳይያስ 49:1 — “ ደሴቶች ሆይ ፥ ስሙኝ ፥ እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ ፥ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን ጠርቶኛል ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን አንሥቶአል “
ኢሳይያስ 49:7 — “ የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም ፥ እግዚአብሔር ፥ ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል ፦ ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፥ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።