God Of Plans And Promises
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 45-46 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትንቢት ምን መሆን አለበት ? አንድ ትንቢት ነጠላ፣ እጥፍ ወይም ሰዎስት እጥፍ ንብብር መሆኑን ሁል ጊዜ አናዉቅም ፡፡ ትንቢት የወቅቱን ጊዜ፣ የወደፊቱን ጊዜ ወይም ቀልድ ሊሆን የሚችልን በጣም ሩቅ የሆነ ወደፊትን እንደሚገልፅ መለየት ፡፡ የዛሬዉ መልዕክት በእግዚአብሄር በመሾም ተመርጦ የነበረዉን የፋሪስን ንጉስ ቂሮስን ያመለክታል ፤ በእግዚአብሄር እቅድ እና በእግዚአብሄር አላማ በመመራት ቂሮስ የእስራኤል ተከራካሪ ሆነ ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (45፡ 1-4)፡ ቂሮስ ዝነኛ/በጣም የታወቀ ከመሆኑ በፊት በሚገባ እንደ እግዚአብሄር ተሾዐሚ ተናገረ ፤ ይህ በኤርምያስ ላይ የእግዚአብሄርን ንግግር ፡ “ በሆድ ሳልሰራህ አዉቄሃለሁ ከማኅጸንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሀለሁ “ (ኤር 1፡ 5) የሚለዉን ንግግር ይመስላል ፡፡
እግዚአብሄር እቅድ አለው ፡፡ ሕዝቡ አሁንም በስፍራቸዉ ባይሆንም እንኳን እግዚአብሄር ሊያወጣቸዉ ይችላል ፡፡ የተቀባ መሆን ማለት ለእግዚአብሄር አላማ የተለዬ መሆን ማለት ነው ፡፡ “ አሕዛቦችን ለማስተዳደር…. የነበገስታቶችን ትጥቅ ለማስፈታት “ ቂሮስን እንደመሳሪያነት እግዚአብሄር በመጠቀ አሕዛቦች ያሻሽላል ፡፡ ቂሮስ ባቢሎንን የሚያሸንፍን የፋሬስን ሕዝም ይመራል ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን በሚጠቅም መንገድ ፍቃዱ የታወቀ እንዲሆን አይሁዳዊ ያልሆነን ሰዉ ተጠቀመ ፡፡
ኢሳይያስ (45፡ 5-8)፡ እግዚአብሄር በቀጥታ ለቂሮስ ተናገረ ፡፡ ምንም እንኳን ቂሮስ እርሱን ባያዉቀዉም እግዚአብሄር ቂሮስን እንደሚያበረታዉ ተስፋን ሰጥቶታል (ቁጥር 5) ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር ስኬትን እንደሚያደርግ እና ጥፋትን እንደሚፈጥር ተናገረ (ቁጥር 7) ፡፡ መፅኀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ፍቅር እንደሆነ ቢያስተምርም እግዚአብሄር ፍርድን በማምጣት ችግርን ያመጣል ፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም ዙሪያ ሰፍረዉ የነበሩት 185,000 የአሶራዊያንን ወታደሮች እንዲገድል አንድ መልዓክን አዘዘው (2ነገ 19፡ 35) ፡፡
ኢሳይያስ (45፡ 9-10)፡ እግዚአብሄር ያልተወለደ ንጉስም እንኳን ቢሆን “ ከሰሪዉ ጋር ለሚከራከር “ ወዬዉለት ይላል (ቁጥር 9) ፤ እግዚአብሄር የሸክላ እንስራ ሰሪዉን ሲጠይቅ እና ልጅ ቤተሰቦቹን ሲጠይቅ የሚለዉን ምሳሌ ይጠቀማል ፤ በሁለቱም ምሳሌ እቅድን የመስራት ኃላፊነት ስልጣን ነበራቸው ፡፡
ኢሳይያስ (45፡ 11-13)፡ ምንም እንኳን ቂሮስ በራሱ መንገድ በግትርነት የሚሄድ ቢሆንም እግዚአብሄር የሚፈፅመዉ እቅድ ነበረው ፤ እግዚአብሄር ቂሮስን “ ከተማዉን መልሶ እንደሚገነባ እና ምርኮኞቹን ነፃ እንደሚያወጣለት “ ተናገረ (ቁጥር 13) ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህን ሁሉንም ፍላጎቶች በቂሮስ ልብ ዉስጥ አስቀመጠ ፡፡
ኢሳይያስ (45፡ 14-17)፡ በቁጥር 15 መጀመሪያ ላይ ቂሮስ በክርስቶስ አይነት ታይቶ የነበረ እና የኢሳይያስ ትንቢት በምልከታው ሁለት እጥፍ ሆነ ፡፡ በመጨረሻም እስራኤል “ በጌታ በዘላለማዊ ማዳኑ የዳነ ይሆናል “ (ቁጥር 17) ፡፡ ዘላለማዊ የሚለዉ ቃል መጀመሪያ የሌለዉ እና መጨረሻ የሌለዉ ማለት ነው ፡፡
ኢሳይያስ (45፡ 18-25)፡ ስለ ወደፊቱ በነቢያቶቹ ከእግዚአብሄር አዋጅ የተነሳ ጣዖቶች ሙሉ በሙሉ ሀሰተ እንደ ነበሩ ተነቅፈዋል (ቁጥር 20-21) ፡፡ አሁን እግዚአብሄር ወደፊት ሰዎች ሁሉ “ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል ምላስ ሁሉ በእኔ ይምላል “ በማለት ተናግሯል (ቁጥር 23) ፡፡
ይህ ጥቅስ ከሮሜ (14፡ 11) ጋር ይመሳሰላል፡ “ እኔ ሕያዉ ነኝ ይላል ጌታ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሄርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና “ ፤ በአዲስ ኪዳንም እንኳን የኢሳይያስ ትንቢት ሁሉም ሰዉ እንደሚያዉቀዉ እና እንደሚሰግድለት “ አሁንም ወደፊት እንደሚመጡ “ ጳዉሎስን አስታወሰው ፡፡
ኢሳይያስ 46፡ ከሌሎች አማልዕክት በተቃራኒ ጌታ/እግዚአብሄር ሕዝቡን ከምርኮ መታደግ እንደሚችል ራሱን ያሳያል (ቁጥር 1-4) ፡፡ እግዚአብሄር ከሌሎች አማልዕክት ጋር የሚወዳደር አይደለም (ቁጥር 5-8) ፡፡ እግዚአብሄር እንደ እግዚአብሄር ኃይል እና ማዳን ምልክት (ቁጥር 13) በእስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም በመመለስ እንደሚደመደም“ ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ያለዉን እዉቀት “ (ቁጥር 10) ተናገረ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ተወልዶ ባልነበረዉ ንጉሱ ቂሮስ አላማዉን ይፈፅማል ፡፡ እግዚአብሄር ከመጀመሪያዉ እስከ መጨረሻዉ ስለሚያውቅ እስካሁን ባልተወለደ ንጉስ አላማዉን እንደሚፈፅም ነግሯችሁ አላማዉን በእኛ በኩል እና በቤተ ክርስቲያኑ እንደሚፈፅም አናምንም ?
ጥያቄዎች
-
በኢሳ (45፡ 1-13) እግዚአብሄር ስለ ቂሮስ ቀድሞ ምን ተናገረ ? እግዚአብሄር ይህን ያክል ለቂሮስ የሚያደርገዉ ለምንድን ነው ? የተነገረ ነገር ወደ ማለፍ መጥቷል ? (ዕዝ 1፡ 1-8)
-
በኢሳይያስ 45 የክርስቶስን አይነት ተግባር የት ታያላችሁ ?
-
እግዚአብሄር በኢሳይያስ በኩል በኢሳይያስ 45 ዉስጥ “ ከእኔ ዉጪ ሌላ አምላክ የሚለዉን “ ሰባት ጊዜ ለምን እንደደጋገመው ምን ታስባላችሁ (ኢሳ 45፡ 5, 6, 14, 18, 21(2ጊዜ), 22) ? ሰባት ጊዜ ያለበት እዉነት አስፈላጊ ነው ?
-
በኢሳይያስ 45 ላይ ላለዉ ነገር ሁሉ ምንጭ እንደሆነ እግዚአብሄር ራሱን በምን መንገድ ገለፀ ? ይህን ለምን እንዳደረገ ምን ታስባላችሁ ?
-
ኢሳ (45፡ 9) በምን መንገድ በዚህ (በግል ወይም በህብረት) ጥፋተኞች እንሆናለን ? (ኢሳ 64፡ 8, ሮሜ 9፡ 20-21)
-
በኢሳ (46፡ 10) እግዚአብሄር ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ብሎ መናገሩ ምን ማለቱ ነው ? ይህ እግዚአብሄር እንደሆነና ሌላ እንደሌለ የተደጋገመ ንግግሩን እንዴት ይደግፋል ? (ኢሳ 46፡ 9-11)
-
በኢሳይያስ (45-46) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 45:18
“For this is what the LORD says—God is the Creator of the heavens. He formed the earth and made it. He established it; He did not create it to be empty, but formed it to be inhabited—‘I am Yahweh, and there is no other.’”
እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል ፡- “ እኔ ምድርን የሠራሁና ያደረኩ ያጸናሁዋትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ አይደለም ” በማለት ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር ምድርን ሰርቷታል ፣ እርሱም አጽንቷታል ፡፡ እግዚአብሔር ሰርቷችኋል ፡፡ እርሱ ስለምድርና ስለእናንተ ሁሉን ያውቃል ፡፡ እርሱ ያህዌ ነው ፡፡ እንደ እርሱ ያላ ሌላ አምላክ የለም ፡፡ ይህም ሁሉን የፈጠረ አምላክ እርሱ በስማችሁ ጠርቷችኋል ፡፡
ጥያቄውን ሰምታችኋል ? እንዴት ነበር ዓለም የተፈጠረው ? እንዴት ነበር ወንድና ሴትስ ወደ መኖር የመጡት ? በእግዚአብሔር ቃል የምታምኑ ከሆነ ፣ ይህን እውነት እመኑ እወቁም ፡- እግዚአብሔር ምድርን ፈጥሯል ደግሞም እንድሁ እናንተንም ፈጥሯል ፡፡ እንደ ያህዌ ያለ ሌላ አምላክ የለም ፡፡ አሳቡ ይከናወናል ፍቃዱንም ይፈጽማል ፡፡ እናንተ በእቅዱ ውስጥ ናችሁ ፡፡ ለእናንተ ብቻ የሚሆን እቅድ አለው ምክንያቱም በስም ጠርቷችኋልና ፡፡ እስኪ በስማችሁ ስለሚጠሩዋችሁ ሰዎች አስቡ ፡- ቤተሰቦቻችሁ ፣ ጓደኞቻችሁ ፣ የሥራ ባልደረቦቻችሁ እናም ጎረቤቶቻችሁ ፡፡ እነዚህ ሰዎች በደንብ አድርገው ያውቋችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በስም ጠርቻችኋለሁ ይላል ፡፡ አዎን የአለም ፈጣሪ የሆነው እርሱ በስም ጠርቻችኋለሁ ይላል ፡፡ እርሱ ለዚህ ጊዜ ፣ ለዚህ ዘመን እናንተን ሾሟችኋል ፡፡ እርሱ እንዲህ ይላል ፡- “ እኔ ሠርቻችኋለሁ እኔም አነሣችኋለሁ ፤ እኔ እሸከማችኋለሁ እኔም አድናችኋለሁ ። “ እናንተ ለዚህ አለም ፈጣሪ ለእርሱ አስፈላጊ ናችሁ ፡፡
“ ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር ፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም ፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ ፥ እንዲህ ይላል ፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ። “
- ኢሳይያስ 45፡18
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘፍጥረት 1:1, 26–28 — “ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ…… እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን ፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው ፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ። እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት ፥ ግዙአትም ፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው ። “
ኢሳይያስ 45:4 — “ ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ ፥ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም ። “
ኢሳይያስ 46:4 — “ እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ ፥ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።