Restoration Of Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 43-44 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስ (43-44) ቶም ቼይፈር ትናትና ባስተማረዉ ላይ የሚቀጥል ነው ፤ እነዚህ ምዕራፎች የአገልጋይ አስተሳሰብን ያወያያሉ - አገልጋዩ እስራኤል ወይም ኢየሱስ እንደሆነ እንድንደነቅ ይተወናል ፡፡ በኢሳይያስ 43 ላይ ማስተማርን መርጠናል ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ መታደስ አስፈላጊ ስለሆነ ፡፡ እግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ምን እያደረገ እንደሆነ ሰዎች እይታቸዉን እንዲያጡ አንፈልግም ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (43፡ 1)፡ በምዕራፍ 43 እስራኤል በምርኮ እንደሆነች ተደርጋ ታይታለች ነገር ግን እግዚአብሄር እንደሚቤዣቸዉ ተስፋን ይገባል ፤እግዚአብሄር ፈጥሯቸዉ ስለ ነበር ይጠነቀቅላቸዋል ፡፡ የዕብራዊያን ቃል ለመቤዠት የሚቤዥ ዘመድ ለሚለዉ ቃል ጥቅም ላይ ዉሎ ከነበረዉ ዕብራዊያን ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ቡዔዝ ሩትን በተቤዣት/በዋጃት ጊዜ የሚቤዥ ዘመድ መልሶ ከሩት መፅሀፍት ጋር ያስተሳስራል ፡፡ አንድ የሚቤዥ ዘመድ “ የቤተሰብ አባልን እና ንብረታቸዉን ከባርነት ለእነርሱ እዳቸዉን መክፈል የሚችል የቅርብ ዘመድ ነው “ ፤ ይህ አስፈላጊ ነዉ ምክንያቱም እስራኤል በባቢሎን ምርኮ ነበረች ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ማድረግ የሚፈልገዉ ትልቅ ስዕል ነው ፤ እግዚአብሄር ከሕዝቡ ጋር ያለዉን የቀረበ ግንኙነት/ትስስር በሚያሳይ መንገድ በስማቸዉ ይጠራቸዋል ፡፡ በዚህ ላይ ለመመልከት ሁለት የተለያዩ መንገዶች አሉ ፤ አንዱ ለእነዚህ ሰዎች እግዚአብሄር ስሙን ገልጧል (ዘጸ 6፡ 2-8) ፤ ሁለተኛው እግዚአብሄር እስራኤልን እንደ በኩር ልጅ እንደሆነ ተናግሯል (ዘጸ 4፡ 22) ፡፡ እግዚአብሄር በስማቸዉ ያውቃቸዋል ፡፡
ኢሳይያስ (43፡ 2)፡ እግዚአብሄር በዉሃዎች እና በወንዞች ዉስጥ በሚያልፉ ጊዜ አብሯቸዉ እንደሚሆን ተስፋን ሰጥቷቸዋል ፤ እግዚአብሄር ከግብፅ በመዉጣት ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር ነበር ፡፡ እግዚአብሄር በእሳት ዉስጥ ከእነርሱ ጋር ነበር - ከዳንኤል መፅሀፍት ወደ አይምሮዬ ሲድራቅ፣ ሚሳቅንና አብድናጎን በማምጣት ያስታዉሰኛል ፡፡ በምርኮ ዉስጥ ቢሆኑም እንኳን እግዚአብሄር ቀድሞ እንደነበረዉ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ተስፋን ይሰጣቸዋል ፤ መፅናናትን ያመጣላቸዋል ፡፡
ኢሳይያስ (43፡ 3)፡ እግዚአብሄር ስለ ቤዛነታቸው ግብፅን፣ ኩሽን እና ሳባን እንደ ቤዛነት በመስጠት ከፈለ ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ከባቢሎን ለመቤዠት እነዚህን ሰዎስት ሀገራት እንደ ቤዛነት ተጠቀማቸው ፤ በማቴ (20፡ 28) ኢየሱስ “ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣምና “ አለ ፡፡ ይህ ክስተት በመጀመሪያዉ መምጣት ጊዜ ኢየሱስ ህይወቱን እንደቤዛ እንደሚሰጥ እንደ ጥላ ያገለገለ ነው ፡፡
ኢሳይያስ (43፡ 4)፡ የከበርህ የሚለዉ ቃል ኃብትን ወደ አይምሮ ያመጣል ፡፡ መዝ (135፡ 4) እስራኤልን እንደ “ እግዚአብሄር የተያዝ ኃብት “ ይገልፃል ፤ እግዚአብሄር በግልፅ እስራኤላዊያንን ይወዳቸዋል እኛንም እንዲሁ ይወደናል ፡፡ ዛሬም ይህን መስማት ያስፈልገናል ፤ እግዚአብሄር እስራኤልን በሌሎች ሕዝቦች መሞት በኩል ተቤዣቸው ፡፡
ኢሳይያስ (43፡ 5-7)፡ በግልፅ የእግዚአብሄር ሰዎች ተበታትነዋል ፤ አሶራዊያን ከሰሜኑ መንግስት ብዙ ሕዝቦችን አጥፍተዋል ፤ ተገድለዉ ያልነበሩት ሰዎች ደግሞ ሌላ ስፍራ ተብነዉ ነበር ፡፡ ከዚያም የደቡቡ መንግስት ደግሞ በምርኮ ወድቆ ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ሁሉም አንድ ሕዝብ ሆነዉ እንደ ነበሩበት እንደ ሰለሞን ዘመን መልሶ በማምጣት አንድ እንደሚያደርጋቸው ተስፋን ገባ ፤ አንዳንድ ሰዎች እነዚህ ጥቅሶች እንደተፈፀሙ ይናገራሉ ፡፡ ከምርኮ ነፃ በወጡ ጊዜ ተመልሰዉ ወደ ምድራቸዉ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ ፡፡
History.com የእስራኤልን ታላቅ የጊዜ ቅደም ተከተልን ይሰጣል ፡፡ ንጉስ ዳዊት ከክርስቶስ መወለድ በፊት 1000 ዐመት አስተዳድሯል ፤ ልጁም ሰለሞን እርሱን በመተካት በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደሱን ገነባ ፡፡ ከክርስቶስ መወለድ በፊት 931 አመት ያክል እስራኤል ወደ ሁለት መንግስት ተከፍላ ነበር - ወደ ሰሜን መንግስትና ወደ ደቡብ መንግስት ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት አሶር የሰሜኑን መንግስት በመዉረር አጠፋ ፤ ከክርስቶስ ልደት በ586 በፊት ባቢሎን ኢየሩሳሌምን ያዘ ፡፡ የቀደመዉ ቤተ መቅደስ ከክርስቶስ ልደት በ516 በፊት በሁለተኛው ቤተ መቅደስ የተተካ ነበር ፡፡
በቀጣዮቹ ክፍለ ዘመኖች ላይ ብዙ ቡድኖች እስራኤልን በመያዝ አስተዳድረዋል፡ ፋሪስ፣ ግሪክ፣ ሮም፣ አረብ፣ ፋትሚድስ፣ ሰልጂክ ቱርክ፣ የእስላማዊ ቡድን፣ ግብፃዊያን፣ ማምሉክ፣ እስላማዊያን እና ሌሎች ቡድኖች ፡፡ ከ1517 እስከ 1917 ድረስ እስራኤል በኦቶማን ኢምፓየር የተዳደረች ነበረች ፤ በመጀመሪያዉ የአለም ጦርነት የብሪቴን የዉጪ ጉዳይ ፀሀፊ ያዕቆብ ባልፎር በፍልስጤም የአይሁዶች የመኖሪያ ስፍራ መመስረትን ደገፈ (የባልፎር አዋጅ) ፡፡ የመጀመሪያዉ የአለም ጦርነት በ1918 ሲያበቃ የኦቶማን ኢምፓየር በማብቃቱ ብሪቴን ፍልስጤምን ተቆጣጠረች ፤ ይህ የአረብ ተቃዉሞ ቢኖርም በ1922 በተባበሩት መንግስታት ፀደቀ ፡፡ ዛሬም በጋዛ ስርጥ፣ ጎላን ከፍታዎች እና ዌስት ባንክን ጨምሮ በብዙ ስፍራዎች ግጭቱ ይቀጥላል ፡፡
በህይታችን ላይ ነቢዩ ኢሳይያስ አዉርቷቸዉ ስለ ነበሩት ነገሮች ትንቢታዊ ቃሎች ወደ ፍሬአማነት መምጣታቸዉን እየለመድናቸዉ ነው ፡፡ በኋላም በአስራ ዘጠነኛዉ እና በሀያኛዉ ክፍለ ዘመን የፂዎናዊት እንቅስቃሴ የአይሁዶችን የቀድሞ ምድር እንደገና ለማቋቋም ሰራ ፡፡ ብዙ አይሁዶች ወደ ቀድሞ ቅዱስ ምድራቸዉ ፈለሰዉ ገቡ ፤ በ1882 እና 1903 መካከል 35,000 ያክል አይሁዶች ወደ ፍልስጤም እንደገና ስፈረዋል ፤ ሌላ 40,000 በ1904 እና በ1914 መካከል በፍልስጤም ሰፍረዋል ፡፡ በናዚ አገዛዝ ጊዜ አይሁዶች በፍልስጤም የስደት መሸሸጊያን በማግኘት በአዉሮፓ ሀገራት መከራ ገጠማቸው ፤ የአይሁድ ሕዝቦች ለሆኑት የቀድሞ ምድርን ድንበር የሚመሰርቱትን ፂዎናዊያንን ያዝአቸው ፡፡ ይህ የፖለቲካ እንቅስቃሴ አልነበረም የመፅኀፍ ቅዱስ ትንቢት ወደ ፍሬ እንዲመጣ መንገድን የሚያዘጋጅ እንጂ ፡፡ በ1947 የተባበሩት መንግስታት ፍልስጤምን ወደ አይሁዶች እና አረብ ሀገራት የመከፋፈል እቅድን አፀደቀ ነገር ግን እቅዱን አረቦች ተቃወሙ ፡፡ በ1948 ዳዊት ቤን ጊሪዎን ጠቅላይ ሚንስተራቸዉ በሆነ ጊዜ እስራኤል አንድ የታወቅች አገር በመሆን አወጀች ፤ ይህ ትክክለኛዉን የድንበር ቅርፅ በወሰድች ጊዜ ነበር ፡፡ ይህ ሕዝብ ለእግዚአብሄር የከበረ ስለነበረ ይህ ተፈጠረ ፤ ስለሚወዳቸዉ በአንድ ላይ እንደገና ሰበሰባቸው (ኢሳ 43፡ 4-5)፡፡
በዊክፒዲያ የሕዝብ ቁጥርን በሰጠዉ መሰረት ከ890,000 በላይ ሩሳዊያን ከሰሜን መጥተዋል ፤ ሮማኒያ ወደ ዚች ትንሽ ሀገር 199,000 ልካለች ፤ ፖላንድ 184,000 ልካለች ፤ ፍራንስ 87,000 ልካለች ፡፡ እነዚህ ተጨባጭ ቁጥሮች እግዚአብሄር ሕዝቡን አይሁዶችን መልሶ ወደ ምድራቸዉ እንዳመጣቸዉ ያሳያል ፡፡ በ2015 6.2ሚሊዮን አይሁዶች ነበሩ ፤ በአሁኑ ጊዜ 8.9 ሚሊዮን ሰዎች ወደ ምድሪቱ መጥተዋል ፡፡ በ2017 በተለዬ ስለ አይሁዶች (ስለሙስሊም፣ ክርስቲያኖች ወይም ዶርዝ ሳይሆን) በምድሪቱ ላይ 6.5 ሚሊዮን አይሁዶች ነበሩ ፡፡ ከደቡብ ኢትዮጲያ 133,000 አይሁዶችን ስትሰጥ ሞሮኮ 480,000 አይሁዶችን ሰጥታለች ፤ ከኢራን 140,000 አይሁዶች ተመልሰዋል ፡፡ ዮናይትድ ስቴት፣ ካናዳ፣ አዉስትራሊያ እና ኒዉ ዝላንድ 181,000 ልከዋል ፡፡ ቁጥር በ1950 ካለዉ 1.3ሚሊዮን በ2019 በግምት ወደ 9ሚሊዮን ማደጉን ቀጥሏል ፡፡ እስራኤል የእግዚአብሄር አይን ብሌን ነው ፤ መዝ (132፡ 13-14) ኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ቤት ነች ይላል ፡፡ የእግዚአብሄር ፍላጎት ቤተ ሰቦቹ አብረዉት እንዲሆኑ ነው ፤ እግዚአብሄር ልጆቹን ይወዳል እንዲሁም እነርሱን መልሶ ለማምጣት የሚወስደዉን ማንኛዉንም ነገር ያደርጋል ፡፡
ኢሳይያስ (43፡ 19-20)፡ በምርኮ እያሉ እግዚአብሄር አዲስ የሆነ ነገር እንደሚያደርግ እየተናገረ ነው ፤ ታዩታላችሁ? ኢሳይያስ አሁን አይሁዶች ባቢሎንን እንደሚለቁ እየተነበዬ ነው ፡፡ እግዚአብሄር በምድረበዳ መንገድን እንደሚያዘጋጅ እና በኋላም እግዚአብሄር ይህን ለማድረግ ቂሮስን ሲጠቀምበት እናያለን ፡፡
ኢሳይያስ (44፡ 24-28)፡ እግዚአብሄር አይሁዶችን ከባቢሎን ምርኮ በማዉጣት እንደሚያመጣቸው ተስፋን ገባ ፤ እግዚአብሄር ሁሉም ነገር ከተሞቹ እና ማህበረሰቡ ተመልሰዉ ይመጣሉ ማለቱ ነው ፡፡ እግዚአብሄር እነዚህ ነገሮችን ለማድረግ እረኛዉን ቂሮስን እጠቀምበታለሁ አለ ፤ ነገር ግን ኢሳይያስ ይህን በፃፈበት ጊዜ ቂሮስ በአካል እንዳልነበረ ማወቅ አስፈላጊ ነው ፤ ኢሳይያስ ይህን ትንቢት ካሳወቀ ከአንድ መቶ ዘጠና አመታት በኋላ (190) በመጨረሻም ቂሮስ ወደ መልክ/ወደ ገሀዱ አለም ገባ /ተገኘ ፡፡ ከክርስቶስ ልደት 538 በፊት ቂሮስ አይሁዶች በመመለስ ኢየሩሳሌምን መልሰዉ እንዲገነቡ የሚፈቅድ ድንጋጌን አዘጋጀ ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ለሕዝቡ እቅድ አለኝ ሲል ይህን ማለቱ ነው ፤ ይህ እግዚአብሄር ሕዝቡን ወደ ምድራቸዉ መልሶ ለማምጣት ስለተጠቀመበት የፋሪሲ ንጉስ ስናነብ እንኳን በጣም ቀልድ ይሆናል ፡፡
7 “Demographics of Israel”; available from https://en.wikipedia.org/wiki/Demographics_of_Israel.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 1186.
Wiersbe, p. 1186.
Wiersbe, p. 1186.
History.com, “Israel,” 30 June 2017; available from https://history.com/topics/middle-east/history-of-israel.
History.com, “Israel,” 30 June 2017; available from https://history.com/topics/middle-east/history-of-israel.
History.com, “Israel,” 30 June 2017; available from https://history.com/topics/middle-east/history-of-israel.
ጥያቄዎች
-
እንዴት እና ለምን እግዚአብሄር እስራኤልን መረጠ (ዘዳ 7፡ 6-11) ? በኢሳይያስ 43 ለእስራኤል ምን ተስፋን ሰጠ ?
-
እግዚአብሄር እስራኤልን ከምን ነበር ተቤዥቷቸዉ የነበረው ? ይህ መቤዠት መቼ ነዉ የሚፈፀመው ? (ዘካ 12፡ 10- 13፡ 1, ሮሜ11፡ 25-27)
-
በኢሳይያስ 43 እግዚአብሄር ምን ነገርን ደገመ አለ ? እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች ለምን እንዳብራራ ምን ታስባላችሁ ? መንፈስ ቅዱስ የሚያብራራላችሁና የሚደግምላችሁ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው ?
-
በኢሳይያስ 44 መሰረት ሌሎች አማልዕክትን እና ጣዖትን በሚያመልኩት ላይ የሚሆኑት አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው ?
-
እስራኤል ጣዖትን ሳይሆን እርሱን ሲያመልከዉ እግዚአብሄር ምንን አድርጎ ነበር (ኢሳ 44፡ 21-22) ? እግዚአብሄር ለእናንተ ስለመታመኑ እንድታስታዉሱ የሚጠይቃችሁ ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው ? (1ሳሙ 7፡ 12)
-
በኢሳይያስ (43-44) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 43:1–2
“Now this is what the LORD says—the One who created you, Jacob, and the One who formed you, Israel—‘Do not fear, for I have redeemed you; I have called you by your name; you are Mine. I will be with you when you pass through the waters, and when you pass through the rivers, they will not overwhelm you. You will not be scorched when you walk through the fire, and the flame will not burn you.’”
ኢሳይያስ በግልጽ እግዚአብሔር የእስራኤልን ህዝብ ምርኮ እንደሚመልስ ወደ ምድራቸው መልሶ እንደሚያመጣቸው ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔርም ለእነርሱ ፡- እወዳችኋለሁ ፤ በስምም ጠርቻችኋለሁ ፣ በፊቴ ውድና የተከበራችሁ ናችሁ በማለት አረጋገጠላቸው ፡፡ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ ፣ አትፍሩ በማለትም አስገነዘባቸው ፡፡ ህዝቡ በህይወታቸው ጥፋትን በሚስከትሉ ነገሮች ውስጥ ያልፋሉ ሆኖም ግን አይጎዱም ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስለነበር ፡፡
እግዚአብሔር እንደ ሌሎቹ አማልዕክትና ጣዖታት አይደለም ፡፡ ይሄ እግዚአብሔር ያድናል ፡፡ ይሄ እግዚአብሔር ይታደጋል ደግሞም ምርኮን ይመልሳል ፡፡ ይህ አዳኙ እግዚአብሔር አዲስን ነገር ያደርጋል ደግሞም ምንም መንገድ በሌለበት እርሱ መንገድን ያዘጋጃል ፡፡ እንደ ዓለታችሁ ፣ መሸሸጊያችሁ ፣ ነጻ አውጫችሁና እንደ ደህንነታችሁ እንደ ያህዌ ያለ ሌላ አምላክ የለም ፡፡ ዛሬ ያላችሁት የትም ይሁን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ይወዳችኋል ደግሞም ወደ እርሱ ይመልሳችሁ ዘንድ ይናፍቃል ፡፡ በእሳት ውስጥ ስትሄዱ እርሱ በዚያ አለ ደግሞም በጥልቁ ውኃም ውስጥ ስትሄዱ እርሱ በዚያም አለ ፡፡ እርሱ ይጠብቃችኋል ደግሞም ወደ ቀድሞው ይመልሳችኋል ፡፡ ዛሬ ለህይወታችሁ ይህን እውነት ብቻ ተቀበሉ እርሱም ፡- አንዱና ብቸኛው አዳኝ እግዚአብሔር ይወዳችኋል ፡፡ በፊቴ የተከበራችሁ ናችሁ ብሎ ይጠራችኋል ፤ እርሱ ከእናንተ ጋር ነው ፡፡
“ አሁንም ያዕቆብ ሆይ ፥ የፈጠረህ ፥ እስራኤልም ሆይ ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ ፥ አንተ የእኔ ነህ ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም ፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም ፥ ነበልባሉም አይፈጅህም ። “
- ኢሳይያስ 43፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 43:4a — “ በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና ፥ እኔም ወድጄሃለሁና ፡፡ “
ኢሳይያስ 43:10–12 — “ ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም ። እኔ ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም ። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም ፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ እኔም አምላክ ነኝ ። “
ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።