The Servant's Mission
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 41-42 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ከኢሳይያስ 40 የዚህ “ መፅኃፍ ፍርድ “ ወደ “ መፅናናት መፅኃፍት “ ስለመሻገሩ ጥቂት ነገሮችን አጉልቶ በማየት እንጀምር ፡፡ ኢሳይያስ በፍፁም በምዕራፎቹ ወይም መፅሀፉን በዚያ መንገድ በማስቀመጥ ቢፅፍም በምዕራፍ 40 የመጀመሪያዎቹ ቁጥሮች ይህን ለዉጥ አጉልተዉ ያሳያሉ፡ “ አፅናኑ ሕዝቤን አፅናኑ “ (ቁጥር 1) ፡፡ ኢሳይያስ ወደ ንግስና የፅሁፍ ክፍሉ እየተጓዘ ነበርይህም ንጉስ በኢሳይያስ 42 እንደምናየዉ አገልጋይ ነው ፡፡
ከኢሳይያስ (40፡ 31) ወደ ኢሳይያስ 41 ሁሉም ሽግግሮች እስራኤልን የያዟት ሕዝቦች ሁሉ ወደ ፍርድ የተጠሩ እንደሆነ ይናገራል ፤ ይህ በባቢሎን ስደት ያሉትን ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዉ እንዲጓዙ ያዘጋጃቸዋል ፡፡ በኢሳ (41፡ 1-7) ኢሳይያስ በባቢሎን አማልዕክቶች ላይ የመከራ ፍርድን ያስቀምጣል ፤ በኢሳ (41፡ 8-20) ኢሳይያስ እግዚአብሄር ህዝቡን እያረካ እንደሆነ ያሳያል ፡፡ በቁጥር (8-10) እግዚአብሄር ከሕዝቡ ጋር እንደሚሆን፣ እንደሚያበረታቸዉ እና እንደሚያፀናቸው ተስፋዉን እንደ ገና ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ስለሚረዳቸዉ እንዳይፈሩ ነገራቸው ፤ እግዚአብሄር ተቤዢአቸዉ እየመጣ እንደ ነበር ነገራቸው (ኢሳ 41፡ 14) ፡፡ ኢሳይያስ ምዕራፍ 41 ስለ ባቢሎን ጣዖቶች ማስረጃ በመስጠት (ቁጥር 21-29) እና የእግዚአብሄር ከተማ እና ሕዝቦች ስለሚሆኑት ስለ እስራኤል በማዉራት ይጨርሳል ፡፡ ኢሳይያስ ሕዝቡን እና ምድሩን ሁለቱንም በመጥቀስ እንደ ፂዎን ገለፃቸው ፤ ይህ ሁሉ ኢሳይያስ 42 ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤል ድነትንና ነፃ መዉጣትን በማሳወቅ በመንፈስ ቅዱስ የሚያበረታቸዉን እና የሚሰጣቸው አገልጋዩን እንደሚልክላቸዉ ተስፋን ሰጠ ፡፡ ይህ ምዕራፍ የአገልጋዩ መዝሙር ተብሎ የሚታወቀዉን የኢሳይያስ ክፍልን ያስተዋዉቃል ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (42፡ 1)፡ ይህ ጥቅስ በኢሳይያስ መፅኀፍት ዉስጥ በመጀመሪያዎቹ አራት የአገልጋይ ዝማሬ ይጀምራሉ ፡፡ እነዚህ አራት መዝሙር ጥቅሶች የጌታ አገልጋይን የመሲሁን አገልግሎት፣ መከራ እና ብልጫ/ከፍታ ይገልፃሉ ፤ ኢሳይያስ በመሲሁ ላይ በማተኮር ሁሉም ኃይል በእርሱ ላይ ያለበት የእግዚአብሄር ባሪያ እና አገልጋይ እንደሆነ ይገልፃል ፡፡ ባሪያ እና አገልጋይ ቢሆንም እንኳን አሁንም በኃሳብ ቅርጽኣ የእስራኤልን ንጉሳዊ መልክ የሚወክል ነበር፡፡ ለአለም ኃጢዓት የሚያስተሰረይ ሊቀ ካህን ነው ፤ በቀድሞዉ በምስራቅ አጠገብ አገልጋይ የሚለዉ ቃል “ የታመነ መልዕክተኛ “, “ ሙሉ የሚታመን ተወካይ “ ወይም “ የተመረጠ “ ማለት ነበር ፡፡
ዛሬ የአገልጋዩን የመጀመሪያዉን መዝሙር እንመለከታለን - ኢሳ (42፡ 1-9) ፤ ኢሳ( 49፡ 1-13) በጥቂት ቀናት ዉስጥ ጎልቶ ይታያል ፡፡ ኢሳ (50፡ 4-11) እና ኢሳ (52፡ 13 – 53፡ 12) በጣም ኃይል ያለዉ መዝሙር እና የአገልጋይ መዝሙር ዉበት በቀጣዩ ሳምንንት ይሸፈናል ፡፡
በዚያን ጊዜ ላይ ኢሳይያስ የእግዚአብሄርን አገልጋዮች እንደ እስራኤል ሕዝቦች ይገልፃቸዋል ፤ በሌላ ጊዜ ላይ ኢሳይያስ “ ስለ አገልጋዩ “ (ቁጥር 1) ማለት ስለ እግዚአብሄር አገልጋይ መሲሁ ማለት ነው ፡፡ በአዉዱ ላይ በመመልከት ትርጉሙን መወሰን እንችላለን ፡፡ አንዳንድ ጊዜ አገልጋይ ሕዝቦች ተልዕኮአቸዉን ይረሳሉ ወይም ወደ አለማየት እና አለመስማት ተቀየሩ (ቁጥር 18-20) ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሄር ምህረት አስፈልጓቸዋል (ኢሳይያስ 44) ፤ “ በንፅፅር የእግዚአብሄር አገልጋይ መሲሁ ኢየሱስ እንዲያደርግ የተሰጠዉን ሁሉንም ስራ በመታመን ፈፅሟል “ ፡፡ በሐዋ (3፡ 13) ጴጥሮስ እንደ ሰበከው እግዚአብሄር አገልጋዩን ኢየሱስን አከበረው ፤ ጴጥሮስ ኢየሱስን እንደ እግዚአብሄር አገልጋይ የሚለዩትን በርካታ ቃላቶችን እንኳን ለይቷል ፡፡
እግዚአብሄር አገልጋዩን በመለየት በሕዝቦች ላይ ፍትህን ማምጣት እንዲችል መንፈሱን በእርሱ ላይ ለማስቀመጥ መረጠው ፤ ኢየሱስ “ አገልጋይ “ ብቻ አይደለም የእግዚአብሄር አገልጋይ ነዉ እንጂ ፡፡ በማቴ (20፡ 25-28) ኢየሱስ ራሱን “ የሰዉ ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም “ (ማቴ 20፡ 28) በማለት ለዬ ፤ ኢሳይያስ ይህን ከክርስቶስ ልደት 600 አመት በፊት ሲያየዉ ኢየሱስ ከክርስቶስ ሞት በኋላ በመጀመሪያዉ ክፍለ ዘመን አጉልቶ አሳየው ፡፡ እዚህ ስፍራ በኢሳይያስ ላይ የሚያምረው ነገር ጴጥሮስ፣ ጳዉሎስ እና በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ያሉት ቀሪዎች ያመጡትን የወንጌልን ቃል እና መልክ ማየት መጀመራችን ነው ፡፡ “ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል “ (ቁጥር 1) የሚለዉ ሀረግ ኢየሱስን በምድረበዳ ባየዉ ጊዜ የመጥምቁ ዮሐንስ ማስታወሻ/ትዉስታ ነው ፤ መጥምቁ ዮሐንስ ኢየሱስን “ እነሆ የዓለምን ኃጢዓት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ “ በማለት ገለፀው (ዮሐ 1፡ 29) ፡፡ በተጨማሪም መንፈስ ከሰማይ በመዉረድ በእርሱ ላይ ሲያርፍበትም አዬ (ዮሐ 1፡ 32) ፤ ዮሐንስ ኢሳይያስ ፅፎት የነበረዉን መፈፀም አዬ ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 2)፡ ይህ ጥቅስ የወንጌልን መግለጫ የሚናገር ይመስላል ፤ ይህ ኢየሱስ አያስተምርም ማለት አይደለም ነገር ግን እንደ መሲህ ራሱን የሚያስተዋዉቅ ወይም ትኩረት የሚያስፈልገዉ አስተዋዋቂ አልነበረም ፤ ለእኛ እንደ መስዋዕት እንደ እግዚአብሄር በግ በመዘጋጀት በመከራዉ እንኳን በሙሉ አገልጋይነት ተቀመጠ/ቆዬ ፤ ነገሩ ትክክል እንዳልነበር አልተቃወመም አልጮኸም አላለቀሰምም ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 3)፡ ይህ ቁጥር የኢየሱስን የጥንቃቄ ተፈጥሮ ይገልፃል ፤ የተቀጠቀጠ ሸምበቆን አይሰብርም ፡፡ ሊያጠፋን እና ሊወረዉረን አልመጣም ፤ ሊያድሰን ይፈልጋል ፡፡ በምንደክም እና በምንጨነቅ ጊዜ ያን ከዙሪያችን ይመልሰዋል ፤ በመታመን ፅድቅን ያመጣል ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 4)፡ ኢየሱስ በፍፁም ተስፋ አይቆርጥም ፤ ኢየሱስ በእኛ ተስፋ የሚቆርጥበት ጊዜ በፍፁም አይኖርም ፡፡ በመሰረቱ ማቴ (12፡ 18-21) ከኢሳይያስ እነዚህን አራት ጥቅሶች ይጠቅሳል ፤ ማቴዎስ ኢየሱስ የኢሳይያስ ትንቢቶች መፈፀም እንደሆን መረዳታችንን እርግጠኛ መሆን ፈለግ ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 5)፡ ዳዊት ጉሲክ “ ሰማያትን እንደፈጠረና እንደዘረጋቸው ወደ ላይ እንድንመለከት ፤ ከእርሱ የመጡትን ምድርን ስለዘረጋ ወደ ታች እንድንመለከት ፤ ለሰዎች እስትንፋስን ስለሰጠ በመስታወት እንድንመለከት “ ያሳስበናል ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 6-7)፡ ይህ በትንሹ ለአሕዛብ ሁሉ በረከት ለመሆን የአብርኃምን ጥሪ ይመስላል ፤ ይህ ኪዳናዊ ቋንቋ ነው …. ኢየሱስ ለአይሁዶች እና ለአሕዛቦች ድነትን ያመጣል ፡፡ መንፈሳዊ እና አካላዉ መታደስን እና ፈዉስን ይናገራል ፡፡ ከእስራኤል በመዉጣት የዕዉራንን አይኖችን የሚያበራ፣ የታሰሩትን የሚፈታ እና በመንፈሳዊ ጨለማ ዉስጥ ያሉትን የሚያነፃ መሲህ ይመጣል ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 8)፡ “ እኔ ያህዌህ “ እግዚአብሄር ነኝ የአራት ፊደላት ስሞች - ያህዌህ ነው ፤ ይህ የእግዚአብሄር ቅዱስ ስም ነው - እኔ ያህዌህ ነኝ ፡፡ ጆሆቫን እንፅፋለን ነገር ግን አይሁዶች በፍፁም ይህን አይጠሩትም ፡፡ የእግዚአብሄር አገልጋይ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ክብርን ይጋራል ፡፡ ዮሐንስ (17፡ 5) አለም ከመፈጠሩ በፊት ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ጋር በክብርን እንደ ነበር ይናገራል ፤ ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ በአገልጋዩ ላይ ስላረፈ ሰዎስቱም እግዚአብሄር አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአንድ በአንድ ላይ እንደ እግዚአብሄር የተጣመሩ ናቸው ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 9)፡ የቀድሞዉ፣ የአሁኑ እና የወደፊቱ እግዚአብሄር ነው ፤ ሁሉም ነገር በእርሱ ቁጥጥር ስር ነው ፡፡ እዚህ ጋር ስለ ኢሳይያስ 42 መረዳት የሚያስፈልገን የተልዕኮ መልዕክት አለ ፡- እግዚአብሄር ኢየሱስን እንደአገልጋዩ አወጀዉ ፡፡ የሙስሊም ምሁራን እነዚህ ዘጠኝ ቁጥሮች ስለ ሙሀመድ ትንቢት የሚያረጋግጡ ናቸዉ በማለት ይከራከራሉ ፡፡ እንደ ክርስቲያን ይህ ፅሁፍ እንዴት ወደ ኢየሱስ እንደሚያመለክት መረዳት ያስፈልገናል ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 10-13)፡ የእግዚአብሄር ንግግር በምስጋና መዝሙር -የመለከት መዝሙሮች ያስከተለ ነበር ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ነው ! ሁሉም የታገሱት አስቸጋሪ ነገሮች እና ምርኮኝነት በአማኑኤል - ከእግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነዉ በሚለዉ ነፃ ወደመዉጣት ይመራሉ ፡፡ ለእኛ በሚዋጋዉ እና በዉጊያ ነፃ በሚያወጣን ነፃ እንወጣለን ፤ የእግዚአብሄር አገልጋይ ሁሉም ቀስቶችን፣ የእሾክ አክሊልን ይገጥሙታል/ይደርስበታል መጠየቅ ወይም ማሰብ ከምንችለዉ በላይ ስፍራ ያስቀምጠናል ፡፡
ኢሳይያስ (42፡ 14-25)፡ እግዚአብሄር የኃሰት አማልዕክትን በሚያገለግሉት ላይ ሁሉ ፍርዱን ያመጣል (ቁጥር 14-17) ፡፡ ደንቆሮዎች እና እዉሮች ወደ አገልጋዩ ይመጣሉ (ቁጥር 18-20) ፤ እግዚአብሄር የተበዘበዙትን ሕዝቦች በመከላከል (ቁጥር 21-25) መልሶ ያመጣቸዋል ፡፡
መደምደሚያ
መሲሁን እና እግዚአብሄር ለእኛ ያለሁን ሁሉ በምናይበት ጊዜ በኢሳይያስ ላይ ይህ የመፅናናት መፅሀፍት መጀመሪያ ነው ፤ በኢሳይያስ ቁልፉ ሀሳብ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው የሚለዉ ኢየሱስ አማኑኤል ነው ፤ ተመልሶ ይመጣል ፡፡
Gotquestions.org, “What are the four Servant Songs in Isaiah?”; available from https://www.gotquestions.org/Servant-Songs.html..
Gotquestions.org, “What are the four Servant Songs in Isaiah?”; available from https://www.gotquestions.org/Servant-Songs.html..
David Gusik, “Study Guide for Isaiah 42”; available at https://www.blueletterbible.org/Comm/guzik_david/StudyGuide2017-Isa/Isa-42.cfm?a=721005.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር ከምስራቅ (ኢሳ 41፡ 2) እና ከሰሜን (ኢሳ 41፡ 25) (ኢሳ 44፡ 28, 45፡ 1) ማንን አስነሳ ? እግዚአብሄር ለምን አላማ ይህን ሰዉ አስነሳው ?
-
በመፅሀፍ ላይ መጀመሪያ “ እኔ “ (ኢሳ 41፡ 4) የሚለዉ ስያሜ የተገኘ ነበር (ዘጸ 3፡ 14) ? ይህ ስያሜ ኢየሱስን ለመግለፅ እንዴት ነበር ጥቅም ላይ የዋለው ? (ማር 13፡ 6, 14፡ 61-62፣ ዮሐ 8፡ 28, 58, 13፡ 19)
-
በኢሳ (41፡ 10) አገላለፅ ይህ ጥቅስ ለማን ነበር የተነገረው ? የማይፈሩት ለምን ነበር እንዲያበረታቸዉ እና እንዲረዳቸዉ እግዚአብሄርስ ለምን አስፈለጋቸው ? ይህ ጥቅስ በኑሮአችሁ ዉስጥ እንዴት ህያዉ ሊኖር ይችላል ?
-
በኢሳ (42፡ 1) እግዚአብሄር የመረጠዉ፣ የሚደሰትበት እና መንፈሱን በራሱ ላይ ያስቀመጠበት ግለሰብ ማን ነበር ? (ማቴ 3፡ 16-17, ሉቃ 9፡ 35, 1ጴጥ 1፡ 20, ራዕ 13፡ 8)
-
በምዕራፍ 42 ኢሳይያስ ስለመጀመሪያዉ ብቻ ሳይሆን ስለሁለተኛዉም ክርስቶስ መምጣት እንዴት እየተመለከተ ነበር ? (መዝ 2፡ 8-9, ራዕ 2፡ 27)
-
በኢሳይያስ (41-42) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 41:9–10
“I brought you from the ends of the earth and called you from its farthest corners. I said to you: You are My servant; I have chosen you and not rejected you. Do not fear, for I am with you; do not be afraid, for I am your God. I will strengthen you; will help you; I will hold on to you with My righteous right hand.”
በእግዚአብሔር ለአብርሃም በኪዳን ስለተሰጠው ተስፋ እርሱም እስራኤል የእግዚአብሔር የተመረጠ ህዝብ እንደሆነ ኢሳይያስም እንደገና አረጋገጠ ፡፡ እግዚአብሔር መርጧቸዋል ፣ አልጣላቸውምም ፡፡ ስለዚህም አስራኤል ሊፈራ አልተገባውም ፡፡ ከእስራኤል ጋር የገባውን ኪዳን በማስታወስ እግዚአብሔር “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ “ ብሎ ተናገረ ፡፡ በኃይለኛና በጻድቅ ቀኝ እጁ እንደሚይዘው በመናገር እግዚአብሔር አስራኤልን እንደሚጠብቀው ቃል ገባ ፡፡
እግዚአብሔር አስራኤልን መርጦታል ሆኖም ግን ኢሳይያስ ሲተነብይ ሁሉም በፍቅሩ ይድኑ ዘንድ እግዚአብሔር ልጁን ፣ አገልጋዩን ፣ የአለም አዳኝና ቤዛ የሆነውን ኢየሱስንም ልኳል ፡፡ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች በመሆን በዚህ ማንነት ተመላለሱ ፡፡ ምናልባት እንደተጣለችሁ ፣ እንደማትፈለጉ ደግሞም እንደማትወደዱ ሊሰማችሁ ይችላል ፡፡ እነዚህ ሁሉ ከጠላት የሆኑ ውሸቶች ናቸው ፡፡ ክርስቶስ በሰጣችሁ ተስፋ ላይ አትኩሩ ፡- ተመርጣችኋል ፡፡ ተቀብሏችኋል ፡፡ ደግሞም ጥልቅ በሆነ ፍቅር በኋይል ተወዳችኋል ፡፡ ምናልባት ፍርኃቶች ፣ ጭንቀቶች እናም ስጋቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ ፡፡ ነገር ግን ተዋቸው ፡፡ ጻድቅ የሆነችውን የእግዚአብሔርን ቀኝ እጅ ያዙ ፡፡ እርሱ ይዟችኋል ፡፡ እርሱ ያውቃችኋል ፡፡ እርሱ ያበረታችኋል ይረዳችኋልም ፡፡ ስለ ዛሬ ብቻ አስቡ ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ለመሆን ቃል ገብቷል ፡፡ በዚህ ተስፋ ላይ ተጣበቁ ፡- እናንተ የተመረጣችሁ የእግዚአሔር ልጆች ናችሁ ፡፡
“ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና ፦ አንተ ባሪያዬ ነህ ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ ፤ አበረታሃለሁ ፥ እረዳህማለሁ ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
- ኢሳይያስ 41፡9-10
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 34:17–19 — “ ጻድቃን ጮኹ ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው ። እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል ። የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል ። “
ኢሳይያስ 41:13–14 — “ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር ፦ አትፍራ ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና ። አንተ ትል ያዕቆብ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ ፥ አትፍሩ ፤ እረዳሃለሁ ፥ ይላል እግዚአብሔር ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው ። “
ሮሜ 3:23–24 – “ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።