God's People Comforted
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 39-40 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስን ስናጠና እስካሁን የሸፈነዉን መከለስ አስፈላጊ ነው ፡፡ ወደ ኢሳይያስ 40 ከመሄዳችን በፊት ምዕራፍ 36-39 መከለስ ያስፈልገናል ፤ ምዕራፍ 36 መጨረሻ እና ምዕራፍ 37 መጀመሪያ ላይ ሕዝቅያስ የሐዘን ልብስን በመልበስ ወደ እግዚአብሄር ፀለዬ ፡፡ ምዕራፍ 37 መጨረሻ ላይ እግዚአብሄር ለሕዝቅያስ ፀሎት ምላሽ በመስጠት በተዓምራታዊ መንገድ ጣልቃ ገባ (185,000 አሶራዊያን በሰፈራቸዉ ዉስጥ ተገደሉ ሕዝ 37፡ 36) ፡፡ በምዕራፍ 38 ሕዝቅያስ በመጨረሻነት የታመመ ሆነ ኢሳይያስም ጉዳዩን በስርዓት ነገረው ፤ በምላሹም ሕዝቅያስ ወደ እግዚአብሄር በማልቀስ እግዚአብሄርን በእርሱ ፊት በታማኝነት ተመላልሶ እንደ ነበር አሳሰበ ፡፡ እግዚአብሄር በህይወቱ ላይ ተጨማሪ አስራ አምስት አመታትን በመስጠት መለሰለት ፡፡
በኢሳይያስ 39 ነገሮች ተቀይሯል ፡፡ የባቢሎን ንጉስ ለሕዝቅያስ ከህመሙ ስለ መዳኑ መልዕክትንና ስጦታን ላከለት ፤ ሕዝቅያስ ስጦታዎቹን በመቀበል መልዕክት ላመጣው (ለንጉሱ ልጅ) የመዝገብ ቤቱን ሙሉዉን ኃብቱንና የቶር መሳሪያዉን አሳየው (ቁጥር 1-2) ፡፡ ኢሳይያስ ሰዎቹ ከባቢሎን እንደሆኑ ባገኛቸዉ ጊዜ ሕዝቅያስን ለእነዚህ ሰዎች አሳይቷቸዉ የነበሩት ነገሮች ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚወስዱበት ጊዜ እንደሚመጣ ነገረው (ቁጥር 3-7) ፡፡ ሕዝቅያስም በእርሱ ዘመን “ ሰላምና “ “ ደህንነት “ ስለሚሆን መልካም ነበር በማለት ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 8) ፡፡
ቻርለስ ኤች.ድየር የኢሳይያስን ክፍሎች በእነዚህ ልዩነቶች አወዳድሯል፡
ኢሳይያስ (1፡ 39)፡ ኢሳይያስ (40-66)፡
በአሶራዊያን ዛቻ/ማስፈራራት ላይ ያተኩራሉ ፡፡ በባቢሎና ችግር በፋሬስ ድርጊት ላይ ያተኩራሉ ፡፡
ታሪካዊ ዝርዝሮች የተካተቱ ናቸው ፡፡ በጥቂቱ ታሪካዊ ዝርዝሮች የተካተቱ ናቸው ፡፡
መሲሁ እንደ ዳዊት ስር የታዬ ነው ፡፡ መሲሁ እንደ አገልጋይ የታዬ ነው ፡፡
የኢሳይያስ ሕይወት በዝነኝነት የታወቀ ነው ፡፡ የኢሳይያስ ሕይወት የለም ፡፡
ማክአርቱር “ የምዕራፍ (40-66) ትንቢቶች የባቢሎናዊያን ምርኮኝነት ቀድሞ እዉነታዉ እንደቀረበ ይሁዳን የሚደርሱ ቢሆኑም ምርኮዉ ከክርስቶስ ልደት 605-586 በፊት ድረስ እንዳልተጀመረ “ ይገልፃል ፡፡
ዋይርስቤ በምዕራፍ (40-66) ዉስጥ ሰዎስት ክፍሎች ይለያል፡ ምዕራፍ (40-48)፣ (49-57) እና 58-66) ፡፡ በምዕራፍ 48 እና 57 መጨረሻ ላይ በክፍፍሎቹ መካከል መስበሪያ ስፍራ አንድ ንግግር የተሰጠ ነው፡ እግዚአብሄር “ ለክፉዎች ሰላም የላቸዉም “ ይላል ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (40፡ 1-11)፡ ዋይርስቤ የኢሳይያስን መልዕክት በመጀመሪያዎቹ 11 ቁጥሮች ዉስጥ “ ከኋላችን ያሉ ሁኔታዎች “ በማለት ይገልፃል ፡፡ የኢሳይያስ መልዕክት ለእግዚአብሄር ነቢያቶች ወደ ምርኮ ተወስደዉ ለነበሩት መፅናናትን እንዲያደርጉ የሚያበረታታ ነበር (ቁጥር 1-2) (ሮሜ 11፡ 2) ፡፡ ኢሳይያስ የኢየሩሳሌም ኃጢዓት (ምዕራፍ 39) ይቅርታ የተደረገለት እንደ ነበር ይናገራል ፤ ምናልባትም ይህ ከባቢሎን ምርኮ ነፃ መዉጣትን ያመለክታል ፡፡ ቁጥር 3 ስለሚመጣዉ ኢየሱስ አብሳሪ የሆነዉን መጥምቁ ዮሐንስን እንደሚያሳይ መንገዱ ለጌታ ተመልሶ መምጣት ቀጥ ያለ እንደሚሆን ስለመጨረሻዉ ያመለክታል (ማቴ 3፡ 1) ፡፡ ኢሳ (35፡ 8) ስለ ሁለተኛ መምጣቱ ያመለክታል ፤ መሰናክሎች ለእርሱ መምጣት የተወገዱ ይሆናሉ (ቁጥር 4) ፤ ይህ ሁሉ ለጌታ መገለጥ/መታየት ክብርን ያመጣል (ቁጥር 5) ፡፡
ቁጥር (3-5) ለዚህ ፅሁፍ ቁልፍ የሆኑና በአሁኑ፣ በወደፊት እና ሁለተኛ መምጣቱን የሚያመለክተዉን ሁሉ መረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡
ስለ ምዕራፍ 40 ጥቂት አስተምሬአለሁ ነገር ግን ቁጥር 31 በምታነቡት ጊዜ ሁሉም ትርጉም ይሰጣል፡ “ እግዚአብሄርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸዉን ያድሳሉ ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ፤ ይሄዳሉ አይደክሙም “ ፡፡ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች የት እንደ ነበሩ በምታስታዉሉ ጊዜ ወደ ባቢሎን ምርኮ እንደተወሰዱ ታዉቃላችሁ ቁጥር 31 አንድ ቀን በነፃነት እንደሚመላለሱ መዝግቧል ፡፡
መደምደሚያ
ለጌታ ተመልሶ መምጣት ቀድመን በመመላለስ ማዘጋጀት እንድንጀምር “ የመጥምቁ ዮሐንስ ጥሪ “ በአብዛኞቻችን ላይ እንዳለ አምናለሁ ፡፡ ተግባራችሁ መሰናክሎችን እንደ ሐሰተኛ አስተማሪዎች እና የሐሰት ትምህርት አይነቶችን ማስወገድ ይሆናል ፡፡ ለጌታ ሁለተኛ ተመልሶ መምጣት ለማዘጋጀት የምንፈልግ ከሆነ በብዙ መጥምቁ ዮሐንስን ልንመስል ያስፈልገናል ፡፡ በኑሮአችን እና በእምነታችን በሚገባ ፍፁም ልንሆን ያስፈልገናል ፡፡
1 Charles H. Dyer., and Eugene H. Merrill. The Old Testament Explorer. Nashville: Word Publishing, 2001. Reissued as Nelson's Old Testament Survey. Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2001, p. 561; adapted in Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes; Isaiah, p 252; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 804.
W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 48.
Wiersbe, p. 49.
ጥያቄዎች
-
በኢሳይያስ 39 ንጉስ ሕዝቅያስ የባቢሎናዊያንን አጃቢዎችን/መልዕክተኞችን በመዉስድ ጠቅላላ መንግስቱንና ኃብቱን አሳያቸው ፤ በግል አስተያየታችሁ ይህን ያደረገዉ ስለ ግል ኃብቱ ለመጎራት ወይስ በትህትና የነበረዉን ለማየት በመምጣታቸዉ ስሜታዊ ስለሆነ ነበር ?
-
በኢሳይያስ 39 ንጉስ ሕዝቅያስ እርሱን ይጎዳዉ ስላልነበር በእግዚአብሄር ስርዓት ደህና የሆነ ይመስላል ፤ ስለዚያ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢሳ (40፡ 1-11) ነቢዩ ኢሳይያስ ለሕዝቡ የመፅናናትን ቃል ሰጠ ፤ በመፅኀፍት ላይ ሌላ የት ስፍራ ኢሳ (40፡ 3) ጥቅም ላይ ዉሏል ? ማቴዎስ ኢሳይያስ ስለ ዮሐንስ እያወራ ነበር አለ ፤ ያ እንዴት ቀላል ነው ?
-
በኢሳ (40፡ 29-31) እንዳለው ራሳችሁን በእግዚአብሄር ጥንካሬ ላይ ተደግፋችሁ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? ሁኔታዎቹ ምን ነበሩ ዉጤታቸዉስ ? ይህን ለአዲስ ክርስቲያን ለመግለፅ እንዴት እንደምታደርጉት በደንብ እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
-
በኢሳይያስ (39-40) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 40:28–31
“Do you not know? Have you not heard? Yahweh is the everlasting God, the Creator of the whole earth. He never grows faint or weary; there is no limit to His understanding. He gives strength to the weary and strengthens the powerless. Youths may faint and grow weary, and young men stumble and fall, but those who trust in the Lord will renew their strength; they will soar on wings like eagles; they will run and not grow weary; they will walk and not faint.”
ኢሳይያስ እግዚአብሔር የእስራኤልን ህዝብ ነጻ እንደሚያወጣ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር በተስፋ መቁረጣቸው ውስጥ ነበር ፡፡ እግዚአብሔር ዘላለማዊና የምድር ዳርቻ ፈጣሪ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ አይደክምም ማስተዋሉም ገደብ የለውም ፡፡ ለደከመው ብርታትን ኃይል ለሌለውም ኃይልን ይሰጣል ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ በግዞትና በመከራ ውስጥም ሆነው እንኳ ፣ ነጻ ያወጣቸው ዘንድ እንድሁም እንድያበረታቸው ያህዌን መታመን አስፈልጓቸው ነበር ፡፡
እግዚአብሔር ዛሬም በስሙ እንድትታመኑ ይሻል ፡፡ እርሱ እንደሚያበረታችሁ ይናገራል ፡፡ ኢሳይያስ በእግዚአብሔር ስትታመኑ “ እንደ ንስር በክንፍ “ እንደምትበሩ ጽፏል ፡፡ በቃ ዝም ብላችሁ ራሳችሁን የንስር ክንፍ እንዳላችሁ አድርጋችሁ አስቡ ፡፡ ንስር በሰማዩ ላይ ያለድካምና ያለ ምንም ችግር ይበራል ፡፡ ንስር አይታክትም ደግሞም አይደክምም ፡፡ ጌታም እንዲሁ የእናንተም ህይወት ከእርሱ ጋር ይህንን ስዕል እንድመስል ይሻል ፡፡ በምንም አይነት መከራ ውስጥ ብትሆኑም እንኳ እርሱ እንድታምኑት ይፈልጋል ፡፡ እርሱን በዝለታችሁ ፣ በድካማችሁና በትዕግስታችሁ ውስጥ ማመን ትችላላችሁ ፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ እግዚአብሔር የንስር ክንፍና እረፍት እንድሆንላችሁ ፍቀዱለት ፡፡ እርሱም ሳትደክሙና ሳትታክቱ ትጸኑ ዘንድ ያበረታችኋል ፡፡ ዛሬ በእግዚአብሔር ተደገፉ እረፉ እርሱም ነጻ ያወጣችኋል ፡፡
“አላወቅህምን ? አልሰማህምን ? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው ፤ አይደክምም ፥ አይታክትም ፥ ማስተዋሉም አይመረመርም ። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል ። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል ፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ ፥ አይታክቱም ፤ ይሄዳሉ ፥ አይደክሙም ። “
- ኢሳይያስ 40፡28-31
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 62:5–8 — “ ነገር ግን ፥ ነፍሴ ሆይ ፥ አንቺ ለእግዚአብሔር ተገዢ ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና ። እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነውና ፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው አልታወክም ። መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፤ የረድኤቴ አምላክ ተስፋዬም እግዚአብሔር ነው ። የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ ፥ በእርሱ ታመኑ ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ ፤ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው ። “
ማቴዎስ 11:28–30 — “ እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና ። “
ዕብራውያን 13:8 — “ ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።