How To Deal With Enemies When Walking In The Will Of God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 37-38 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስ እና ኤልያስ ሁለቱም ነቢያት ተብለዉ የተጠሩ ናቸው ፡፡ ኤልያስ የሚሰራ ነቢይ ነበር ኢሳይያስ ደግሞ የሚሰማና የሚናገር ነቢይ ነበር ፡፡ የእነዚህ የሁለቱም ነቢያት ስራ በእግዚአብሄር እቅድ ዉስጥ ነበር ፡፡ በእግዚአብሄር ሀሳብ ዉስጥ ሂደት አለ ፡፡ እግዚአብሄር ወደፊት የሚመጣዉን ባህሪይ አምጥቷል ፡፡ ዛሬ “ እግዚአብሄር ምንድን ነዉ የሚለዉ ? “ በማለት ራሳችንን መጠየቅ አለብን ፡፡ በመካከላችን ኢሳያሶች አሉ ? ዛሬ ለእኛ የሚለን የቤተ ክርስቲያን መንፈስስ ምንድን ነው ?
የኢሳይያስ መፅሀፍ ብሉይ ኪዳንን ከአዲስ ኪዳን ጋር የሚያገናኝ ማጣበቂያ ነው ፡፡ ኢሳይያስ ስለመሲሁ እና ስለፍርዱ ትንቢትን ተናግሯል ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ 36፡ ሕዝቅያስ መልካም ንጉስ ነበር ነገር ግን ብዙ ማስፈራራቶች ከራፉስቂስ በእርሱ ላይ መጡ ፤ ኮንስታብል ራፉስቂስ “ ከጦር ሜዳ አዛዥ ስያሜ ጋር ተመሳሳይ እንደ ነበር ፤ ቃሉ ቃል በቃል የጠጅ አሳላፊ አለቃ ማለት ነው ነገር ግን ይህ አሁን ከሚከናወንበት ጋር የመጀመሪያ ዘርፍ ስያሜ በመሆን ይገለጣል ፤ አለቃዉ ጠጅ አሳላፊ የንጉሱ የግል አማካሪ ነበር (ነህ 1፡ 11) “ በማለት ይገልፃል ፡፡
ሕዝቅያስ ሕዝቅያስ እና መንግስቱ እንደሚያዙና በአሶር አስተዳደር ስር ይሆናሉ ካለዉ ከራፉስቂስ ወደ እርሱ በመጣዉ መልዕክት የደነገጠ/የደከመ ነበር ፡፡ ከሰናክሬም ራፉስቂስ ከባድ የሆነአስቸጋሪና አስፈሪ ማስፈራሪያዎችን በሕዝቅያስ ላይ አመጣ ፡፡
ኢሳይያስ 37፡ የሕዝቅያስ ምላሽ ከመንግስቱ እና አገዛዙ መጨረሻ አንፃር ለማስፈራሪያዎቹ/ለዛቻዎቹ በምዕራፍ 37 ይጀምራል ፡፡ ሕዝቅያስ የኢሳይያስ እርዳታ እና ከሰናክሬም ለሆነዉ ማስፈራሪያ መልስ ለማግኘት የእግዚአብሄር ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ አስተዋለ ፤ ከዚህም የተነሳ ሕዝቅያስ ራሱን በማቅ ልብስ በመሸፈን ወደ እግዚአብሄር ቤት ሄደ ፡፡ በተጨማሪም የቤቱ አዛዥ ኤልያቄም፣ ፀኀፊዉ ሳምናስ እና የካህናት ሽማግሌዎች ራሳቸዉን የማቅ ልብስ በማልበስ ከነቢዩ ምክርንና ለመጠየቅ ወደ ኢሳይያስ የሚሄዱም ነበሩት ፡፡
ከሕዝቅያስ ለኢሳይያስ በእነዚህ መሪዎች የቀረበዉ ሪፖርት በእዉነት የእስራኤል ሕዝቦች የእግዚአብሄር ምርጦች ቢሆኑም እንኳን ይህን ሰራዊት መቋቋም እንደማይችሉ ነበር ፤ ሕዝቅያስ ይህን ስለ እስራኤል ጥበቃ በእግዚአብሄር ፊት አስቀመጠው ፡፡
ቁጥር 4 ምናልባትም ሕዝቅያስ ያ የተሰማው ከእግዚአብሄር ተመልሰዉ በነበር ጊዜ በተሰጣቸዉ በራሳቸዉ ስህተት እስራኤላዊያን ፍርዳቸዉ የሚገባቸዉ እንደሆነ ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቅያስ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማየት ከኢሳይያስ ጋር ማዉራት እንዳለባቸዉ ተሰማው ፡፡ ሕዝቅያስ ኢሳይያስን ስለ ቅሬቶቹ እንዲማልድ ጠየቀው ፡፡
ኢሳይያስ ለሰራተኞቹም ለሕዝቅያስ እግዚአብሄር “ ከሰማኸዉ ቃል የተነሳ አትፍራ “ (ቁጥር 6) ይላል ብላችሁ ንገሩት ብሎ በማዘዝ መለሰላቸው ፤ በተጨማሪም ኢሳይያስ ሰናክሬም ወሬ በመስማት በስይፍ ወደሚሞትበት ምድሩ እንደሚመለስ ቃልን ላከ ፡፡ ሰናክሬም አሶርን ሊይዘ መምጣቱን ከሰማዉ ከቲርሐቅ ጋር ለመዋጋት ከመሄዱ በፊት አሁን ኢየሩሳሌምን ለመያዝ ባይመጣም እንኳን እንደሚመለስ ለሕዝቅያስ መልዕክትን ላከለት ፡፡ ሰናክሬም ሕዝቅያስን የጎዛንን፣ የካራንን፣ የራፊስን፣ የዔድንን፣ የሐማት፣ የአርፉድ፣ የሴፈርዋይ፣ የሄናንና የዒዋ ንጉስ እንደደረሰባቸዉ እጣ ተመሳሳይ እንደሚደርስበት ነገረው ፡፡
ይህን መልዕክት ከተቀበለ በኋላ ሕዝቅያስ ወደ ቤተ መቅደስ በመሄድ መልዕክቱን በእግዚአብሄር ፊት በማስቀመጥ ፀለዬ ፤ በመፀለይም እግዚአብሄርን ፀሎታቸዉን እንዲሰማ፣ ሁኔታቸዉን በማየት እንዲታደጋቸዉ ጠየቀው ፡፡ በዚህም ሁሉም መንግስት እግዚአብሄር አምላክ ብቻዉን እዉነተኛ አምላክ እንደሆነ ያውቃሉ ፡፡
ቁጥር 21 መጀመሪያ ላይ ኢሳይያስ እስራኤልን እጠብቃለሁ/እከላከላለሁ የሚል ከእግዚአብሄር የሆነ መልዕክት ተሰጠው ፡፡ እግዚአብሄር በፍርድ ዘመን ህዝቡን ለማስተቃቀል ሌላ ሕዝብን (እንደ አሶር) እጠቀማለሁ አለ - ለማስተካከል ብቻ እንጂ ለማጥፋት አይደለም ፡፡ ሕዝቅያስ እግዚአብሄር እንዴት አዝዟቸዉ እንደ ነበር ቃሉን ለማግኘት ወደ ኢሳይያስ ሄደ ፡፡ እግዚአብሄር ሰናክሬምናና ራፉስቂስን እግዚአብሄርን በማያከብሩት ወይም በማይሰሙት መንግስታት ላይ እንደ በትር እና መቅጫ እንዲያገለግሉ እንደፈቀደላቸዉ ነግሯቸዉ ነበር ፤ አሁን ያ ጊዜ አብቅቷል ፡፡
በቁጥር 27 እግዚአብሄር ለራፉስቂስ እንዲሰጠዉ ለሰናክሬም ሌሎቹ ከተሞች የተሸነፉ እንዲሆኑ ደካሞች አድርጓቸዉ እንደ ነበር ቃልን ሰጠው ፡፡ ኢሳይያስ ለሰናክሬም ጌታ እግዚአብሄር በስራ ላይ እንደ ነበር ነገረው ፡፡ ሕዝቅያስ እንደ እግዚአብሄር አላም የተጠራ እንደ ነበር ነገር ግን እስራኤልና ይሁዳ የእግዚአብሄርን አላማ የተከተሉ አልነበሩም ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር በመልካም መስራት ይችላል ፤ ይህ በነቢዩ በኢሳይያስ በራሱ የታዬ ነበር ፡፡ የመዳን ተናጋሪ ነቢይ ነበር ፤ እግዚአብሄር እቅድ ነበረው ፡፡
እግዚአብሄር ይህን ዉጊያ ለመዋጋት የራሱን አስተናጋጅን ተጠቅሟል ፤ እግዚአብሄር ከቁጥር የሚበልጥ ሰራዊት አለው ፡፡ ከአሶራዊያን ጋር በዚህ ዉጊያ እግዚአብሄር ስለ ራሱ ራሱን እና ስለ ዳዊት እየተከላከለ ነበር ፡፡
በዚህ መግለጫ መጨረሻ ላይ የእግዚአብሄር መልዓክቶች በአሶራዊያን ሰፈር ዉስጥ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ሰራዊት ገደሉ ፡፡ በማግስቱ በማለዳ ሰናክሬም ወደ አሶር ዋና ከተማ ወደ ነነዌ ተመለሰ ፡፡ በኋላም/ቆይቶ ሰናክሬም በአምላኩ በናሳራክ ቤተ መቅደስ ዉስጥ እየሰገድ እንደ ነበር ወደ አራራት በኮበለሉት በሁለቱ ወንድ ልጆቹ በሰይፍ ተገደለ ፡፡ ከወንድ ልጆቹ ሌለኛው አስራዶን እንደ አዲስ ንጉስ በእርሱ ቦታ ተተካ ፡፡
መደምደሚያ
በአንድ ድርጊት እግዚአብሄር በአሶር ላይ በማለፍ ወደ ትንንሽ እንድትሆን አደረጋቸው ፤ እግዚአብሄር እግዚአብሄር አምላክን የማይከተሉ ሕዝቦችን ለማዋረድ ተጠቅሞባቸዉ ነበር ፡፡ አሶር የእስራኤልን ሕዝብ ለመቅጣት ጥቅም ላይ የዋለች ነበረች ከዚያም በኋላ በራሱ በእግዚአብሄር ላይ በመበሳጨት/በመተበት መስመሩን አለፉ (ኢሳ 37፡ 29) በምላሹም እግዚአብሄር እነርሱንም ቀጣቸው ፡፡ ሕዝቅያስ እና ኢሳይያስ በዚህ ሂደት እና ልምምድ ዉስጥየእግዚአብሄርን ኃይልንና ታላቅነት አዩ ፡፡
በኢሳይያስ ምዕራፍ 38 ስለ ሕዝቅያስ የታመመ መሆን መግለጫ ነው ፤ ኢሳይያስ ለሞቱ እንዲዘጋጅ ነገረው ነገር ግን ሕዝቅያስ ወደ እግዚአብሄር ፀለዬ ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቅያስን እንዲድን በመፍቀድ እግዚአብሄር በሕዝቅያስ ሕይወት ላይ ሌላ አስራ አምስት አመትን ጨመረለት ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 229; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.
ጥያቄዎች
-
ንጉስ ሕዝቅያስ ተጨንቆ ነበር ፤ በኢሳ (37፡ 1) ልብሱን በመቅደድ ማቅ ለበሰ ፡፡ በመፅኀፍት ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ እና እነማን ናቸዉ ልብሳቸዉን የቀደዱት በምን ምክንያትስ ? (ዘፍ 37፡ 34, 1ነገ 21፡ 27, አስ 4፡ 1-3)
-
በኢሳ (37፡ 37) ንጉስ ሰናክሬም በነነዌ ወደ ቤቱ ሄደ ፤ ነነዌ ሌላ የት ተጠቅሳለች (ዮና 1-4) ? በምን አይነት ሁኔታ ?
-
ንጉስ ሕዝቅያስ የተማመና እያጣጠረ ነበር ፤ በመፀለይ ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፤ በኢሳ (38፡ 1-8) እግዚአብሄር በመስማት በህይወቱ ላይ አስራ አምስት አመታትን በመጨመር ፀሎቱን መለሰለት ፡፡ በመፀለይ ወደ እግዚአብሄር የጮኻችሁበት እና እርሱም የመለሰላችሁ ጊዜ አለ ? ከሌሎች ጋር ያን ምስክርነት ተነጋገሩ
-
በኢሳይያስ (37-38) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 37:14–17
“Hezekiah took the letter from the messengers, read it, then went up to the LORD’s temple and spread it out before the LORD. Then Hezekiah prayed to the LORD: LORD of Hosts, God of Israel, who is enthroned above the cherubim, You are God—You alone—of all the kingdoms of the earth. You made the heavens and the earth. Listen closely, LORD, and hear; open Your eyes, LORD, and see. Hear all the words that Sennacherib has sent to mock the living God.”
ንጉሥ ሕዝያቅስ ከንጉሥ ሰናክሬም የተላከ ደብዳቤ ደረሰው ፤ ደብዳቤውም ኢየሩሳሌም በአሶር እጅ ስለምትወድቅ ያድነኛል ብሎ በያህዌ እንዳይታመን የሚያስጠነቅቅ ነበር ፡፡ ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ተቀብሎ ካነበበ በኋላ ወድያውኑ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ ፡፡ ደብዳቤውንም በእግዚአብሔር ፊት ዘርግቶ እንድህ ብሎ ጸለየ ፡- “ የሠራዊት ጌታ ሆይ …… አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ ……. አምላካችን አቤቱ ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን ። “
ራስህን በችግር ውስጥ ፣ በጠላት ከበባ ደግሞም በሰልፍ ውስጥ ካገኘኸው ወድውኑ ሄደህ በኃያሉ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ነገሩን አቅርብ ፡፡ እርሱ ብቻ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ ውጊያህን ይዋጋልሃል ፡፡ እርሱ የሚያስፈልግህን ይሰጥሃል በስሙም ድልን ያቀዳጅሃል ፡፡ በንጉሥ ሕዝቅያስም ጉዳይ እግዚአብሔር መልአክ ልኮ በአንድ ለሊት የጣላትን ጦር ካምፕ ደመሰሰ ፡፡ ሕዝቅያስ ጉዳዩን በእግዚአብሔር ፊት ይዞ ከቀረበ በኋላ ፣ እግዚአብሔር ለንጉሥ ሕዝቅያስ ጠላቱን ተዋጋለት ፡፡ ዛሬ ህይወትህን በእግዚአብሔር ፊት አቅርብ ፡፡ እግዚአብሔር ህይወትህን ይቆጣጠር ዘንድ ፍቀድለት ደግሞም ውጊያህን ይዋጋልህ ዘንድ ጸልይ ፡፡ በክርስቶስ ድልን ትቀዳጃለህ !
“ ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው ፤ ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው ። ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ ፦ አቤቱ ፥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ ፥ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል ። አቤቱ ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ ፤ አቤቱ ፥ ዓይንህን ክፈትና እይ ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬም ቃል ስማ ። “
- ኢሳይያስ 37፡14-17
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 3:21–22 — “ በዚያም ጊዜ ኢያሱን ፦ አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል ፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታት ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል ። አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንተ ይዋጋልና አትፍራቸውም ብዬ አዘዝሁት ። “
2ኛ ዜና 32:7–8 — “ ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ ፥ አትደንግጡም ። ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው ፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው ። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና ። “
ኢሳይያስ 37:20 — “ እንግዲህም አምላካችን አቤቱ ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።