Major Prophets Isaiah

The Ransom Returned To Zion

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 34-36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 589 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኢሳይያስ 66 ምዕራፎች እንደ ብሉይ ኪዳን ተመሳሳይ ክፍል አለው ፤ የመጀመሪያዎቹ 39 ምዕራፎች ስለ ፍርድ ናቸው ፡፡ ቀሪዉ 27 ምዕራፍ ደግሞ የመፅናናት እና የነፃ መዉጣት ጭብጥ አለው ፡፡ ምዕራፍ (28-33) በሰማሪያ፣ በኢየሩሳሌም እና በአሶር ላይ ያለዉን ፍርድ በማንፃት ይጀምራል ፡፡

በዚህ ክፍል ዉስጥ ለኢሳይያስ መልዕክት ሁለት ክፍሎች አሉ ፤ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ መሰረት “ ከስድስቱ ሀዘኖች/ለቅሶዎች ከተጨማሪ መግለጫዎች ሁለት ትንቢቶች አሉ ((ምዕራፍ 33)፣ 1) የተበዘበዙት ሕዝቦች ለም መሬት ወደ በርሃነት ይቀየራል (ምዕራፍ 34) እና 2) በርሃዉም ወደ ለም መሬትነት ይቀየራል (ምዕራፍ 35) “ ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (34)፡ በቁጥር 1 ኢሳይያስ እግዚአብሄር በሁሉም ሕዝብ ላይ ስለተበሳጨ ሁሉም ይስማ በማለት ትንቢቱን ይጀምራል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ በምዕራፍ 34 ይህ ትንቢት “ ሁለት ክፍሎችን ይይዛል 1) በሁሉም ሕዝብ ላይ ያለን ፍርድ (ቁጥር 1-4) እና በዉክል በኤዶም ላይ ያለን ፍርድ (ቁጥር 6-1) “ ፡፡ ምዕራፍ 34 ፍርድን ሲዳስስ/ሲደርስ ምዕራፍ 35 ደግሞ ስለ ነፃ መዉጣት ይናገራል ፤ ምዕራፍ 34 በመጀመሪያ ደረጃ ስለ ሞት ነው ፡፡ በኢሳይያስ 34 በቁጥር 4 ዉስጥ መላዉ አለም በዚህ ፍርድ ዉስጥ ይሳተፋሉ/ይካተታሉ ፤ ይህ ሰማያትንም ያካትታል ፡፡

እግዚአብሄር ለምድር ሁሉ የሚሆን የበቀል ቀን አለው ፡፡ ኮንስታብል “ እግዚአብሄር ፂዎንን በጮቆኑት ላይ በልን ይወስዳል ፤ እነርሱንም በሰደባቸዉ ላይ ስለ ህዝቡ ይሰራል/ይነሳል (ዘፍ 12፡ 3) ፤ ይህ መቼ እንደሚሆን ባናዉቅም እንኳን እግዚአብሄር ለፍርዱ የጊዜ ሰለዴ ነበረዉ ይጠብቀዋልም “ በማለት ይገልፃል ፡፡ በተጨማሪም ኮንስታብል “ ነቢዩ የኤዶሚያስን መጥፋት/ወርወርን ኤዶም ከኢየሩሳሌም እንደወጣበት በተመሳሳይ አቅጣጫ ላይ በማስቀመጥ የሰዶምና የጎሞራን መጥፋት በትዝታ ገለፀ (ዘፍ 19፡ 24-28, ዘዳ 29፡ 23, መዝ 11፡ 6, ኤር 49፡ 18, ራዕ 14፡ 10-11) ፤ የኤዶምያስ ድርጊት በዚህ ጥፋት መጣ ፤ በአጠቃላይ የአለም መጨረሻ ከዚያን በኋላመኖሪያዎቿም ባዶ/ማንም የማይኖርባቸዉ ይሆናሉ (ዘሌ 6፡ 13, ኢሳ 66፡ 24, ራዕ 19፡ 3) “ ይናገራል ፡፡

ኮንስታብል በኢሳ (34፡ 11-13) የኢሳይያስ መልዕክት “ የሰዉ መሪዎች እንደማይኖሩ እና የዱር እንስሳቶች አረሞች ምድሪቱን ይሞሏታል “ ማለት እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ኢሳይያስ ከክርስቶስ መመለስ በፊት ምድር የመከራዉ መጨረሻ ላይ እንደምትሆን ትንቢትን ተናግሮ ነበር ፡፡

እንደ ኔልሰን ማብራሪያ “ ፔሊካን፣ ፓርኩፒን፣ ጉጉት እና አሞራ ሁሉም በሆነ ስፍራ የማይኖሩ የርቀት ንፁህ ያልሆነ ፍጥረቶች ናቸው (ዘዳ 14፡ 14-17) ፤ በእግዚአብሄር የፍርድ ቀን ላይ ኤዶምያስ ጠፍ ምድር ይሆናል ፡፡ የዕብራዊያን ቃል መወዛገብ እና ባዶነትን በዘፍጥሪት 12 ቅርፅ የሌለዉ እና ባዶ በማለት ተርጎሞአቸዋል ፤ ኤዶምያስ ወደ ትርምስ ይመለሳል “ ፡፡

ኮንስታብል “ እንደ ራዕ (6፡ 8) እና (9፡ 18) መሰረት በስድስተኛዉ የፍርድ መለከት መጨረሻ ላይ የምድር ግማሽ ያክሉ ሕዝብ ይጠፋሉ ፤ በጣም ብዙዉ የጥፋት ፍርዶች ከስድስተኛዉ የፍርድ መለከት በኋላ በተለየም ከሁሉም በሚከፋው በሰባተኛዉ የፍርድ መለከት ሲነፋ በምድር ነዋሪዎች ላይ እንደሚወርድ “ ይገልፃል ፡፡

ኢሳይያስ 34 በራዕይ መፅኀፍ ማንበብ ስለምንችለዉ ስለ መጨረሻዉ ጊዜ ትንቢትን እየተናገረ ነበር ፡፡ የምዕራፍ 34 ይህን ንግግር በምድር ላይ ሁሉ ፍርድ እንደሚመጣ ትንቢትን እየተናገረ እንደሆነ መረዳት አለብን ፤ ይህ መፅኀፍት በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ ከሆነ ሁሉም ስለሚመጣዉ ነገር መዘጋጀት አለበት ፡፡

ኢሳይያስ (35)፡ በምዕራፍ 34 ምድሪቱ ጠፍ መሬት ስትሆን ምዕራፍ 35 ደግሞ ተስፋ፣ ብርኃን እና ፍሬአማነትን ያቀርባል ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ በመሲሁ ዘመን ጊዜ አስደናቂ ለዉጦች በምድሪቱ ላይ ይመጣሉ (ኢሳ 30፡ 23-2, 32፡ 15-20) ፡፡ ሊባኖስ…..ቀርሜሌዎስ እና ሻሮን ፤ በባህሩ አጠገብ ያሉ ስፍራዎች በግብርና ለምነታቸዉ የታወቁ ናቸው ፤ ይታያሉም ፤ እስራኤል ከእግዚአብሄር የሚመጣዉን የምድር አዲስ ፍሪያማነት እንደተገኘ እና ለእርሱ ትክክለኛዉ ባህሪይ እንደሚገባዉ የሚያስተዉሉ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡

የኢሳይያስ ትንቢት አተገባበር ለእስራኤላዊያን የአሁን እና እንዲሁም ምን እንደሚሆን የወደፊት ትንቢያ ነበር ፡፡ በቁጥር 3 “ በእስራኤል አለማቀፋዊ ሚና የወደፊቱ መቀየር በህዝቦች መካከል ተስፋ የቆረጡትን ለማበረታታት የታቀደ ነው “ ፡፡

ለቅሬቶቹ መልዕክቱ እግዚአብሄር ያድናችኋል ነው ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር በቀል (ኢሳ 34፡ 8) ለረጅም ጊዜ የተጨቆነዉን የእስራኤልን ሕዝብ ለመቤዠት የተዘጋጀ ነው (ኢሳ 34፡ 8) “ ፡፡ ራዕይ 13 እና 14 ተመሳሳይ ቃል አላቸው ፡፡

በኢሳይያስ ምዕራፍ 35 ያለዉ መልዕክት ቅሬቶቹ ደካሞች ከሆኑ እግዚአብሄር ሊያድናቸዉ ስለ ነበር ለመታገስ እና እምነታቸዉን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር እቅድ ሁኔታዉን አይቀይርም ነገር ግን በሁኔታዉ ዉስጥ እኛን ይቀይረናል ምክንያቱም ነገሮች የተሸሉ ስለሚሆኑ ፤ በምዕራፍ 35 ባለዉ የተስፋ መልዕክት እንኳን ለዉጤ አዎንታዊ ይሆናል ነገር ግን ቀላል አይደለም ፡፡ ይህ በለዉጥ ሂደቱ ዉስጥ በእግዚአብሄር ላይ መመልከትን መቀጠል ከህዝቡ ይጠይቃል ፡፡

ቁጥር 5 እስከ 7 የመንፈሳዊ ሁኔታን ተቃራኒን ያመለክታል ፤ ዉሃ በአዲሱ ሺህ አመት ይፈስሳል ፤ እስራኤል ከምርኮኝነት በመዉጣት ነፃ ትሆናለች ፤ ቅዱሱ መንገድ ሕዝቡን ወደ ቅዱስ ከተማ ይመራቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

ምዕራፍ 34 በሚገባ ስለ መከራዉ እያወራ ከሆነ መንገዱ ወደ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የሚመራዉን ያመለክታል ፡፡ ነፃ ወጥተዉ የነበሩት ቅሬቶች በመንገዱ ሲመላለሱ ደስታ ብስጭትን ያሸንፈዋል ፡፡ በእስራኤል መታደስ ቀን ደስታ ይሆናል ፤ ኢሳይያስ 35 ይመጣ ስለ ነበረዉ ሁሉም ነገር መልክ ነው ፡፡ ምዕራፍ 34 በምዕራፍ 35 የሚገኘዉ የተስፋ መልዕክት ለህዝቡ ለምን እንዳስፈለገው ያመለክታል ፤ ኢሳይያስ 36 ከምዕራፍ 40 እስከ 66 ድረስ እንደ ድልድይ የሚያገለግል እንዲሁም ደግሞ ንጉስ ሕዝቅያስ ማን እንደ ነበር የሚስል ነው ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 841.

  2. Nelson’s Commentary, p. 841.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, pg. 222; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  4. Constable, p. 222.

  5. Constable, p. 222.

  6. Nelson’s Commentary, p. 841.

  7. Constable, pp. 223.

  8. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 799.

  9. MacArthur, p. 799.

  10. MacArthur, p. 799.

ጥያቄዎች

  1. ኢሳ (34፡ 3-4) ስታነቡ ማቴ (24፡ 29) እና ራዕ (16፡ 1-2) እናነባለን ፤ አንዳንድ አንድነቶቻቸዉ ምንድን ናቸው ? በግል አስተያየታችሁ እነዚህ ጥቅሶች ተመሳሳይ ነገርን ይጠቅሳሉ ?
  2. ኢሳይያስ 35 ስለመፅናናት ተስፋ ነው ፤ በመፅኀፍ ላይ ከቁጥር 3 እና 4 ጋር የሚገናኝ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተስፋን ታያላችሁ ? (ዘዳ 31፡ 6, 2ጢሞ 4፡ 18, ዕብ 13፡ 6)
  3. ኢሳ (35፡ 9-10) ከራዕ (21፡ 4 እና 8) ጋር በማንበብ አወዳድሩ ፤ እነዚህ ተመሳሳይ ነገር ይናገራሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ? እነዚህ ጥቅሶች እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጓችኋል ?
  4. በኢሳ (36፡ 4-15) ለአሶር ንጉስ የሰራተኞች ሁሉ አለቃ በኢየሩሳሌም ያሉትን ሰዎች አስፈራራም አንጓጠጠም ፤ ነገር ግን በቁጥር 16 መጀመሪያ ላይ በታላቂቱ ምድር ተስፋና ነፃነት ጀመረ ፡፡ ከጠላቶቻችን እና ከሚነግሩን ዉሸት ጋር ተመሳሳይነትን ማየት ትችላላችሁ ? በጣላት እና በዉሸቱ ሰምታችሁ የተሳባችሁ ሆናችኋል ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
  5. በኢሳይያስ (34-36) ዉስጥ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 35:9b–10

“But the redeemed will walk on it, and the redeemed of the LORD will return and come to Zion with singing, crowned with unending joy. Joy and gladness will overtake them, and sorrow and sighing will flee.”

እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳይያስ ህዝቡን ከኃጢአት እንደሚያድን ፣ እንደሚለውጥና እንደሚቤዥ ተናገረ ፡፡ እግዚአብሔር የለውጥ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ ሁሉንም ነገር ይቤዣል ፡፡ በረሀውን ወደ ጽጌ ረዳ አበባ ይቀይራል ፡፡ ደረቁንም ምድር ወደ ወራጅ ወንዝ ይቀይራል ፡፡ እርሱ የዛሉ እጆችን ደግሞም የሚብረከረኩ ጉልበቶችን ያበረታል ፡፡ እርሱ ለሚፈራው ደግሞም ማየት ለተሳነው ድፍረትን ይሰጣል ፡፡ የተጠማውን ያረካል የራበውንም ያጠግባል ፡፡ እርሱ በስሙ ለሚታመኑ ለእነርሱ የሚታደግ የሚቤዥ አምላክ ነው ፡፡

ከምስራቅ አስከ ምዕራብ ድረስ ፤ ከሰሜንም እስከ ደቡብ እርሱ ይወዳችኋል ደግሞም ለህይወታችሁ ቤዛነትን ያደርግ ዘንድ ይሻል ፡፡ ምናልባት አሁን በማያቋርጥ መከራ ውስጥ እያለፋችሁ ይሆናል ፡፡ መከራ ፣ ኀዘን ፣ ፈተና ደግሞም በዙሪያችሁ የማታውቁት ነገር በዙሪያችሁ ሊኖር ይችላል ፡፡ ሆኖም በዚያም ቦታ ቢሆን እንኳ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ ምናልባት ያላችሁበትን ሁኔታ ወድያውኑ ላይቀይረው ይችላል ሆኖም ግን ቆይቶም ቢሆን ሁኔታውን ቀይሮ ይታደጋችኋል ፡፡ ፊታችሁን ወደ እርሱ መልሱ ፡፡ እርሱ በሚያይበት መንገድ የሚያዩ አይኖች ይሰጣችሁ ዘንድ እርሱን ጠይቁ ፡፡ ጉልበታችሁን ያጸና ዘንድ ደግሞም እጆቻችሁን ያበረታ ዘንድ ጸልዩ ፡፡ ወደ እርሱ ስትጣሩ እርሱ ይመልስላችኋል ፡፡ እግዚአብሔር እንደ ኃይለኛ ተዋጊ ያስታጥቃችኋል ፡፡ ከስሞች ሁሉ በላይ በስሙ ታመኑ ፡፡ በእግዚአብሔር ብቻ ታመኑ ፡፡

“ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ ፤ እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል ፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ ። “

  • ኢሳይያስ 35:9b–10

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 107:2-3, 8–9 — “ እግዚአብሔር ያዳናቸው፥ ከጠላቶች እጅ ያዳናቸው ይናገሩ ። ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥ ከየአገሩ ሰበሰባቸው …….. ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ ፤ የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና ። “

ኢሳይያስ 35:1–4 — “ ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፥ በረሀውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል ። እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ ። የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ ። ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው ። “

ኤፌሶን 1:7–8 — “ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ። “