Major Prophets Isaiah

The Lord Rises Up

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 32-33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 588 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በእነዚህ ምዕራፎች ዉስጥ መልዕክቱ ትኩረት ስለመስጠት እና የሚመጣ ዉጤት እንዳለ ነው ፡፡ እዚህ ጋር የታሪኩ ትክክለኛ ነገር እግዚአብሄር የሚጠይቀዉን ነገር ማድረግ ነው ፡፡ የኢሳይያስ 66 ምዕራፎች የመፅኀፍ ቅዱስ 66 መፅኀፍት ነፀብራቅ ናቸው ፡፡ የብሉይ ኪዳን 39 መፅኀፍቶቹ ሁሉም ስለማስጠንቀቂያ ሲሆኑ የአዲስ ኪዳን 27 መፅሀፍት ደግሞ ስለ ቤዛነት እና መፅናናት ናቸው ፡፡ በኢሳይያስ 30 መልዕክቱ እግዚአብሄርን ስትጠብቁ ይጠነቀቅላችኋል ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (32፡ 1-20)፡ በምዕራፍ (28-33) ሰዎስት በተለያዩ ቡድኖች ላይ ሸክሞች አሉ፣ በሰማሪያ፣ በኢየሩሳሌም እና በአሶር ላይ ያሉ ሸክሞች ፡፡ በአጠቃላይ ስድስት ለቅሶዎች/ሀዘኖች በእነዚህ ምዕራፎች የተካተቱ ናቸው (ኢሳ 28፡ 1, 29፡ 1, 15, 30፡ 1, 31፡ 1, 33፡ 1) ፡፡ ለቅሶ ቁጥር ስድስት በይሁዳ ላይ ከፈፀመዉ ክህደት የተነሳ ቀጥታ ወደ ንጉስ ሰናክሬም ላይ ነበር ፡፡

ምዕራፍ 32 ወደ ሁለት ክፍሎች ሊከፋፈል ይችላል ፤ የመጀመሪያው ክፍል ቸርነትን ስለሚያደርጉ መሪዎች እና ስለ መሪነት ተፅዕኖአቸዉ የሚተነብይ ሲሆን ፤ ሁለተኛዉ ደግሞ ስለ ስስታም መሪዎች ትንቢትን የሚናገር ነው ፡፡ “ አምስቱ ለቅሶ/ሀዘኖች (ምዕራፍ 31) ስለ መሪነት (ቁጥር 1-8) እና ስለ ተፅዕኖዎቹ በትንቢት ያጠቃልላሉ (ቁጥር 9-20) ፤ በምዕራፍ 32 በብዛት ቸርነትን የሚያደርጉ መሪዎች (ቁጥር 1-5) መትረፍረፍን እና ቋሚ ደህንነትን ያመነጫሉ (ቁጥር 16-20) ስስታሞቹ ደግሞ ኃሰት የሆነ ደህንነትን እና መለያዬትን ያመነጫሉ (ቁጥር 9-14) “ ፡፡

በቁጥር 1 የንጉሱ ማጣቀሻ በቀላሉ እንደ መሲህ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡ “ ይህን ንጉስ በተለከተ የተነገረዉ ትንቢት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የተፈፀሙ ናቸው (7፡ 14, 9፡ 1-7, 11፡ 1-5, 28፡ 16, ዮሐ 10፡ 11, 16) ፤ አገልጋዮች በእርሱ ስር እረኞች ናቸው (1ጴጥ 5፡ 2-4) “ ፡፡

ኢሳይያስ (33፡ 1-24)፡ ቁጥር 1 ወደ አሶራዊያን የተነገረ ነበር ፤ “ ስድስተኛዉ ለቅሶ/ሀዘን ይሁዳን ሳይሆን አሶርን የደረስ ስለሆነ ከሌሎቹ የተለዬ ነው “ ፡፡ ይህ ሀዘን/ለቅሶ “ በይሁዳ ላይ ካደረገዉ ክህደት የተነሳ በሰናክሬም ላይ በር ፤ ባለማመን ንጉስ ሕዝቅያስ ለአሶር ለመስጠት ሞክሮ ነበር (2ነገ 18፡ 13-15) ነገር ግን ሰናክሬም ስምምነቱንሰብሮ ስለ ነበር ይሁዳን ወረረ ፤ ዘራፊ፣ ከዳተኛ እና አምባገነን ነበር “ ፡፡

“ ሕዝቅያስ የቤተ መቅደሱን ሁሉንም እቃ በመዉሰድ ሰናክሬምን ጉቦ በመስጠት ሞከረ (2ነገ 18፡ 13-16) ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ሕዝቅያስን ይቅር በማለት እግዚአብሄርን መፍራትም ኃብቱ እንደሆነ አሳሰበው (ኢሳ 33፡ 6) “ ፡፡ ኢሳይያስ የአጥፊዎችን ጥፋት ተነበዬ (ቁጥር 1) ፡፡

የቅሬቶቹ ፀሎት በቁጥር 2 መጀመሪያላይ የቀረበ ነዉ ፤ ይህ ቅሬትም ኢሳይያስን ያካተተ ነው ፡፡ በሙሉ ልበ ሙሉነት በመጠበቅ ፀለዩ ፤ እግዚአብሄርም በመለሰላቸዉ ጊዜ ክብሩን እና ማረጋገጫዉን አሳያቸው ፡፡

“ ከጣላቶቹ ጋር የእግዚአብሄር የሆነ የእግዚአብሄር ጦርነት ዝርፊያ እዉነተኛ ድል ነው (ኢሳ 23፡ 18, 34፡ 2) ፡፡ የእግዚአብሄር ፍርድ ያለማስጠንቀቂያ በፍጥነት ስለሚመጣ አባ ጨጓሬ እና አንበጣ በፍጥነት እና ሙሉ ለሙሉ አንድን ማሳ እንደሚከፋፍሉ የተሰበሰበ ይሆናል (1ተሰ 5፡ 2) “ ፡፡ እግዚአብሄርን መፍራት የፂዎን ሀብት ነው ፤ ይህ ከሕዝቅያስ ድርጊት ጋር የሚፃረር ነው፡ “ ይህ ምዕራፍ ከአሶር እና ከሌሎች ሕዝቦች እነርሱን በመታደግ የአዳኙን ንጉስ ከፍ ያለ ክብርን በሕዝቡ ላይ ያቀርባል ፤ ፍትሕ እና ጽድቅ ምናልባትም እንደ እዉነተኛ ፍትህ እንደ ገና ገልፆአል” ፡፡

ቁጥር (5-6) የፂዎንን መቀየር በማሳየት ይጀምራል ፡፡ በቁጥር (7-9) አሁንም ይሁዳ ድነት ያስፈልገዋል ፤ የኢሳይያስ ትንቢት አሽሙር የሚመስል ነው ፡፡ “ የይሁዳ አምባሳደሮች በምሬት አለቀሱ ምክንያቱም አሶር ስጦታቸዉን በመዉሰድ ኢየሩሳሌም ሰለከበበ ፤ በአሶር እና በይሁዳ መካከል ያለዉ ስምምነት በመሰበሩ መንገዶቹ ደህና አይደሉም “ ፡፡ የሚያስፈልጋቸዉ ነገር ነበር እግዚአብሄርም ምላሹን አሳያቸው ፤ ቁጥር (11-12) የአሶርን መጥፋት ይደርሳሉ ፡፡ የእግዚአብሄር መስፈርት እስራኤላዊያን ቅዱሱን መቅረብ ከፈለጉ በቅድስና እንዲኖሩ ነበር ፤ ጌታን ለመቅብ የሚጠበቁት ነገሮች ሁሉም ወደ እግዚአብሄር በቅድስና መምጣት፣ በትክክል መናገር፣ በጉልበታቸዉ በትህትና በመንበርከክ መምጣት ነበሩ ፡፡ “ በትልቅ ማጣቀሻ የእግዚአብሄር ማደሪያ ያመለክታል (ቁጥር 5) - ፃድቃን ከእግዚአብሄር ጋር ለዘላለም የሚኖሩበት ስፍራ “ ፡፡

እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ይሰጣል ፡፡ “ ድግሶቹ ከልብ የተከበሩ የነበሩና (ኢሳ 30፡ 29) የግብር ይዉጣ ስራ አልነበረም (ኢሳ 29፡ 1) ፤ የተወሰዱ አይሆንም ማለት ስደት ያበቃል ማለት ነው ፡፡ የይሁዳ ወዲያዉኑ/ፈጣን የሆነዉ ድነት ከመጨረሻዉ ነፃ መዉጣታቸዉ ጋር ይገናኛል “ ፡፡

የይሁዳ መከላከያ በቁጥር ከእግዚአብሄር ጥበቃ የተነሳ መርከብ የማይሸከም በሰፊ ወንዞች እና ጎርፎች የተገለፀ ነበር ፤ የወንዝ ማጣቀሻ /ማሳያ ወንዝ ከቤተ መቅደሱ በደቡብ በኩል በፈሰሰ ጊዜ ሕዝቅኤል 47 ላይ ይመልሳል ፡፡

መደምደሚያ

ከኢሳ (33፡ 17-24) “ የእግዚአብሄር ድል አድራጊነት በአሶር ላይ አንድ ቀን ቅዱሷን ከተማ ለማጥፋት የሚሰበሰቡትን የመላዉ የአሕዛብን ስርዓት ላይ ለድል አድራጊነቱ የአደራረግ ልምድ ነበር (ዘካ 14፡ 1-9) “ ፡፡ የኢሳይያስ 33 ትንቢት ቅደም ተከተሉ፡ የወቅቱ ሁኔታ፣ ከዚያ በመቀጠል በንጉስ ሰናክሬም ላይ መተንበይ፣ የመሲሁ መምጣት እና በመጨረሻም ለሁለተኛ ጊዜ የክርስቶስ መምጣት ነው ፡፡ ዉጤቱ በኢየሩሳሌም ሰላም እና አንድነት ነው ፡፡ ኢሳ (32፡ 1) ንጉሱ በፅድቅ እንደሚገዛ ይናገራል ፡፡

የታላላቅ ነቢያት ጥናት አላማ በሁሉም መፅኀፍት ላይ መሲሁ የት እንደሚታይ እና እነዚህ መፅሀፍቶች እንዴት በአንድ ላይ እንደሚጣጣሙ ነው ፡፡ ቁልፍ ሀሳቡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ጋር ነው አማኑኤል የሚል ነው፣ እንደገናም ይመጣል ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p.839.

  2. Nelson’s Commentary, p. 839.

  3. Nelson’s Commentary, p. 839.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1990), p. 40.

  5. Wiersbe, p. 40.

  6. Nelson’s Commentary, p. 840.

  7. Nelson’s Commentary, p. 840.

  8. Nelson’s Commentary, p. 840

  9. Nelson’s Commentary, p. 840.

  10. Nelson’s Commentary, p. 840.

  11. Wiersbe, pp. 40, 41.

ጥያቄዎች

  1. እነዚህ መፅኀፍት በምን የጋራ/ተመሳሳይ ናቸው፡ ኤር (5፡ 21), ሕዝ (12፡ 2), ማቴ 13፡ 15, ሐዋ 28፡ 27 እና ሮሜ (11፡ 8) ? በእነዚህ መፅኀፍት እና በኢሳ (32፡ 3) መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ?
  2. ኢሳ (32፡ 6-7) ከፈታችሁ የቀደመ/የተጫወተ ሲሆን አይታችሁታል ወይስ ሰምታችሁታል ? የሐሰት ትምህርትን የሚያስተምሩ /የሚሰብኩ ሐሰተኛ ሰባኪዎች አሉ ? በፍርዶች ላይ ያሴራሉ ይዋሻሉስ ? በግል አስተያየታችሁ መቼ ያበቃል ?
  3. ኢሳ( 33፡ 15-24) የክርስቶስን ሁለተኛ መምጣት እና የሚከተለዉን አገዛዝ ጊዜ የገለፁ በመሆን ይከሰታሉ / ይታያሉ ፤ በዚህ ዳሰሳ/ጥናት ትስማማላችሁ ወይስ በግል አስተያየታችሁ ከኢሳይያስ ዘመን የነበር እና ቀድሞ እንደሆነ ትስማማላችሁ ? ለምን ?
  4. በኢሳይያስ (32-33) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 33:2

“LORD, be gracious to us! We wait for You. Be our strength every morning and our salvation in time of trouble.”

የእግዚአብሔር ህዝብ ሁሉንም ነገር ፈልጓል ነገር ግን እግዚአብሔርን አልፈለገም ፡፡ በሌሎቹ ህዝቦች ከጠፉ ከተካዱ በኋላ ይመልሳቸው ፣ ይጠብቃቸው ደግሞም ከጊዜው ሽንፈትና ጥፋት ይቤዣቸው ዘንድ የቀራቸው ብቸኛ ተስፋ እግዚአብሔርን መጠበቅ ብቻ ነበረ ፡፡ እግዚአብሔር ፈራጃቸው ፣ ህግ ሰጫቸው ደግሞም ንጉሣቸው ነበር ፡፡ ከእግዚአብሔር ርቀው የነበሩትም ጭምር የእርሱን መልካምነት ይፈልጉታል ፡፡ ከእግዚአብሔርም ጋር አብረው ሲራመዱ የነበሩት እነርሱ እርሱ ኋይላቸው እንደነበር አውቀዋል ፡፡

ስኬትን ስትፈልጉ ፤ በሰዎች ዘንድ እውቅናን ዋጋን ለማግኘት ስትጥሩ ፤ በራሳችሁ ኋይል ታግላችሁ ሲያቅታችሁ ስትወድቁ …… ተስፋን እና እርዳታን ለማግኘት ወደዬት ነው የምትዞሩት ? በተስፋ መቁረጥ ጉድጓድ ውስጥ ለመቀመጥ ልትወስኑ ትችላላችሁ ፡፡ ወይም ደግሞ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ በጌታ ተስፋ ልታደርጉ ትችላላችሁ ፡፡ በችግራችሁ ሰዓት በዚያ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ከጎናችሁ ይገኛል ፡፡ ኃጢአትን ማድረግ በጣም ብታበዙም ፤ ወደ ሚወዳችሁ አባታችሁም እቅፍ ለመመለስ በጣም ብዙ ነገር ብታበላሹም እንኳ ነገር ግን ለእርሱ በፍጹም ሩቅ አይደላችሁም ፡፡ እርሱ አማኑኤል ነው ፡፡ እርሱ ከእናንተ ጋር የሆነ አምላክ ነው ፡፡ ፍቅሩ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ይደርሳል ፡፡ ከታላቅ ፍቅሩም ፈጽሞ ምንም ነገር ሊለያችሁ አይችልም ፡፡ ሁልጊዜ ወደ እርሱ መመለስ ትችላላችሁ ፡፡ ስለዚህም በንጋት እርሱን ጠብቁ ፡፡ በኃይል ከፍ እንድያደርጋችሁ እርሱን ጠብቁ ፡፡

“ አቤቱ ፥ ማረን አንተን ተማምነናል ፤ ጥዋት ጥዋት ክንድ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን ። “

  • ኢሳይያስ 33፡2

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 33:13 — “ እናንተ በሩቅ ያላችሁ የሠራሁትን ስሙ፥ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እወቁ ። “

ኢሳይያስ 33:22 — “ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው ፥ እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው ፥ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው ፤ እርሱ ያድነናል ። “

ዕብራዊያን 13:5 — “ አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን ፥ ያላችሁም ይብቃችሁ ፤ እርሱ ራሱ ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና ፡፡ “