The Lord Rebuked Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እስካሁን በሕዝቡ ላይ ስለሚመጣዉ ፍርድ ሂደት በማየት ቆይተናል በዚህ ሂደት ደግሞ በረከት የተካተተ ሲሆን በመጨረሻም ለመሲሁ የተዘጋጁ ስለሚያደርጉ የንስኃ መልዕክቶች እናያለን ፡፡ ሸክም ወይም ፍርድ በሰማሪያ፣ በይሁዳ እና በአሶር ላይ በተደጋጋሚ የተደረጉ ነበሩ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ኢሳይያስ በእግዚአብሄር ላይ ከመደገፍ ይልቅ የሰዉን ድጋፍ የሚፈልጉትን ነቀፋቸው (በምዕራፍ 29) ፤ በምዕራፍ 30 እና 31 ኢሳይያስ በተለዬ በግብፅ ላይ ስላለ ከንቱ መደገፍን ደርሷል/እንደዳሰሰ “ ይናገራል ፡፡ ለኢየሩሳሌም መልዕክቱበራሳቸዉ ጥንካሬ ላይ እንዲደገፉ - በግብፅም ላይ እንዲደገፉ አልነበረም ፡፡ ኢሳይያስ ከእግዚአብሄር የሆነዉን መልዕክቱን መስማት የሚያስፈልጋቸዉ ትኩረቱን እንዲሰጡት እርቃኑን በመሆን ትንቢት መናገሩን /መተንበዩን ቀጠለ ፤ ነገር ግን እስራኤል ከእግዚአብሄር ፍቃድ በተቃራኒ ታማኝነትን ማድረግ ቀጠሉ ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (30፡ 1-7)፡ እስራኤል እቅድን ለማቀድ ሞከረች ነገር ግን የእግዚአብሄር እና የመንፈስ ቅዱስ አልነበረም ፡፡ እስራኤል በተደጋጋሚ በኃጢዓት ላይ ማስተካከያበሚሰጠው የእግዚአብሄርን ምሪት ሳይፈልጉ ዉሳኔዎችን አደረጉ ፡፡ በሕዝቅያስ አማካሪ ምክር ላይ ህብረትን/ጥምረትን በመፈለግ ወደ ግብፅ ወረዱ (ቁጥር 2) ፡፡ ዋይርስቤ “ እንደ ታላላቅ መሪዎቻቸው - እንደ ሙሴ (ዘኁ 27፡ 1)፣ ኢያሱ (ኢያ 9፡ 14)፣ ዳዊት (1ሳሙ 30፡ 7-8) እና ኢዮሳፍጥ (1ነገ 22፡ 7) - የኢየሩሳሌም መሪዎች የእግዚአብሄርን ፍቃድ አልፈለጉም “ በማለት ገልጾአል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የትምህርቱ ንፅፅር በኃያሉ አምላክ ጥላ ስር በመታመን ይሆናል “ (መዝ 91፡ 1) ፡፡
በቁጥር 3 እስከ 5 ድረስ ኢሳይያስ እስራኤል ኢሳይያስ ምክርን በጠየቀች ጊዜ ከግብፅ እርዳታን በመፈለግ ለምን እስራኤል እርዳታን ለመጠየቅ ዉሳኔ እንዳደረገች ጠየቀ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ከካየሮ ጥቂት 50 ማይል በስተ ደቡብ በጣኔስ ቅያሬ (19፡ 11-13) ከጺዎን የመጡ የአይሁድ ሕዝቦች አምባሳደሮች እንደሚሆኑ “ ይናገራል ፡፡ እስራኤላዊያን ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ መዋጮን በመክፈል በአሶራዊያን ላይ ጥበቃን ለመግዛት በእንስሳቶች ላይ ንብረታቸዉን ጫኑ/አደረጉ ፡፡
በቁጥር 7 ግብፅ ከረዓብ ጋር የተነፃፀረች ነው፡ “ ቃል በቃል ረዓብ ተፈጥሮን እንደሚቃወም አምላክ ከሌላቸዉ አስተምሮዎች የነበረ ማዕበል ወይም ብስጭት ድራጎን ነበር ፡፡ ረዓብ እና ሌዋታን እግዚአብሄር የሚያጠፋቸዉ የአለም የክፋት ኃይል ምሳሌዎች ናቸው (51፡ 9) “ የግብፅ ርዳታ ከንቱ ነው ፡፡
ኢሳይያስ (30፡ 8-17)፡ ኢሳይያስ ይሁዳን/ኢየሩሳሌምን አክብረዉት ያልነበረዉን የእግዚአብሄርን ትዕዛዞችን በሰሌዳ እና በመጽሐፍ ላይ እንዲፅፉ ነገራቸው ፡፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ “ እስካሁን ያጠናነው ቀድሞ የተፃፉት ሰሌዳዎች ከክርስቶስ ልደት እስከ 1350 በፊት የተጠቀሰ ሊሆን ይችላል ፤ በደቡብ ቱርክ ወደብ መርከብ ማረፊያ ከክርስቶስ ሞት 1986 በኋላ የተገኙ ነበሩ ፤ እስከዚህ ጥናት ድረስ የቀደሙት ሰሌዳዎች በኒቬህ አጠገብ በኒመሩደ ግንብ ላይ እስከ ከክርስቶስ ልደት 700 በፊት የተመዘገቡ ነበሩ ፡፡ ኢሳይያስ የእስራኤልን ሰዎች ያላየዉን እና ነቢዩ ያልተነበየዉን ራዕዩን በመናገር ከሰሳቸው ፤ ምንም ነገር የተነገራቸዉ ለመሆን አልፈለጉም ፤ ዉዥንብርን ብቻ መስማት ፈለጉ ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ኢሳይያስ ብቻቸዉን እንዲተዋቸዉ ፈለጉ ፡፡ በቁጥር 11 ኢሳይያስ ትንቢት መናገሩን እንዲያቆም በነገሩት ጊዜ በጣም ጉልህ ቃላቸው ይመጣል ፡፡
የእግዚአብሄርን ፍርድ ዉጤት የተደጋገመ ምሳሌ በመከተል ቁጥር 15ወደ ንስኃ እና እረፍት መልዕክት ይመለሳል ፤ ይህ ንስኃ በእግዚአብሄር ላይ የመጨረሻ መታመንን ይፈልጋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ዝምታ እና ሙሉ መታመን ምናልባትም እንደመጨረሻ መታመን ደግሞ ይነገራል ፤ ከራሳችን ጥንካሬ ይልቅ በእግዚአብሄር ኃይል ብቻ እዉነተኛ እረፍት ማግኘት እንደሚችል “ ይገልፃል ፡፡
እንዲህ አይነቱ መታመን መጠበቅን ይፈልጋል ፡፡ ምንድነዉ የሚፈጥነው ? መፈጥን ለምን ይሰማል ? በእግዚአብሄር ታመኑ እንጂ አትበሳጩ ፡፡ ማስተዋል ያለበት እቅድ ዋጋ አለዉ ነገር ግን በእግዚአብሄር ለማመን አያስፈልግም ፡፡ ምላሽ መስጠት እና ማምለክ አለብን ፡፡
ቁጥር (1-17) ስለ እስራኤል በግብፅ ላይ ስላሉ መደገፎች ሲሆኑ የኢሳይያስ ቃል ደግሞ በአጭሩ እንዲያቆሙ ነው ፤ ነገር ግን ፍርድ፣ ከዚያም ተስፋ፣ ቃል መግባት እና በመጨረሻም በረከት ሁሉንም የኢሳይያስ ትንቢት ይይዛቸዋል ፡፡
ኢሳይያስ (30፡ 18-33)፡ እነዚህ ጥቅሶች እግዚአብሄር እስራኤልን እንደሚያድናት እና አሶርን እንደሚያጠፋት ቃል ይገባሉ ፡፡ ጌታን መጠበቅ በረከትን ያመጣል ፤ እግዚአብሄር በመጀመሪያ ጩኸታቸዉ እንደሚሰማቸዉ እና እንደሚመልስላቸዉ ተስፋን ይሰጣል ፡፡ “ በእስራት እንደ ነበሩ እግዚአብሄር ብዛት ያለዉ ኃሳብን/ምርጫን እየሰጠ ነበር (1ነገ 22፡ 27) ፤ ነገር ግን ከፍርድ በኋላ እግዚአብሄር ድነትን ይሰጣቸዋል፡ የእስራኤል አይን ያያሉ (29፡ 24) ፡፡ ምናልባትም አስተማሪዎች ነቢያትን ያመለክታሉ (ቁጥር 10) “ ፡፡
በቁጥር 21 በመሰረቱ የእስራኤል ሰዎች ኢሳይያስን በየት መንገድ እንዲሄዱ የሚነግራቸዉ አስተማሪ እንደሆነ እንደ አስተማሪይ ያስተዉሉታል ፡፡ “ ህዝቡ መንፈሳዊ አባቶቻቸዉ በግልፅ እንደ ነበሩበት አይነት መንገድ እየኖሩ ነበር (ቁጥር 20)፣ አሁን በህያዉ እግዚአብሄር መንፈስ ያስባሉ “ ፡፡
ዉጤቱ ህዝቡ ጣዖቶችን/የተለበጡ እቃዎችን ያስወግዳሉ (ቁጥር 2) የእግዚአብሄርም በረከት ከማሳ እስከ መንጋ ድረስ ይዘረጋል (ቁጥር 23) ፡፡ የሚመጣዉ ድነት ተፅዕኖ በቁጥር (23-26) ላይ የተገለፀ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እነዚህ ፅኁፎች የሚመጣዉን ድነት ግዝፈት ያብራራሉ ፤ በእግዚአብሄር ላይ ከመታመን የሚመጣዉ ድነት በቂ የሆነ ዝናብ መምጣት እና ኃይለኛ ጎር ጋር የተገናኘ በረከት እንደሆነ (32፡ 2, 41፡ 17, 18) “ ይገልፃል ፡፡
በቁጥር (27-33) ኢሳይያስ የአሶርን መጥፋት በተመለከተ ገልፆአል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የአሶር መጥፋት ትንቢያ ሁለት ኡደቶችን ይይዛል፡ 1) አንዱ ከማጥቃት (ቁጥር 27, 28, እና 30-31) እና 2) አንዱ ከደስታ (ቁጥር 29 እና 32)” ፡፡
ዋይርስቤ “ ሲዖል ለባቢሎን ንጉስ እንደተዘጋጀ (ኢሳ 14፡ 9) ቶፌት ለአሶር ንጉስ የተዘጋጀ ነበር ፤ ቶፌት የሞሎክ አምላኪዎች ልጆቻቸዉን ይሰዉበት የነበረ ስፍራ ነበር (2ነገ 16፡ 3, 21፡ 6, ኤር 7፡ 31-32, 19፡ 6, 11-14) “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ቶፌት የሲዖል ምስልልን የሚወክል ነው ፡፡
መደምደሚያ
እነዚህ ቁጥሮች ከአርማጌድዮን እና ከክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው ፡፡ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሄር ተመለሰች ፤ ወደ እግዚአብሄር ጮኹ ፤ በመጨረሻም ቆይቶ ገሀነም ወይም ሲዖል ተብሎ ታዉቆ በነበረው የአሶር ንጉስ ማብቂያ በነበረዉ በቶፊት ዉጊያ እና መስዋዕትነት ነበር ፡፡ በመጨረሻም የእግዚአብሄር ተስፋ ይገለጣል ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p.837.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p.37.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837..
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Nelson’s Commentary, p. 837.
Wiersbe, p. 38.
ጥያቄዎች
-
ኢሳ (30፡ 1-5) ከእግዚአብሄር ይልቅ በፈርዖን ላይ ስለመደገፍ ይናገራል ፤ ይህንን በማድረግ የይሁዳ እና የኢየሩሳሌም ሰዎች ዉርደት፣ ክብር ማጣት እና እፍረት ገጠማቸው ፡፡ ከእግዚአብሄር ዉጪ ሌላ የተደገፋችሁበት ጊዜ አለን ? እነዚህ ተመሳሳይ ስሜቶች ተሰምቷችኋል ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
-
የእግዚአብሄርን ስሌት ማሰብ አቁማችሁ ታውቃላችሁ ? በኢሳ (30፡ 17) እግዚአብሄር “ ከአንድ ሰዉ ዛቻ የተነሳ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ ፤ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሳ ትሸሻላችሁ “ ይላል ፤ በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ እንዲህ አይነት ስሌት ታያላችሁ (ዘሌ 26፡ 8, ዘዳ 32፡ 30, ኢያ 23፡ 10) ? በእነዚህ በሁለቱ መካከል ልዩነቱ ምንድን ነው ? ምንድን ነዉ ልዩነት ያደረገው ?
-
በኢሳ (31፡ 4) አንበሳ እረኞች በመጡበት ጊዜ ሸሽቶ ለምን አልሮጠም ? ይህ ክርስቲያኖች እና ቤተ ክርስቲያኖች በጣላት እና በድምፁ ላይ ፀንተዉ መቆም ያለባቸው አይነት መንገድ ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይሆንም ?
-
በኢሳይያስ (30-31) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 30:18
“Therefore the LORD is waiting to show you mercy, and is rising up to show you compassion, for the LORD is a just God. All who wait patiently for Him are happy.”
ከፍርድ በኋላ እንኳ ፣ ከጥፋት በኋላ እንኳ ኢሳይያስ እስራኤላዊያንን በዚህ እውነት አበረታቸው ፡- እግዚአብሔር እየታገሳችሁ ነው አላቸው ፡፡ እርሱ ምህረቱንና ርህራሄውን ያሳይ ዘንድ ይታገሳል ፡፡ እርሱ ያስብላችኋል ፡፡
የእግዚአብሔር ምህረት አያልቅም ፡፡ የጸሀይ በየቀኑ መውጣት እርግጥ እንደሆነ ሁሉ እንዲሁ የእግዚአብሔርም ምህረት ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ፡፡ በምታልፉበት መከራ ታገሱ ከዚያም ደስተኛ ትሆናላችሁ ፡፡ ምናልባት ህይወታችሁ የተበታተነ ሊመስል ይችላል ፣ ሊጠገን የማይችል ስብራት እንደገጠማችሁ ይሰማችሁም ይሆናል ፤ ሆኖም ግን ጓደኞቼ እግዚአብሔር ከትቢያ ፣ ከተቆራረጠ ከተሰባበረ ነገር ውበትን የሚሰጥ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ እነዚህን ነገሮች ስለ ክብሩ ሲል ወደሚያምር ነገር ይለውጣቸዋል ፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ አታጣድፉ ፡፡ ብዙውን ጊዜ ቶሎ የሚሆን አይደለም ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምህረት እየመጣ ነው ፡፡ ዛሬ ፣ ነገ ፣ ከነገ ወድያም ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ፡፡ የወደቃችሁበት ያላችሁበት ሁኔታ ምንም አይነት ይሁን እግዚአብሔር በምህረቱና ሩህሩህ በሆነ ፍቅሩ ሊያጥባችሁ ይፈልጋል ፡፡ እርሱን ጠብቁ ፡፡ በትዕግስት ጠብቁ ፣ ደስተኛም ትሆናላችሁ ፡፡
“ እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል ፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል ፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው ። “
- ኢሳይያስ 30፡18
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 30:12-15 — “ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፥ በእርሱም ተደግፋችኋልና ፣ ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል ። የሸክለኛ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፥ ሳይራራም ያደቅቀዋል ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም ። የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ ፡፡ “
ኢዩኤል 2:13 — “ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ፥ ቍጣው የዘገየ ፥ ምሕረቱም የበዛ ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ ። “
ያዕቆብ 4:8 — “ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል ። እናንተ ኃጢአተኞች ፥ እጆቻችሁን አንጹ ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ ፥ ልባችሁን አጥሩ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።