Current And Future
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 28-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስ በመፅሀፉ በመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፎች ዉስጥ እስራኤልን እና ይሁዳን ደረሰ ፡፡ ብዙጊዜ ይሁዳና እስራኤል በአንድ ላይ በመድረስ ኢሳይያስ ያለሟቋረጥ በትንቢቱ ኢየሩሳሌምን አቀረበ ፤ ምዕራፍ (13-23) በዙሪያ ባሉ አሕዛቦች ላይ የሚመጣ የፍርድ ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (24-27) በአለም ላይ ስለሚሆነዉ ፍርድ ነገር ግን ቅሬቶቹ በእግዚአብሄር ፍርድ በኩል እንደሚድኑ የሚያወሩ ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (28-33) በሰማሪያ፣ በኢየሩሳሌም እና በአሶር ላይ የጦር ሸክምን ይይዛሉ ፡፡ ለኢሳይያስ ቃላችን አማኑኤል ነው ፡፡ “ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች “ (ኢሳ 7፡ 14) ፤ ይህ በኢየሱስ መምጣት ጊዜ የተፈፀመ ነበር፡ “ ቃልም ስጋ ሆነ ጸጋንና እዉነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለዉ ክብር የሆነዉን ክብሩን አየን “ (ዮሐ 1፡ 14) ፡፡ የዚህ ሁሉ የፍርድ ትንቢት መካከል ላይ የሚመጣዉ አማኑኤል መልክ ናቸው ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ 28፡ ዋይርስቤ በኢሳይያስ 28 አራት እዉቅናዎችን አጉልቶ አሳይቷል፡
- የእግዚአብሄር ፍርድ በኤፍሬም ላይ (ቁጥር 1-6) - በተለዬ ኤፍሬም የሰሜኑ መንግስት ማጣቀሻ/ማመልከቻ ነበር ፡፡ ቢያንስ በአካል ከጨለማቸዉ ዉስጥ የእግዚአብሄር ፍርድ በእነርሱ ላይ ይመጣል ፤ በእግዚአብሄር ፍርድ መካከል ላይ ጥቂቶች -ቅሬቶቹ ብቻ ይቆማሉ (ቁጥር 5) ፡፡
- ይሁዳ የእግዚአብሄርን ትንቢት በማቃለል የእግዚአብሄርን ቃል ገፋ (ቁጥር 7-13) - አንዳንድ ቅሬቶችም እንኳን በኤፍሬም ሰካራሞች ተፅዕኖ የተደረገባቸዉ ነበሩ (ቁጥር 7-8) ፡፡ ሕዝቡ የእግዚአብሄር ፍርድ እንደሚመጣ ያስጠነቀቃቸዉን የእግዚአብሄርን ትንቢት ለማዳመጥ እምቢ አሉ (ቁጥር 10-13) ፡፡
- እግዚአብሄር የሕዝቡን እረፍት ያቀርባል ነገር ግን ቃሉን አይሰሙም (አይታዘዙም) (ቁጥር 12-20) - እግዚአብሄር ሕዝቡ እረፍትን እንዲያገኙ ፈለገ ነገር ግን ለመስማት እምቢ እስካሉ ድረስ በጣም ትንሽ በነበረ አልጋ ላይ እየተኙ እንደ ነበር ይመስላል (ቁጥር 20) ፡፡
- እግዚአብሄር እንደማይፈርድባቸው የይሁዳ በራስ መተማመን ቅዠት/ዉዥንብር ነበር (ቁጥር 21-29) - ይህ ወደ ኢሳይያስ 29 አስፈላጊ መሸጋገሪያ ነዉ ምክንያቱም በተመሳሳይ የኃጢዓት ጥፋተኝነት በይሁዳና በኤፍሬም ላይ የእግዚአብሄር ፍርድ እየመጣ ስለሆነ ፡፡
ኢሳይያስ (29፡ 1-14)፡ ማክአርቱር በዚህ ምዕራፍ በእግዚአብሄር የተነገሩ ሁለት ዋና ዋና አዘኖችን አመልክቷል ፡፡ የመጀመሪያዉ ሀዘን ስለ ኃይማኖታዊ ቅርፅ ዝርዝሮች ነበር ፡፡ “ አርኤል “ ማለት የከተማዋን ጥንካሬ የሚያመለክት “ የእግዚአብሄር አንበሳ “ ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄር ፍርዱና በኢየሩሳሌም ላይ በመናገር በቃሉ ላይ ጨዋታን ጥቅም ላይ አዋለ ፡፡ አርኤል ኢየሩሳሌምን ለመጥቀስ ጥቅም ላይ የዋለ ነበር ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ አንበሳ የአሶር ሐገራዊ ምልክት ነበር ፡፡ ነቢዩ ኢየሩሳሌም በስሟ ብቻ እንደተቀመጠች አሶር ፍርዱን ለመፈፀም የእግዚአብሄር አንበሳ እንደምትሆን አመልክቷል ፡፡ ጥንካሬዋ ምንም ቢሆን እግዚአብሄር ከተማዋን ይፈርድባታል “ ቃሏም ከአፈር ይወጣል “ (ቁጥር 4) ፡፡
ዋይርስቤ በከተማዋ ላይ የተዋጉት ራሳቸዉም በእግዚአብሄርም ፍርድ/ቅጣት ስር እንደሚመጡ ፅፏል (ቁጥር 5-8) ፡፡ ኢሳይያስ የእግዚአብሄር ፍርድ “ በቅፅበት “ እንደሚመጣ ተንብዮአል ምናልባትም በኢሳ (37፡ 36) ተገልፆአል ተብሎ ይታመናል “ የእግዚአብሄርም መልዓክ ከአሶራዊያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ ፤ ማለዳም በተነሱ ጊዜ እነሆ ሁሉ በድኖች ነበሩ “ (ኢሳ 37፡ 36) ፡፡
ቁጥር (5-6) ወደፊት በቅርቡ የሚሆን በአሶራዊያን ላይ ፍርድን ሲናገሩ ቁጥር (7-8) በጣም ሩቅ ያለዉን ክስተት አስቀምጠዋል/ተናግረዋል ፡፡ ምናልባትም እነዚህ ጥቅሶች በመከራዉ መዝጊያ ላይ ስለ አርማጌዲዎን ጦርነት ይናገራሉ ፡፡ ሁሉም ሕዝብ በኢየሩሳሌም ላይ ቢመጡባትም ኢየሩሳሌም ትድናለች ፡፡ ራዕ (19፡ 11-21) የኢሳይያስን ትንቢት ያሳያል/ይገልፃል፡
“ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ እነሆም አምባ ላይ ፈረስ የተቀመጠበትም የታመነና እዉነተኛ ይባላል በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም ፡፡ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው በራሱ ላይም ብዙ ዘዉዶች አሉ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተፃፈ ስም አለው ፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጎናጽፎአል ስሙም የእግዚአብሄር ቃል ተብሏል ፡፡ በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠዉ ይከተሉት ነበር ፡፡ አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል ፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሄርን የብረት ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል ፡፡ በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት ፡- የነገስታት ንጉስና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው ፡፡ አንድም መልዓክ በፀሐይ ዉስጥ ቆሞ አየሁ በሰማይም መካከል ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፡- መጥታችሁ የነገስታትን ስጋና የሻለቃዎችን ስጋ የብርቱዎችንም ስጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ስጋ የጌታዎችንና የባሪያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ስጋ እንድትበሉ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሄር እራት ተከማቹ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ፡፡ በፈረሱም የተቀመጠዉን ጭፍራዎቹንም ይወጉ ዘንድ አዉሬዉና የምድር ነገስታት ጭፍራዎቻቸዉም ተከማችተው አየሁ ፡፡ አዉሬዉም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአዉሬዉን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባህር ተጣሉ “ ፡፡
መደምደሚያ
ከእነዚህ ከወደፊት ዉጊያዎች የተነሳ በፍራት ልንመላለስ አይገባም ፡፡ አንድ ነቢይ ከክርስቶስ ልደት 800 አመት በፊት ገና አሁንም ወደ ፊት የሚሆንን ዊጊያ/ጦርነት ግለፁ የሚያስደንቅ ነው ፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሄር ሕዝቡን ይታደጋል/ያድናል ፡፡
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2007), pp. 34- 35.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 792.
Wiersbe, p. 36.
Wiersbe, p. 36.
ጥያቄዎች
-
ከመዉደቃቸዉ በፊት በእስራኤል በሰሜኑ መንግስት በኤፍሬም ምንድን ተገለጠ ? (ኢሳ 28፡ 3, 7, አሞ 4፡ 1, 6፡ 1, 6)
-
እዉነተኛ የክብር አክሊልን ሀሰት ከሆነዉ ጋር አነፃፅሩ ፤ (ኢሳ 28፡ 1, 5, ያዕ 1፡ 12, ራዕ 2፡ 10)
-
የኢየሩሳሌምን መሪዎች ተስፋቸዉን በሐሰተኛ ነገር ላይ ተስፋቸዉን አድርገዉ እንደ ነበር ሲናገር እግዚአብሄር አድርጎት የነበረዉ ተስፋ ምን ነበር ? በመጨረሻ ይህ ትንቢት ወደ ማን ይመራል ? (ማቴ 21፡ 42, ሐዋ 4፡ 11, ኤፌ 2፡ 20, 1ጴጥ 2፡ 6-8)
-
በኢሳ (29፡ 1) አርኤል ምን ከተማን የሚወክል ይመስላል (ኢሳ 29፡ 7-8) ? አብዛኛው ሕዝቦች በተቃወሟት ጊዜ ምን ተፈጠረ ?
-
በኢሳ (29፡ 13-14) ያ ህዝብ የነበረዉ ችግር ምን ነበር ? ከዚህስ የተነሳ እግዚአብሄር ምን አደረገ ? በጳዉሎስ ዘመን በግሪክ አለም እንዴት እንደተጫወቱ እንዴት ታዩታላችሁ (1ቆሮ 1፡ 19) ? በአሁኑ ጊዜ ይህ እንዴት እየተተገበረ እንደሆነ እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
በኢሳይያስ (28-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 29:13
“The Lord said: Because these people approach Me with their mouths to honor Me with lip-service yet their hearts are far from Me, and their worship consists of man-made rules learned by rote.”
ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ሁሉንም ህዝቦች የሚያካትት ታላቅ ጦርነት እንደሚኖር ኢሳይያስ ተነበየ ፡፡ በጦርነቱም ኢየሱስ ድል ያደርጋል ፡፡ ኢየሱስ ስለሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር ያውቃል ፡፡ እርሱ አካሄዱን ከእርሱ ጋር ያደረገውን ያውቃል ፡፡ አመጸኛ ልብ ያለውንም ያውቃል ፡፡ ምንም እንኳ ከውጪ ሲታዩ ጠንካራ ክርስቲያን ቢመስሉም ጌታ ግን በቤታቸው በራቸውን ዘግተው ምን እንደሚሰሩ በተለይም ደግሞ በልባቸው ምን እንዳለ ያውቃል ፡፡ እግዚአብሔር ያውቃል ያያልም ፡፡ ከመገኘቱ ልታመልጡ አትችሉም ፡፡
ከእግዚአብሔር በመደበቅ በእናንተ ላይ የሚከሰተው ሀዘን ዋጋ የለውም ፡፡ በውሸት ፣ በማታለል እንድሁም ስለ ራሳችሁ በመዋሸት የሚከሰተው ስቃይ ወጋ የለውም ፡፡ አለም ፡- የውሸት ጥፍር ፣ የውሸት ቆዳ ፣ የውሸት ዜና ይሰራል ፡፡ በመጨረሻም ውሸት ሲገለጥ እውነቱ ይታያል ፡፡ ጌታ ልባችሁን ያያል ፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ በጌታ ፊት ኑና በህይወታችሁ ውስጥ ስላለ ማንኛውም ውሸትና ሽንገላ ተናዘዙ ፡፡ ልክ ልትሆኑ እንደተፈጠራችሁት በጌታ ፊት እውነተኛና ግልጽ ሁኑ ፡፡ ፊቱን ፈልጉ ደስታና ሰላምም ይኖራችኋል ፡፡ ሰላም በጨለማ ውስጥ የለም ፡፡ ደስታ በጨለማ ውስጥ የለም ፡፡ ጸጋና ምህረት ወደተትረፈረፈበት ወደ ክርስቶስ ብርሃን ግቡ ፡፡ በአሸናፊነት ልትኖሩ ነው የተፈጠራችሁት ፡፡ እርሱ ለእናንተ ወዳለው ወደ ታላቅ ፍቅሩ ለመግባት ጊዜው አሁን ነው ፡፡
“ ጌታም ፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና ፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና ፡፡ “
- ኢሳይያስ 29፡13
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 139:7-12 — “ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ ? ወደ ሰማይ ብወጣ ፥ አንተ በዚያ ነህ ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ ፥ በዚያ አለህ ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር ፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች ። በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች ፤ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው ። “
ኢሳይያስ 29:15 — “ ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው ፦ ማን ያየናል ? ወይስ ማን ያውቀናል ? ለሚሉ ወዮላቸው ! “
ዕብራዊያን 4:13 — “ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።