Waiting On The Trumpet
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 26-27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የኢሳይያስ ትንቢቶች ቀላል እና እንዲሁም ደግሞ የተወሳሰቡ ናቸው ፡፡ ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት 640-680 መካከል በፊት ለአራት እስራኤላዊ ነገስታቶች፡- ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝ እና ለሕዝቅያስ ትንቢት ተናገረ ፡፡ ኢሳይያስ በዋናነት ለደቡቡ መንግስት ለይሁዳ ትንቢትን ተናገረ ፤ ይሁዳ በባቢሎን በምርኮ አልተወሰደም ነበር ነገር ግን ኢሳይያስ ያለማቋረጥ በምርኮ ከእስራኤል ጋር የሚጣመሩትን ህዝቦች ያስጠነቅቃል ፡፡
ኢሳይያስ (24-27) በመላዉ አለም ላይ የሚነገሩ ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ ይህ ፍርድ ከነፃ መዉጣት ጋር በመጣመር ይመጣል ፡፡ ኢሳይያስ 25 ከእግዚአብሄር ፍርድ ድነዉ በነበሩት ቅሬቶች መዝሙር ይጀምራል ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (26)፡ ዋይርስቤ ምዕራፍ 26 በአራት ክፍል አቅርቦታል፡
- ጠንካራ ከተማ (ቁጥር 1-6)- የፂዎን ተራራ ከፍ ከፍ ይላል፡ “ በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢዓትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል “ (ዘካ 13፡ 1) ፡፡
- የተስተካከለዉ መንገድ (ቁጥር 7-11) - መንግስቱ በተመሰረተች ጊዜ እግዚአብሄር ለከተማዋ መንገዱን እና መስመሩን ያስተካክላል ቀጥም ያደርጋል ፡፡
- ሴቶች በጉዞ (ቁጥር 12-18) - ልክ እንዳረገዘች አንድ ሴት በጌታ የመጨረሻ ቀን ጊዜ በስቃይ ዉስጥ እናልፋለን ፡፡
- ህይወት የሚሰጥ ጤዛ (ቁጥር 19-21) - ኢሳይያስ የእስራኤልን እንደ ሕዝብ መመስረት እና የግላዊ ኃሳብ ትንሳኤ ሁለቱንንም ማመልከት ይችላል ፡፡
ኮንስታብል “ ምንም እንኳን ከእስራኤል መታደስ በፊት የእግዚአብሄር ሰዎች አስቸጋሪ ጊዜያትን ቢቀምሱም ….. ለመቤዠት የአዲሲቱ ከተማ በርን እግዚአብሄር ከመክፈቱ በፊት በጠላቶቻቸዉ ላይ በሮቻቸዉን መዝጋት ያስፈልጋቸዋል “ በማለት ፅፏል ፡፡
ኢሳይያስ (27፡ 1-6)፡ እስራኤል ስለ ባህር ዘንዶዎች ብዙ አፈ ታሪኮች ነበሯቸው ፤ ምናልባትም ሌዋታን አዞ ሳይሆን አይቀርም ፡፡ ምንም ይሁን ሌዋታን እግዚአብሄር እንደሚቀጠቅጠዉ መልክ ነው ፡፡ ኮንስታብል ሌዋታን “ በእግዚአብሄር ሕዝቦች ላይ ግዙፍ የሆነ የኃይለኛ ሰልፍ ምልክት እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡
“ የተወደደዉ የወይን ስፍራ “ (ቁጥር 2) እስራኤል ነበረች ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን በመላው ታሪካቸዉ ዉስጥ አሳደጋቸዉ ጠበቃቸዉም ፤ ይሁን እንጂ “ እሾህና ኩርንችት በእኔ ላይ በሰልፍ ከነበሩ “ “ ለማረጋገጥ ትክክል የሆነዉን በመገልበጥ በምድር ላይ ያለዉን ያቃጥለዋል “ (ቁጥር 4) ፡፡ በመጨረሻም “ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል ፤ በፍሬያቸዉም የዓለሙን ፊት ይሞላል “ (ቁጥር 6) ፡፡ ይህ በዘፍጥረት 12 ለአብርሐም የእግዚአብሄር ግማሽ ተስፋ መፈፀም ሊሆን ይችላል ፡፡
ኢሳይያስ (27፡ 7-11)፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ለመቅጣት ችግሮችን በመጠቀም ለመንግስቱ ያዘጋጃቸዋል ፡፡ የግል ስቃይ/መከራ ኃጢዓትን አይሰተሰረይም ነገር ግን “ እግዚአብሄር በእኛ ላይ መታዘዝን ለማምጣት እንደ መቅጫ ችግርን ስለሚጠቀም እርሱን እና ቅዱስነቱን እንፈልጋለን “ ፡፡
ቁጥር (10-11) ለእስራኤላዊያን ከባቢሎናዊያን ምርኮ ከተመለሱ በኋላ ህይወታቸዉ ምን እንደሚመስል ምስሉን ይይዛል ፡፡ “ የባቢሎናዊያን ምርኮ የአይሁዶችን ጣዖታታ ለአንዴ እና ሁሉንም አዳነ/አጠፋ “ (ቁጥር 9) ፤ እስራኤላዊያን መረዳትን/ማስተዋልን በማጣት እግዚአብሄር ትኩረታቸዉን ለመያዝ ጥብቅ የሆነ ነገር አደረገ ፡፡
ኢሳይያስ (27፡ 12-13)፡ ኮንስታብል “ እግዚአብሄር የሕዝቡን ቅሬቶች አንድ ገበሬ ምርቱን እንደሚሰበስብ ከተስፋይቱ ምድር ይሰበስባቸዋል ፤ ጠላቶቹን ብቻ የሚያጠፋ ሳይሆን ወደ መንግስቱ የተዋጁትን እስራኤላዊያንም ይሰበስባል “ ፡፡ እግዚአብሄር ቀድሞ ጠላቶቹን አሸንፏቸዋል እንዲሁም ደግሞ አሁን “ አንድ በአንድ “(ቁጥር 12) ሕዝቡን ይሰበስባል “ ፡፡
ዋይርስቤ በእስራኤል በስርየት በመጀመሪያዉ ቀን በመጀመሪያዉ ወር ላይ መለከት መለከት እንደተነፋ ፅፏል ፤ ይህ ለእነርሱ የተለመደ ድምፅ ይሆናል ፡፡ የስርየት ቀን እግዚአብሄር ህዝቡን ከአሕዛብ ህዝቦች ባርነት ነፃ በማዉጣት በዘጸዓት ያደረገዉን ተዓምራት በሚደግምበት “ የወደፊቷ መንግስት ደስት መልክ ለሆነው “ ህዝቡን ለዳስ በዓል ያዘጋጃል ፡፡
መደምደሚያ
ለቤተ ክርስቲያን እና በእስራኤል ወደ እርሱ የተመለሱትን የጌታን መምጣት ለማሳወቅ የመለከቱን ድምፅ መጠበቅ አለብን ፡፡ መለከቱ በተነፋ ጊዜ በእርሱ መገኘት ፊት በመሆን ለበጉ ሰርግ ግብዣ በመዘጋጀት ለዘላለም ከእርሱ ጋር እንሆናለን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 755.
Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary (Colorado Springs: David C Cook, 2007), pp. 1171-1172.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 171; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.
MacArthur, p. 593.
Constable, p. 172.
Wiersbe, p. 33.
Wiersbe, p. 33.
Constable, p. 175.
Wiersbe, p. 34.
ጥያቄዎች
-
በኢሳይያስ 26 መሰረት አዕምሮአችሁን በፍፁም ሰላም እንዴት አድርጋችሁ መጠበቅ ትችላላችሁ ? ፍፁም በሆነ ሰላም በሚመስል ለመጠበቅ በሆነ ነገር ወይም ሰዉ ላይ ተደግፋችኋል ?
-
በተለመዱት ከተሞች እና “ በጠንካራ ከተማ “ መካከል ያለዉን ዉዝንብር ንፅፅር አስተዉሉ (ኢሳ 24፡ 10, 25፡ 2, 26፡ 5) ፤ ይህ “ጠንካራ ከተማ “ በምን የታሰበ ነው ለከተማዉ የእግዚአብሄርስ ወደፊት ምንድን ነው ? (ኢሳ 26፡ 1, 60፡ 14, ዘካ 14፡ 11)
-
ሞገስ ወይም ፀጋ ለክፉዎች በተገለፀ ጊዜ ምን ይሆናል (ሮሜ 2፡ 4) ? ለምን ይህ እንደሚሆን ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢሳ (26፡ 20) እግዚአብሄር “ ሕዝቤ “ ብሎ ያመለከተዉ ማንን ነው ? በአሶር አምባገነንነት ስር በመከራ ቢሆኑም እግዚአብሄር ምን ይሆናል አለ ? (መዝ 30፡ 5, ኢሳ 26፡ 19, 54፡ 7, 2ቆሮ 4፡ 17)
-
ሌዋታን ምንድን ነው ? በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ሌዋታን ከእግዚአብሄር ጋር ያልተሳካ ዉጊያ አድርጎ ይገኛል ? (ኢዮ 3፡ 8, 41፡ 1, መዝ 74፡ 14)
-
በኢሳይያስ (26-27) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 27:12
“On that day the LORD will thresh grain from the Euphrates River as far as the Wadi of Egypt, and you Israelites will be gathered one by one.”
ኢየሱስ ተመልሶ ሲመጣ ማለትም ፡- “ታላቅ መለከት ሲነፋ “ እስራኤላውያን አንድ በአንድ ይሰበሰባሉ ፡፡ በርግጥ በመጨረሻዎቹ ቀናት ጭምር እግዚአብሔር አንዳንዶችን ይጠብቃል ፡፡ እግዚአብሔር እርሱ የሚወድ ፣ የሚያይ ፣ ሁሉን የሚያውቅና የሚረዳ አምላክ ነው ፡፡ እናንተ እግዚአብሔር ከሚጠብቃቸው ውስጥ ናችሁ ፡፡
ሁሉም ሰው የሆነ ቡድን አካል መሆን ፣ መታወቅ ፣ እንክብካቤን ማግኘት ከሁሉም ይልቅ ደግሞ መወደድ ይፈልጋል ፡፡ እናንተም እንዲሁ መሆናችሁን እንዳትክዱ ! ዛሬ በዙሪያችሁ ምንም አይነት ነገር ይፈጠር በቃ ተወዳችኋል በዚህ ተስፋ ላይ እረፉ ፡፡ እግዚአብሔር እናንተን ለመሰብሰብ ሁሉን ነገር ይተዋል ፡፡ ልክ ለሜዳ አህዮች እንደሚያስብ ሁሉ ለድንቢጥ ወፍም ያስባል በርግጥም ደግሞ እግዚአብሔር ለእናንተም ያስባል ፡፡ እርሱ እናንተን ይረዳል ፡፡ ያያችኋል ይከተላችኋልም ፡፡ ከነሸክማችሁ እርሱን እመኑት ፡፡ ከነህመማችሁ እርሱን እመኑት ፡፡ በብቸኝነታችሁ እርሱን እመኑት ፡፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸው በእርሱ ለምትደገፍ ለእነርሱ ፍጹም ሰላም እንደሚሆንላቸው ተናግሯል ፡፡ እግዚአብሔርን አለታችሁ ፣ መጠለያችሁ ፣ ምሽጋችሁ አድርጉት ፡፡ ጊዜያዊ እርካታን በሚሰጡት በዚህ አለም ነገሮች ላይ ሳይሆን በእርሱ ላይ ታመኑ ፡፡ እግዚአብሔርን ብቻ ፈልጉ ሰላምንም ታገኛላችሁ ፡፡
“ በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል ፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ ። “
- ኢሳይያስ 27፡12
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 26:3-4 — “ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ ። ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ ። “
ማቴዎስ 6:30 — “ እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት ? “
ሉቃስ 15:4-6 — “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው ? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል ፤ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፦ የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።