Major Prophets Isaiah

Living With The End In Mind

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 23-25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 584 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዛሬዉ ትምህርት/ክፍል ኢሳይያስ የፍርድ ቃላቶችን መናገሩን ቀጠለ ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (23፡ 1-7)፡ ጢሮስ እና ሲዶና በባህር አካባቢ የሚገኙ ከተሞች ነበሩ ፡፡ ዳዊት እና ሰለሞን ፕሮጀክቶቻቸዉን ለመገንባት ከእነዚህ ከተሞች ዝግባዎችን ተጠቅመዋል ፡፡ ዋይርስቤ በእነርሱ ላይ ያለን ፍርድ “ እንደ ለቅሶ እና ቤት መሄድ “ በማት አጠቃልሎአቸዋል ፡፡

ኢሳይያስ (23፡ 8-14)፡ ኢሳይያስ ይህ የእግዚአብሄር ስራ ስለ ነበር ያ ፍርድ በጢሮስ እና ሲዶና እንደሚወርድ ገለፀ፡፡

ኢሳይያስ (23፡ 15-18)፡ ጢሮስ እና ሲዶና የአንድ ንጉስ ህይወት እንደሚሆን የታሰበዉን ለ70 አመታት ያክል አይኖሩም ፡፡

ኢሳይያስ (24)፡ ምዕራፍ (24-27) የአለም አቀፍ ፍርድ እና ነፃ የመዉጣት ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ በመላዉ አለም ያለ ፍርድ በቀጥታ ከመጨረሻዉ ጊዜ ጋር የተገናኜ ነው ፤ እንዲህ አይነቱ ትንቢት የመልካም እና የመጥፎ ዜናዎችን ቅልቅል ይይዛል ፤ በዚህ ክፍል ስለ መሲሁ ትንቢቶችን መረዳት ቀልድ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በመሲሁ የመጀመሪያ መምጣት እና ከሁለተኛ መምጣቱ አንፃር መካከል ልዩነት ስላለ ፡፡

የኔልሰን ማብራሪያ የምዕራፍ 24 አምስት ክፍሎችን ፅፏል፡

  1. ከኃጢዓት የተነሳ የምድር ባዶነት (ቁጥር 1-6) ፡፡
  2. በከተማዋ የጠላትነት ማብቃት (ቁጥር 7-13) ፡፡
  3. ለእግዚአብሄር ክብር ሲሆን በምድር ላይ ደግሞ ሀዘን ይሆናል (ቁጥር 14-16) - በዝማሬ ቅርፅ ይደረጋል ፤ ምንም እንኳን ምድር ቢፈረድባትም እግዚአብሄር በቅሬቶቹ ይመሰገናል ፡፡
  4. ለመላዉ ምድር መናወጥ ተስፋ ስለሌለዉ በራራ (ቁጥር 17-20) ፡፡
  5. የእግዚአብሄር ራዕይ በህዋ ላይ በፂዎን ተራራ ላይ ይገዛል (ቁጥር 21-23) ፡፡

ኢሳይያስ (25፡ 1-5)፡ ኮንስታብል በመሲሁ የሺህ አመት አገዛዝ መጀመሪያ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም የሚገቡትን ቅሬታዎችን ለመግለፅ እንደሆነ የኢሳይያስ የትንቢት ሂደት ፅፎታል ፡፡ የኢሳይያስ 24 ፍርድ በራዕይ 6 ከተገለጣ ጋር ይዛመዳል ፤ ወደ ኢሳ (24፡ 23) ስንመለስ “ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሳልና ጨረቃ ይታወካል ፀሐይም ይፍራል “ ፤ ራዕ (21፡ 23) ኃይለኛ የሆነ ስዕልን ይስላል “ ለከተማይቱ የእግዚአብሄር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር “ ፡፡

በቁጥር 3 “ የሚያከብሩህ “ “ ጠንካራ ሰዎች “ እነዚህ ሰዎች ጌታን ይከተላሉ ማለት አይደለም ፤ በአጭሩ እርሱን እዉቅና ይሰጣሉ ፡፡ “ በእነዚህም መቅሰፍቶች ያልተገደሉት የቀሩት ሰዎች ለአጋንንትና ያዩ ወይም ይሰሙ ወይም ይሄዱ ዘንድ ለማይችሉ ከወርቅና ከብር ከናስም ከድንጋይም ከእንጨትም ለተሰሩ ለጣዖቶች እንዳይሰግዱ ስለ እጃቸው ስራ ንስሐ አልገቡም ፤ ስለ መግደላቸዉም ቢሆን ወይም ስለ አስማታቸው ወይም ስለ ዝሙታቸው ወይም ስለ ስርቆታቸው ንስሐ አልገቡም “ (ራዕ 9፡ 20-21) ፡፡ በመከራዉም ጊዜ እግዚአብሄር እርሱን ለሚመለከቱት ይገለጥላቸዋል ፡፡

ኢሳይያስ (25፡ 6-8)፡ የሺህ አመቱ ጅማሬ ተገልፆአል ፡፡ ማክአርቱር “ በዚህ መንግስት እግዚአብሄር ለታመኑት ቅሬቶቹ በፂዎን ተራራ ላይ ታላቅ ግብዣን እንደሚያዘጋጅ “ ተናግሯል ፡፡ ቅሬቶቹ ሁሉንም ፍርዶች ካዩ በኋላ በጌታ የተዘጋጀዉን ግብዣ ይቀምሳሉ/ያገኛሉ ፤ በዚህ ጊዜ ጌታ ሞትን ለዘላለም ያጠፋዋል ፡፡

ኢሳይያስ (25፡ 9-12)፡ ቅሬቶቹ በመከራዉ ዉስጥ ለእነርሱ የጌታን ማዳን እና ታማኝነት ያስተዉላሉ/ያዉቃሉ ፡፡ የእግዚአብሄርን ፍርድ መቋቋም የሚችሉ ሰዎች አይኖሩም ነገር ግን የነገስታት ንጉስን እና የጌቶች ጌታን የታመኑ ይቆማሉ ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ አናዉቅም ነገር ግን ኢየሱስ ልክ ዛሬ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል መኖር አለብን ፤ “ ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና “ (ሮሜ 13፡ 11) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), pp. 785-786.

  2. Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C Cook, 2007), p. 1168.

  3. Earl Radmacher, et. al. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 832.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 163; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.

  5. MacArthur, p. 788.

ጥያቄዎች

  1. በምድር ላይ ስለሚሆነዉ ፍርድ በኢሳይያስ 24 ቀድሞ የተነገረ ነው ፤ ኢሳ (24፡ 5) የምድር ነዋሪዎች “ ሕጉን ተላልፈዋል፣ ስርዓቱን ለዉጠዋልና የዘላለሙንምቃል ኪዳን አፍርሰዋልና “ ይላል ፤ ይህ የትኛዉን የዘላለም ኪዳን ያመለክታል ? (ዘፍ 9፡ 16, 17፡ 7, ዘሌ 24፡ 8, 2ሳሙ 23፡ 5, ኤር 32፡ 40, ዕብ 13፡ 20)
  2. ስለዚህ ስለሚመጣዉ ፍርድ ስታነቡ እንዴት ምላሽ መስጠት አለባችሁ (1ጢሞ 2፡ 4, 2ጴጥ 3፡ 7-9) ? በክፉዎች ፍርድ ስር ለወደቁት መልካሙን ዜና ለማጋራት መነሳት እንዳለባችሁ ይሰማችኋል ?
  3. ኢሳ (24፡ 16) በኢሳይያስ የፍርድ መግለጫ መካከል ላይ “ ክብር ለቅዱሱ “ የሚል ዝማሬ እንደሚሰማ ይጠቅሳል ፤ ይህ ለሚመጣዉ መሲህ ማጣቀሻ ሊሆን ይችላል ? (ኢሳ 53፡ 11, ሐዋ 3፡ 14, 7፡ 52, 22፡ 14)
  4. “ በሰማይ ከፍታ ላይ የተዘጋጀው “ ለማን እንደሆነ ታስባላችሁ ? በኢሳ (24፡ 21) በጌታ ማን የተቀጣ ይሆናል (ይሁዳ 6፣ ራዕ 12፡ 7-9) ? ይህ እንደሆነ እና እንደሚመጣ ሁለቱም እንደሚሆን ታስባላችሁ ?
  5. በኢሳ (25፡ 8) ቀድሞ እንደተነገረው እግዚአብሄር ሞትን ለዘላለም መቼ ያስወግደዋል ? (1ቆሮ 15፡ 52-55, ራዕ 21፡ 4)
  6. በኢሳይያስ (23-25) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 25:9

“On that day it will be said, ‘Look, this is our God; we have waited for Him, and He has saved us. This is the LORD; we have waited for Him. Let us rejoice and be glad in His salvation.’"

ኢሳይያስ ኢየሱስ ተመልሶ ስለሚመጣበት ቀን ተነበየ ፡፡ ምንም እንኳ ብዙዎች እግዚአብሔርን ባይጠብቁም ደግሞም መንገዱን ባይሹም ፣ ቅሬታዎች ታማኝነታቸውን ይቀጥላሉ ፡፡ ቅሬታዎቹም በኢየሱስ ፊት ቆመው ፡- “ እነሆ ፥ አምላካችን ይህ ነው ፤ ጠብቀነዋል ፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን “ ይላሉ ፡፡

ጌታ ታምናችሁ ያገኛችሁ ይሆን ? እርሱም ሲያያችሁ ፡- “ መልካም ፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ “ ይላችሁ ይሆን ? ወይስ ህይወታችሁ በአለማዊና በጊዜያዊ ደስታ ላይ ነው የተመሰረተው ? የራሳችሁን ህይወት ብቻ ነው የምትመሩት ደግሞስ የእግዚአብሔርን መንገድ አትሹም ? ጌታ ለዳግም መምጣቱ እንድትዘጋጁ ይሻል ፡፡ ስለዚህም ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ፡፡ ደህንነታችሁ በእርሱ ነውና ሁልጊዜ አመስግኑ ! በምድር ላይ ያላችሁን ጊዜ እርሱን በፍጹም ልባችሁ ፣ ነፍሳችሁ ፣ አሳባችሁና ኃይላችሁ በመውደድ እያሳለፋችሁ ከኢየሱስ ጋር ለሚኖራችሁ ዘላለማዊ ኑሮ ራሳችሁን አዘጋጁ ፡፡ ንስሀ ለመግባትና ወደ ፈጠራችሁ ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው ፡፡ እግዚአብሔር ፍጹምነታችሁን አይፈልግም ፡፡ እርሱ የእናንተን ብርታት አይፈልግም ፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ሙሉ ልባችሁን ከትህትና ጋር ነው ፡፡ ልባችሁን ለእርሱ ስትሰጡ ፣ እርሱ ከፍ ያደርጋችኋል ደግሞም እርሱ ባዘጋጀላችሁ ሙላት ውስጥ እንድትኖሩ ያስችላችኋል ፡፡ ዛሬ እርሱ እናንተን እየጠበቀ ነው ፡፡ እርሱን ለመጠበቅ ትፈቅዳላችሁን ?

“በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል ፥ ያድነንማል፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን ይባላል ። “

  • ኢሳይያስ 25፡9

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 27:13-14 — “ የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ ። እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ፥ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። “

ማቴዎስ 25:21 — “ ጌታውም ፦ መልካም ፥ አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሃል፥ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው ። “

ሮሜ 13:11 — “ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና ። “