The Oracle Of The Coming Judgment Of Jerusalem
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 21-22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ኢሳይያስ በደቡቡ መንግስት መልዕክቱን ለማድረስ በጥንካሬ እንዴት እየሞከረ እንደነበርና ለሰዎስት አመታት በዙሪያአ ያለ ልብስ መመላለሱን ተመልክተናል ፡፡ በዚህ ስፍራ ላይ ኢሳይያስ ልብሱን እንደ ገና ጠይቆ ከነበር ወይም ሸክምን እየሰጣቸዉ ስለነበር ስለማይሆን መናገር አንችልም ፡፡ በኢሳይያስ 21 በባቢሎን፣ በኤዶም እና በአረብ ሕዝቦች ላይ ተጨማሪ ሰዎስት ሸክሞች ወይም ፍርዶች ተሰጥተዋል ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (22፡ 1-4)፡ በቁጥር 1 ኢሳይያስ ኢየሩሳሌምን በሚወክለው “ በራዕዩ ሸለቆ “ ላይ የፍርድን ሸክም ተናገረ ፡፡ ማክአርቱር “ ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር ራሱን ለኢየሩሳሌም በራዕይ ከመግለፁ የተነሳ ይህ እስራኤልን እንደሚያመለክት “ ይገልፃል ፡፡ አሁንም ኢየሩሳሌም የይሁዳ የደቡቡ መንግስት አካል ነበረች ፡፡ ኢሳይያስ “ በእናንተ ጉዳዩ ምንድን ነው ? “ በማለት ጠየቀ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የኢሳይያስን ጥያቄ “ በቤት አናት ላይ በበድን ከመሆን ይልቅ የተዋሀዱት ከተማዎች በጸሎት ሳጥናቸዉ ዉስጥ መሆን እንዳለባቸው “ የሚል እንደሆነ ይገልፀዋል ፡፡ ማክአርቱርም በደንብ በጥልቀት በመሄድ “ ነቢዩ ከኃጢዓታቸዉ የተነሳ በትልቅ ንስኃ መግባት ዉስጥ በሚሆንበት ጊዜ እንግዳ ከሆነ ቡድን ጋር ስለ ማክበራቸዉ እንደወቀሳቸው “ ይናገራል (ኢሳ 5፡ 11) ፡፡ በቁጥር 2 ኢሳይያስ በከተማዋ ደስተኛ ሰዎችን አመለከተ ፡፡ ማክአርቱር “ ባቢሎናዊያን ከተማዋን ሲይዟት ሞት በርሀብ ወይም በበሽታ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጣ “ ይናገራል ፡፡
በተጨማሪም ኢሳይያስ ሁሉም አስተዳዳሪዎች ከከተማዋ ሸሽተው እንደ ነበርና በአንድ ላይ እንደተያዙ ተናገረ (ቁጥር 3) ፡፡ “ ከተማቸዉን ከመከላከል ይልቅ የሄዱበት መንገድ የራሳቸዉን አንገድ ለማዳን መሪዎቹ ብዙ በማድረግ ሸሹ ተያዙም “ (2ነገ 25፡ 4-7) ፤ ስለዚህም ኢሳይያስ በሕዝቡ ላይ በሚመጣዉ ጥፋት በትልቅ ሀዘን ስለ ነበር መፅናናትን አልፈለገም (ቁጥር 4) ፡፡ “ የኢሳይያስ ህመም ጥልቅ ነበር ፤ የመንፈሳዊ ጉዳዮች እዉነታዎችን ስላዬ በጠላትነት መሳተፍ አልቻለም “ ፡፡ የኢሳይያስ ትንቢት ስለ ሕዝቡ መሸሽ እና የተያዙ መሆን ከ100 አመት በኋላ ይፈፀማል ፡፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ ሕዝቡ ኢሳይያስ ነግሯቸዉ ከነበረዉ ተቃራኒ አደረጉ፡ 1) ከርሀብና ከበሽታ የተነሳ ሞቱ፣ 2) አስተዳዳሪዎቻቸው ለራሳቸዉ ደህንነት ሸሹ፣ 3) እግዚአብሄርን ከመታመን ይልቅ ሕዝቡ በአቅርቦት ከበባዉን ለመቋቋም መጡ፣ 4) የጦር ልብሶችን እና መሳሪያዎችን ሰበሰቡ፣ 5) የከተማዋን የዉጭ ቅጥርን አጠነከሩ እና 6) ለከበባዉ የዉኃ ማጠራቀሚያን ገነቡ ፡፡
ኢሳይያስ (22፡ 5-7)፡ ባቢሎንን ዘርፈዉ የነበሩት ሰራዊቶች ኢየሩሳሌምን ወደ መዝረፍ ይመጣሉ (ቁጥር 7) ፡፡
ኢሳይያስ (22፡ 8-11)፡ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ወደ እግዚአብሄር ከመመለስ ይልቅ ለባቢሎን ሰራዊት መምጣት ተዘጋጀ (ቁጥር 8-11) ፤ “ በዚያን ቀን “ እግዚአብሄር የይሁዳ መከላከያን ይወስዳል (ቁጥር 8) ፤ “ የይሁዳ መከላከያ የተበተኑ ናቸው ፤ በተሳሳተ በራስ መተማመናቸው “ እግዚአብሄር እንዲጠነቀቅላቸዉ ጠበቁ ፡፡ “ የዱር ቤት “ (ቁጥር 8) የሀገራዊ የቶር መሳሪያ ግምጃ ቤትን ያመለክታል ፤ (1ነገ 7፡ 2-6, 10፡ 17, 2ዜና 9፡ 20, ኢሳ 39፡ 2) ፡፡ ሕዝቡ ቀድሞ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን አላስተዋሉም (ቁጥር 11) ፡፡
የሕዝቅያስ የዋሻ ስርዓት/ዘዴ በዚህን ጊዜ ከመሬት በታች ካለ ዉኃ ጋር በማገናኘት የተገነባ ነበር ፡፡ የዋሻዉ ስርዓት/ዘዴ አሁንም በስፍራዉ እና የሚያስደንቅ የምህንድስና ጀብድ ነበር ፡፡ ዋሻው ስለሚመጣዉ ከበባ የተገነባ ነበር ፡፡ ችግሩ ዋሱን መገንባታቸዉ ሳይሆን ሕዝቡ ይህን ሲያደርጉ እግዚአብሄርን እንደ ጠባቂያቸዉ አለመመልከታቸዉ ነበር እንጂ ፡፡
ኢሳይያስ (22፡ 12-13)፡ ኢሳይያስ በችግሩ መካከል ላይ ሕዝቡ ከመደሰት ይልቅ ንስኃ(በማልቀስ፣ በማዘን፣ ራሳቸዉን በመነቅነቅ፣ ማቅ በመልበስ) እንደሚገቡ ተናገረ (ቁጥር 12) ፡፡ ይልቁንም ሕዝቡ ምን እየመጣ እንደ ነበር ባለማስተዋል ህይወትን እየተዝናናበት ነበር (ቁጥር 13) ፡፡
ኢሳይያስ (22፡ 14)፡ ኢሳይያስ ኃጢዓታቸዉ በፍፁም እንደማይወገድ ተናገረ (ቁጥር 14) ፤ ያ ማለት ሕዝቡ በፍጹም ስርየት አልተሰጠው ፡፡
ኢሳይያስ (22፡ 15)፡ ኢሳይያስ ሌላ ሸክምን በሳምናስ ላይ አወጀ/ተናገረ (ቁጥር 15) ፡፡ ሳምናስ “ ምናልባትም የግብፃዊያን አዉጪ “ እና “ ከንጉሱ በስልጣን ሁለተኛም ነበር “ እንዲሁም እንደ አንድ ጸሀፊም አገለገለ (2ነገ 18፡ 37, ኢሳ 36፡ 22, 37፡ 2) ፡፡ ሳምናስ ለራሱ የተቀረፀ መቃብር ያለዉ ስልጣን ያለዉ ነበር (ቁጥር 16) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በከፍታ ስፍራ የራሱን መቃብር ስፍራ በመቁረጥ አባት የሆነዉን ንጉሱን ተፎካከረ (2ዜና 6፡ 14) “ በማለት ይገልፀዋል (ቁጥር 21) ፡፡ ኢሳይያስ ሳምናሶ በእግዚአብሄር ፍርድ እንደሚሞት እና በአገልጋዩ በኤልያቄም እንደሚተካ ተናገረ (ቁጥር 17-24) ፤ ኤልያቄም አስተማማኝ በመሆን ለአባቱ ለኬልቅያስ ማስታወሻ ክብርን የሚያመጣ ይሆናል (ቁጥር 23) ፡፡
ቁጥር 22 በመፅኀፍ ላይ አንዱ ጠንካራ የተስፋ መልክ ነው ፤ ኤልያቄም የዳዊት ቤት ቁልፍ ይሰጠዋል፡ “ ይህ ስልጣን ለመቀበል ወይም ተቀባይነትን ለመግፋት ወደ ንጉሱ መገኘት ፊት በኤልያቄም የንጉሱን ታላቅ እምነት የመኖር ማስረጃ ነው ፤ ኢየሱስ ራሱን ወዳዊት መንግስት ማን ሊገባ እንደሚችል እንደ አንድ ይህ ቃል ቃል ተግባራዊ አድርጎታል (ራዕ 3፡ 7) “ ፡፡
መደምደሚያ
አንዳንድ ጊዜ ይህ ለኤልያቄም ባይሆን ኖሮ ምን እንደሚወገድ እድነቃለሁ ፤ በግልፅ ኤልያቄም የቅሪቶች ምሳሌ ሲሆን እና በመንግስቱ በሙሉ ስልጣን እና ኃይል የዳዊት ቁልፍ የተሰጠዉ ነበር ፡፡ ኤልያቄም በመወለድ በዚህ ስልጣን ላይ ለመቀመጥ መብት አልነበረዉም ነገር ግን በእግዚአብሄር ለእርሱ ተሰጠው ፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ቁጥር 25 መሰረት ኤልያቄም አንድ ቀን የስራዉን ሸክም መሸከም አይችልም ፤ ይህ የእግዚአብሄርን መንግስት ቁልፍ የሚይዘዉ እና ሁሉም ስልጣን እና ኃይል ያለዉ የክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ጥላ ነው ፡፡ ክርስቶስ ስለ እኛ ሸክምን ይሸከማል (ኢሳ 9፡ 6-7) ፤ የዘላለም ህይወትን እንድናገኝ ይፈቅድልናል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 784.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 839.
MacArthur, p. 784.
MacArthur, p. 784.
MacArthur, p. 784.
MacArthur, p. 784.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 28.
Wiersbe, p. 28.
Nelson’s Commentary, p. 830.
MacArthur, p. 785.
MacArthur, p. 785.
ጥያቄዎች
-
በኢሳ (21፡ 2) እግዚአብሄር ኢሳይያስን ያስፈራዉን አንድ ራዕይ ስለ ባቢሎን ሰጠው ፤ ለምን ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ተተንብዮአል ? (ኤር 51፡ 6-8, ራዕ 18፡ 1-2)
-
በኢሳ (22፡ 1) ኢሳይያስ “ የራዕይ ሸለቆ “ አመልክቷል ፤ ይህ የት ነው (2ዜና 32፡ 1-2) ? ኢየሩሳሌም ጠፍታ ነበር ? ይህን ለመከላከል የኢየሩሳሌም ሕዝብ ምን ጥንቃቄ አደረገ ? ምን ማድረግ አለባቸው ? ከዚህ ምን ዋጋ ያለዉ ነገር ልንማር እንችላለን ?
-
ሳምናስ ማን ነበር የኢሳይያስን ምክር ባለመከተሉ/ባለማክበሩ በእርሱ ላይ ምን ሆነበት (ኢሳ 22፡ 15-21) ? ከእግዚአብሄር ዞር ባሉ ሕዝቦች እና አስተዳዳሪዎች ላይ ምን ሊሆን እንደሚችል ምን ያስተምረናል ?
-
በኢሳይያስ (21-22) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 22:11
“You made a reservoir between the walls for the waters of the ancient pool, but you did not look to the One who made it, or consider the One who created it long ago.”
ኢየሩሳሌም ራስዋን ከአሶር ጥቃት ለመከላከል በምትሞክርበት ጊዜ ኢሳይያስ ኢየሩሳሌም ራስዋን ለመከላከል ስለምታደርገው አካሄድ ጠየቀ ፡፡ በድጋሚ የራሳቸውን መከላከያ አደራጁ ፤ የራሳቸውን ጦር ገነቡ እንድሁም በውኃ ማከማቻዎች ውኃ ሞሉ ፡፡ ይህ ሁሉ የሚያስገርም ነበር ሆኖም ግን ፈጽመው ወደ እግዚአብሔር አልተመለከቱም ፡፡ በእቅዳቸው ውስጥ እግዚአብሔርን አላሰቡም ነበር ፡፡
ቀናችሁን ስታሳልፉ ፣ እግዚአብሔር ስራችሁን ለእርሱ አሳልፋችሁ እንድትሰጡ ይሻል ፡፡ እርሱ እንደዚህ ላለ ጊዜ የሚሆን ስጦታ ፣ ብቃትና ማንነት ጋር ነው የፈጠራችሁ ፡፡ በእርሱ ደስ ይበላችሁ በምታደርጉትም ሁሉ እርሱን አስቡ ፡፡ ነገሮችን በራሳችሁና የራሳችሁን ፍላጎት በማሰብ ብቻ አትፈጽሙ ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስም ኢየሩሳሌምን እንዲህ በማለት ይጠይቃል ፡- “ ምን ሆናችኋል ? “ ዛሬ በእቅዳችሁ ውስጥ እግዚአብሔርን የማታስቡ የማታካትቱ ከሆነ ራሳችሁን እንዲህ በማለት ጠይቁ ፡- ምንድን ነው የሆንኩት ? እግዚአብሔር ለእናንተ ባዘጋጀው ነገር ሁሉ ሊያስገርማችሁ ይፈልጋል ፡፡ ይህም ማሰብ ከምትችሉት የበለጠ ነው ፡፡ ስለዚህም በራሳችሁ ላይ ብቻ ማትኮር አቁሙ ፡፡ በመንገዳችሁ ሁሉ ለእርሱ እውቅና ስጡ እርሱም መንገዳችሁን ያቀናል ፡፡
“ በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም ፥ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም ። “
- ኢሳይያስ 22 ፡ 11
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 3:6 — “ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “
ኤርምያስ 29:11-12 — “ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። እናንተም ትጠሩኛለችሁ ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ ፥ እኔም እሰማችኋለሁ ። “
ቆላስይስ 3:17 — “ እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።