Major Prophets Isaiah

Judgment Against Egypt

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 582 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በኢሳይያስ ካሉት 66 ምዕራፎች ዉስጥ የመጀመሪያዎቹ 39 በፍርድ ላይ ሲሆኑ የመጨረሻዎቹ 27 ደግሞ በመፅናናት እና በቤዛነት ላይ ያተኮሩ ናቸው ፡፡ ይህ ስዕል ከ39 የብሉይ ኪዳን መፅሀፍት እና ከ27 የአዲስ ኪዳን መፅሀፍት ጋር በብሉይ ኪዳን ፍርድ እና ሊዋጀን የክርስቶስን መምጣት በአዲስ ኪዳን ያወዳድራል ፡፡ በመጀመሪያዎቹ በኢሳይያስ 12 ምዕራፎች ይሁዳን እና ኢየሩሳሌምን በተመለከተ ትንቢቶች አሉ ፡፡ ይሁዳ በደቡብ መንግስት ዉስጥ ነው ፤ የሰሜኑ መንግስት የሌሎቹ አስር ነገዶች ድብልቅ ነበር ፡፡ አንዳንድ ታናናሽ ነቢያቶች ለሰሜኑ መንግስት ስለተናገሩ የኢሳይያስ መልዕክት ለደቡቡ መንግስት ነበር ፡፡ ምዕራፍ (13-23) ከይሁዳ ጋር በተገናኜ በሕዝቦች ላይ ያለን ሸክም ወይም ኃዘን ይይዛሉ ፤ ትናትና ኢትዮጲያዊያን እና ኩሽ ነበሩ ፡፡ ዛሬ ምዕራፍ 19 በይሁዳ ላይ ካለዉ ተግባር የተነሳ በግብፅ ላይ ያለን ሸክም ይይዛል ፡፡ በመጀመሪያዎቹ 15 ቁጥሮች ፍርድ በግብፅ ላይ እየመጣ ነበር ፡፡ እንደ ዊልቡር ስሚዝ ገለፃ ኢሳይያስ 19 “ በሁሉም ብሉይ ኪዳን ግብፅን በተመለከተ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ትንቢታዊ ንግግሮችን ይይዛል ….. ኢሳይያስ ሰዎስቱ ጠላቶች - ግብፅ፣ እስራኤል እና አሶር (የአሁኗ ኢራቅ) አንድ ቀን ጌታን በማምለክ እና በረከትን በመካፈል የተዋሀዱ እንደሚሆኑ ይናገራል “ ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (19፡ 1-4)፡ በዳመና ላይ እየፈጠነ የእግዚአብሄር መምጣት ለዚህ መፅሀፍ ያለንን ቃላችንን ትርጉሙ “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ የሚለዉን ያሳስበናል ፡፡ ማቴ (26፡ 64) የኢየሱስን ከሰማይ በዳመናት ላይ መምጣትን ይገልፃል ፤ እንደ ገና ኢሳይያስ ይህ “ አሁን “ ወይም “ ቀጥሎ /ወደፊት “ የሚሆን ነገር ትንቢት ከነበር እንድንደነቅ ይተወናል ፤ ስለ ኢየሱስ መጀመሪያ መምጣት ወይስ ሁለተኛ መምጣት እያወራ ነበር ? ፍርድ እየመጣ ስለ ነበር ግብፅ በፍራት ትንቀጠቀጣለች ፤ ግብፃዊያን እርስ በእርሳቸዉም ይዋጋሉ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ፡ “ የግብፅ 42 ግዛቶች ኖሜስ በመባል ሲጠሩ ወደ ትርምስ እና እርስ በእርስ መዋጋት ወደ መጀመር የተወረወሩ ይሆናሉ “ በማለት ፅፏል ፡፡ ግብፅ ጣዖቶችንና መናፍስት መፈለግ ስለሚጀምሩ እግዚአብሄር ለኃይለኛ አስተዳደር ይሰጣቸዋል (ቁጥር 3-4) ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ አገላለፅ “ የግብፃዊያን መዉደቅ የብዙ አማልዕክት ግርግር ዉጤት “ እንደሆነ ይገልፃል ፤ እስራኤላዊያን ግብፃዊያንን እንደ ክፉ ጌታ ገልፀዉ እንደነበረው ግብፃዊያን ለአስቸጋሪ አስተዳዳሪ የተሰጡ ይሆናሉ ፡፡

ኢሳይያስ (19፡ 5-10)፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የናይል ዉድቀት ወደ ኢኮኖሚካል ዉድቀት እንደሚመራ “ ያመለክታል ፤ የግብፃዊያን አጠቃላይ ኢኮኖሚይ በናይል ወንዝ ላይ የተመሰረተ ስለ ነበር ወንዙ በደረቀ ጊዜ (ቁጥር 5-7) ኢኮኖሚው ይጠፋል፡- አሳ አጥማጅ ሰዎች ያዝናሉ (ቁጥር 8)፣ በተልባ የሚሰሩት ያፍራሉ (ቁጥር 9) እና ደገፋዎች እና ደሞዝ ተከፋዮችም ይተክዛሉ (ቁጥር 10) ፡፡ ከወንዙ ችሮታነት ዉጪ ህዝቡ ለመኖር ገቢ ለማግኘት የሚሰራዉ ምንም ነገር አይኖራቸዉም ፡፡ በግብፁ ሁሉም ከባለቤቶች እስከ ደሞዝ ተከፋዮች ተፅዕኖ ያመጣል ፡፡

ኢሳይያስ (19፡ 11-15)፡ ግብፃዊያን በራሳቸዉ ጥበብ፣ ምልከታ እና ችሎታ ላይ ተደግፈዋል ነገር ግን ከአስተዋይ ሰዎቻቸዉ ዉስጥ ማንም በእነርሱ ላይ ምን እየሆነ እንደ ነበር ለመግለፅ አልቻሉም ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የቀድሞ እና ከንቱ የሆነዉ ጥበብ ተስፋ በሌለዉ መሸነፍ የመጣ ነው “ ፤ ከዚህ በኋላ ግብፃዊያን የራሳቸዉ ሰዎች ባደረጓቸዉ ስትራቴጂዎች እና ምልከታ መደገፍ አይችሉም ፡፡ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስርዓቱ ይጠፋል ፡፡ ዋይርስቤ ኃይማኖታዊ እና የጥበብ ስርዓታቸዉ የጠፉ እንደ ነበሩ ጨምሯል ፡፡ የግብፃዊያን አማካሪዎች ጥበብ እና እዉቀት በእግዚአብሄር ፍርድ ፊት ወድቋል ፡፡ በማር (6፡ 2) የኃይማኖት መሪዎች ጥበብ “ ብዙዎች በመስማት የተደነቁበት እና የተገረሙበትን “ “ ለእርሱ የተሰጠው ይህ ጥበብ ምን እደሆነ እና እነዚህ ተዓምራቶች እንዴት በእርሱ እጅ ሆኑ ? “ በምኩራብ ከኢየሱስ ትምህርት ጋር ሲነፃፀር ደብዝዟል ፡፡

ኢሳይያስ (19፡ 16-25)፡ “ በዚያን ቀን “ (ቁጥር 16) ብዙ በተለያዩ ጊዜ የተጠቀሰ ነው (ቁጥር 18, 19, 23, 24) ፡፡ አምስት የተለያዬ ጊዜ ኢሳይያስ “ በዚያን ቀን “ የሆነ ነገር ይሆናል ይላል ፡፡ ዋይርስቤ “ ግብፅ እስራኤልን እንደምትፈራት (ቁጥር 16-17) “ ያመለክታል ፡፡ አንዴ በግብፅ የተጨቆኑ ሕዝቦች እስራኤልን ይፈራሉ ፡፡

ግብፅም “ የከነዓንን ቋንቋ ትናገራለች “ (ቁጥር 18) ፡፡ በመሰረቱ ግብፅ በዕብራዊ እግዚአብሄርን ወደ ማምለክ ትቀየራለች ፤ ግብፅ መሰዊያን እና አምድን ለእግዚአብሄር ታቋቁማለች (ቁጥር 19) ፡፡ መሰዊያዉ እና አምድ ወደ አብርሃም እና ያዕቆብ ይሳባሉ ፡፡ በዘፍ (12፡ 8) አብርሃም ለእግዚአብሄር በቤቴል መሰዊያን ሰራ ፤ በዘፍ (28፡ 22) ያዕቆብ እንደ እግዚአብሄር ቤት አንድ ድንጋይን እና ምልክትን በማስቀመጥ እግዚአብሄር ሰጥቶት ከነበረዉ ሁሉ ለእግዚአብሄር አስራትን ሰጠ ፡፡ “ በዚያ ቀን “ (ቁጥር 19) ግብፃዊያን “ ከእግዚአብሄር ጋር የህብረትን ስጦታ ይቀበላሉ “ ፤ ግብፅ ወደ እግዚአብሄር በጮኸች ጊዜ በመስማት ይፈዉሳቸዋል (ቁጥር 20-22) ፡፡

በግብፅ ላይ በእርሱ ትንቢት ኢሳይያስ ፍርድ ወደ ግብፅ እየመጣ ነበር ከማለት ወደ ግብፅ እስራኤልን በመፍራት ወደ እዉነተኛዉን እግዚአብሄርን ለማምለክ የተቀየሩ እንደሚሆኑ ወደ ማለት በጥብቅ ሀሳብ መለወጥን አደረገ ፡፡ ሙስሊም በግብፅ ቢኖሩም ይህ ስዕል ወደ ዮሹዋ ወደ ኢየሱስ በሙስሊም የሆነ ታላቅ መነቃቃትን መልክ ነው ፡፡ ክርስቶስ በመምጣት የመሲሀዊ መንግስቱን በምድር ላይ በመሰረተ ጊዜ እነዚህ ነገሮች ይከናወናሉ ፤ ስለዚህም ይህ ትንቢት የኢየሱስን የመጀመሪያ መምጣት (የሞቱን፣ የመቀበሩን እና የመነሳቱን ) አያመለክትም የሁለተኛ መምጣቱን እንጂ መንግስቱን በቋሚነት በሚመሰርት ጊዜ ፡፡

“ በዚያን ቀን “ (ቁጥር 23) ግብፅ ከአሶር(ከኢራቅ) ጋር ታመልካለች ፤ በተጨማሪም “ በዚያን ቀን “ (ቁጥር 24) እስራኤል፣ ግብፅ እና ኢራቅ የሰዎስትዮሽ ትብብር ይፈጥራሉ እግዚአብሄርም ሁሉንም ይባርካቸዋል ፡፡ በብዙ ሀገራት እና የህዝብ ቡድኖች አንድነት ይኖራል ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ አገላለፅ ይህ የአንድነት መወገድን እና የኃገራት መለያየትን መወገድ ያሳያል ፡፡

“ በዚያን ቀን “ ግብፅ እስራኤልን ትፈራለች ፤ ግብፅ የተቀየረች በመሆን እዉነተኛዉን እግዚአብሄርን በማምለክ የከነዓንን(የዕብራዊያን) ቋንቋ ይናገራሉ ፡፡ ግብፅ፣ አሶር(ኢራቅ) እና እስራኤል ለሌሎች ሕዝቦች በረከት ይሆናሉ ፡፡ ዘፍ (12፡ 3) እግዚአብሄር በእስራኤል በኩል አሕዛብን ለመባረክ ተስፋ የገባው ወደ ፍሬአማነት መምጣት ይጀምራል፡፡

ኢሳይያስ (20፡ 1-6)፡ ኢሳይያስ እነዚህ ሰዎስት አገራቶች ለአሕዛብ በረከቶች እንደሚሆኑ ተናግሮ ነበር (ኢሳ 19፡ 24-25) ፤ ነገር ግን አሁን ኢሳይያስ በኢሳ (19፡ 1-15) ተናግሮት የነበረውን ደግሞ ተናገረው ፡፡ ኢሳይያስ ለይሁዳ ትኩረታቸዉን ለማግኘት ለመሞከር በደቡቡ መንግስት ጊዜ በግብፅ እና በኩሽ (በኢትዮጲያ) የነበረዉ ሁሉንም ተስፋ በማለት እነርሱን እንደማይረዳቸዉ ማስጠንቀቂያን ሰጠው ፤ ይልቁንም እነዚህ ሀገራት ፍርድን ግርግርን እና የኢኮኖሚ ዉድቀት እና ተስፋ የሌለዉ ሽንፈት ይገጥማቸዋል ፡፡ ኢሳይያስ ይሁዳን በሰዉ ላይ ተስፋዉን እንዳያስቀምጥ አሳሰበው ፤ እንደ አንድ የሚታይ ማሳያ ኢሳይያስ ሰዉ ሰራሽ ትብብሮች ተስፋ ቢስነታቸዉን ለማሳየት ለሰዎስት አመታት እርቃኑን እና በባዶ እግሩ በዙሪያ ተመላለስ ፡፡ ኢሳይያስ ይሁዳን የህብረታቸዉ መጨረሻ ዉድቀት እንደሆነ አስጠነቀቀው ፤ የማያስተዉሉት የይሁዳ ሰዎች ይህን የሚያምኑበት ብቸኛዉ መንገድ ኢሳይያስ ሀሳቡን ለማረጋገጥ እርቃኑን ለሰዎስት አመታት በመመላለሱ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ የሕዝቡን ትኩረት ማግኘት የሚፈልግ ፍፁም ነብይ ነበር ፡፡

መደምደሚያ

ኢሳይያስ (13-23) በሕዝቦች ላይ ሸክሞችን ይይዛሉ ፤ ነገር ግን በዛሬዉ ክፍል አሕዛቦች የሚፈረድባቸዉ ቢሆንም እንኳን በተለዬ ግብፅ የዳነች እና የተባረከች ትሆናለች ፡፡ ነገር ግን ኢሳይያስ ይሁዳን ስለሚወድቁ በጥምረታቸዉ አብሮ እንዳይቀመጥ አስጠነቀቀው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 1167.

  2. Wiersbe, p. 1167.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 828.

  4. Nelson’s Commentary, p. 828.

  5. Nelson’s Commentary, p. 828.

  6. Wiersbe, p. 1167.

  7. Nelson’s Commentary, p. 828.

  8. Nelson’s Commentary, p. 828.

  9. Wiersbe, p. 1167.

ጥያቄዎች

  1. በግል አስተያየታችሁ ኢሳ (19፡ 1-2) ስለ ምን መቼ እያወራ ነው ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ በደመና ላይ እንደሚበርር ኢየሱስ የተገለፀ ነው ? (ዘጸ 24፡ 16, ሐዋ 1፡ 9, ራዕ 14፡ 14)
  2. በኢሳ (19፡ 2-3) እንደተገለፀው ህዝቦች እርስ በእርሳቸዉ በመዋጋት ወደ ጣዖትእና ወደ አስማት/ድግምት እንዲዞሩ ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ? በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ እግዚአብሄር ተመሳሳይ ነገር ሲያደርግ ታዩታላችሁ (ሮሜ 1፡ 24-32) ? ይህ የዚህን ጥያቄ የመጀመሪያ ክፍል ለመመለስ እንዴት ይረዳችኋል ?
  3. ኢሳይያስ 19 ዛሬ የተፈፀመ ሆኖ ታዩታላችሁ ? እንዴት እና የት ?
  4. ኢሳይያስ በኢሳ (20፡ 2-3) ያደረገዉን ለማድረግ ፍቃደኞች ትሆናላችሁ ? በቀረዉ በኢሳይያስ 20 መሰረት ኢሳይያስ ይህን ለምን አደረገ ?
  5. በኢሳይያስ (19-20) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 20:2-3

“During that time the LORD had spoken through Isaiah son of Amoz, saying, ‘Go, take off your sackcloth and remove the sandals from your feet,’ and he did so, going naked and barefoot—the LORD said, ‘As My servant Isaiah has gone naked and barefoot three years as a sign and omen against Egypt and Cush.’”

ህዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ብቻ እንድታመኑ ለማሳሰብ እግዚአብሔር እንደገና ስለ ግብጽ መናገር አስፈልጎት ነበር ፡፡ እንደገና እግዚአብሔር ነቢዩ ኢሳይያስን ጠርቶ ግልጽ የሆነ ትዕዛዝን ሰጠው ፡- በግብጽ ስለሚሆነው ውርደትና ችግር ምልክት ይሆን ዘንድ ለሶስት አመት ራቁትህን ሆነህ በባዶ እግርህ ሂድ ፡፡ ኢሳይያስም ሌሎች ፊታቸውን ወደ እግዚአብሔር እንድመልሱ ሲል ወድያውኑ ራቁቱንና በባዶ እግሩ በመሄድ እግዚአብሔርን ታዘዘ ፡፡

እግዚአብሔር እንደ ኢሳይያስ ሁሉ አንተም ፈጥነህ እንድትታዘዝ ይጠራሃል ፡፡ ይህም የሚሆነው የራስህን አጀንዳ ፣ ኩራትህን እንድሁም ህይወትህንም ጭምር ወደ ጎን በማድረግ ነው ፡፡ ኢየሱስ እርሱን ለመከተል ራስህን መካድና መስቀልህን መሸከም እንደሚያስፈልግ ተናግሯል ፡፡ ስለ ወንጌል ፈጥነህ ታደርገው ዘንድ የሚገባ እግዚአብሔር በልብህ ያስቀመጠው ነገር አለን ? ነቢዩ ኢያሱ በኢያሪኮ ግንብ ዙሪያ ለስድስት ቀን እንድዞሩ ህዝቡን ሰበሰበ በሰባተኛውም ቀን ታላቅ ጩኸት ጮኹ ፡፡ ከታዘዙም በኋላ ልክ እግዚአብሔር እንደተናገረው የከተማዋ ቅጥር ወደቀ ፡፡ ምናልባት እግዚአብሔር በቤትህ ሆነህ እንድትጸልይ ፤ እርቅን እናም ይቅር መባባልን እንድትሻ ፤ በቢሮ ሆነህ ለአንድ ወር ያህል በጾም እንድታሳልፍ ወይም ቤትህን ስራህንም ጭምር እንድትተው እያዘዘህ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል ፡፡ በልብህ ያለውን ነገር እንዳትሰርዝ ፡፡ ልክ እንደ ኢሳይያስ ሁሉ ፈጥነህ ስትታዘዝ ይህ በሆነ ሰው ህይወት ውስጥ ለውጥን ሊያፋጥን ይችላል ከዚህም አልፎ የመላ አገሪቱንም ለውጥ እንዲሁ ፡፡ እግዚአብሔር በአንተ ውስጥና በአንተ ሊሰራ የሚፈልገውን ነገር እንዳትዘነጋ ፡፡

“ በዚያ ዓመት እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን ፦ ሂድ ፥ ማቅህን ከወገብህ አውጣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ ብሎ ተናገረው ። እንዲህም አደረገ ፥ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ ። እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ ፡፡ “

  • ኢሳይያስ 20፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢያሱ 6:2-5 — “ እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው፦ ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ ። ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት፤ እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ ። ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ፤ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ ። ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱንም ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል ። “

ማቴዎስ 16:24 — “ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ። “

2ኛ ዮሐንስ 1:6 — “ እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው ፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት ። “