Major Prophets Isaiah

Oracle Against Damascus, Israel, And The Nations

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 17-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 581 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ኢሳይያስ በአዲስ ኪዳን ዉስጥ ከ65 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል ፡፡ እያወራን ያለነው ስለ ድነት ርዕሶች ብቻ ሳይሆን ስለመጨረሻው ጊዜም ነዉ እንጂ ፡፡ በኢሳይያስ የመጀመሪያዎቹ 39 ምዕራፎች አንዳንድ ጊዜ እንደ ፍርድ መፅሀፍት ተጠቅሰዋል ፤ የመጨረሻዎቹ 27 ምዕራፎች ደግሞ ስለ መፅናናት እና መቤዠት ናቸው ፡፡ የመጀመሪያዎቹ 12 ምዕራፎች ስለ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ስለሚመጣባቸዉ ባርነት እና ምርኮ የማመልከት ትንቢቶችን ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (13-23) በአሕዛቦች (ምሳሌም አሶርን እና ባቢሎንን ያካትታል) ላይ የፍርድ ኦራክሎችን ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (24-27) የአለም አቀፍ ፍርዶችን እና ነፃ መዉጣቶችን ያካትታል ፤ ምዕራፍ ( 28-33) በሰማሪያ፣ በኢየሩሳሌም እና በአሶር የሀዘን ኦራክሎችን ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (34-35) የአለም አቀፍ ፍርዶችን እና ነፃ መዉጣቶችን ይይዛሉ ፤ በመጨረሻም ምዕራፍ (36-39) ታሪካዊ መጠላለፍን እና ሽግግሮችን ይይዛሉ ፡፡ ኢሳይያስ ስለ ሚመጣዉ ፍርድ የተናገረ ቢሆንም ለዚህ መፅኀፍ ቃላችንን “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ የሚል ትርጉም ያለዉን አማኑኤልን አካትቷል (ኢሳ 7፡ 14) ፡፡

የመጨረሶቹ 27 ምዕራፎች የመፅናናት መፅኀፍት በመባል ይጠራሉ ፡፡ ምዕራፍ (40-48) የመቤዠት እና የመፅናናት ትንቢቶችን ያካትታሉ ፤ ምዕራፍ (49-55) የእግዚአብሄር አገልጋይን የመሲሁን ትንቢት ይይዛሉ ፡፡ ምዕራፍ (55-66) የኩነኔ እና የመቃጠል/የመጥፋትን ትንቢቶች ይይዛሉ ፡፡ ኢሳይያስ መጥፎ መልዕክትን እንደተናገረዉ ሁሉ መልካም ዜናም እንደሚመጣ ተናግሯል ፡፡

ዛሬ በአሕዛቦች ላይ ስለ ኦራክል ፍርድ እናወራለን ፤ ኦራክሉ ወይም ሸክሙ “ በእርግጠኝነት ስለሚከሰት ትንቢታዊ ክስተት እና ንግግሮችን ያሳያል ፤ በተለያዩ መልከዓ ምድር ክልል ስፍራ በሚኖሩ ሰዎች በአጠቃላይ 14 ትንቢቶች ባለበት በምዕራፍ (13-23) ላይ 11 ትንቢቶች ጥቅም ላይ ዉለዋል “ ፡፡ “ ኦራክል “ የሚለዉ ቃል አዉሬዉ የሚሸከመዉን ሸክም ለመግለፅ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ እነዚህ ትንቢቶች ለነቢዩ እና ለተቀባዮቹ ለመሸከም በጣም ከባድ ሸክም ነበሩ ፤ ለምሳሌ በኢሳ (13፡ 1) በባቢሎን ላይ የሚመጣዉ ኦራክል የባቢሎን ሸክም በመባል ይጠራል ፡፡ እግዚአብሄር በይሁዳ ላይ ፍርድን ለማድረግ ይሁዳ ለ70 አመታት በዚያ በምርኮ እንዲያዙ በመፍቀድ ባቢሎንን ተጠቀመ ፤ ነገር ግን ከዚያ በኋላ እግዚአብሄር በሚያደርጉት በዚያ እፈርድባቸዋለሁ አለ ፤ ይህ መልካም ዜናን የያዘ ያልተለመደ ሸክም ነበር ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (17፡ 1-3)፡ ይህ ምዕራፍ የሶሪያ ዋና ከተማ ስለሆነችዉ የደማስቆን ሸክም ይዟል ፡፡ ከተማዋ ከተማዋን ተፅኖ ፈጣሪ ባደረጋት በዋናዉ ምድር በሚሶፔታሚያ እና በግብፅ መካከል መንገድ ከሀርሞኒየም ተራራ ሰሜን ምስራቅ ላይ የምትገኝ ነበረች ፡፡ ሸክሙ ይቺ ከተማ “ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች “ አለ (ቁጥር 1) ፡፡ ከተማዋ “ ከሙት ባህር ምስራቅ በደቡብ ከአሮኔር በመራቅ በአርኖን ወንዝ ላይ ተዘርግታለች (2ነገ 10፡ 32,33) ፤ ይሁን እንጂ የሶሪያ ቅሬቶች ይተርፋሉ (ቁጥር 3) ፡፡

ኢሳይያስ (17፡ 4-6)፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ በኢየሩሳሌም ምዕራፍ እንደሚያፈራ ሸለቆ እንደ ተከፋፈለ አምራች ተሸካሚ ስለሆኑ የእግዚአብሄር ፍርድ በሰሜኑ መንግስት እንዲያፈራ ንም ነገር አይተዉም “ በማለት ያጠቃልላል ፡፡ ቃርሚያ ብቻ በእስራኤል ይቀራል (ቁጥር 6) ፡፡ የእግዚአብሄር ፍርድ በኤፍሬም ላይ ከተትረፈረፈ ከመጀመሪያዉ ምግብ ጥቂት ብቻ ያስቀራል ፡፡

ኢሳይያስ (17፡ 7-8)፡ ፍርድ በመጣ ጊዜ እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር ይለሳሉ (ቁጥር 7) ፡፡ እንደ ማክአርቱር ንግግር “ በሚመጣዉ ጊዜ/ወደፊት ኃይለኛ ፍርድ የኤፍሬምን ቅሬቶች ከዉድቀታቸዉ በእግዚአብሄር ላይ ለመደገፍ ያነቃቸዋል ፤ ከዚያም ንስኃ ይገባሉ “ ፡፡ ኤፍሬም የሰሜኖቹን አስር ነገዶች ይወክላል ማለትም ሁሉም ምሽጋቸው ይጠፋል (ቁጥር 3) ፤ የቀረ ነገር ምንም አይኖራቸዉም ፡፡ በመጀመሪያ የእግዚአብሄር ክብር በ 12 ነገዶች ላይ እንደ ነበር አሁን ደግሞ የእግዚአብሄር ክብር ከአስሩ ነገዶች ላይ እየጠፋ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ “ የእስራኤል ቅዱስ “ የሚለዉ በመፅኀፍ ላይ አልፎ አልፎ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ከተጠቀሙት ጥቂቶች መካከል ዉስጥ ኢሳይያስ አንዱ ነው ፤ ይህ ማለት ያህዌ ላይ መመልከት ጀምረዋል ማለት ነው ፡፡ “ ያ ቀን “ ከተማዋ የምትጠፋበት ወይም በምርኮ የሆኑበት እንደሆነ ለመወሰን አስቸጋሪ ነው ፤ ነገር ግን የሆነ ስፍራ ላይ እስራኤል እግዚአብሄር ብቻ እንዳላት ታስታዉላለች ፡፡ አንድ ጊዜ ታቹን/መሰረቱን ከመቱ ያህዌ ላይ እንጂ ሌላ የሚመለከቱት አይኖራቸውም ፡፡ እስራኤል በሰራችዉ በመሰዊያዎች እና መስገጃዎች ላይ አትመለከትም (ቁጥር 8) ፡፡

ኢሳይያስ (17፡ 9-11)፡ እስራኤል ወደ እግዚአብሄር ብትመለስም አሁንም ሕዝቡ መርጠዉት የነበረዉን መንገድ ዉጤት ይደርስባቸዋል (ቁጥር 9) ፡፡ ነገሮችን በራሳቸዉ ጥንካሬ ለማድረግ ሞክረዉ ነበር (ቁጥር 10) ነገር ግን እግዚአብሄር በሂደቱ ዉስጥ በፍፁም ስላልተሳተፈ/ስለሌለ መከሩ ከንቱ ይሆናል (ቁጥር 11) ፡፡

ኢሳይያስ (17፡ 12-14)፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ገሰፀ ጠላቶቹ የነበሩትንም ገሰፃቸው (ቁጥር 12-13) ፡፡ ከላይ ያሉት ሁሉ ዝብርቅርቅ/ትርምስ ነው ፡፡ ሸክሙ የእግዚአብሄር ፍርድ በሁሉም ላይ ይመጣል ይላል ፡፡ እስራኤል ሲተክሉ ወይም በከተማቸው ላይ ጌታን ስላላሳተፈች ተወሰዱ ፡፡ አስሩ ነገዶች ሁሉም ብለዉት እና አድርገዉት በነበር ጊዜ ጠፋ/ተወሰደ ፤ አዎ ከእነዚህ ከተሞች ቅሬቶች ይኖራሉ ነገር ግን በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰጥቷቸዉ የነበረዉን አጡት ፡፡

መደምደሚያ

ቁጥር 7 “ በዚያን ቀን “ ሕዝቡ ወደ “ እስራኤል ቅዱስ ይመለሳሉ “ ይላል ፡፡ ወደ ጌታ ለመመለስ ሸክም እስክትቀበሉ ድረስ እንዳትጠብቁ ፤ ወደ እግዚአብሄር ከመመለሳችሁ በፊት ከነገሩ ታች እና ሁሉም ነገር ተለይቶ የወደቀ እስኪሆን ድረስ እንዳትጠብቁ ፡፡ አሁን እርሱን በሁሉም ነገር፡- በእቅድ ዉሳኔአችሁ ዉስጥ፣ በፋይናንሺያል ዉሳኔአችሁ እና በህይወታችሁ ታሳትፉታላችሁ ? በሁሉም ነገር ወደ እርሱ ልንመለከት ያስፈልገናል ፡፡ ራሳቸዉን ዞር ስላደረጉ እስራኤል ለኑሮአቸዉ የተለዬዉን እቅድ አጣች ፡፡ እንድናገኘዉ እግዚአብሄር የሚፈልገዉ ሙሉነት አለ ፤ የእግዚአብሄርን ሙሉነት ለመቅመስ አብዛኞቻችን በጣም ቅርብ ነን ነገር ግን ከእርሱ እንመለሳለን - ነገሮችን በራሳችን ኃይል‹ በራሳችን ጉልበት ወይም በራሳችን ፍቃድ ለማድረግ አንሞክር ፡፡ ሁል ጊዜ ወደ ሰራተኛው እንመልከት ያ ከሆነ እርሱን እና መገኘቱን ማግኘት/መቅመስ እንችላለን ፡፡

  1. R. Bruce Compton, “Outline of Isaiah,” p. 1; available from https://www.fbcaa.org/BibleStudies/ot/isa/Postiff/IsaiahOutline.pdf.

  2. Compton, p. 1

  3. Compton, p. 1.

  4. Compton, p. 2

  5. Compton, p. .

  6. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 780.

  7. MacArthur, p. 780.

  8. MacArthur, p. 780.

ጥያቄዎች

  1. ኢሳ (17፡ 1) “ ደማስቆ ከተማ ከመሆን እንደተቋረጠች “ ይናገራል ፤ ይህ ትንቢት እስካሁን ተፈፅሟል ? እግዚአብሄር ይህን ያክል ቁጣዉን መልሶ ለምን እንደያዘዉ ምን ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ የአሁኑ ጊዜ ደማስቆ አስፈላጊነት ምንድን ነው ?
  2. ደማስቆ በጠፋች ጊዜ ምን ይሆናል ብለን እንጠብቃለን (ኢሳ 17፡ 7) ? ይህ ምን እንደሚመስል ምን ታስባላችሁ ?
  3. አንድ ሕዝብ ከክርስቲያን መሰረት በጣም ስለራቀው ስለነዚህ ከተሞች ከኢሳያያስ ትንቢቶች ምን ልንማር እንችላለን ?
  4. በኢሳይያስ (17-18) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 17:7–8

“On that day people will look to their Maker and will turn their eyes to the Holy One of Israel. They will not look to the altars they made with their hands or to the Asherahs and incense altars they made with their fingers.”

ኢሳይያስ በህይወታቸው ላይ ስለሚመጣው ጥፋት ትንቢታዊ መልዕክትን በጥንታዊዎቹ የደማስቆ ከተሞች ላይ ተናገረ ፡፡ በእርግጥ ንስሀ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰዋል ሆኖም ግን ቀድመው ለመረጡት ምርጫ ውጤቱን ይቀበላሉ ፡፡ እግዚአብሔር እነርሱ ያገኙት ዘንድ የወደደውን ደስታ ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ መልካምነት አልተቀበሉም ፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ ፣ እግዚአብሔር እናንተ በምታደርጉት ሁሉ ወደ እርሱ እንድትመለከቱ ይፈልጋል ፡፡ እርሱ በእቅዳችሁ ውስጥ እንድታስገቡት ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሔር ፈጥሯችኋል ፣ እርሱ ሰሪያችሁ ነው ፡፡ እርሱ ለእናንተ እቅድ አሳብ አለው ፡፡ እርሱ በፍቅሩ ፣ በጸጋውና በምህረቱ ሙላት ውስጥ እንድትኖሩ ይፈልጋል ፡፡ የራሳችሁን ነገር ለማድረግ መምረጥ ትችላላችሁ ፡፡ በኃጢአት ለመመላለስ መመረጥ ትችላላችሁ ፡፡ ጊዜያዊ ደስታን ለማግኘት መሻትን መምረጥ ትችላላችሁ ፡፡ እግዚአብሔር አይተዋችሁም ፡፡ እርሱ አማኑኤል ነው ፣ ከእናንተ ጋር ያለ አምላክ ነው ፡፡ እርሱ አለም ለእናንተ ሊያቀርብ ከሚችለው የበለጠ እግዚአብሔር ለእናንተ ብዙ ነገር አለው ፡፡ ስለዚህም በነገር ሁሉ እርሱን እሹ ፡፡ እርሱን ፈልጉ እርሱም በመከራ ቀን ይደግፋችኋል ፡፡ ዛሬ ንቁና ቀናችሁን ፣ ግንኙነታችሁን ደግሞም አላማችሁን ለእግዚአብሔር አሳልፋችሁ ስጡ ፡፡ ጥበብና ኃይል ይሰጣችሁ ዘንድ ጠይቁት ፣ እርሱም ይመልስላችኋል ፡፡ ከአለም ጋር አታመቻምቹ ፡፡ እግዚአብሔርን በየጊዜው በነገራችሁ አስገቡት እርሱም ይባርካችኋል እጁም በእናንተ ላይ ይሆናል ፡፡

“ በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል ፥ ዓይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ ። እጁም የሠራችውን መሠዊያ አይመለከትም ፤ ጣቶቹም ወደ አበጁአቸው፥ ወደ ማምለኪያ ዐፀዶች ወይም ወደ ፀሐይ ምስሎች ፥ አያይም ። “

  • ኢሳይያስ 17፡7-8

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 16:3 — “ ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ ፥ አሳብህም ትጸናለች ። “

ሐዋርያት ሥራ 17:26–27 — “ ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው ። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም ። “

ኤፌሶን 3:19 — “ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ ። “