The Song of Deliverance
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 14-16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስ ከክርስቶስ ልደት በ740-680 በፊት መካከል ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ የኢሳይያስ መልዕክት በዚያን ጊዜ ለእስራኤል አስፈላጊ ነበር ፡፡ በሙሉነት ለእግዚአብሄር የታዘዘ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ አንዲት ሚስት እና ሁለት ወንድ ልጆች ነበሩት እግዚአብሄርም ለሕዝቦች በተለይም ለነገስታቶቻቸዉ እንዲናገር ጠየቀው ፡፡ ኢሳይያስ በህይወቱ ለእግዚአብሄር እንዴት የታዘዘ ለመሆን እንደተሰጠ አናስታዉልም ፤ እግዚአብሄር ኢሳይያስን አገልግሎት እንዴት አስቸጋሪ እንደሚሆን በኢሳይያስ 6 ነገረው፡ “ እርሱም ሂድ ይህን ሕዝብ መስማትን ትሰማላችሁ አታስተዉሉምም ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው ፡፡ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸዉም እንዳይሰሙ በልባቸዉም እንዳያስተዉሉ ተመልሰዉም እንዳይፈወሱ የዚህ ህዝብ ልብ አደንድን ጆሮአቸዉንም አደንቁር አይናቸዉንም ጨፍን አለኝ ፡፡ እኔም፡- ጌታ ሆይ እስከመቼ ድረስ ነው ? አልሁ ፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፡- ከተሞች የሚኖሩባቸዉን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆን ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስትቀር ድረስ እግዚአብሄርም ሰዎችን እስኪያርቅ በምድርም መካከል ዉድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው “ (ኢሳ 6፡ 9-12) ፡፡
እስራኤል ወደ ምርኮ እንደምትሄድ ለሚያወራዉ መልዕክት ሰዎች እንዴት ምላሽ እንደሰጡ ምን ታስባላችሁ ? የኢሳይያስ ምልዕክት ለአመታት እስራኤል በታሪኳ በሚያስቀይም ጊዜ ዉስጥ እንደምታልፍ ነበር ፡፡ ያን መልዕክት በተደጋጋሚ እንዲናገረዉ ምን አነሳሳው ? ለእግዚአብሄር ያለዉ ታዛዥነት ፡፡
በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ለእግዚአብሄር ጥሪ በመታዘዝ ሌሎች ሰዎች ለኢሳይያስ መንገድን ጠርገዉለታል/አዘጋጅተዉለታል፡
- አብርሐም ለእግዚአብሄር በመታዘዝ ምላሽ ሰጠ፡ “ አብርሐምም መለሰ አለም፡- እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ “ (ዘፍ 18፡ 27) ፡፡
- ያዕቆብ እግዚአብሄርን ተዘዘ፡ “ ለባሪያህ ከሰራኸው ከምህረትህና ከእዉነትህም ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሰራዊት ሆንሁ “ (ዘፍ 32፡ 10) ፡፡
- ኢዮብ ወደ ገበታዉ ምንም ነገር ማምጣት እንደማይችል አስተዋለ፡ “ እግዚአብሄርም መለሰ ኢዮብንም እንዲህ አለው፡- በዉኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን ? ከእግዚአብሄር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት ፡፡ ኢዮብም መለሰ እግዚአብሄርንም እንዲህ አለው ፡- እነሆ እኔ ወራዳ ሰዉ ነኝ የምመልስልህ ምንድር ነው ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ ፡፡ አንድ ጊዜ ተናገርሁ አልመልስምም ፤ ሁለተኛ ጊዜም ከእንግዲህ ወዲህም አልናገርም “ (ኢዮ 40፡ 1-5) ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (14፡ 1-2)፡ ኢሳይያስ 13 በባቢሎን ላይ የእግዚአብሄርን የጥበብ አሰራርን ይይዛል ፤ ባቢሎን እስራኤልን ለመዳት ጥቅም ላይ ዉላ ነበር ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር ፍርድ በባቢሎን ላይ በመጡ ጊዜ እስራኤል የእግዚአብሄርን መፅናናት ታገኛለች ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ከመፃተኞች ጋር “ ወደ ራሳቸዉ ምድር “ መልሶ እንደሚያመጣቸዉ ተስፋን ገብቷል (ኢሳ 14፡ 1) ፤ ይህ በዘጸዓት ጊዜ ከሆነዉ ጋር ይመሳሰላል፡ “ የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነስተው ወደ ሱኮት ሄዱ ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ ፡፡ ደግሞም ሌላ ብዙ ድብልቅ ሕዝብ መንጎችና ላሞችም እጅግ ብዙም ከብቶች ከእነርሱ ጋር ወጡ “ (ዘጸ 12፡ 37-38) ፡፡ ከዚያም በኋላ ማክአርቱር “ አንድ ጊዜ የገዟቸዉን ህዝቦች እስራኤላዊያን የሚያስተዳድሩበት “ የተለዋዋጭ ተግባር “ እንደ ሆነ ፅፏል ፡፡
ኢሳይያስ (14፡ 3-4)፡ እግዚአብሄር ባቢሎንን ከፈረደባት በኋላ እስራኤል “ የንቀትን መዝሙር ትዘምራለች “ (ቁጥር 4) ፡፡
ኢሳይያስ (14፡ 5-8)፡ ባቢሎን ከተፈረደባት በኋላ ሁሉም ነገር የተረጋጋ/የተደሰተ ይሆናል ፡፡ የሊባኖስ ዛፎችም ደስ ይላቸዋል ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ሊቆርጣቸዉ የሚመጣ ስለሌለ (ቁጥር 8) ፡፡
ኢሳይያስ (14፡ 9-11)፡ “ ገሀነም “ ለምንለዉ ቃል ሲዖል ተመሳሳይ ነው ፡፡ ማክአርቱር “ ቀድመዉ በሙታን ስፍራ የሆኑ የአሕዛቦች ነገስታቶች የባቢሎን ንጉስ መድረስ የእንኳን ደህና መጣህ ግብዣ እንደሚያዘጋጁለት “ ፅፏል ፡፡ የባቢሎንን ንጉስ በሞት በፍርድ እና በዉርደት ስፍራቸዉ ላይ በደህና ተቀበሉት ፡፡
ኢሳይያስ (14፡ 12-15)፡ ኢሳይያስ በተመሳሳይ ሰይጣንን “ እኔ “ በሚሉ አምስት ንግግሮች በመግለፅ የባቢሎንን ንጉስ ገልፆታል፡
ወደ ሰማይ አርጋለሁ ፤ ሰይጣን ወደ ስልጣን/የበላይ ስፍራ ከፍ ማለትን ፈለገ ፡፡
ዙፋኔን አዘጋጃለሁ ፤ ሰይጣን በስልጣን ስፍራ መቀጥን ፈለገ ፡፡
በአማልዕክት ጉባኤ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ፤ ሰይጣን ከሌላ ከማንኛዉም የበለጠ ለመሆን ፈለገ ፡፡
ከዳመናት በላይ ከፍ ከፍ እላለሁ ፤ ሰይጣን ከፍ ከፍ ያለዉን መዉጣት መቀጥን ፈለገ ፡፡
ልክ እንደ ቅዱሱ ራሴን አደርጋለሁ ፤ በመጨረሻም ሰይጣን እግዚአብሄርን መሆን ፈለገ ይፈልጋልም ፡፡
ነገር ግን ሰይጣን አይሳካለትም፡ “ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ “ (ኢሳ 14፡ 15) ፡፡ “ ያሳታቸዉም ዲያብሎስ አዉሬዉና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሳቀያሉ “ (ራዕ 20፡ 10) ፡፡
መደምደሚያ
ከእኛ ዉስጥ አብዛኞቻችን ልክ እንደ ኢሳይያስ ተጠርተናል ፡፡ የጌታን መልዕክት እንደምንልክ በጦርነቱ መካከል ላይ ነን ፡፡ ጠላት ያለማቋረጥመልዕክተኞችን መልዕክቱን እንዳያደርሱ ይከለክላል ፤ ስራችን ሰዎችን ነፃ የሚያወጣዉን መልዕክት ማድረስ እና በትምህርታችን መቀመጥ ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 755.
MacArthur, p. 777.
MacArthur, p. 777.
MacArthur, p. 777-778.
ጥያቄዎች
-
ኢሳይያስ በኢሳ (14፡ 1) የተናገረላቸዉ እንግዶች እነማን ነበሩ (ኢሳ 56፡ 6-7, 60፡ 10, 61፡ 5) ? ለአሕዛቦች ይህ መልካም ዜና የነበረዉ ለምንድን ነበር ? ይህ ከመጀመሪያው ለሁላችንም የዳንን እንድንሆን የእግዚአብሄር አሳብ ነበር (ዘፍ 12፡ 3) ?
-
ኢሳ (14፡ 12-15) ሰይጣንን በማመልከት ወይስ ምድራዊ ንጉስን ማመልከት እንደ ነበር ታስባላችሁ ? ይህን ምስል ኢሳይያስ “ ሉሲፈር “ ብሎ ከገለፀ ዉጪ የራሳችሁን ሀሳብ ግለፁ
-
ኢሳይያስ በሞዓብ ላይ በኃይለኛዉ ለምን ተናገረ ? ሞዓባዊያን ዘራቸዉ ከማን የመጣ ነበር (ዘፍ 19፡ 31-38) ? በእስራኤላዊያን ላይ የተነሱ ነበሩ ?
-
በኢሳይያስ (14-16) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 14:12–13a, 15
“Shining morning star, how you have fallen from the heavens! You destroyer of nations, you have been cut down to the ground. You said to yourself: ‘I will ascend to the heavens; I will set up my throne above the stars of God.’ But you will be brought down to Sheol into the deepest regions of the Pit.”
የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ የሆነው ሰይጣን በትዕቢት ፡- “ ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ “ እንድሁም ከሌሎች “ እንዲህ እሆናለሁ “ ከሚሉ አረፍተ ነገሮች ጋር ተናገረ ፡፡ ውጊያ ሲነሳ ሁልጊዜ ሰይጣን እራሱን ከእግዚአብሔር በላይ አድርጎ ለማሳየት ይሞክራል ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ታላቅ “ እሆናለሁ “ የሚል ሳይሆን “ ታላቅ የሆንኩት እኔ “ የሚል ነው ፡፡ ያለውና የሚመጣው ፡፡ ባለቤትና ፈጣሪ ፡፡ መጀመሪያውና መጨረሻው ፡፡ እርሱ ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነው ስም ነው ፡፡ እርሱ በአሸናፊነት ከፍ ብሏል ፡፡ ምናልባት ሌሎች ከፍ እንደሚሉ ታላቅ እንደሚሆኑ ለመናገር ይሞክሩ ይሆናል ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ብቻ በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል ፡፡ እግዚአብሔር ብቻ በአሸናፊነት ይነግሳል ፡፡
ታላቁ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ ፡፡ እርሱ ውጊያችሁን ይዋጋል ፡፡ ፈጽሞ ብቻችሁን አይደላችሁም ፡፡ ሰይጣን ትዕቢተኛው በህይወታችሁ የሆነን ቦታ ለመያዝ ይሞክራል ሆኖም ግን እኔ ታላቅ ነኝና አይዟችሁ ደግሞም በእናንተ ዘንድ ያለው በአለም ካለው ይበልጣል ፡፡ ልክ በራሳችሁ ህይወት ውስጥ ትዕቢትና ኩራት ወደ ሽንፈት እንደሚመሩ ሁሉ ትዕቢትና ኩራት ለሰይጣንም ምንም አያስገኙለትም ፡፡ በጊዜው ከፍ እንድትሉ ልክ ክርስቶስ በትህትና እንደተመላለሰው ሁሉ እናንተም በትህትና ተመላለሱ ፡፡ ምርጫው የእናንተ ነው ፣ ትዕቢት ወይም ትህትና ፡፡ ትህትናን ምረጡ ታሸንፋላችሁም ፡፡
“ አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ ! አንተን በልብህ፦ ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ……ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ ። “
- ኢሳይያስ 14:12–13a, 15
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘጸአት 6:2 — “ እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው አለውም ፦ እኔ እግዚአብሔር ነኝ “
- ኢሳይያስ 41:10 — “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
- 1ኛ ጴጥሮስ 5:6 — “ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።