Reign Of Davidic King; Israel Regathered
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 11-13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ኢሳይያስ በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝያስ እና በሰዴቂያስ ዘመን የተናገረ ነቢይ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ ለሕዝቡ መልዕክትን እንዲናገር ከጠራዉ ከእግዚአብሄር ራዕይን ተቀበለ ፡፡ ኢሳይያስ ለህዝቡ ለእስራኤል ከባድ ቃልን እንደሚያደርስ በጥሪዉ በሙሉ መተማመን ተመላለሰ ፤ ኢሳይያስ በይሁዳ ይኖሩ ለነበሩት ለእግዚአብሄር ካለመታዘዛቸዉ እና በኃጢዓተኝነት የተነሳ ወደ ምርኮ እንደሚወሰዱ ነገራቸው ፤ ነገር ግን ኢሳይያስ የተስፋን መልዕክት ሰጣቸው ፡፡ በትንቢታዊ ቃሉ ዉስጥ ወደ ፍሬ ስለሚመጣው ስለ ወደፊቱ መልዕክትን አድርሷል ፤ ከእነዚህ ምልክቶች ዉስጥ እንዱ በኢሳ (7፡ 14) ላይ የተሰጠ ነበር ፡፡ ድንግል ወንድ ልጅን ትወልዳለች ስሙንም “ አማኑኤል “ ትለዋለች ትርጉሙም “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ ማለት ነው ፤ ይህ ኢየሱስን እንደሚያመለክት እናዉቃለን ፡፡ ዮሐ (1፡ 1-3) “ ቃል “ - ኢየሱስ ነበር “ በመጀመሪያም ከእግዚአብሄር ጋር ነበር “ ፡፡ ስጋም በመሆን በሰዉ መካከል አደረ (ዮሐ 1፡ 14) ፡፡ ኢሳይያስ 10 እግዚአብሄር የአሶርን ሕዝብ እንደ ጠላት ፍርዱን ለማምጣት እንደሚጠቀምባቸዉ ይገልፃል ፤ እግዚአብሄር ይሁዳ ላይ ለመፍረድ እነዚህን ጠላቶችም ቢጠቀም እንኳን በመጨረሻም ይህ ፍርድ በአሶራዊያን ላይ ይወድቃል ፡፡ ነገር ግን የታመኑ ቅሬቶች ወደ እግዚአብሄር በመመለስ በእርሱ ላይ በመታመን ይደገፋሉ (ኢሳ 10፡ 20-21) ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (11፡ 1)፡ ማክአርቱር “ ከክርስቶስ ልደት 586 በፊት በሆነዉ ምርኮ የዳዊታዊዉ ስሮዉ መንግስት የአሶርን ሰራዊት ሙሉ በማጥፋት ተከስቷል ፤ በሁለቱ መካከል ያለዉ ዋና ልዩነት የቀረዉ ህይወት በዳዊት ዘር ላይ በሆነ ስር እና ማህተም ነበሩ “ አለ ፡፡ እግዚአብሄር በምርኮም ቢያስቀምጣቸዉም በእነርሱ ተስፋ አልቆረጠም ፤ እግዚአብሄር ከቅሬቶቹ ህይወትን ለማስፋት/ለመግፋት ተስፋ ገብቷል ፡፡ “ ቁጥቋጦ “ ለመሲሁ ስያሜ ነው (ኢሳ 4፡ 2) ፡፡ ከሚድኑትም -ቅሬቶቹ - ወደፊት መሲሁ ይመጣል ፡፡ “ የእሴይ ልጅ ማህተም “ የሚያስደንቅ መልክ ነው ፤ እሴይ የዳዊት አባት ነበር ፤ መሲሁ ከእሴይ ልጅ በዳዊት በኩል ይመጣል (ሩት 4፡ 22 የዘር ግንዱን ይሰጣል ) ፡፡ በ 1ሳሙ (16፡ 1) እግዚአብሄር ሳሙኤልን በቤተ ልሄም ወደ እሴይ ቤት በመሄድ አንድ ንጉስ እንዲመርጥ ነገረው ፡፡ 1ሳሙ (16፡ 12-13) ፡፡
ኢሳይያስ (11፡ 2)፡ በዳዊት መስመር ላይ የሚመጣው ይህ ቅባት “ የእግዚአብሄርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት በኃይል መጣ “ በሚለው በ 1ሳሙ (16፡ 13) ላይ የሚያቀነቅን ነው ፡፡ ኢሳይያስ በመንፈስ ኃይል ስለሚሰራው ባህሪይ ገልፆአል፡- የጥበብ እና የማስተዋል መንፈስ፣ የመምከር እና የኃይል መንፈስ፣ እግዚአብሄርን የመፍራት እና የእዉቀት መንፈስ ፡፡ እነዚህን ባህሪያት በኢሳ (61፡ 1) ስለሚመጣዉ መሲህ ከኢሳይያስ መግለጫዎች ጋር አወዳድሩ ፡፡ በጌታ ቅባት/መመረጥ እና በእግዚአብሄር መንፈስ ስር መሲሁ ለድሆች፣ ልባቸዉ ላዘነ፣ በግዞት ላሉ ነፃነትና እና ለታሰሩት የመፈታት መልካም ዜናን ያመጣል ፡፡ ኢሳይያስ ወደ ባርነት እየሄዱ ለነበሩ ሰዎች እያወራ ነበር ፤ ይህ በግልፅ ክርስቶስ የፈፀመዉ ሞደል ነበር ፡፡ በሉቃ (4፡ 18-21) ኢየሱስ ይህ ጥቅስ እርሱን ይገልፀኛል አለ ፡፡
ኢሳይያስ (11፡ 3-9)፡ ኢሳይያስ የሺዋ ብሎ ስለማይሰይም ቃሎቹ በግልፅ ኢየሱስን ይገልፃሉ ፡፡ ስለ መስማት እና ማየት ይናገራል (ቁጥር 3) ማክአርቱር “ እነዚህ ለማስተዳደር መረጃን ለማግኘት ለአንድ ንጉስ የተለመዱ ነገሮች ናቸዉ ነገር ግን የወደፊቱ ንጉስ ከዚህ ከተለመደዉ ምንጭ የበለጠ መለኮታዊ መረዳት አለው “ አለ ፡፡ መሪዎቹ በድሆች እና በተጨቆኑት ላይ ጥቅምን ወስደዉ ከነበር አሁን ኢየሱስ ሁኔታዉን ይቤዠዋል (ቁጥር 4) ፡፡ ቁጥር 5 የእግዚአብሄርን እቃ ጦር የቀደመ ስዕልን ይሰጣል (ቁጥር 4) ፤ ጽድቅ እና መታመን ለመጨረሻዉ ዝግጅቶች ናቸው፡፡ በኢሳይያስ የተገለፁትን ክስተቶች ለመረዳት የተጠቀምንባቸዉን ሰዎስት ዙሮች እናስታዉሳለን ፡- የህዝቡ የወቅቱ ሁኔታ፣ የኢየሱስ የመጀመሪያ መምጣት፣ የኢየሱስ መመለስ እና የሺሁ ጊዜ ፡፡
በቁጥር (1-2) ኢሳይያስ ስለኢየሱስ የመጀመሪያ መምጣት አዉርቷል ነገር ግን የኢየሱስን ተመልሶ መምጣት ሊያመለክት የሚችል የፍርድ ጊዜም እንደሚኖር ተናግሯል ፡፡ በቁጥር (6-9) ኢሳይያስ ስለ ሺህ አመቱ ገልፆአል ፡፡ በቁጥር 9 ኢሳይያስ “ ዉኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሄርን በማወቅ ትሞላለች “ አለ ፡፡ ምን አይነት የሚያስደንቅ ምስል ነው ! የኢሳይያስ ትንቢት ከመጥፎ ሁኔታዎች ወደ መጨረሻ ከሚወስዱት መንገድ ሰዎች የእግዚአብሄርን መገኘት ወደ ሚያዉቁበት ሄደ ፡፡
ኢሳይያስ (1፡ 10- 11, 16)፡ “ ስለ ሕዝቦች “ በምናወራ ጊዜ ስለ አሕዛቦች እያወራን ነው ፡፡ ኢየሱስ አይሁድ ነው ፤ ሕዝቦቹ ወደ እርሱ ይመለሳል አሕዛቦችም ደግሞ ይመለሳሉ ፡፡ ቤቱ ኢየሩሳሌም ትሆናለች የማረፊያም ስፍራዉ የከበረች ትሆናለች ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሄር ሕዝቡን በዘፀዓት ዉስጥ ከግብፅ በመሰብሰብ ወደ ተስፋይቱ ምድር አመጣቸው ፤ በመቀጠልም ምድሪቱን አጡአት ፡፡ እግዚአብሄር እነርሱን “ የተረፈት የሚኖሩት ቅሬቶቹን “ (ቁጥር 11) የሚባርክበት ሁለተኛ ጊዜ - በዚህ ምድር ይኖራል ፡፡ ቅሬቶቹ “ የቀሩ “ ወይም “ የተረፉ “ በማለት ሊገለፁ ይችላሉ ፡፡ ማክአርቱር ይህ “ ከጥፋቱ በኋላ የተረፉትን ጥቂት ሰዎችን ይጠቅሳል -… እንዲሁም በይበልጥ ከምርኮ /ከግዞት በመትረፍ ያልጠፉትን የእስራኤል ህዝቦች ያመለክታል “ አለ ፡፡ ነቢያቶች እነዚህን ቃላቶች ለእግዚአብሄር ታምነዉ የቀሩትን ለመግለፅ ተጠቅሞአቸዋል (አሞ 5፡ 14-15) ፡፡ ኢሳይያስ መሲሁን አንድ ቀን ከሁሉም ሕዝቦች ቅሪቶቹን እንደሚሰበስብ ገልፆአል (ኢሳ 10፡ 20-22) ፡፡ ይህ የተለመደ ቋንቋ ነው - እግዚአብሄር ቅሬቶቹን ለመጠቀም ይፈልጋል ፡፡ በቁጥር 16 ኢሳይያስ ከግብፁ በወጡት ጥቅም ላይ በዋለዉ መንገድ በተመሳሳይ “ ከአሶር ለሚተረፉት ቅሬት ሕዝቦቹ የሆነዉን መንገድ “ ገልፆአል ፡፡ እግዚአብሄር በግልፅ ለቅሬቶቹ መንገድን ያደርጋል ፤ ሁሉም እግዚአብሄር እንዲያደርጉት የጠየቃቸዉን ለማድረግ ታዛዥ ሆነዉ ማድረግ ነበር ፡፡
በዚህ ሁሉ ዘር አለ ፤ ይህ ዘር ቅሬት ነው፡ ኖህ እና ቤተሰቦቹ (ዘፍጥረት 7)፣ ዮሴፍ እና ከርኃብ በግብፅ የተረፉት ቤተ ሰቦቹ (ዘፍጥረት 45)፣ እስራኤል በራሷ ምድር (ዘዳግም 4) እና ባዖልን ያላመለኩት 7,000 (1ነገስት 19) ፡፡ ሚክ (2፡ 12-13) እግዚአብሄር “ የእስራኤልን ቅሬቶች ይሰበስባል “ ይላል ፤ ንጉሱም ቅሬቶቹን መንገዱን ይመራቸዋል ፡፡
ኢሳይያስ (11፡ 12)፡ ይህ ጥቅስ እስራኤል እንደ ሕዝብ በ1948 መመስረቷን ሊገልፅ ይችላል ? ይህ ጥቅስ “ ቀድሞ ያለ ነገር ግን አሁንም ያልተሳለ ነው “ ፡፡ ይህን ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካለዉ ከራዕ (20፡ 8) ጋር አወዳድሩ ፤ ይህ ስለ ቅሬቶቹ ወይስ ስለሁሉም ሕዝቦች ይናገራል ሁል ጊዜ ኢየሱስ መንገዱን እያዘጋጀ ነው ፡፡
ኢሳይያስ (11፡ 13-15)፡ ኢሳይያስ ሺህ አመቱን ገልፆታል ፡፡ ይህ ቅሬት የእስራኤልን መታደስ የሚመራበት ጊዜ ይመጣል ፡፡
መደምደሚያ
በእምነታችሁ ላይ በመፅናት ኢየሱስ ለህዝቦቹ ቅሬቶች መንገድ ማዘጋጀቱን እንዲቀጥል ይፈቅዳል ፤ እግዚአብሄር እርሱን እንድትከተሉት በመታመናችሁ እና በፍቃደኛነታችሁ በኩል መንገድን ያዘጋጃል ፡፡ ምናልባትም ለእግዚአብሄር እንደ ቅሬቶች አገልግሎታችሁ ለእስራኤል መነሳት እና መታደስ እንደ መንገድ ያገለግላል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 773.
MacArthur, p. 773.
MacArthur, p. 772.
MacArthur, p. 772.
ጥያቄዎች
-
ኢሳ (11፡ 10) በተለያዩ ትርጓሞች (www.blueletterbible.org) ፤ በዚህ ጥቅስ ዉስጥ አሕዛቦችን እንዴት ተገልፀዋል ? (ኢሳ 49፡ 6, ሐዋ 13፡ 47, ሮሜ 15፡ 12) ? የአሕዛብን ምላሽ በሐዋ (13፡ 48) አስታዉሉ ፡፡ በእግዚአብሄር የመዳን እቅድ ዉስጥ በመካተታችሁ ይህን የሚመስል ተመሳሳይ ደስታ ተሰምቷችኋል ?
-
ኢሳ (11፡ 2) “ የእግዚአብሄር መንፈስ እንደ ወረደበት “ ይገልፃል ፤ ይህ መፈፀም ምን ይመስላል ? (ኢሳ 61፡ 1, ማቴ 3፡ 16, ሉቃ 4፡ 18, 1ቆሮ 1፡ 30)
-
የኢሳይያስ 11 ትንቢት “ በአንደበቱ ንግግር ክፉዎችን ያጠፋቸዋል “ በሚለዉ ይጨርሳል ፤ 2ተሰ (2፡ 8) አንብቡ ፤ ይህ ትንቢት እስካሁን ተፈፅሟል ?
-
ነቢዩ ኢሳይያስ በቀሪዉ በምዕራፉ ዉስጥ በገለፀበት በኢሳ (13፡ 9) ስለ ጌታ ቀን ፅፏል ፤ ኢሳይያስ ፅፎ የነበረዉ ስለ ባቢሎን ብቻ ነበር ወይስ ስለ ወደፊቱም ክስተት ነበር (ማቴ 24፡ 29, ማር 13፡ 24, ሉቃ 21፡ 25, ራዕ 6፡ 12-13) ?በመጀመሪያዎቹ ሁለት ማጣቀሻዎች ኢየሱስ ከኢሳይያስ 13 ጠቅሷል ፡፡
-
ዮሐንስ በራዕ (18፡ 2) ስለ ባቢሎን ዉድቀት ፅፏል ፤ በኢሳ (13፡ 21) ግንኙነቱን ታዩታላችሁ ? አዎ ከሆነ ይህ ትንቢት ሁለቱም ትንቢት ተፈፅሟል ወይስ ገና ይመጣል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በኢሳይያስ (11-13) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 11:1–2
“Then a shoot will grow from the stump of Jesse, and a branch from his roots will bear fruit. The Spirit of the LORD will rest on Him—a Spirit of wisdom and understanding, a Spirit of counsel and strength, a Spirit of knowledge and of the fear of the LORD.”
ኢየሱስ በዳዊት ኪዳን መሰረት ከእሴይ ግንድ እንደሚመጣ ኢሳይያስ ተነበየ ፡፡ ምንም እንኳ ሰዎች የእሴይ ግንድ እንዳበቃ ቢያስቡም ኢሳይያስ እንድህ በማለት አስቀድሞ ተነበየ ፡- “ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል ፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል ። “ በትሩ የሚያመለክተው ኢየሱስን ነው ፤ እርሱም ከሌሎቹ የዳዊት ዘሮች የተለየ ይሆናል ፡፡ ኢየሱስም ስራውን በምድር ላይ በጥበብና በማስተዋል መንፈስ ፥ በምክርና በኃይል መንፈስ፥ በእውቀትና እግዚአብሔርን በመፍራት መንፈስ ያከናውናል ፡፡
የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን የእግዚአብሔርን መንግስት ስራ ትፈጽሙ ዘንድ የክርስቶስ ልብና የእግዚአብሔር መንፈስ አላችሁ ፡፡ ምናልባት ኃይላችሁን እንደጨረሳችሁ ታስቡ ይሆናል ፡፡ ይህ ከጠላት የሆነ ውሸት ነው ! የእዚአብሔር ኃይል በእናንተ ውስጥ ታላቅ ነውና ከምታስቡት የበለጠ ብዙ መስራት ትችላላችሁ ፡፡ ስለዚህ ጽኑ ! አይኖቻችሁንም በክርስቶስ ላይ አድርጉ ፡፡ ዛሬ አሳባችሁን ከራሳችሁ ላይ በማንሳት ፡- “ ለመንግስትህ ምን እንዳደርግ ትፈልጋለህ ? “ በማለት እግዚአብሔርን ጠይቁ ፡፡ የጥበብና የእውቀት መንፈስ እንደሚሰጣችሁ እግዚአብሔርን እመኑት ፡፡ የምክርና የኃይል መንፈስ ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ እንዳላችሁ በማስታወስ ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን ፡፡ የጌታ መንፈስ በእናንተ ላይ ነው ፡፡ ይህን በክርስቶስ ኢየሱስ ዘንድ ባለ ድፍረት ፈጽሙት ፡፡
“ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል ፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል ። የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል ። “
- ኢሳይያስ 11፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 2:16 — “ እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን ። “
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ12:6–8 — “ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል ። ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል ፡፡ “
ፊልጵስዩስ 2:5 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።