The Prince of Peace
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
ትምህርት
ኢሳይያስን ማጥናት ከባድ ስራ ነው ፤ አራት ክፍል ከማጥናታችን ይልቅ 40 ክፍሎችን የፈፀምን ይመስላል ፡፡ እግዚአብሄር መልዕክቱን ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም እንዲያደርስ ኢሳይያስን ጠራው ፡፡ አብዛኛዎቹ ትንቢቶች አዎንታዊ አይደሉም (በይሁዳ ላይ ስለሚመጣዉ ፍርድ) ነገር ግን በመፅኀፉ ላይ ተስፋ አለ (በመሲሁ በኩል ስለሚመጡት ቅሬቶች) ፡፡ አሶራዊያን የሰሜኑን መንግስት ለመዉረር እየመጣ ስለ ነበር አብዛኞቹ ሰዎች ወደ ግዞት ይሰደዳሉ ፡፡ የይሁዳ ንጉስ አካዝ ወደ ይሁዳ እየመጣ ባለዉ ነገር ፈርቶ ነበር - የኢሳይያስ መልዕክት እግዚአብሄርን እንዲታመኑ ነበር ፤ ኢሳይያስ እየመጣ ስለ ነበረዉ ነገር አምስት ትንቢቶችን ሰጥቷል ፤ ከእነዚህ ዉስጥ ሁለቱን ትናትና በምዕራፍ 7 ሸፍነናቸዋል ፡፡ በምዕራፍ (7-8) ተጨማሪዎች አሉ ፡፡ ለኢሳይያስ ቃላችን የእግዚአብሄርን ሰዎች “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ የሚለዉን የሚያስታዉስ አማኑኤል የሚል ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ለመገናኘት ወደ ምድር መጣ፤ በትርምስ መካከል ላይ ተስፋ አለ ፡፡
ምዕራፍ 8 ይሁዳ የጌታን መልዕክት እና ምልክት ካለማዳመጡ የተነሳ ስለ አሶራዊያን መምጣት የኢሳይያስን መልዕክት ይሸፍናል ፡፡ አሶራዊያን ሰሪያን እና ደማስቆን ይይዛሉ ፤ አሶራዊያን በይሁዳ ስለሚያልፉ ይሁዳ እነርሱን ተቋቁሞ መቆም አይችልም ምክንያቱም ጌታ ከአሶራዊያን ጋር ስለሚሆን (ቁጥር 8-9) ፡፡ ጌታም ኢሳይያስን በዙሪያቸዉ ካሉ ኃያላን ህዝቦች ጋር ጥምረትን በመፍጠር ህዝቦቹ በተመላለሱበት መንገድ እንዳይመላለስ አስጠነቀቀው ((ቁጥር 11-15) ፡፡ ይሁዳ የኢሳይያስን መልዕክት ሳይቀበል ቢቀርም ከሕዝቡ ዉስጥ አንዳንዶቹ ሰምተዉታል (ቁጥር 16-22) ፤ የእግዚአብሄር ቃል ሙሉ በሙሉ አይረሳም ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (9፡ 1-7)፡ ኢሳይያስ በመቀጠልም ስለ መልዕክቱ መልካም ዜና መናገርን ቀጠለ ፤ ኢሳይያስ አንዳንድ ነገዶች (ዛብሎን እና ንፍታሌም) ጨለማ እና ዉርደት ገጥሟቸዉ እንደ ነበርና ከዮርዳኖስ ማዶ ያለዉ ምድርም የከበረ እንደተደረገ ገልፆአል (ቁጥር 1) ፡፡ ዛብሎን እና ንፍታሌም ከገሊላ ዉጪ የነበሩና የአሶራዊያን የመጀመሪያ መያዝ የሚገጥማቸዉ ምድሮች ይሆናሉ ፤ የምርኮን የጨለማ ቀን የሚገጥማቸዉ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ ነገር ግን እግዚአብሄር ለዚያ ስፍራ ክብርን ያመጣል (7፡ 14) ፡፡ ቁጥር 2 የሚመጣዉ የመሲሁን ብርኃን የሚገጥማቸዉ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ ይላል (ማቴ 4፡ 15-16, ሉቃ 1፡ 78-79, ዮሐ 8፡ 12) ፡፡ ኢየሱስ የኢሳ (9፡ 1-2) መፈፀም ነው ፡፡ የኢሳይያስ ትንቢት ስለሚመጣው መሲህ በግምት ከክርስቶስ መወለድ ከ700 አመት በፊት ነበር (ኢሳ 42፡ 16, 49፡ 6, 58፡ 8, 60፡ 1, 19, 20) ፡፡ ብርኃኑ ወደ ዛብሎን እና ንፍታሌም እንዲሁም ወደ ሕዝቡ ሲመጣ ሰዎቹ ለሁሉም ሕዝብ ብርኃኑን አስተላለፉ ፡፡
በቁጥር 3 “ ጌታ እንደ ገና እንደ ምድር አሸዋ ዘሩን እንደሚያበዛ ከአብርኃም ጋር የገባዉን ተስፋ አረጋገጠ (ገላ 22፡ 17) “ ፡፡ በምርኮ የያዛቸዉን ቀንበር እግዚአብሄር ይሰብረዋል - በመጀመሪያዉ መምጣት (ቁጥር 4) ፤ ሰላም ለዘላለም ይመጣል - በሁለተኛዉ መምጣት (ቁጥር 5) ፡፡ ማክአርቱር “ አለም የዉጊያ መሳሪያዎች/እቃዎች አያስፈልጉትም የአለም ሰላም ጊዜ የክርስቶስን ተመልሶ መምጣት ተከትሎ ስለሚመጣ “ በማለት ይናገራል ፡፡
ቁጥር 6 ከገና ትንቢቶች በአንዱ ይጀምራል - ስለመሲሁ መምጣት ከሚናገሩት ዉስጥ ፤ ሌሎቹ የሚያካትቱት፡
- ሚክ (5፡ 2)፡- ኢየሱስ በቤተ ልሄም ይወለዳል (ማቴ 2፡ 6) ፡፡
- ኢሳ (7፡ 14)፡- ከድንግል ይወለዳል (ማቴ 1፡ 23) ፡፡
- ኢሳ (7፡ 14)፡- አማኑኤል(እግዚአብሄር ከኛ ጋር ነው) ተብሎ ይጠራል ( ማቴ 1፡ 23) ፡፡
- ኢሳ (9፡ 6)፡- በሰዉ መልክ አምላክ ይሆናል (ዮሐ 1፡ 1) ፡፡
- ኢሳ (9፡ 6)፡- በምድር ላይ ሰላምን ያመጣል (ሉቃ 2፡ 14) ፡፡
- ኢሳ (9፡ 7)፡- ከዳዊት ዘር ይወለዳል (ማቴ 1፡ 1) ፡፡
በቁጥር 6 የሚመጣዉ ክርስቶስ ተግባራት የተሰጡ ሲሆን ( ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት እና የሰላም አለቃ ) በቁጥር 7 ከዳዊት ዙፋን በስልጣናት ላይ ያለዉ ስልጣን የተብራራ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ኢሳ (9፡ 6) ሰብዓዊነቱን “ ሕፃን ተወልዶአል “ እና አምላክነቱን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን “ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል “ በማለት ሁለቱንም እንደተናገረ “ ይገልፃል ፡፡
ከኢሳ (9፡ 6) ሌላ የሚጠቅሙ ቃላቶች፡-
መንግስት/አለቅነት፡- የመዝ (2፡ 9) መፈፀምን ያሳያል (ራዕ 2፡ 27, 19፡ 15) ፡፡
ድቅ መካር (ቁጥር 6)፡- “ ከአካዝ አንፃር ይህ ንጉስ ተግባሩን በመፈፀም መለኮታዊ ጥበብን ይተገብራል “ (2ሳሙ 16፡ 23, 1ነገ 3፡ 28) ፡፡
ኃያል አምላክ (ቁጥር 3-5)፡- “ እንደ አንድ ኃያል ተዋጊ መሲሁ በ(9፡ 3-5) የተጠቀሰዉን የዉትድርና የጀግንነት ተግባር ይፈፅማል “ ፡፡
የዘላለም አባት (ቁጥር 6)፡- መሲሁ ለሕዝቡ ለዘላለም አባት ይሆናል ፤ እንደ ዳዊታዊ ንጉስ በርህራሄነት ይጠነቀቅላቸዋል እንዲሁም ይገስፃቸዋልም “ (መዝ 68፡ 5-6, 103፡ 13, ኢሳ 40፡ 11, 63፡ 16, 64፡ 8) ፡፡
የሰላም አለቃ (ቁጥር 6)፡- “ የአማኑኤል መንግስት በአለም ሕዝብ መካከል ሰላምን በማምጣት ቀጣይ እንዲሆን ያደርጋል “ (ኢሳ 2፡ 4, 11፡ 6-9, ሚክ 4፡ 3) ፡፡
ኢሳይያስ (9፡ 8 – 10፡ 4)፡ የእግዚአብሄር ትንቢታዊ ቃል የተነገረ ነበር ፤ እስራኤል (ኤፍሬም እና ሰማሪያ) በትዕቢታቸዉ ቢቀጥሉም ፡፡
ኢሳይያስ (9፡ 13-17)፡ እስራኤል ወደ ጌታ ለመመለስ እና ንስኃ ለመግባት እምቢ ስላለች በወራሪ ሰራዊቶች ይወድቃሉ ፡፡
ኢሳይያስ (9፡ 18-21)፡ እነዚህ ቁጥሮች ይመጣ ስለ ነበረዉ የእስራኤል ቅጣት ያጠቃልላሉ ፡፡
መደምደሚያ
በትህትና በንስኃ ለመመላለስ ማንኛቸዉም ፍቃደኞች አልነበሩም ፤ ማንም ወደ ጌታ ለመመለስ ፍቃደኛ አልነበረም፡፡ ላለመታዘዛቸዉ በኃይለኛዉ ዋጋ ከፈሉ ፡፡
እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን እንጂ ሁኔታዉ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳን አሁንም በጌታ ተስፋ አለ - በድንቅ መካር፣ በኃያል አምላክ፣ በዘላለም አባት እና በሰላም አለቃዉ በኩል ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 770.
MacArthur, p. 770.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 21.
MacArthur, p. 770.
MacArthur, p. 770.
MacArthur, p. 770.
MacArthur, p. 770.
ጥያቄዎች
-
በአዲስ ኪዳን በኢሳ (9፡ 1-2)የተነገረዉ ትንቢት የት ላይ ተፈፅሞ እናየዋለን ? ኢየሱስ የአለም ብርኃን እንደ ሆነ ሲናገር ምን የተለዬ ጥቅስ ታስባላችሁ ?
-
በኢሳ (9፡ 6-7) የዚህን ልጅ አምላክነት የትኛው መግለጫ ይገልጠዋል ? በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ኢየሱስ እንዴት ይህን ትንቢት እንዴት ፈፀመዉ የትኛዉ መፅሀፍ መልሳችሁን ይደግፋል ?
-
እንደ ኢሳ (9፡ 8-21) መሰረት የጌታ ቁጣ ያልተመለሰችዉ እና እጆቹ በእስራኤል ላይ የተዘረጉት ለምንድን ነው ?
-
ኢሳ (10፡ 22-23) በሮሜ (9፡ 27-28) ተጠቅሷል ፤ ጳዉሎስ እየፃፈ ባለዉ ትርጉም/አገባብ መሰረት እነዚህን ጥቅሶች ለምን እንደጠቀሰ ምን ታስባላችሁ ?
-
በኢሳይያስ (9-10) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 9:6
“For a child will be born for us, a son will be given to us, and the government will be on His shoulders. He will be named Wonderful Counselor, Mighty God, Eternal Father, Prince of Peace.”
አሶር ጥፋታቸውን በተመለከተ ጊዜ የእግዚአብሔር ህዝብ ዛለ ሆኖም ግን እግዚአብሔር ለኢሳይያስ የተስፋ መልዕክትን መስጠቱን ቀጠለ ፡፡ ኢሳይያስ ስለሚመጣው አዳኝ ፣ ለህዝቡ ስለሚወለደው ልጅ ፣ አለቅነት በጫንቃው ላይ ስለሆነው የንጉሥ ልጅ ስለ አማኑኤል ተነበየ ፡፡ ልጁም በዳዊት ዙፋን ላይ ሲቀመጥ ስሙ ፡- ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ይባላል ፡፡ ተስፋ የቆረጡም መልሰው ተስፋን ያገኛሉ ፡፡
የልጁ ፣ የአዳኙ ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ስም ኢየሱስ ነው ፡፡ አንዱ እግዚአብሔር አለምን ከሞት እንድያድንና የዘላለምን ህይወት እንድሰጥ የላከው ፡፡ ስለዚህም በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሳላችሁ አይኖቻችሁን በኢየሱስ ላይ አድርጉ ፡፡ በኢየሱስ ዘንድ ባለው ተስፋ ላይ ተጣበቁ ፡፡ ያላችሁበት ሁኔታ ግራ የሚያጋባ ቢሆን እንኳ ፤ እየወደቃችሁ ደግሞም ብቸኛ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እንኳ ፣ ይህንን አስታውሱ እግዚአብሔር ስሙ ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ የሆነውን ልጁን ለእናንተ ልኳል ፡፡ እርሱን እወቁ ፡፡ ምክርን ታገኙም ዘንድ ልቡን አሳቡን ፈልጉ ፡፡ በእርሱ ኃይል ታመኑ ፡፡ በዘላለማዊ ፍቅሩ እመኑ ፡፡ በሰላሙ እረፉ ፡፡ ወደ ምድር የመጣውን ፣ በምድርም የኖረውን ደግሞም እናንተ የዘላለም ህይወትንና የማያላቅ ተስፋን ታገኙ ዘንድ የሞተውን እርሱን እሹ ፡፡ ክርስቶስን ብቻ ፈልጉ ፡፡
“ ሕፃን ተወልዶልናልና ፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ፤ ስሙም ድንቅ መካር ፥ ኃያል አምላክ ፥ የዘላለም አባት ፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ። “
- ኢሳይያስ 9፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 72:17 — “ ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል ፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል ፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል ። “
ኢሳይያስ 9:7 — “ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል ፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም ። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል ። “
ማቴዎስ 1:23 — “ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል ፥ ትርጓሜውም ፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።