The Immanuel Prophecy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በታላላቅ ነቢያቶች ጥናታችን ኢሳይያስ የመጀመሪያ መፅሀፍ ነው ፡፡ የቀሩትን አምስት የአዲስ ኪዳን መልዕክቶች ለማጥናት ከመለሳችን በፊት በአጠቃላይ አምስት መፅሀፍትን እናጠናለን ከዚያም በመቀጠል አስሩን ታናናሽ ነቢያቶችን ለማጥናት ወደ ብሉይኪዳን እንመለሳለን ከዚያም እንደ ገና ለራዕይ ወደ አዲስ ኪዳን እንመለሳለን ፡፡ የሪቫይቭ ት/ቤት ቀሪዉ ጥናቶች ወደ መጨረሻዉ ጊዜ የሚያመለክቱ ይመስላሉ ፡፡ ብዙ ጊዜ ይህን አልልም ነገር ግር ከሚመጣዉ የተነሳ እና እነዚህ ሁሉ በአንድ ላይ እንዴት እንደሚገናኙ ቀኑን እንዳትስቱት እፀልያለሁ ፡፡ ጥቂት ክፍሎችን ማለፍ ችግር የለዉም ባልኩበት ጊዜ ከአሁን ጀምሮ እስከ አመቱ መጨረሻ ጊዜ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ አለ ፤ ከእኛ ጋር ለመያያዝ ሞክሩ ፡፡
በኢሳይያስ (5-6) ከትናትናዉ ጥናት ላይ የወሰድነው እስራኤል የጌታን ቃል እንዳልተቀበለች ነው - የመጣዉን መሲህ ተቀብለዉት እንዳልነበር ነው ፡፡ የኢሳይያስ መጀመሪያዎቹ ስድስት ምዕራፎች መንፈሳዊ ትኩረት አለው ፤ የመጀመሪያዎቹ አምስት ምዕራፎች በአንድ ላይ ሊኖሩ እንደሚገባቸዉና ተመልሰዉ በእግዚአብሄር ላይ እንዲያተኩሩ ይናገራሉ ፡፡ በምዕራፍ 6 የኢሳይያስ አንደበት ንፁህ ተደርጎ ስለ ነበር የእግዚአብሄርን መልዕክት ማድረስ ይችላል ፡፡ ኮንስታብል ምዕራፍ (7-39) “ በኢሳይያስ ዘመን የእስራኤል ዋና ዉሳኔዎች ላይ እንደሚያወሩ ፤ እስራኤል በእግዚአብሄር ወይም በሌሎች ሕዝቦች ? “ እንደሚያወሩ ይገልፃል ፡፡ በምዕራፍ (34-35) የእግዚአብሄር መልዕክት “ በሕዝብ መታን የጥፋት ዉጤትን እንደሚያመጣ ነገር ግን በእርሱ መታመን መትረፍረፍን እንደሚያመጡ “ ነበር ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ምዕራፍ (7፡ 1-12፡ 6) “ በተለዬ ሶሪያ-ኤፍሬማዊያን ጦር ጋር የተገናኙ ኃይለኛ የሆኑ ትንቢቶችን ይይዛል - ረአሶ እና ፋቁሔ የይሁዳን መዋረር “ ፡፡ ኤፍሬም ከአስሩ ከእስራኤል ነገዶች የሰሜኑ መንግስት ክፍል ነበር ፡፡ ንጉስ አካዝ “ እስራኤል ለአሕዛብ መልዕክት እንደ ነበራት ወይም እንዳልነበራት እና ለአሕዛብ ተልዕኮዋን እንደምትፈፅም ወይም እንደማትፈፅም ዉሳኔን ያደርግ ነበር ፤ ይህ ዉሳኔ በሁሉም ዘመን የእግዚአብሄርን ሰዎች የሚገጥም ዉሳኔ ነው “ ፡፡
በምዕራፍ 7 ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሄር እንዴት እየሰራ እንደ ነበር ለማሳየት አምስት ትንቢቶችን አምጥቷል ፡፡ በተጨማሪም ምዕራፍ 7 ለኢሳይያስ መፅሀፍ አንድ ቃላችን የሆነዉን አማኑኤልን የምናገኝበት ነው ፡፡
ትምህርት
ኢሳይያስ (7፡ 1-9)፡ ቁጥር 1 የመጀመሪያዉ እና ሁለተኛዉን የይሁዳ ነገስታት ዖዝያን እና ኢዮአትም ሞተዉ እንደ ነበርና የኢዮአታም ልጅም አሁን ንጉስ ነበር ፡፡ ወዲያዉኑም የሶሪያ ንጉስ ረአሶን እና የእስራኤል ንጉስ ፋቁሔ በንጉስ አካዝ እና በኢየሩሳሌም ላይ ጦርነትን አወጁ አክዓዝም ሊሳካለት አልቻለም ፡፡ በቁጥር 2 ሁል ጊዜ “ ለዳዊት ቤት “ የዳዊትን ኪዳን ያመለክታል (2ሳሙ 7፡ 16) ፤ አካዝ እና የይሁዳ ሕዝብ ያንን በሰሙ ጊዜ የሶሪያ ሰራዊት ኤፍሬምን ይዞ ስለ ነበር ልባቸው “ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ “ (ቁጥር 2) ፡፡ አንድ መሪ ፍርኃትን በሚያደርግ ጊዜ የሚከተሉት ህዝቦችም ይፈራሉ ፡፡ ይሁን እንጂ የዳዊት የኪዳን ተስፋ በስፍራዉ እንደ ነበር ያስታዉሳሉ - ለዘላለም ይታገሳል ፡፡ ሊያድናቸዉ የሚመጣ አንድ ነበር ፡፡
እግዚአብሄር ለአካዝ ኢሳይያስን እና የኢሳይያስን ልጅ ያሱብ (“ ቅሬቶቹ ይመለሳሉ “ የሚል ትርጉም ያለዉ ) ላካቸው (ቁጥር 3) ፡፡ አካዝ “ በከበባ ጊዜ የኢየሩሳሌምን የዉሃ አቅርቦት ለመታደግ በከተማዋ የዉሃ መስኖ ስፍራ ነበር (2ዜና 32፡ 30) “ ፡፡ ኢሳይያስ አካዝን እንዲረጋጋና “ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶችን “ እንዳይፈራ ነገረው (ቁጥር 4) ፡፡ አክአዝ ለምን የሚፈራ መሆን የለበትም ? ምክንያቱም እግዚአብሄር ቀድሞ ራሱን “ የዳዊትን ቤት እንደሚጠብቅ “ ተስፋ ገብቶ ስለ ነበር (ኢሳ 26፡ 3) ፡፡ ረአሶን እና ሶሪያ ለራሳቸዉ ለመያዝ በይሁዳ ላይ ቢያሴሩም እግዚአብሄር ይህ እንዲሆን አይፈቅድም (ቁጥር 5-7) ፡፡ በቁጥር 8-9 ኢሳይያስ የመጀመሪያዉን ትንቢት ሰጠ - በ65 አመት ዉስጥ ፤ ኤፍሬም (የሰሜኗን መንግስት እስራኤልን ሰርተዉ ለነበሩት አስር ነገዶች የቆመው) እንደ ሕዝብ ለመቆም ላይችሉ ይበታተናሉ ፡፡ ይህ ተስፋ እና ትንቢት ሁለቱንም ነበር ፤ ይህ ትንቢት ስለ እስራኤል ጣዖት አምልኮ የተነሳ ነበር (ሆሴ 4፡ 17) ፡፡ ማክአርቱር “ በ65 አመት ዉስጥ ህዝብ ለመሆን የተረሱ ይሆናሉ መጀመሪያ ከክርስቶስ ልደት 722 በፊት በምርኮኝነቱ ዉስጥ ሲሆን በመቀጠል ከክርስቶስ ልደት 670 በፊት በምድሪቱ ዉስጥ በሌላ ሰዎች መኖር “ እንደሆነ ይገልፃል ፡፡ (2ነገ 17፡ 6, 17፡ 24, 2ዜና 33፡ 11, ዕዝ 4፡ 2) ፡፡ የአካዝ ምርጫዎች በጌታ ፀንቶ መቆም ወይም በሚመጡት ሰራዊቶች በምርኮ መዉደቅ ነበር ፡፡
ኢሳይያስ (7፡ 10-16)፡ በቁጥር 10-11 ሁለተኛዉ ትንቢት አካዝ እግዚአብሄርን እንዲጠይቀዉ በመንገር ይጀምራል ይሁን እንጂ አካዝ እምቢ አለ (ቁጥር 12) ፡፡ ማክአርቱር “ እምነቱን ለማበርታት እግዚአብሄር አካዝን ምልክት እንዳቀረበለት ነገር ግን አካዝ ምልክቱን ባለመቀበል ትህትናን ላለማድረግ ምክንያትን እንደፈጠረ “ ይገልፃል፡፡ ቀድሞም አካዝ ለእርዳታ ከኤፍሬም እና ከሶርያ ዉጪ ለሆኑ ሕዝቦች ጥሪን አድርጎ ነበር (2ነገ 16፡ 5-9) ፤ ኢሳይያስ ለአካዝ እንደ ገና ለዳዊት የተገባዉን የእግዚአብሄርን ተስፋ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ምላሽ በመስጠት አካዝን የይሁዳ እና የእግዚአብሄር ሰዎች ትዕግስት እየሞከረ እንደ ነበር ነገረው (ቁጥር 13) ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር እግዚአብሄር ምልክትን ይሰጣል - ስሙ አማኑኤል የሚባል ልጅን በምትወልድ አንድ ድንግል በኩል (ቁጥር 14) ፡፡
ኮንስታብል የዚህ ፅሁፍ የተለያዩ መረዳቶች ቀላል እንደሆኑ ይመዘግባል ፡፡ ኢሳይያስ ድንግል የነበረች ሁለተኛ ሚስት ነበረችው ፤ የኢሳይያስ የመጀመሪያ ሚስቱ ከሞተች በኋላ አሁንም ድንግል የሆነችዉ ሁለተኛ ሚስቱ ወንድ ልጅን ወለደች (8፡ 1-4) ፡፡ “ ድንግል “ ለሚለዉ የእብራዊ ቃል ያላገባች ወጣት ሴትን ነገር ግን ለጋብቻ በእድሜ የደረሰችን ሴት ያመለክታል ፡፡ ምናልባትም “ የኢሳይያስ ልጅ ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛ ቸኮለ መጀመሪያ የአማኑኤልን ትንቢት የሚያሟላ ነው ፤ በዕብራዊያን ማህበረሰብ ዉስጥ አንድ ያላገባች ለጋብቻ እድሜዋ የደረሰች ሴት ድንግል መሆን አለባት … ይሁን እንጂ ዕብራዊያን ለድንግልና ቤሁላ የሚል ቃል ስላላቸው የልጁ እናት ድንግል ነበረች ማለቱ ከሆነ ለምን ይህን ቃል አልተጠቀመም ? ምናልባትም ኢሳይያስ ከቤሁል ይልቅ አልማ የተጠቀመዉ በሚገባ የእናቲቱን ድንግልነት መናገር አልፈለገም ነገር ግን ይህ ቃል ከሁለቱም በአንዱም ድንግልነትን አያሳይም … እግዚአብሄር በማስረጃነት አልማ የሚለዉን ቃል እንዲጠቀም ስለመራው የተተነበየችዉ/የተመላከተችዉ ሴት ያላገባች ወጣት ሴት ወይም ድንግል ልትሆን ትችላለች ፤ ይህ የሁለት የመፈፀም እድልን ይፈቅዳል በኢሳይያስ ዘመን ስላለች አንድ ድንግል እና ከመቶ አመታት በፊት ስላላ አንድ ድንግል “ ፡፡ አምላክ በሰዉ ስጋ ላይ በመሆን የሰዉ እናት ሲኖረዉ ለእኛ ተስፋን ለመስጠት ወደ ምድር ላይ የላከው አባቱ እግዚአብሄር አለው (ዮሐ 4፡ 34, 5፡ 23-24, 30, 9፡ 4) ፡፡ ቁጥር 15-16 በአማኑኤል ምን እንደሚሆን የእግዚአብሄር ትንቢት ጊዜአዊ መፈፀም ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ በሚለዉ ቲዎሪይ ዋጋ የሚሰጥ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡
መደምደሚያ
ዋረን ዋይርስቤ “ የኦርቶዶክስ የአይሁድ ወንድ ልጆች በ12 አመታቸው የህግ ልጆች ይሆናሉ ፡፡ ይህ የተለዬ ልጅ ኤፍሬም እና ሶሪያ በሚቀጥሉት 12 አመታት ዉስጥ ከምስል ዉጪ እንደሚሆኑ ቀሪ/አስታዋሽ ነበር ፡፡ ኢሳይያስ ትንቢቱን ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ734 በፊት አደረሰ/ተናገረ ፤ ከክርስቶስ ልደት በ732 በፊት አሶር ሶሪያን ሲያሸንፍ ከክርስቶስ ልደት በ722 በፊት አሶር የሰሜን መንግስት ወረረ ፤ ትንቢቱም ተፈፀመ “ ፡፡ ያ ልጅ የሚመጣውየአማኑኤል ጥላ ሊሆን ይችላል - ቃል ስጋ በሆነ ጊዜ ፡፡
8 Richard Niessen, “The Virginity of the ‘alma in Isaiah 7:14,” Bibliotheca Sacra 137:546 (April–June 1980): 133–50; Paul D. Wegner, “How Many Virgin Births Are in the Bible? (Isa 7:14): A Prophetic Pattern Approach,” Journal of the Evangelical Theological Society 54:3 (September 2011): 467–84; quoted in Constable, pp. 74–75.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Isaiah, p. 68; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/isaiah.pdf.
Constable, p. 68.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 814.
Constable, p, 68.
Nelson’s Commentary, p. 815.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 768.
MacArthur, p. 768.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 19.
ጥያቄዎች
-
የኢሳይያስ ልጅ ስም ምርኮ ፈጠነ ብዝበዛም ቸኮለ ምን ማለት ነው ? (በመፅኀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ ወይም በኦን ላይ መፈለግ ያስፈልጋችኋል) ፤ በእርሱ ስም ዉስጥ የእግዚአብሄር የማስተማር አላማ ምንድን ነው ?
-
አካዝ ምን አይነት ንጉስ ነበር (2ነገ 16፡ 1-4) ? እግዚአብሄር ኢሳይያስን ለአካዝ እንዳይፈራ እንዲነግረዉ ለምን አዘዘው ? አካዝ ሁለቱን ወራሪ ነገስታቶች እንዴት አያቸው ? እግዚአብሄርስ እንዴት አያቸው ? ችግሮቻችሁን ወይም ሁኔታዎችን እንዴት እንደምታዩአቸው እና እግዚአብሄር እንዴት እንደሚያያቸው ተመልክታችኋል/አትኩራችኋል ?
-
በኢሳ (7፡ 10-11) እግዚአብሄር አካዝን ለምልክት እርሱን እንዲጠይቀው ለምን እንደነገረዉ ምን ታስባላችሁ ? የአካዝ ምላሽ ምን ነበር ? ኢሳይያስ ለአካዝ ምላሽ እንዴት ምላሽ ሰጠ ?
-
አካዝ ለአንድ ምልክት ለመጠየቅ እምቢ አለ ፤ ምንም ይሁን ምን የሚሰጠዉ የእግዚአብሄር ምልክት እና ምላሽ ምን ነበር (ማቴ 1፡ 23) ?
-
በኢሳይያስ 8 ኢሳይያስ ከጌታ ለህዝቡ ምን ተናገረ ? ሰዎቹ በሚፈልጉት እና እግዚአብሄር በሚፈልገዉ መካከል ልዩነቱ ምን ነበር (ኤር 37፡ 13-15) ?
-
ኢሳ (8፡ 14) ለእስራኤል እና ኢየሱስን እንደ መሲህ በቀጠለዉ አለመቀበላቸው አዲስ ኪዳን እንዴት ይተገብረዋል ? (ሉቃ 2፡ 34, ሮሜ 9፡ 32-33, 1ጴጥ 2፡ 8)
-
በኢሳይያስ (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳቸው (አሳያቸዉ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Isaiah 7:14
“Therefore, the Lord Himself will give you a sign: The virgin will conceive, have a son, and name him Immanuel.”
ንጉሥ አካዝ ራሱን በጣም በተካረረ የፓለቲካ አጣቢቂኝ ውስጥ አገኘ ፡፡ ዛፍም በንፋስ እንደሚወዛወዝ ሁሉ የአካዝም ልብ እንዲሁ ተናወጠ ፡፡ ይህን ስሜት ታውቁታላችሁን ? ስለ ሆነ ሁኔታ ተጨንቃችሁ ታውቃላችሁን ወይም ደግሞ በፊታችሁ ያለውን ውጊያ እንዴት እንደምታሸንፉ ግራ ገብቷችሁ ያውቃል ? ኢሳይያስ ደጋግሞ ለንጉሥ አካዝና ለህዝቡ እንዲህ በማለት ጠንካራ ትዕዛዝን አስተላለፈ ፡- አትፍሩ ፡፡ በእምነታችሁ ጸንታችሁ ካልቆማችሁ ፈጽማችሁ መቆም አትችሉም ፡፡ ከሰራዊት ቅዱስ እግዚአብሔር ውጪ ለሆነ የሰው ኃይል አትፍሩ አትሸበሩም ፡፡ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ሊፈራና ሊከበር የሚገባው ፡፡ እግዚአብሔርም ቅድስናችሁ ይሆናል ፡፡ በመጨረሻ ኢሳይያስ እንዲህ አለ ፡- “ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ። “
ኢሳይያስ ቀድሞ እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሰዎች ጋር እንድሆን ወደ አለም እንደሚልከው እያጠቆመ ነበረ ፡፡ አማኑኤል ማለት ፡- “ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር “ ማለት ነው ፡፡ ስለዚህም ህዝቡ ሰውን መፍራትም ሆነ ስለ ሰው መሸበር የለባቸውም ፡፡ የሚስፈልጋቸው የተአምራት አምላክ የሆነውን መታመን ብቻ ነው ፡፡ ለእናንተም ይህ እውነት ነው ፡፡ ልክ ዛፍ በንፋስ እንደሚወዛወዝ ሁሉ ህይወታችሁንም እንዲሁ እያናወጠ ስላለ የትኛውም ነገር አስቡ ? ይህንን አስታውሱ ደግሞም ልብ አድርጉ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው ፡፡ እሱ የተአምራት አምላክ ነው ፡፡ በእምነታችሁ ጸንታችሁ ቁሙ ፡፡ እግዚአብሔር አይቷችኋል ፡፡
“ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ። “
- ኢሳይያስ 7፡14
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 7:2, 4 — “ ለዳዊትም ቤት ፦ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል የሚል ወሬ ተነገረ ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ …….. እንዲህም በለው ፦ ተጠበቅ ፥ ዝምም በል ፤ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች ፥ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፥ ልብህም አይድከም ። “
ኢሳይያስ 8:12b–14a — “ መፈራታቸውንም አትፍሩ ፥ አትደንግጡ ። ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን ። እርሱም ለመቅደስ ይሆናል ፡፡ “
ዮሐንስ 5:23 — “ ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ፥ ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።