Major Prophets Isaiah

Isaiah's Call and Mission

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 576 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የኢሳይያስን ጥናት ስንቀጥል ወደ ደቡቡ መንግስት ወደ ይሁዳ በተለይም ስለ ይሁዳ እና ቢንያም ነገድ እና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ እየተናገረ እንደ ነበር እናስታውሳለን ፡፡ ነቢያቶች የወቅቱን ሁኔታ በመመርመር መልካሞች ነበሩ፡፡ እዚህ ስፍራ ላይ በኢሳይያስ ንግግር የጊዜ መዋቅሩ በግምት ከክርስቶስ ልደት 740 እስከ 680 በፊት ስለሆነ ለመሲሁ እንዲመጣ ወደታች መቆጠሩ የተጀመረ ነበር ፡፡ በተጨማሪም ኢሳይያስ ለክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት አሳመረ ፤ ነገር ግን ትናትና እንደተወያየነው ኢሳይያስ ስለ ሚሊኒዮም ጊዜ አዉርቷል ፡፡ ኢሳይያስ እግዚአብሄር ሰጥቶት የነበረዉን መልዕክት ተናገረ ፡፡ ለዚህ መፅኀፍ አንድ ቃላችን በኢሳ (7፡ 14) እንዳገኘነው “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ የሚል ትርጉም ያለዉ አማኑኤል የሚል ነው ፡፡ በዚህ ፍርድ ይኖራል ፤ በምዕራፍ 1 በእግዚአብሄር እና በእግዚአብሄር ልጆች መካከል ስለ ነበረዉ ነገር አይተናል ፡፡ በምዕራፍ 2 ኢሳይያስ ስለ ሚሊኒዮም በረከት አዉርቷል፡፡ ከኢሳ (2፡ 6- 4፡ 1) ነቢዩ ስለ ፍርድ አዉርቷል ፤ ከኢሳ (4፡ 2-6) ወደ ሚሊኒየሙ በረከት ተመለስ ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (5፡ 1-2)፡ ኢሳይያስ ስለፍርድ ዝማሬን/ቅኔን አካትቷል ፡፡ በዚህ መፅኀፍ ዉስጥ ማርቆስ ኮፒላንድ “ የተወደደች የወይን ተክል እና ከበርኃ ፍሬን አገኘ “ አለ ፡፡

ኢሳይያስ (5፡ 3-7)፡ የጌታ ፍርድ ተስፋ ተብቶ ነበር፣ እግዚአብሄር የወይኑን ስፍራ የሚያጠፋ ነበር ፡፡ ቁጥቋጦዋን በማስወገድ ቅጥርዋን ያፈርሰዋል በእርሷ ላይ የሚወርደዉን ዝናብ ስለሚያቆመው የሚቃጠል፣ የማይኮተኮት እና እንደ ባድማ ምድር ሆኖ ይቀራል (ቀጥር 3-6) ፡፡ በመጨረሻም ኢሳይያስ ስለ ባቢሎናዊያን ምርኮኝነት እየተናገረ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ለሕዝቦቹ የተሸለዉን ነገር ቢመርጥም ሌላ ነገርን መረጡ (ቁጥር 7) ፡፡ የኢሳይያስ መልዕክት ዛሬም ለእኛ እዉነት ነው ፤ እግዚአብሄር ለእኛ ምርጡን ነገር ይፈልጋል፣ በእኛ ላይ ሊያፈሰዉ/ሊያመጣዉ ይፈልጋል ፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ጌታን ሳናማክር እንኳን የራሳችንን መንገድ እንመርጣለን ፡፡ በህይወት ዘመናችን ሀገራዊ የእግዚአብሄርን እንቅስቃሴ አላየንም - ባድማ የወይን ስፍራ ሆነናል ?

ኢሳይያስ (5፡ 8-25)፡ ዋረን ዋይርስቤ፡- እንደ ተመኚ (ቁጥር 8-10)፣ እንደ ስካር (ቁጥር 11-17)፣ ትኩረት እንደ ማጣት (ቁጥር 18-19)፣ እንደ ማታለል (ቁጥር 20)፣ እንደ ትዕቢት (ቁጥር 21) እና ፍትህን እንደሚያጓድሉ (ቁጥር 22-25 ) እንደ መደባቸዉ ኢሳይያስ ስድስት አስከፊ ነገሮችን ሰጥቷል ፡፡ እነዚህ ነገሮች ወደ አካላዊ ባሪያነት በመምራት ወደ መንፈሳዊ ባሪያነት ሊመሩን ይችላሉ ፡፡ እስራኤል የእግዚአብሄርን ቃል ስላልተቀበለች (ቁጥር 24) የእግዚአብሄር ቁጣ በእነርሱ ላይ ነደደ (ቁጥር 25) ፡፡ የእግዚአብሄር እጅ የተነሳች እና ለመምታት የተዘጋጀች ነበረች - ይህን ፍርድ ለማምጣት ሁልጊዜ የተዘጋጀ ነበር ፡፡

ኢሳይያስ (5፡ 26-30)፡ በመቀጠልም ኢሳይያስ አሕዛብ ሁሉ የእስራኤልን ቤት ለመዉረር እና ቤቷን ለማንፃት ይመጣለ አለ ፡፡ እግዚአብሄር አቁም የሚለዉን በተን በመጫን ሕዝቡን ወደ 70 አመት የምርኮ ጊዜ ይልካቸዉ ፡፡

ኢሳይያስ (6፡ 1-8)፡ ኢሳይያስ የእግዚአብሄርን ራዕይ በማየት የገጠመዉን በመግለፅ ተገቢነቱን መሰረተ (ቁጥር 1) ፡፡ የገጠመዉን ነገር ጳዉሎስ በ 2ቆሮንቶስ 12 ላይ ከገለፀዉ ጋር ማወዳደር ይችላል ፡፡ 52 አመታት ከገዛ በኋላ ከክርስቶስ ልደት 739 በፊት ለምፅ/የቆዳ በሽታ ለዖዝያን ሞት ምክንያት ሆነ ፤ በሞተም ጊዜ ጌታ በኢሳይያስ በኩልትንቢታዊ ቃልን ተናገረ ፡፡ ማክአርቱር “ ነቢዩ ለእርሱ የተገለጠለትን እግዚአብሄርን በማየት ዉጪ ባለዉ አለም ላይ የማያስብ ሆነ “ በማለት ይናገራል ፡፡ ሱራፌል እንዴት እንደሚመስል እና ምን እንዳሉት ገለፀ (ቁጥር 2-3) ፤ ይህ ራዕይ ከራዕ (4፡ 8) ጋር ሊወዳደር ይችላል ፡፡ የሱራፌልም ምስጋና ለመሰረቱ መናወጥ እና ለቤተ መቅደሱ በጢስ ለመሞላት ምክንያት ሆነ (ቁጥር 4) ፡፡ ኢሳይያስ የእርሱ ብቁ አለመሆንን/ዋጋ ቢስነትን ከእግዚአብሄር ብቁነት ጋር ያለዉን ልዩነት አስተዋለ (ቁጥር 5) ፡፡ ኢዮ (42፡ 6) ተመሳሳይ መልክን ይገልፃል ፤ በሉቃ (5፡ 8) ጴጥሮስ ተመሳሳይ ሀሳብን ገልፆአል ፡፡

ከእግዚአብሄር መገኘት ጋር በምንገናኝ ጊዜ እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ ? ይሁዳ የእግዚአብሄርን ቅዱስነት መረዳታቸዉን አጥተዉ ስለ ነበር ኢሳይያስ ይህ ራዕይ ተሰጠው ፡፡ ከሱራፌልም አንዱ ከመሰዊያው ላይ ፍም ለመዉሰድ ጉጠትን ተጠቀመ (ቁጥር 6) ፤ ማክአርቱር ይህ በራዕ (8፡ 3-5) እንደተገለፀው በሰማይ ላይ የዕጣኑ መሰዊያ ነበር አለ ፡፡ ሱራፌልም የኢሳያስን አንደበት በፍም እሳት በመንካት የኢሳይያስን መርገም አነፃ ኃጢዓቱንም አስተሰረየለት (ቁጥር 7) ፡፡ ማክአርቱር ይህን ጥቅስ ለጌታ ለተለዬ አገልግሎት መንፈሳዊ መንፃትን እንጂ የድነትን ማግኘትን እንደማይገልፅ ተናግሯል ፡፡ ይህ አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር ቃሉን ለሕዝቡ እንዲናገር ለኢሳይያስ እየሰጠዉ ስለ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ልጆቼ የሚጠነቀቅ ማን መላክ እችላለሁ በማት ጮኾ ጠየቀ (ቁጥር 8) ኢሳይያስም “ እኔን ላከኝ “ በማለት መለሰ ፡፡ ጌታም የኢሳይያስን ምላሽ ለመስማት ፈለገ - እንዲሁም ለእርሱ ምላሻችንን ለመስማት ይፈልጋል ፡፡

ኢሳይያስ (6፡ 9-13)፡ እግዚአብሄር ኢሳይያስን እርሱን ለተዉት ሕዝቦች መልዕክትን ሰጠው ኢሳይያስም ለምን ያክል ጊዜ ስለዚህ እንደተናገረ ጠየቀ (ቁጥር 9-11) ፡፡ የእግዚአብሄር ጥሪ በኢሳይያስ ህይወት ላይ የተገፋዉን መልዕክት እንዲናገር ነበር ፡፡ ሕዝቡ በራሷቸዉ መንገድ/ርቀዉ ሄደዉ ስለ ነበር እግዚአብሄር ኢሳይያስን ይህን መልዕክት ከተሞቹ እስኪጠፉ፣ ብቻቸዉ እስኪቀሩ እና መኖሪያ እስከማይሆኑ ድረስ ይናገራል አለ (ቁጥር 11-12) ፡፡ እንደ ገና ኢሳይያስ ወዲያዉኑ በመመለስ ስለ ሚመጣዉ የባቢሎን ምርኮ እየተናገረ ነበር ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር በትንሽዬ ተስፋ አጠቃለለ ፡፡ ቅሪቶች እንደሚቀሩ ተስፋን ገብቷል - የሕዝቡ አንድ አስረኛ በምድራቸዉ ላይ ይቀራሉ (ቁጥር 13) ፡፡ ቅዱስ ዘር “ በመስማት እና በማመን ማዕከል የሚሆኑት በእስራኤል የታመኑትን ቅሬቶች ይወክላል “ ፡፡ እስራኤላዊያን አማኑኤል እንደሚመጣና እግዚአብሄር ወደ ምድሪቱ ለመመለስ እና እግዚአብሄር የጀመረዉን መልሶ ለማቋቋም የቀሩትን እንደሚጠቀምባቸዉ ያምናሉ ፡፡

መደምደሚያ

ይህ ኢሳይያስ 5 እና 6 ይሸፍናል እንዲሁም ነገ እንቀጥላለን ፡፡

  1. Mark A. Copeland, The Book of Isaiah, (ExecutableOutlines.com, 2006), p. 11. Available from https://executableoutlines.com/pdf/isa_se.pdf.

  2. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2007), p. 1159.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 765–766.

  4. MacArthur, p. 766.

  5. MacArthur, p. 766.

  6. MacArthur, pp. 766-767

ጥያቄዎች

  1. በኢሳ (5፡ 20) የተገለፁት አሳዛዥ ሁኔታዎች አሁን ከሚሆነዉ ነገር ጋር ተመሳሳይ ነገር ይናገራሉ ? እንዴት አድርገው ?
  2. በግል አስተያየታችሁ በኢሳ (6፡ 2) ሱራፌል በእግዚአብሄር ፊት አይኖቻቸዉን እና እግሮቻቸዉን ለምን ሸፈኑ ?
  3. በኢሳ (6፡ 8) የጌታ ድምፅ “ ማንን እልካለሁ ? ማንስ ይሄድልናል ? “ በማለት ሲጠይቅ ኢሳይያስም “ እነሆኝ እኔን ላከኝ “ አልሁ ፤ ለጌታ “ እነሆኝ እኔን ላከኝ/ተጠቀምብኝ “ ብላችሁ ታውቃላችሁ ? አይደለም ከሆነ እንዳትሉ ወደ ኋላ ምን ያዛችሁ ?
  4. በኢሳይያስ (5-6) በጥናት ወይም በትምህርት መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 6:8

“Then I heard the voice of the LORD saying: Who should I send? Who will go for Us? I said: Here I am. Send me.”

እግዚአብሔር ነቢዩ ኢሳይያስን ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም የፍርድን መልዕክት ይናገር ዘንድ ጠራው ፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ፊታቸውን ዘወር ወዳደረጉ ሰዎች ሄዶ የሚናገርለት የሆነ ሰው ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ በማለት ይጣራል “ ማንን ልላክ ? ማንስ ይሄድልናል ? “ ኢሳይያስም የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምቶ “ እኔ አለሁኝ ፣ እኔን ላከኝ “ በማለት መለሰ ፡፡

እግዚአብሔር ሰዎችን ለተለየ ኃላፊነት ይጠራል ፡፡ እግዚአብሔር በሚጣራበት ጊዜ ለድምጹ ምላሽ ይፈልጋል ፡፡ መጀመሪያ ራስህን ጠይቅ ፡ - የእግዚአብሔርን ድምጽ እየሰማሁ ነውን ? ከዚያም ለሰማሁት የእግዚአብሔር ድምጽ ምላሽ እየሰጠሁ ነውን ? ፍቃደኛ ከሆንክ ለእግዚአብሔር ድምጽ ምላሽ ስጥ ፡፡ እኔ አለሁኝ እኔን ላከኝ በል ፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም እንዲትሆን አይፈልግም ፡፡ እርሱ የአንተን ብርታትህንም ሆነ ያለህን የቆየ ልምድ አይፈልግም ፡፡ እግዚአብሔር የአንተን ፍቃደኝነት ይፈልጋል ፡፡ እርሱ በድካም ፣ በትህትና እናም በጉድለት በደንብ ይሰራል ፡፡ እርሱ በኃይሉ ይፈጥራል ፣ ይሰራል ፣ ያበረታል ደግሞም ያበዛል ! ተመሳሳይ ነገር ከሰማህ ደግመህ ደጋግመህ በለው ወይም ስለሆነ ነገር ሸክም ከተሰማህ ወይም የሆነ ሰው በልብህ ከተመላለሰ ፣ እግዚአብሔርን እንዲህ በለው “ ጌታ ሆይ እኔ አለሁ ፣ እኔን ላከኝ ፡፡ “ እንድ ጊዜ ፈቃደኛ መሆንህን ከሰማ እርሱ ቀጣዩን እርምጃ ያሳውቅሃል ፡፡

“ የጌታንም ድምፅ፦ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም፦ እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ ። “

  • ኢሳይያስ 6፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ዘጸአት 35:5 — “ ከእናንተ ዘንድ ለእግዚአብሔር ቍርባንን አቅርቡ፤ የልብ ፈቃድ ያለው የእግዚአብሔርን ቍርባን ያምጣ ፤ ወርቅና ብርም ናስም “

1ኛ ዜና 29:9 — “ ሕዝቡም ፈቅደው ሰጥተዋልና ፥ በፍጹም ልባቸውም ለእግዚአብሔር በፈቃዳቸው አቅርበዋልና ደስ አላቸው ፤ ንጉሡም ዳዊት ደግሞ ታላቅ ደስታ ደስ አለው ። “

2ኛ ዜና 8:12 — “በጎ ፈቃድ ቢኖር ፥ እንዳለው መጠን የተወደደ ይሆናል እንጂ እንደሌለው መጠን አይደለም ። “