Major Prophets Isaiah

Zion's Future Glory

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 575 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ከትናትናዉ እንደ ዳሰሳ ነቢዩ ኢሳይያስ በተለዬ ለደቡቡ መንግስት ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ራዕይ ነበረው ፡፡ ከባቢሎን ግዞታቸዉ በፊት ወዲያዉኑ መጣ (ምዕራፍ 1) እንዲሁም ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም መታደስም ነበር (በምዕራፍ 2) በተጨማሪም ስለ ፂዎን ፍርድ እና ክብር ነው (ምዕራፍ 3-4) ፡፡ ቃላችን ለኢሳይያስ ኢማኑኤል ሲሆን እግዚአብሄር በሰዉ ስጋ እንደሚታይ ነበር ፡፡

ትናትና በሰዎስት ክብ ቀለበቶች ኢሳይያስን አይተነዋል/ስለነዋል ፡፡ የመጀመሪያዉ ዙር በአሶሪያዊያን እና በባቢሎናዊያን በሚመጣዉ ስደት ከጌታ የመጣዉን የይሁዳን የወቅቱን ሁኔታ ጥናትን ይወክላል ፡፡ ሁለተኛው ዙር በአንዲት ድንግል የኢማኑኤልን የመጀመሪያዉን መምጣት ይወክላል (ኢሳ 7፡ 14) ፡፡ ሰዎስተኛዉ ዙር የመሲሁን ሁለተኛ ጊዜ መምጣትን እና ሚሊኒየምን የሚወክል ነው ፡፡

በምዕራፍ 2 ኢሳይያስ እስራኤላዊያንን ጥፋተኞች እንደ ነበሩ ነገር ግን የጌታ ሰላም እየመጣ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 1-4) ፤ ይህ የተስፋ መልዕክት ነበር ፡፡ በመቀጠልም ኢሳይያስ ተመልሶ በመሄድ ስለሚመጣዉ ፍርድ እስከ ኢሳ (4፡ 2) ድረስ ይቀጥላል ፡፡ በምዕራፍ 3 የፍርዱ ዉይይት ይቀጥላል ፤ ማርቆስ ኮፔላንድ ምዕራፍ 3 እንደሚከተለዉ ያቀርበዋል፡

  1. የመልካም መሪነት መወገድ፡
  • ጌታ ሕዝቡን የሚያቀርብለትን ብቻ ሳይሆን መልካም አስተዳዳሪዎችንም ይከለክላቸዋል(3፡ 1-7)
  • የይሁዳና የኢየሩሳሌም ብልሹ የሆነዉ ክፋታቸው እንዲወድቁ ምክንያት ይሆናቸዋል (3፡ 8-9)
  • ለፃድቁ መልካም ይሆንለታን ለኃጢዓተኛዉ ግን አይደለም (3፡ 10-11) ፡፡
  • ደካማ መሪዎች ለሕዝቡ ይሰጣሉ ስልጣናቸዉን ያለአግባብ የሚጠቀሙ መሪዎች ይፈረድባቸዋል 3፡ 12-15
  1. ሴቶቹን እና የሚመጣዉ አሳዛኝ ክስተትን፡
  • ፍርድ ስለ እብሪታቸዉ እና ስለ ከንቱነታቸዉ በእነርሱ ላይ ይመጣል (3፡ 16-17) ፡፡
  • ማጣታቸዉ የሚያስከትለዉን ዝርዝር መግለጫ (3፡ 18- 4፡ 1)
  • ጌታ የጌጥ ልብሳቸዉን ከእነርሱ ይወስደዋል ፡፡
  • ወንዶቻቸዉ በሰይፍና በጦር ይወድቃሉ ፡፡
  • ዘለፋቸዉን ለማስወገድ ብቻቸዉን መቅረት እና ተስፋ መቁረጥ ፡፡

ወንዶቹ በሰይፍ ከመዉደቃቸዉ የተነሳ የወንዶች እና የሴቶቹ የቁጥር ስሌት በሴቶች ቁጥር መብለጥ ያልተመጣጠነ ስለሚሆን (ቁጥር 25) ሴቶቹ ከእነርሱ ዉጪ ብቻቸዉን የሚኖሩ ይሆናሉ (ቁጥር 26) ፡፡ ይህ ለምዕራፍ 4 መነሻነትን ይሰጣል ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (4፡ 1)፡ ኢሳይያስ ትንቢት ተናግሮአቸዉ በምዕራፍ 3 ከሚሆኑት ሁለ የተነሳ ሴቶች ልጆች ሊኖራቸዉ እንደማይችል እና በዚያም ያፍራሉ ፤ ስለዚህም በቁጥር 1 ኢሳይያስ “ በዚያ ቀን “ “ የሚታበዩት የኢየሩሳሌም ሴቶች ለልጆቻቸዉ አባት እንዲኖራቸዉ እና ዘለፋቸዉን እንዲያስወግድ ይለምናሉ - እዉነቱ ልጆች ስለሌላቸዉ ነው ፡፡ አብዛኞቹ የኢየሩሳሌም ወንዶች ከተማቸዉን በመጠበቅ ሂደት ዉስጥ ስለሞቱ (3፡ 25) “ ፡፡

ኢሳይያስ (4፡ 2-6)፡ በቁጥር (2-6) ኢሳይያስ የሚሊኒየሙን በረከት ሰጠ ፡፡ ቁጥር 2 “ ወደ ፊት በምድር ላይ ስለሚገለጠዉ የጌታ ክብር (ቁጥር 2፡ 2-4) “ ስለሚናገረው “ በዚያም ቀን “ በሚለዉ ይጀምራል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የፂዎን መታደስ ሰዎስት ክፍል እንዳለዉ ይገልፃል፡ 1) የጌታ ቁጥቋጦ ለክብር ይሆናል (ቁጥር 2)፣ 2) ቅሬቶቹ ይነፃሉ (ይፀድቃሉ) (ቁጥር 3, 4) እና 3) ጌታ በፂዎን ተራራ ላይ የሚጠብቅ መጋረጃን ይሰጣል (ቁጥር 5, 6) “፡፡ ዋይርስቤ “ የጌታ ቁጥቋጦ ከዚያ ቀን በማለፍ በምድር ላይ መንግስቱ እስክትመሰረት ድረስ እንደሚያልፍ “ እና “ ከዳዊት ስሮዉ መንግስት ከሞተዉ ማህተም የመጣ ለሚመስለዉ ለኢየሱስ ክርስቶስ መሲሀዊ ስያሜ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፡፡ “ የምድሪቱ ፍሬ “ የእስራኤልን ቅሪቶች ያመለክታል ፡፡

የጌታ ቁጥቋጦ ይመጣል በዚህም ሂደት የሚያምር ይሆናል ፡፡ ይህ የሚመሰረተዉ የመሲሁ መንግስት እዉነተኛ መልክ ነው (ኢሳ 11፡ 1, 53፡ 2, ኤር 23፡ 5) ፤ ቁጥቋጦው እንዲሆን የምንጠብቀዉን አይሆንም ፡፡ ኢየሱስ ከእኛ ጋር እና ያ መልዕክት የቅሪቶቹ እንደሆነ ከያዙት ጋር ለመሆን ይመጣል ፡፡ ማክአርቱር “ ቅዱስ በዚያ ቀን የእግዚአብሄርን ብልፅግና የሚወርሱትን ቅሬታዎች የሚገልፅ ሌለኛዉ መንገድ “ እንደሆነ ያመለክታል (ቁጥር 3) ፡፡ ዮሐ (15፡ 4-5) ፍሬን ለማፍራት እንደ ቅርንጫፍ መቀመጥ እንዳለብን ይናገራል ፡፡ ኢሳይያስ 4 የዮሐ (15፡ 4-5) ጥላ ነው ፡፡ ሁሉም ታላላቅ ነቢያቶች ወደ ቅርንጫፎች አመልክተዋል (ኤር 33፡ 15, ዘካ 3፡ 8, 6፡ 12) ፤ ይህ ሁሉ ምርኮኝነት እየመጣ እንደነበር ወደሚለዉ እዉነት ይስባል ነገር ግን ከዚያ ምርኮኝነት የሚያወጣ ተስፋ የሚያመጣ አለ - ስሙ ቅርንጫፍ የሹዋ መሲሁ ኢየሱስ ነው ፡፡

ስለዚህም ቅርንጫፉም የፂዎንን ሴት ልጆች ቆሻሻ ያጥባል ኢየሩሳሌምንም ያነፃል (ቁጥር 4) ፤ ይህ በመንፈስ የማንፃት ጊዜ እና በመንፈስ የማቃጠል ጊዜ(ሁለተኛዉ የመምጣት የመከራዉ ጊዜ) ነው - የእግዚአብሄር የእሳት ፍርድ ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር “ በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤአቸዉም ላይ በቀን ዳመናንና ጢስን በሌሊትም የሚቃጠለዉን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል “ (ቁጥር 5) ፡፡ የእግዚአብሄር ጥላ ክብሩን ይሸፍነዋል በዚያም ቀን ጊዜ ጎጆ ጥላን ሲሰጥ መጠለያም ከማዕበል እና ከዝናብ ይጠብቃል (ቁጥር 6) ፡፡

መደምደሚያ

ሁሉም ሰዉ የእግዚአብሄርን መገኘት ያየዋል ፡፡ ጥያቄዉ በየትኛዉ ጎን ላይ ነን ? በቀደመዉ በኢሳይያስ ዉይይታችን እግዚአብሄር ሰዎችን ይኖሩበት ከነበረዉ ህይወት - ተገቢ ካልሆነዉ፣ ዝሙት ከነበረዉ፣ አመንዝራነት ከሆነዉ፣ ጣዖት አምላኪነት እና ከንቱ ከነበረዉ ህይወት በመጥራት ወደ ቅርንጫፉ ብቻ የሚመለከቱ ከሆነ ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ እንደሚያወጣቸዉ ነገራቸው ፡፡ እግዚአብሄር ፍርዱን እና በረከቱን ይጠብቃል ፡፡ የትኛዉን ለማየት/ለመቅመስ ትፈልጋላችሁ ? እኔ የእግዚአብሄርን በረከት መቅመስ እፈልጋለሁ ፡፡ በረከቱ በመሲሁ በኢየሱስ በኢማኑኤል ብቻ በኩል ሊመጣ ይችላል ፡፡

  1. Mark A. Copeland, The Book of Isaiah: Student Edition, pp. 12–13; available at executableoutlines.com.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 810.

  3. Nelson’s Commentary, p. 810.

  4. Nelson’s Commentary, p. 810.

  5. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 2002), p. 16.

  6. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 764.

ጥያቄዎች

  1. በመፅሀፍት የኢሳ (3፡ 4) መፈፀምን የት ላይ ታዩታላችሁ ? (2ነገ 21፡ 1, 22፡ 1, 24፡ 8)
  2. ኢሳ (3፡ 8) ይሁዳን እስራኤል “ ንግግራቸዉ እና ተግባራቸዉ ከእግዚአብሄር የራቀ ስለ ነበር “ እንደሚወድቁ ይናገራል ፤ ፀኃፊዉ በዚያ ምን እያለ ነው ? በዚህ ባህሪይ ጥፋተኛ የሆነ ሰዉ ታውቃላችሁ ? በምን መንገድ?
  3. “ የጌታ ቅርንጫፍ “ ማን ነው (ዮሐ 15፡ 1-2) ?
  4. ኢሳ (4፡ 2-6) በምታነቡ ጊዜ ስለሚመጣዉ መከራና በክርስቶስ አገዛዝ ጊዜ ስለ ኢየሩሳሌም ይናገራል ብላችሁ ታምናላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታምኑም ?
  5. በኢሳይያስ (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 4:2–3

“On that day the Branch of the LORD will be beautiful and glorious, and the fruit of the land will be the pride and glory of Israel’s survivors. Whoever remains in Zion and whoever is left in Jerusalem will be called holy—all in Jerusalem who are destined to live.”

እግዚአብሔር ምህረትን በሰጠ ጊዜ ልክ እንደ ይሁዳ ሁሉ እስራኤልም በፍርድና በቁጣ ውስጥ ነበረ ፡፡ እግዚአብሔር ወዶ ይምራችኋል ፡፡ ምናልባት ከሁሉም ነገር ጋር ደግሞም ከሁሉም ሰው ጋር መስማማት እንዳልቻላችሁ ሁሉም ነገር እንደተበላሸባችሁ ይሰማችሁ ይሆናል ፡፡ ደግሞም እንዲሁ ሰላምን ለማግኘትም በአይናችሁ የምትፈልጉት የትኛውም ነገር እንዲሁም የትኛውም ሰው ከአይናችሁ ጠፍቶም ይሆናል ፡፡ ሆኖም ነገሩ ምንም ይሁን ፣ ይህን አስታውሱ እግዚአብሔር ከጎናችሁ አለ ፡፡ እርሱ ጸጋና ምህረትን ይሰጣችኋል ፡፡ እርሱ የሚምር ይቅር የሚል አምላክ ነው ፡፡ እርሱ በጭንቅ ጊዜ በጨለማ ጊዜ ወዳጅ የሚሆን አምላክ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ክብሩን የሚገልጠው በዚህ የምህረትና የጸጋ ስፍራ ላይ ነው ፡፡

እስኪ አስቡት በባህር ዳርቻ ላይ ጨለማ የሆነ አስፈሪ ቀን ፡፡ ልክ ለጸሀይ መውጣት ምንም ተስፋ እንደሌለ ሲሰማችሁ ፤ ብርሃን ከደመና ኋላ ሲፈነጥቅ ! ቀና በማለት ወደ ጸሀይ ብርሃን በደስታ ስትራመዱ እንድሁም ከፊታችሁ የሚያምር ቀን እንዳለም ተስፋ ስታደርጉ ፣ ቀኑም እንደተዋጀ ሲመሰክር ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በህይወታችሁ ያላችሁን ተስፋ ሁሉ እንደጨረሳችሁ ሲሰማችሁ ፤ መዳረሻችሁ እንደጠፋ ሲሰማችሁ ይህን አስታውሱ እግዚአብሔር በጨለማችሁ ላይ በተስፋ መቁረጣችሁ ላይ ጸጋና ምህረትን ያበራላችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ተስፋ አይቆርጥም ፡፡ አይኖቻችሁን ከፍታችሁ ለህይወታችሁ የርሱን የሚዋጅ ፍቅር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ተቀበሉ ፡፡ ኢየሱስ ከባርነት ነጻ ያወጣችኋል ፡፡ እርሱ ከህይወት ማዕበል ወጀብ መሸሸጊያና መጠለያ ይሆንላችኋል ፡፡ በእርሱ አይኖች ተወዳችኋል ፡፡ ዛሬ አይኖቻችሁን ክፈቱና ለህይወታችሁ የርሱን ብርሃንና ክብር ተቀበሉ !

“ በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ለጌጥና ለክብር ይሆናል ፥ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱ ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል ። በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፥ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፥ ቅዱስ ይባላል ። “

  • ኢሳይያስ 4፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 130:3–4 — “ አቤቱ ፥ ኃጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል ? ይቅርታ ከአንተ ዘንድ ነውና ። “

ኢሳይያስ 3:1 — “ እነሆ ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን ፥ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውኃውንም ድጋፍ ሁሉ ፡፡ “

ኤፌሶን 1:7–8 — “ በውድ ልጁም ፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን ፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ። “