Major Prophets Isaiah

Judah On Trial

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Immanuel Isaiah 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 574 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የታላላቅ ነቢያትን ከኢሳያስ መፅሀፍት ማጥናት ስንጀምር በዚያን ጊዜ ስለ ወቅቱ ስለ እስራኤል ሁኔታ፣ ስለ ክርስቶስ መጀመሪያ መምጣት እና ስለ ሁለተኛ ክርስቶስ መምጣት ትንቢቶችን እናያለን ፡፡ ኢሳይያስን ስናጠና ከእነዚህ ጊዜያት ዉስጥ በየትኛዉ እያወራ እንደ ነበር ወይም በአንድ ላይ ስለ ሰዎስቱም እያወራ እንደ ነበር እናተኩራለን ፡፡ ኢሳይያስ ማለት “ ጌታ መድኃኒት ነው “ ማለት ሲሆን የስሙ ትርጓሜም የሚለዉን ሁሉንም ነገር ያሳያል ፡፡ በፅሁፉ ዉስጥ ኢሳይያስ ያለማቋረጥ “ ከእግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው “ ማለት ወደ ሆነዉ ወደ አማኑኤል ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡ በኢሳ (7፡ 14) እንደ አንድ የገና ትንቢት ታዋቂ የሆነ ነው፣ እግዚአብሄር ድንግል እንደምትፀንስ ወንድ ልጅን እንደምትወልድ ስሙንም አማኑኤል እንደምትለዉ ተስፋን ገብቷል ፡፡

ኢሳይያስ ስለ ይሁዳ እና ስለ እስራኤል በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝ እና በሕዝቅያስ (በሁሉም የይሁዳ) ራዕይ ያየዉ የአሞፅ ልጅ ነበር (ኢሳ 1፡ 1) ፡፡ በሳዖል፣ በዳዊት እና በሰለሞን (በሁሉም በእስራኤል ነገስታት) ስር መላዉ አገር አንድ ነበር ፡፡ ከሰለሞን ሞት በኋላ መንግስቷ ወደ ሰሜን እና ወደ ደቡብ መንግስት ተከፈለች ፡፡ የሰሜኑ መንግስት አስሩን ነገድ ሲይዝ የደቡቡ ደግሞ ይሁዳን እና ቢንያምን ያያዘ ነበር ፡፡ መሲሁ በይሁዳ የዘር መስመር በኩል ይመጣል ፤ መንግስቱ ከተከፈለ በኋላ ነቢያቶች ወደ ሁለቱም መንግስታት መናገር ጀመሩ ፡፡ የኢሳይያስ አድማጮች ይሁዳን፣ ቢንያምን እና ኢየሩሳሌምን የያዘዉ የደቡብ መንግስት ነበር ፡፡ ኢሳይያስ ኃጢዓተኛ ባህሪያቸው እንደ ቅደም ግዞት፣ እንደ ግዞት እና ከግዞትበኋላ እንዳለ ጊዜ እንደሚመራቸዉ ነገራቸው ፤ በምርኮ የደቡቡ መንግስት ምን እንደሚገጥመዉ ትንቢት ተናገረ ፡፡ ትንቢታዊ ቃል በሆኑ ቅርፆች በጥበብ ቃል እና በሸክም ተናገረ ፤ በተጨማሪም የደቡቡን መንግስት እና በዙሪያ ያሉ ሕዝቦችን ስለሚጎዳዉም ፍርድ ተናገረ ፡፡

በዚህ ሂደት ሁለት ምርኮኝነቶች ነበሩ - የሶሪያዊያን ምርኮኝነት እና የባቢሎናዊያን ምርኮኝነት ነበሩ ፡፡ በሶሪያ ምርኮኝነት የተወሰዱት በፍፁም አልተመለሱም ፤ አንዳንዶች በባቢሎናዊያን ምርኮኝነት የተወሰዱት ቀስ በቀስ ወደ ይሁዳ እና ኢየሩሳሌም ይመለሳሉ ፡፡ የኢሳይያስ ግብ በዚህ ሁሉ መካከል ዉስጥ ለይሁዳ ተስፋን መሳል/ማሳየት ነበር ፡፡ በዚህ መፅሀፍ መጨረሻ ላይ ስለ ክርስቶስ ተመልሶ መምጣት እና ንጉሳዊ ዘመኑ እናወራለን ፡፡

ኢሳይያስ በአራት በተለያዩ ነገስታት ዘመን ትንቢትን ተናግሯል ፡፡ የንጉስ ዖዝያን መዉደቅ ለአንድ ካህን የሚገባዉን በማሰብ እጣንን በመሰዊያዉ ላይ በማቃጠል ዉጤት መጣ ፤ በሁለቱም ተግባራት ላይ ለመሳተፍ በመሞከሩ በለምፅ ተመታ ነገር ግን በፍፁም አልተቀበለም ፡፡ ዖዝያ ማንነቱን ለመወሰን የታገለ ግራ የተጋባ ሰዉ ነበር ፡፡ 25 አመት ሲሆነዉ ንጉስ የነበረዉ ንጉስ ኢዩአታም የዖዝያን ልጅ ነበር ፡፡ እርሱ ንጉስ በነበረ ጊዜ ሶሪያ በኃይል አደገ ፡፡ ንጉስ አካዝ ከ25 አመት እስከ 41 አመቱ አስተዳደረ ፤ በእርሱ አገዛዝ/ዘመን ጊዜ ሶሪያን ለመዋጋት እስራኤል እና አሶር ጥምረት መስረተዉ ነበር ነገር ግን ነገር ግን አካዝያስ ይሁዳን ወደዚህ ጥምረት ማምጣትን አልተቀለም ፡፡ በሰለሞን ቤተ መቅደስ ዉስጥ የጣዖት መሰዊያን አዘጋጀ ፡፡ በእርሱ ዘመን ጊዜ አሶራዊያን ሰማሪያን በመያዝ ብዙ እስራኤላዊያንን ወደ ምርኮኝነት ወሰዷቸው ፡፡ ንጉስ ሕዝቅያስ በሀያዎቹ ንጉስ ሆነ መታደስም የእርሱ ዘመን ፍሬ/ዋና ነገር ነበር ፤ እንደ መልካም ንጉስ የታዬ ነበር ፡፡ ሕዝቅያስ አሶር በይሁዳ ላይ ማሰፈራራት በደረሰበት ጊዜ ወደ ኋላ አልተመለሰም ምክንያቱም እምነቱን በእግዚአብሄር ላይ ማስቀመጥ እንደሚችል ስለሚያውቅ ፡፡ የእግዚአብሄር ያልነበረዉን ነገር በማስወገድ የእግዚአብሄርን ነገር ከሕዝቡ ጋር አዋሀደ ፤ በዚህ ሁሉ እዉነትን መሰረተ ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር እድሜዉን እንዲያረዝምለት ፀለዬ እግዚአብሄርም ተጨማሪ 15 አመትን ሰጠው ፡፡

በኢሳይያስ መፅሀፍት ዉስጥ 66 ምዕራፎች ሲኖሩ የመጀመሪያዎቹ 39 ስለ ፍርድ እና ህግ ስለሚይዘዉ ነገር ያወራሉ ፡፡ በብሉይ ኪዳንም ተመሳሳይ ነገር የሚያሳዩ 39 መፅሀፎች አሉ ፤ የመጨረሻዎቹ የኢሳይያስ 27 ምዕራፎች በአዲስ ኪዳን “ በእኛ ላይ በእግዚአብሄር በኩል “ ስለመጣዉ ስለ መፅናናት እና ስለ ቤዛነት ያወራሉ ፤ አዲስ ኪዳን 27 መፅሀፍት አሉት ፡፡ ታላላቅ ነቢያት (ኢሳይያስ፣ ኤርሚያስ፣ ሕዝቄል እና ዳንኤል) የፍርድን ጭብጥ እና መፅናናትን እና ተስፋን ተናግረዋል ፡፡

ትምህርት

ኢሳይያስ (1፡ 1-9)፡ ኢሳይያስ መልዕክቱን አላሰማመረም ፡፡ የእግዚአብሄር መንፈስ እርሱን በመናገር ከህዝቡ ጋር የሚጋራዉን መልዕክት ሰጠው ፡፡ በመሰረቱ እግዚአብሄር ኢሳይያስን የፍርድ ጉዳዩ ያሳየዉ እንደ ነበር ነገረው ፤ ጌታ ከሳሽ ነበር እስራኤል ደግሞ ተከሳሽ ፡፡ የእግዚአብሄር ህዝቦች የማይሰሙ ስለነበሩ እግዚአብሄር በክስ ላይ እንደ ነበር እንኳን አላስተዋሉም (ቁጥር 3) ፡፡ እግዚአብሄር የራሱን ልጆች በመናቅ በእግዚአብሄር ላይ ጀርባቸዉን አዞረዉ እንደ ነበሩ እንደ ተንኮለኛ እና ነዉረኛ ልጆች ገለፃቸው (ቁጥር 4) ፡፡

ስለ እነርሱ ጤነኛ የሆነ ምንም ነገር አልነበረም (ቁጥር 5-6) ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉንም ጉዳያቸዉን አየ ስለ እነርሱ ምንም መልካም ነገር አልነበረም ፡፡ ምድራቸው “ በሌሎች የጠፋች ባዶ ነበረች “ (ቁጥር 7) ፡፡ የኢየሩሳሌም ከተማ ማሳያ የሆነችዉ “ የፂዎን ሴት ልጅ “ ብቻዋን “ እንደ ተከበበች ከተማ ነበረች “ (ቁጥር 8) ፡፡ በኢሳይያስ በኩል እግዚአብሄር ፍርድ እየመጣ ነዉ፣ ምርኮ እየመጣ ነዉ እያለ እየተናገረ ነበር ፤ ነገር ግን በምርኮ እግዚአብሄር ያድናቸዉ እና ቅሬቶችን ያስቀር ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ እንደ ማክአርቱር ንግግር “ ይህ ቅሬቶች መሲሁ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ እንደ ገና በተሰባሰቡት ሕዝቦች የእስራኤልን መመለስ ዋና ይይዛል “ ፡፡ ይህ መልዕክት ሁሉም እንደማይጠፉ ተስፋን ሰጥቶአቸዋል ፡፡

ኢሳይያስ (1፡ 10-15)፡ እዚህ ጋር እግዚአብሄር ለልጆቹ እያላቸዉ የነበረዉ ነው ፡፡ መልካምን በመመልከት የእግዚአብሄር የተመረጠ ህዝብ ለመሆን ድርሻችሁን ትጫወታላችሁ ነገር ግን ሁሉም ዉሸት ነዉ፣ ሁሉም ግብዝነት ነው ፡፡ ስለዚህም በቁጥር 11 እግዚአብሄር በቃ ማለት በቃ ነዉ አለ ፤ እግዚአብሄር “ የማይጠቅምን መስዋዕትን ማምጣትን እንዲያቆሙ “ ነገራቸው (ቁጥር 13) ፡፡ ዕጣናቸዉ ምናምንቴ ነበር (ቁጥር 13) እግዚአብሄርም በሚያደርጓቸዉ በዓላቶች ደክሞ ነበር (ቁጥር 14) ፤ እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች ለእስራኤላዊያን አቋቁሞአቸዉ ነበር ነገር ግን ልባቸወ ትክክል ያልነበረዉን እዉነት ለመሸፈን እየተጠቀሙባቸዉ ነበር ፡፡

ጆርጅ ባርና በዩናይትድ ስቴት ለእያንዳንዱ 550 ወጣት አንድ ቤተ ክርስቲያን መኖሩን የሚያሳይ ጥናትን አድርጓል ፤ ከ90ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት አሜሪካዊያን በቤታቸዉ መፅሀፍ ቅዱስ አለን ይላሉ፣ ሁለት ሰዎስተኛ አሜሪካዊያን ደግሞ ኃይማኖተኛ ነን ይላሉ ፤ ነገር ግን ሁለት ሰዎስተኛዎቹ ለሚያደርጉት ለድርጊታቸዉ መፅሀፍ ቅዱስ አስፈላጊ አይደለም ይላሉ ፡፡ ዋናዉ ነገር እኛ ክርስቲያን ህዝብ የሚያደርገ ሁሉም ነገር አለን ስለዚህ የተለየየ ነገር ለምን አናይም ? በባህል እና በዜና ላይ ስንመለከት ምንም ተፅዕኖ እንደሌለን ይመስላል ፡፡

ኢሳይያስ ለይሁዳ አንድ መልዕክትን ተናገረ፡ በቃ ማለት በቃ ነው ፡፡ አሁንም የክርስቶስ አካል የሆኑትን ህዝቦቹን ይወዳቸዋል ነገር ግን የኃይማኖት ጨዋታ እየተጫወቱ ነበር እግዚአብሄርም ወደ ፀሎታቸዉ እያዳመጠ አልነበረም (ቁጥር 15) ፡፡

መደምደሚያ

እዚህ ጋር ስዕሉ እግዚአብሄር ከልጆቹ ጋር የፍርድ ጉዳይ እንዳለዉ ነው ፡፡ እግዚአብሄርም “ጥፋተኛ ! “ ይላል ፤ መጥፎ ዜና እንዳለ እንረዳለን እንዲሁም ደግሞ ኢሳይያስ መልካምን ዜና መናገር ይችላል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 755.

  2. MacArthur, p. 755.

  3. MacArthur, pp. 755–756.

  4. MacArthur, pp. 759.

  5. MacArthur, pp. 759.

ጥያቄዎች

  1. ኢሳ (1፡ 9) የእዉነተኛ አማኞች ትንሽ ቅሬቶች እንዳሉ እና የቀሩት በራሳቸዉ መንገድ እንደሚኖሩ የአሁኗን ቤተ ክርስቲያን ሊገልፅ ይችላል ?
  2. በኢሳ (1፡ 11-15) እግዚአብሄር ብስጭቱን ገለፀ ፤ ብስጭቱ በኃይማኖታዊ ስርዓቶች በራሳቸዉ ነበር ወይስ በእስራኤላዊያን የልብ ሁኔታ ነበር (ኢሳ 29፡ 13, ማቴ 15፡ 8) ? እግዚአብሄርን እያከበሩ የነበሩት በከንፈራቸዉ ወይስ በልባቸዉ ነበር ? ተመሳሳይ ነገር በማድረግ ራሳችሁን ጥፋተኞች ሆናችሁ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ?
  3. ኢሳ (2፡ 10-17) የሀሰተኛዉ ክርስቶስ ጊዜን እና በሁለተኛዉ በጌታ መምጣት መዉደቁን ሊገልፅ ይችላል (ራዕይ 19) ? ለምን ወይስ ለምን ሊገልፅ አይችልም ?
  4. በኢሳይያስ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Isaiah 1:18–20

“‘Come, let us discuss this,’ says the LORD. ‘Though your sins are like scarlet, they will be as white as snow; though they are as red as crimson, they will be like wool. If you are willing and obedient, you will eat the good things of the land. But if you refuse and rebel, you will be devoured by the sword.’ For the mouth of the LORD has spoken.”

ኢሳይያስ ስለ እስራኤልና ይሁዳ ባየው ራዕይ እግዚአብሔር ለህዝቡ ሁለት ምርጫ ሰጠ ፡- ንስሀ መግባትና መታዘዝ ወይም ማመጽና እምቢ ማለት ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ መታዘዝ ከመልካም ነገር ሲያጠግብ በሌላ በኩል አለመታዘዝ ለጥፋት ይዳርጋል ፡፡

በተመሳሳይ እናንተም ኃጢአታችሁን ብትናዘዙ ኢየሱስ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ሊያነጻችሁ እርሱ የታመነና ጻድቅ ነው ፡፡ ኢየሱስ የመጣው እናንተ እርሱን ከሞት የተነሳው የአለም አዳኝ አድርጋችሁ ለመቀበል ከወሰናችሁ ፣ ምህረትንና ጸጋን እንድትቀበሉ ነው ፡፡ አንዴ ንስሀ ከገባችሁ በኃላ እግዚአብሔር ከቀድሞ መንገዳችሁ እንድትመለሱና በክርስቶስ አድስ ሆናችሁ በመታዘዝ እንድትመላለሱ ያዛችኋል ፡፡ በየቀኑ ከእንቅልፋችሁ ስትነሱ ለእርሱ ድምጽ መታዘዝ ትችሉ ዘንድ እንድረዳችሁ ጸልዩ ፡፡ የእርሱን ምሪት ተከትላችሁ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ስትሄዱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡ በእርሱ ስትኖሩና ድምጹን ስትከተሉ ነው በየቀኑ መታዘዝ የሚባለው ፡፡ አለበለዚያማ በእያንዳንዱ ቀን እየተነሳችሁ ከክርስቶስ ዘወር ለማለት ትወዳላችሁ ከዚያም የራሳችሁን ነገር ታደርጋላችሁ ፡፡ የእግዚአብሔርን ድምጽ ልትሰሙ ትችላላችሁ ነገር ግን እንደማይታዘዙ ልጆች የምትፈልጉትን ነገር በምትፈልጉበት ጊዜ ለማድረግ ትወዳላችሁ ፡፡ ምክርን አትቀበሉም ባለመታዘዝም ትሄዳላችሁ ፡፡ ዛሬ ምርጫው የእናንተ ነው ንስሀ መግባትና መታዘዝ ወይም ማመጽና እምቢ ማለት ፡፡ እንዴት ይሆን ከክርስቶስ ጋር ለመመላለስ የምትመርጡት ?

“ ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር ፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች ። እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና ። “

  • ኢሳይያስ 1፡18-19

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 119:9–11 — “ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው ። በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ ። አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ ። “

ምሳሌ 28:13 — “ ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል ። “

1ኛ ዮሐንስ 1:9 — “ በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው ። “