Redemption And Restoration
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Master Philemon 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ 537ተኛ ክፍላችን እና የመፅሀፍ ቅዱስ 40ኛ መፅሀፋችን ነው ፡፡ በዚህ ሁለት አመት ጥናታችን ዉስጥ ግባችን በሁሉም መፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ዉስጥ መሲሁን የቱ ጋር እንደሚታይ እንዲለዩ ተማሪዎችን ማበረታታት ነው ፡፡ የፊልሞና መፅሀፍ የጳዉሎስ አጭሩ መልዕክት ነው፣ 25 ቁጥሮች ያሉት እና ስለ ሰዎስት ሰዎች ብቻ የሆነ ነው ፡፡ በዚህ መልዕክት ጳዉሎስ ከአንድ ጓደኛዉ ጋር ስለ ሰዎስተኛ ሰዉ እየለመነ ነበር ፡፡ ለፊልሞና ቃላችን ጌታ የሚል ሲሆን ጳዉሎስ ራሱን እንደ እስረኛ ወይም “ እንደ ነፃ አገልጋይ “ እና ክርስቶስ ጌታዉ እንደ ነበር ከገለፀበት ከፊልሞና 1 የመጣ ነው ፡፡ በማቴ (23፡ 10) ኢየሱስ “ ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነዉና ሊቃዉንት ተብላችሁ አትጠሩ “ አለ ፡፡
የፊልሞና መፅሀፍ የመቤዠት እና የይቅርታ ታሪክ ነው ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን ቆላስያስን በፃፈበት ተመሳሳይ ጊዜ ከክርስቶስ ሞት 60-62 መካከል በኋላ ፃፈው ፡፡ ምናልባትም ፊልሞና እና ጳዉሎስ በኤፌሶን በመገናኘት በዚያ ጳዉሎስ ፊልሞናን ወደ ክርስቶስ መራው (ቁጥር 19) ፡፡ ፊልሞና ሀብታም ሰዉ ነበር (ቤተ ክርስቲያን በቤቱ ትገኛለች) (ቁጥር 2) በተጨማሪም የስሙ ትርጉም “ ጠቃሚ “ የሆነ ቢያንስ አንድአናሲሞስ የሚባል አገልጋይ ባለቤትም ነበር ፡፡ አናሲሞስ ከጌታው ከፊልሞና ሮጦ በመሄድ ሁሉንም ጳዉሎስን በማግኘት ወደ ተለዉጦበት ወደ ነበረው ወደ ሮም መንገድ አደረገው ፤ ምናልባትም አናሲሞስ ወደ ሮም ሲጓዝ ወጪዉን በመክፈል ለመርዳት ከጌታዉ ከፊልሞና የሆነ ነገርን ሰርቋል ፤ ጳዉሎስ አናሲሞስን መዉደዱ ስላደገ ከእርሱ ጋር በሮም እንዲቀመጥ ፈለገ ነገር ግን አናሲሞስ ሸሽቶ በመሮጥ የሮማዊያንን ህግ ሰብሮ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ አናሲሞስን ለፊልሞና ከፃፈዉ መልዕክት ጋር መልሶ ወደ ቆላስይስ ላከው ፡፡ ጳዉሎስ ቲኪቆስን ለአናስሞስ እንደ ጠባቂነት እንዲሁም በዚያ ላለች ቤተ ክርስቲያን የጳዉሎስን መልዕክት እንዲያደርስ ላከው ፡፡
ዋይርስቤ “ አንድ አገልጋይ ጌታዉን ካመለጠ/ከጠፋ በሰራተኞች ስሙ እና መግለጫዉ በመመዝገብ አገልጋዩ በሚፈለጉ ዝርዝር ዉስጥ ይሆናል ፤ ያመለጠዉን አገልጋይ/ባሪያ ያገኘ ማንኛዉም ነፃ ዜጋ እንደ አሳዳጊ እና ከባለቤቱ እንደተቤዠዉ ይታሰባል ፡፡ ባሪያዉ ወዲያዉኑ ወደ ባለቤቱ አይመለስም ነበር እንዲሁም ወዲያዉኑ እንዲሞት እንደማይፈረድበት “ ይገልፃል ፡፡ በሮም ግዛት 60ሚሊዮን ባሪያዎች እንዳሉ ሲገመት በጥራታቸዉ እና በችሎታቸዉ መሰረትም ከ500 ዲናር እስከ 50,000 ዲናር ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ አናሲሞስ በጌታ ነፃነት አገኘ - የተቤዠ እና ይቅር የተባለ ሆነ ፡፡ ጳዉሎስ የአናሲሞስን ያለፈ ነገር እና አናሲሞስ በክርስቶስ መቀየሩን ያውቃል ፤ ዋይርስቤ የጳዉሎስን ግንኙነት ከአናሲሞስ ጋር “ እንደ ተወደደ ወዳጅ……የሚለምን ማላጅ…..ተሸጋሚ አጋር እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ቲኪቆስን ከአናሲሞስ ጋር አብሮ የላከዉ ሰዎች በደማስቆ መንገድ ላይ ክርስቶስን ካገኘ በኋላ ስለ ጳዉሎስ እንደመሰከሩት በአናስሞስ ህይወት ላይ ስላለዉ ለዉጥ ምስክር መሆን እንዲችል እንደሆነ አስባለሁ ፡፡
ትምህርት
ፊልሞና (1-7)፡ ጳዉሎስ ለፊልሞና፣ ለአፍብያ፣ ለአርክጳ እና በፊልሞና ቤት ለሚገኝ ጉባሄ ሰላምታ በማቅረብ ጀመረ (ቁጥር 1-3) ፡፡ በቁጥር 4-7 የኔልሰን ማብራሪያ ጳዉሎስ “ ፊልሞናን በማመስገን ለመለመን መሰረትን እንደመሰረተ “ አመለከተ ፡፡ ጳዉሎስ ለጌታ እና “ ለቅዱሳን ሁሉ “ ካለዉ ፍቅር የተነሳ ሁልጊዜ ስለ ፊልሞና እግዚአብሄርን እንዳመሰገነ ገለፀ (ቁጥር 4-5) ፡፡ ጳዉሎስም በመቀጠል ክርስቶስ በአማኞች ህይወት አድርጎ የነበረዉን በሚናገር መልካም ስራ ዉስጥ የፊልሞና “ እምነት ፍሬአማ እንዲሆን “ ፀለይኩኝ አለ (ቁጥር 6) ፡፡ የጳዉሎስ ንግግር የፊልሞና እምነት ጠንካራ እንደ ነበር እና በህይወቱ እየተመላለሰበት እንደሆነ እንደተረዳ ነው ፡፡
ፊልሞና (7-8)፡ በሚያስደንቅ ሁኔታ ጳዉሎስ ታላቅ ስለሆነዉ ስለ ራሱ ደስታ እና በእስራት ዉስጥ እያለ እንኳን በፊልሞና ፍቅር ስለተቀበለዉ መበረታታት ይናገራል (ቁጥር 7) ፡፡ በቁጥር 7-8 ጳዉሎስ ለፊልሞና የመጀመሪያዉን ልመና አደረገ፡ በክርስቶስ ፊልሞና ማን እንደ ነበር ከመሆኑ የተነሳ ለጳዉሎስ አሳይቶት ከነበረዉ ፍቅር የተነሳ ጳዉሎስ በድፍረት ለእርሱ ልመና ያቀርብለታል ፡፡ ጳዉሎስ ፊልሞናን ለጳዉሎስ እና በቆላስያስ ላለች ቤተ ክርስቲያን የነበረዉን ዋጋ እንዲያዉቅ በመፍቀድ እየገነባዉ ነበር ፤ ጳዉሎስ እንዲያደርግለት የሚፈልገዉን ፊልሞና እንዲያደርግ የማዘዝ ስልጣን ነበረው ነገር ግን ያን አያደርግም ፡፡ የእርሱ ልመና ለፊልሞና ትክክለኛዉን ነገር እንዲያደርግ ነበር ፡፡
ፊልሞና (9-11)፡ የጳዉሎስ ሁለተኛዉ ልመናው በፍቅር ላይ በመመስረት የተደረገ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ልመናዉን ለማጠንከር ጳዉሎስ የማባበያ ካርድ በመጫወት ጳዉሎስ ሽማግሌ ሰዉ እንደ ነበርና (ማለትም 55አመቱ ወይም ከዚያ በላይ ነበር) ከእምነቱ የተነሳ በእስራት እንደ ነበር አመለከተ (ቁጥር 9) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ፊልሞናን በእስራትም እንኳን ቢሆንም አባት ለሆነው “ ስለልጄ አናሲሞስ “ ለመነ (ቁጥር 10) (1ቆሮ 4፡ 15) ፡፡ የጳዉሎስ አራተኛ ልመናው አናሲሞስ ለእርሱ ጠቃሚ እንደ ነበር አሁንም ለፊልሞናም አስፈላጊ እንደሚሆን ነበር (ቁጥር 11)፡፡
ፊልሞና (12-16)፡ ጳዉሎስ አናሲሞስ ለእርሱ እንዴት ጠቃሚ እንደ ነበር ይገልፃል፡ አሁን የጳዉሎስ አካል ነበር፣ ጳዉሎስ በእስራት እያለ እረዳቱ ነበር (ቁጥር 12-13) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ፊልሞናን በደንብ ስለሚያከብረው ከፊልሞና ፍቃድ ዉጪ አናሲሞስን ከእርሱ ጋር አላቆየሁትም አለ (ቁጥር 14) ፡፡ ጳዉሎስ ፊልሞና የሆነ ነገር እንዲያደርግ ማስገደድ አልፈለገም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ ፍልሞና እንደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ ትክክለኛ ዉሳኔ እንዲያደርግ ፈለገ ፡፡ በቁጥር 15 ጳዉሎስ የፊልሞናና አናሲሞስ መለያየት የእግዚአብሄር መለኮታዊ እቅድ ስለሆነ አናሲሞስ አማኝ የመሆን እድል እንዳለዉ እና እንደ ባሪያ ሳይሆን በክርስቶስ እንደ ወንድም ወደ ፊልሞና ለዘላለም የመመለስ እድል እንዳለዉ ተናገረ (ቁጥር 16) ፡፡
ፊልሞና (17-19)፡ ከዚህም የተነሳ ጳዉሎስ ፊልሞናን ጳዉሎስን እንደተቀበለዉ አናሲሞስን እንዲቀበለዉ ይጠይቀዋል (ቁጥር 17) ፡፡ ቀጥሎም አናሲሞስ የፊልሞና ያለበትን ማንኛዉንም ነገር እንደሚከፍል አቀረበ (ቁጥር 18) ፡፡ ለዚህ ቃሉ “ ማመካኘት “ ወይም “ በእኔ ላይ ቁጠረዉ “ ማለት ነው ፡፡ ሮበርት ግሮማኪ “ የጳዉሎስ አቀራረብ በማመካኘት መሰረት የሚያምር መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማሳያ ነው (ሮሜ 5፡ 13, 2ቆሮ 5፡ 21) “ ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን በራሱ እጅ እንደፃፈው በማመልከት በመካከላቸው መልዕክቱን ህጋዊ ስምምነት ያደርጋል (ቁጥር 19) ፡፡ ጳዉሎስ የአናሲሞስን እዳ ለመክፈል ቃል ገባ ነገር ግን ፊልሞናን ስለ ድነቱ የጳዉሎስ እዳ እንዳለበት አስታወሰው (ቁጥር 19)፡፡
ፊልሞና (20-25)፡ ጳዉሎስ ፊልሞናን “ ልቡን በክርስቶስ እንዲያሳርፍለት “ (ቁጥር 20) ይጠይቀዋል ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ፊልሞናን ጠይቆት ከነበረዉ በላይ ፊልሞና የሚያዉቀዉን ትክክለኛ ነገር እንደሚያደርግ በፊልሞና እርግጠኛ እንደ ነበር ነገረው (ቁጥር 21) ፡፡ ወዲያዉኑም ጳዉሎስ ፊልሞናን ሊጎበኘዉ እንደሚችል ተስፋ ስለደረገ የእንግዳ ማረፊያ እንዲያዘጋጅ ጠየቀው (ቁጥር 22) ፡፡ ጳዉሎስ በብዙ ሰላምታ ይዘጋል፡ በቆላስያስ በጣም ታወቂ ከነበረዉ አብሮት ከታሰረው ከኤጳፍራ እና ከማርቆስ፣ ከአስጥሮኮስ፣ ከዴማስ እና ከሉቃስ በሆነ ሰላምታ ይዘጋል (ቁጥር 23-24) ፡፡ ፊልሞንን የጌታ ፀጋ ከአንተ ጋር ይሁን በማለት በመባረክ ያጠቃልላል (ቁጥር 25) ፡፡
መደምደሚያ
የኔልሰን ማብራሪያ በፊልሞና “ ስለ ትንሽ መልዕክት ስድስት ትልቅ ትምህርቶችን “ ያቀርባል፡
- ሁልጊዜ በክርስቶስ ለማስታረቅ እና ለሁለተኛ እድል እድል ያለ ነው ፡፡
- የእግዚአብሄር ስራ ሰዎችን ወደ እዉነተኛ እምነት እና ከሌሎች ጋር ወደ ታደሰ ግንኙነት ማምጣት ነው ፡፡
- ወንጌል በማንኛዉም ርቀት መስራት ይችላል - ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላዉ እና ከአንዱ አህጉር ወደ ሌላዉ ፡፡
- በክርስቶስ ታናናሽ አማኞችን ለመቆጣጠር በታላላቅ አማኞች እዉነተኛ ዋጋ አለ ፡፡
- አናሲሞስ ስለ ኢየሱስ ለመስማት ርቆ መሄዱ “ ከእግዚአብሄር ትዕግስት እና ጥበቃ ኋላ ምፅዕትን “ የሚያሳይ እዉነት ነው ፡፡
- “ በክርስቶስ ሰዎች ሊቀየሩ ይችላሉ “ ፡፡
ሀሳቡ ህይወታችሁን ለጌታ ታስገዛላችሁ ?
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1826255.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 270.
MacArthur, p. 1826.
Wiersbe, pp. 270–271.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1630.
Thomas Constable, Dr. Constables Bible Study Notes, p. 13; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/philemon.pdf.
Wiersbe, p. 271.
Robert G. Gromacki, Stand Perfect in Wisdom: An Exposition of Colossians and Philemon (Grand Rapids: Baker Book House, 1984), pp. 200–201; quoted in Constable, p. 19.
Nelson’s Commentary, p. 1631
ጥያቄዎች
-
ጳዉሎስ ይህን መልዕክት ለፊልሞና ለምን ፃፈለት በፃፈለትስ ጊዜ የት ነበር ?
-
በፊልሞን መፅሀፍ መሰረት ፊልሞን ምን አይነት ሰዉ ነበር ? አናሲሞስ ማን ነበር ጳዉሎስ በዚህ ጊዜ ከፊልሞና ጋር የታረቀ እንዲሆን ለምን እየጠየቀዉ ነበር ?
-
የፊልሞና ዋና ጭብጡን ምን ትላላችሁ ? ይህ እናንተን እንዴት ይናገራችኋል ?
-
አማኝ ካልነበረ ሰዉ ጋር ግጭት ወይም ልዩነት ነበራችሁ አማኝ ከሆነስ በኋላ ከዚህ የተነሳ ብቻ በማቆም ታርቃችሁ ታውቃላችሁ ? ይህ አስፈላጊ ለምን አስፈላጊ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በፊልሞና በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Philemon 1:15–16
“For perhaps this is why he was separated from you for a brief time, so that you might get him back permanently, no longer as a slave, but more than a slave—as a dearly loved brother. He is especially so to me, but even more to you, both in the flesh and in the Lord.”
ጳውሎስ በእስር ቤት ሁኖ ህይወቱን ለክርስቶስ አሳልፎ ስለሰጠው ከፊልሞን ስለሸሸው ባሪያ አናሲሞስ ይመሰክራል ፡፡ ስለዚህም ጳውሎስ ለጓደኛውና ውድ ለሆነው አማኝ ፊልሞና ደብዳቤ ጻፈ ፤ ደብዳቤውም ፊልሞና ከእንግዲህ አናሲሞስን እንደ ባሪያ እንዳይቆጥረው የሚጠይቅ ነው ምክንያቱም አሁን እነርሱ ሁለቱም በክርስቶስ ስለሆኑ ነው ፡፡ ጳውሎስ ትልቁን የእግዚአብሔርን ጸጋ ምስል በመረዳት ፡- ምናልባት ወንጌልን ይቀበልና በክርስቶስ የተወደደ ወንድም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አናሲሞስን ወደ እስር ቤት እንድገባ አድርጎታል በማለት ያብራራል ፡፡
በህይወትህ ላይ እግዚአብሔርን ገዥህ አድርገህ የምትቀበል ከሆነ ደግሞም ለእርሱ በፍጹም መሰጠት የምትኖር ከሆነ እርሱ ነገርን ሁሉ አያይዞ ለበጎ እንደሚያደርገው ቃል ይገባልሃል ፡፡ መጨረሻህ እስር ቢሆን እንኳ ፣ በጤና ማጣት ውስጥ ብታልፍ እንኳ ወይም ደግሞ በኃጢአት ፈተናም ውስጥ ብትወድቅም እንኳ ፡፡ በእርግጥ እነዚህ ጊዜያት ተግዳሮትን ጉዳትን ያስከትላሉ ሆኖም ግን ምናልባት በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ የምታልፈው እንድትመለስ ፣ ከዚህ በኃላ የአለም ባሪያ እንዳትሆን ፣ ከዚህ በኋላ ለኃጢአት ባሪያ እንዳትሆን ደግሞም በክርስቶስ ወንድም ወይም እህት ሆነህ እንድትቆጠር ቢሆንስ ፡፡ ከኃጢአት ነጻ ፡፡ ከባርነት ነጻ ፡፡ በጸጋውና በክርስቶስ በተገኘው ድል ለማምለክ ነጻ ፡፡ ምናልባት ይህ የሆነው ክርስቶስ ገዥህ ሆኖ ደግሞም ራስህን ለእርሱ ምርኮኛ አድርገህ ሳለ ነገር ሁሉ በአንድ ላይ ለበጎ ሲሆን ማየት እንድትችል ነው ፡፡ እስኪ ዛሬ ራስህን ጠይቅ ፡- በኔ ላይ “ ይህ ነገር ለምን ይሆን የሆነው ? “ እግዚአብሔር የሚጠብቅ አምላክ ነው ፡፡ ጸጋን ታገኝ ዘንድ ደግሞም በእያንዳንዱ አጋጣሚ ድልን ትቀዳጅ ዘንድ ለእርሱ ፍቃድ ራስህን አሳልፈህ በመስጠት ኑር ፡፡
“ ተቀብለህ ለዘላለም እንድትይዘው ስለዚህ ምናልባት ለጊዜው ተለይቶሃልና ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ አይሆንም ፥ ነገር ግን ለእኔ በተለየ የተወደደ ወንድም ከሆነ ፥ ለአንተማ ይልቅ በስጋውም በጌታም ዘንድ ከባሪያ የሚሻል የተወደደ ወንድም እንዴት አይሆንም ። “
- ፊልሞና 1፡15-16
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 103:19 — “ እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች ። “
ሮሜ 6:22 — “ አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው ። “
ሮሜ 8:28 — “ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።