Paul's Letters Titus

Basic Church Instruction

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Savior Titus 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 572 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በመፅሀፍ ቅዱስ ጥናታችን ላይ ከመጀመራችን በፊት ስለዚህ ፅሁፍ መነሻ እንድናስብ እፈልጋለሁ ፡፡ የመጀመሪያዉ በዚህ መፅሀፍ ጳዉሎስ ለቲቶ በጢሞቴዎስ ከተጠቀመዉ ተመሳሳይ የፍቅር ቃል - “ የእኔ የራሴ ልጅ “ በማለት አመለከተ (1ጢሞ 1፡ 2, ቲቶ 1፡ 4) ፡፡

በሁለተኛነት ስለ ቀርጤስ ደሴት እንድናሰብ እፈልጋለሁ ፤ ካይል በቲቶ 1 እንዳመለከተው ጳዉሎስ በቀርጤስ በዚያ ከመድረሱ በፊት በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ የነበሩ አማኞች ነበሩ ፡፡ በአገልግሎት የጳዉሎስ ስራ ከበዓለ ኃምሳ ቀን ከአመታት በኋላ መጣ ፤ እንዲሁም በቀርጤስ ያሉ ሰዎች የራሳቸዉ የደሴት ባህልም ነበራቸው ፡፡ የቀርጤስ ሰዎች “ ሰነፍ “ በመባል ተብለዉ የተጠሩ ነበሩ ፤ በተለዬ መልኩ ደሴቶች ብዙ ኢንዱስትሪዎች የሉም ይልቁንም በቱሪዝም ላይ የተደገፈ ነዉ እንጂ ፡፡ በጣም በፍጥነት ከሚንቀሳቀስ ባህል ዉስጥ ለመጣ ሰዉ የደሴት ባህል በጣም የዘገዬ እና ሰነፍ የሆነ ይመስላል ፡፡ ሸቀጣሸቀጦችን በመርከብ ለማጓጓዝ እና መንገደኞችን በዉሃ ለማጓጓዝ ብዙ ሰዎች በጉዞአቸዉ በቀርጤስ ያልፋሉ ፡፡ በዚያ የሚያልፉት ሰዎች በቀርጤስ ያለችዉን ቤተ ክርስቲያን እድገት በማስተዋወቅ በመርዳት ከዚያ ቃልን ወደ ሌላ ስፍራ ይወስዳሉ ፡፡

ይሁ ሁሉ ለቲቶ የተላከዉ መልዕክት ምን ያክል አስደናቂ እንደሆነ የሚያሳይ ነዉ ምክንያቱም በሰዎስት አጫጭር ምዕራፎች ጳዉሎስ የቤተ ክርስቲያንን ተቋም እና ስራ እንዲሁም የወንጌልን ሙሉ መልዕክት ስለሸፈነ ፡፡ ይህ በቀርጤስ በሚያልፉት ሰዎች ላይ የመስራት የመለኮት ሙሉ እቅድ ነበር ፤ በአሁኑ ጊዜ ማንም በማቋረጥ በዚያ አያልፍም ምክንያቱም በጉዞአቸዉ በላያቸዉ ላይ ስለሚበሩ ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር እያንዳንዱን ትዉልድ እንዴት እንደሚደርሰዉ ያውቃል !

ትምህርት

ቲቶ (3፡ 1)፡ ጳዉሎስ ምዕራፉን ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በማዘዝ ይጀምራል ፡፡ ቲቶን አማኞች ራሳቸዉን በገዢዎች እና በበለስልጣናት ስልጣን ፊት በማስገዛት ፈራጆችን በመታዘዝ ለመልካም ስራ የተዘጋጁ እንዲሆኑ ነገረው (ቁጥር 1) ፡፡ በገዢዎች እና በባለስልጣናት የተረበሻችሁ አትሁኑ (ሮሜ 8፡ 38, ኤፌ 1፡ 21, 3፡ 10, 6፡ 12, ቆላ 1፡ 16, 2፡ 10, 15) ፡፡ ለገዢዎች(ለአስተዳዳሪዎች) የሆነ ቃል የሰዉ መሪዎችን ወይም መንፈሳዊ መሪዎችን ያመለክታል ፤ በግልፅ እዚህ ቶቶ 3 ላይ ሰዎች ናቸው ፡፡ በተለዬ ሁኔታ በደሴት ህዝቦች ዉስጥ የራሳቸዉን ጉዳይ የሚሰሩ ብዙሰዎች ታገኛላችሁ የመንግስትም ስልጣን ትልቅ ጉዳይ አይደለም ፤ ነገር ግን ጳዉሎስ ያ ገጠመዉ ምክንያቱም የእግዚአብሄር መንገድ በእኛ ላይ ለተሸሙ ሰዎች የተገዛን እንድንሆን ስለሚጠብቅ ፡፡

ቲቶ (3፡ 2)፡ ጳዉሎስ ማንኛዉንም ክፉ ነገር እንዳይናገሩ ነገር ግን የተረጋጉ እና ለሁሉም ሰዉ ቅን እንዲሆኑ ነገራቸው ፡፡ የጳዉሎስ ትዕዛዝ አማኞች ግትር እንዳይሆኑ ማለት ነው ፡፡ መልካም /ደህና ለሆነ ማህበረሰብ አስተዋፅዖ የምናደርግ መሆን አለብን ፤ በችግር ዉስጥ ያሉትን ለመርዳት እጃችን የምንዘረጋ መሆን አለብን ፡፡ በሰዎች መካከል በመሆን በመካከላችን እንደሚከፋፍል ሳይሆን መልካም ነገርን ለማድረግ “ የእምነት ልዩነቶችን “ እንደ እድል መጠቀም አለብን ፡፡

ቲቶ (3፡ 3)፡ ጳዉሎስ ቀርጤሳዊያን እንዴት ተጠርተዉ እንደ ነበር ስለሚያዉቅ እርሱና ሌሎች አማኞች በክርስቶስ ፊት የማያስተዉሉ፣ የማይታዘዙ፣ የሚስቱ፣ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያ የሚገዙ፣ በክፋት እና በምቀኝነት እንደሚኖሩ፣ የሚጣሉ፣ እርስ በእርሳቸው የሚጣሉ እንደ ነበሩ በመግለፅ ምላሽ ሰጣቸው ፡፡ የጳዉሎስ ሀሳብ ከየት እንደ መጣን በምናስታዉል ጊዜ በሚገባ ስለሌሎች ተስፋ ስለሚኖረን ነው ፡፡

ቲቶ (3፡ 4-7)፡ ቁጥር 3 ከክርስቶስ በፊት የነበረ መልክ ነበር ፡፡ ቁጥር (4-7) ከክርስቶስ በኋላ የሆነን መልክ ይሰጣል ፤ የአዳኛችንን የእግዚአብሄርን ቸርነትና ፍቅር ተቀብለናል፣ ከታላቅ ምህረቱም የተነሳ በእንደገና ልደት እና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን (ቁጥር 4-5) ፡፡ የእግዚአብሄር ምህረት ሊያፀድቀን እና በእግዚአብሄር ፊት ትክክል ሊያደርገን በአዳኛችን በክርስቶስ በኩል በመትረፍረፍ ስለተሰጠን የዘላለም ህይወት እንዲኖረን በማድረግ ወራሾች ሊያደርገን ይችላል (ቁጥር 6-7) ፡፡

ቲቶ (3፡ 8-11)፡ ጳዉሎስ አማኞች ለመልካም ስራ ራሳቸዉን እንዲያተጉ ደግሞ ተናገረ (ቁጥር 8) ፡፡ ጳዉሎስ ይህ መልካም ምስክርነት እና የሰላማዊ ኑሮ ምስክርነት ስለሆነ አማኞች በዚህ መታወቅ አለባቸዉ አለ ፡፡ ጳዉሎስ የሞኝ ጥያቄዎችን (ዋጋ ቢስ የሆኑ ክርክሮችን) እና የዘር ክርክሮችን፣ ጠበኝነትን (የልዩነት ወሬዎችን) እና ስለህግ የሆነን ክርክር እና ትግልን አስወግዱ (ራቁ) አለ ፤ እነዚህ ለቤተ ክርስቲያን የማያተርፉ እና ለግለሰብ ደግሞ ከንቱ የሆኑ ነገሮች ናቸው - ጥቅም የሌላቸው እና እግዚአብሄራዊ በሆነ አላማ አያገለግሉም (ቁጥር 9) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ከሁለት ማስጠንቀቂያዎች በኋላ ጠማማ(መናፍቅ) የሆነ ሰው ነገርን የሚያጣምም፣ ኃጢዓተኛ እና በራሱ ፈራጅ ስለሆነ ተለይ አለው (ቁጥር 10-11) ፡፡ የደሴት ባህል ተፅዕኖ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሊሆን እንደሚችል አስቡ ፤ ብዙ ደሴቶች ከጠማማ መናፍቅ ሰዎች ካልተለዩ ወደ ደሴት ቤተ ክርስቲያን በቀላሉ ገፍቶ መግባት የቻለ የተለዬ እምነት ወይም ጥንቆላ ወይም የአስማት ባህል ይኖራቸዋል ፡፡

የመናፍቅ አንዱ ትርጓሜ፡ እዉነትን በመዉሰድ ምን አድርጉ ማለት እንደሆነ ከትክክለኛነቱ ዉጪ የሚናገር ማለት ነው ፡፡ ከተገቢነቱ ዉጪ የሆነ እዉነት ማታለል /ሀሰት ነው ፡፡ በጣም ቀላል ማለት እዉነትን ከወንጌል በመዉሰድ መፅሀፍ ቅዱስ ያልሰጠዉን መስፈርቶችን እና ተስፋዎችን መጨመር ማለት ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለልባቸዉ ያሏቸዉን ነገሮች ከኋላ በመመለስ መመልከት ያስፈልገናል ፡፡

ቲቶ (3፡ 12-15)፡ ጳዉሎስ ለቲቶ በመጨረሻ ትዕዛዝ አበቃ ፡፡ ቲቶ በቀርጤስ የእርሱን ቦታ እንዲሸፍኑ አርጢሞንን እና ቲኪቆስን ስለሚልክለት በክረምት በኒቆጵልዮን ከጳዉሎስ ጋር መገናኘት እንደሚችል ነገረው (ቁጥር 12) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ቲቶን በጉዞአቸዉ ዜማስንና አጵሎስን እንዲረዳቸው (የፋይናንሰ ድጋፍ እንዲሰጣቸው) ጠየቀዉ ይህ ከሆነ የሚያስፈልጋቸዉ ሁሉም ነገር ይኖራቸዋል (ቁጥር 13) ፡፡ እንዲሁም ጳዉሎስ ለቲቶ ሰዎቹ የሚያስፈልጋቸዉን ፍላጎቶች ለማሟላት ለመልካም ስራ ራሳቸዉን ማፅናት እንደ ነበረባቸዉ ይህ ከሆነ ፍሬአማ እንደሚሆኑ ደግሞ ነገረው (ቁጥር 14) ፡፡ በመጨረሻም ጳዉሎስ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ጋር ሁሉ ለቲቶ ሰላምታን በመላክ በቀርጤስ ላሉ አማኞችም ሰላምታዉን እንዲሰጥለት ቲቶን ጠየቀው (ቁጥር 15) ፡፡

መደምደሚያ

አብዛኛዉን ጊዜ የቲቶ መፅሀፍ በደንብ የማይታይ ወይም ችላ የተባለ ነው ፤ ብዙ ጊዜ ችላ ብዬዋለሁ ምክንያቱም በጢሞቴዎስ ላይ ስላተኮርኩኝ ፡፡ ነገር ግን አሁን ዛሬ በእኛ ላይ የእግዚአብሄር ጥሪ ምን እንደሆነ ተደንቄአለሁ /አስተዉያለሁ ፡፡ እግዚአብሄር ወንጌሉን ለማቅረብ በትክክለኛዉ ስፍራ ማን እንዳለ አስተዉያለሁ ፡፡

“ እግዚአብሄር ይጠቀምብናል ፤ ቀድማችሁ ስለላካችሁን ለእናንተ ምን እንድናደርግላችሁ የምትፈልጉትን መረዳትን ይሰጠናል “ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ቲቶ (3፡ 1-3 እና 9-10) ስታነቡ እንደ ክርስቲያን በትክክል ልታደርጉት የሚገባችሁ ነገር እንዳለ አይታችኋል ? ይህን ማድረግ እንዴት ማድረግ ትችላላችሁ ?
  2. በቲቶ (3፡ 4-6) ሁሉም ሰዎስቱም የስላሴ ግለሰቦች በአንድ ላይ ሲሰሩ እንዴት ታዩአችዋላችሁ ? በየቀኑ ተግባራት ይህን ይሰማችኋል እንዲሁስ ይታያችኋል ?
  3. በቲቶ (3፡ 5) “ ለአዲስ ህይወት በሚሆን መታጠብ በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን “ የሚለዉ ሀረግ ምን ማለት ነው ? ለመዳን መጠመቅ አስፈላጊ ነው (ሉቃ 23፡ 39-43, ሐዋ 2፡ 21, ኤፌ 2፡ 8-9) ? በመፅሀፍ ቅዱስ አንዳንድ ጥቅሶች ልክ እንደ ማር (16፡ 16) እና ማቴ (28፡ 19) ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሶች የሚፃረሩ የሚመስሉት ለምንድን ነው ? ይህን ላላመኑ ወይም አዲስ ለዳኑ ክርስቲያኖች እንዴት ትገልፁላቸዋላችሁ ? ይህን እንዲረዳችሁ ያዕቆብ 2 አንብቡ ፡፡
  4. በቲቶ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Titus 3:13

“Diligently help Zenas the lawyer and Apollos on their journey,so that they will lack nothing.”

እያንዳንዱ አማኝ ህይወቱን ስለቀየረው የክርስቶስ ፍቅርና ቤዛነት የሚያወራው የራሱ የሆነ ታሪክ አለው ፡፡ ስለ እግዚአብሔር አዳኝ ጸጋ የምታወራው ታሪክ ሌሎችን በጉዟቸው ያበረታታቸዋል ፡፡ ጳውሎስ ቲቶን ኑሮውን በመንፈስ ቅዱስ በደግነትና በየዋኅነት ይኖር ዘንድ ይመክረዋል ፡፡ ጳውሎስ ይህንን እውነት ለቲቶ በመንገር ብቻ አላቆመም ይልቁንም ደግሞ ቲቶ እንደ ዜናስና አጽሎስ ያሉትን ተግቶ በጉዟቸው ይረዳቸው ዘንድ አደራንም ሰጥቶት ነበር እንጂ ፡፡ ጌታ በተጨማሪ ታሪክህን ለሌሎች እንድታካፍል ጠርቶሃል ፡፡

ከክርስቶስ ጋር ባላው ጉዞ የሆነን ሰው ተግተህ እንድትረዳ የምትረዳውን ሰው እንድጠቁምህ ጌታን ጠይቅ ፡፡ ምናልባት እነርሱ ከአንተ የተለየ ስራ ፣ ከአንተ የተለየ ጥሪም ሊኖራቸው ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ተመሳሳይ ነው ፡- እናንተ ሁላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለክርስቶስ ኢየሱስ ልትኖሩ ተጠርታችኋል ፡፡ እግዚአብሔር በማህበረሰቡ ውስጥ ስትኖሩ ክርስቶስን እየተከተላችሁ ያለማቋረጥ እርስ በእርሳችሁ እንድትረዳዱ ይፈልጋል ፡፡ ራስህን አታግልል ፡፡ የሆነ የምትረዳው ሰው ይሰጥህ ዘንድ በጸሎት ጌታን ጠይቅ ፡፡ ጌታ ጸሎትህን ይሰማል ደግሞም ይመልስልሃል ፡፡ በቃ ዝምብለህ ጸልይ ፡፡ ክርስቶስን ስትከተል ፣ እርሱ በመንገድህ እንደሚረዳህ እንደተናገረ ይህንን አስታውስ ፡፡

“ ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ ። “

  • ቲቶ 3፡13

ተጨማሪ ትቅስ

2ኛ ቆሮንቶስ 5:17 — “ ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ፤ አሮጌው ነገር አልፎአል ፤ እነሆ ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል ። “

ያዕቆብ 1:4 — “ ትዕግሥትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም ። “

ቲቶ 3:3–5 — “ እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና ፤ የማንታዘዝ ፥ የምንስት ፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር ፥ የምንጣላ ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን ። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም ፡፡ “