Paul's Letters Titus

Sound Teaching And Christian Living

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Savior Titus 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 571 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለቲቶ የተፃፈዉ መልዕክት በእምነት ለመኖር የሚያነሳሳ መልዕክት ነው ፡፡ ጳዉሎስ ቲቶን ወደ ቀርጤስ በክፉ መንገዳቸዉ እና በዉሸታቸዉ የታወቁ በነበሩት ቀርጤሳዊያን ኑሮ ላይ ልዩነትን እንዲያደርግ ልኮት እንደ ነበር ነገረው፡፡ ደሞሬስት ይህን “ በእረኝነት መልዕክት ዉስጥ የተካተተ በሁሉም ነገር የሚያምር ማጠቃለያ “ በማለት ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

ቲቶ (2፡ 1-5)፡ ጳዉሎስ ቲቶን በምዕራፉ ገልፆአቸዉ ከነበረዉ ነገር በተለዬ መልኩ እንዲያስተምር ነገረው ፡፡ ኃሰተኛ አስተማሪዎች ህግን እና ተረትን ሲያስተምሩ ቲቶ ግን የክርስቶስን ታላቅ ተልዕኮ ለመፈፀም የሚገባዉን ትምህርት ያስተምር ነበር (ማቴ 28፡ 19-20) ፡፡ ይህ ኑሮአችንን እንዴት እንደምንኖር ካልተቀበልን የመፅሀፍ ቅዱስን እዉነት እናምናለን የምንልበት የማስመሰል ከፍታ ነው ፡፡ ኦስዋልድ ቻምበር “ እግዚአብሄር በፍፁም ሆናችሁ የማታዉቁትን የሆነ ነገሮች እንድትሆኑ በፈለገ ጊዜ አንዴ የነበራችሁትን ተመልሳችሁ በማሰብ አስታዉሉ “ በማለት ፃፈ ፡፡

ጳዉሎስ ኖሮባቸዉ የነበረው የግሪክ-ሮም ሁለት የእድሜ ክፍሎች ነበሩ - ወጣትና እና ትልቅ ፡፡ ያ ባህላችን ሰዎችን ወደ ብዙ ትዉልድ ክፍሎች ከሚከፍልበት መንገድ በጣም የተለዬ ነው ፡፡ እነዚህ ሁለት ክፍሎች ቀድሞ በሚታወቁ ቡድኖች ላይ የወደፊትን ኃላፊነትን ለማስቀመጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ነበሩ ፡፡ ጳዉሎስ ሽማግሌዎችን ልከኞች እና ጭምተኞች እንዲሆኑ ነገራቸው (ቁጥር 2) ፤ በጉባኤዉ ዉስጥ ለወጣት ሰዎች ምሳሌ/መሪዎች መሆን ይጠበቅባቸዉ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ የተሰጣቸዉን ዘመን በጥበብ እና በማስተዋል/በብስለት መሄድ አለባቸዉ አለ ፡፡ ሽማግሌዎች በእምነት፣ በፍቅር፣ በትዕግስት እና በተስፋ የፀኑ መሆን አለባቸው (1ተሰ 1፡ 3) ፤ መታገስ የሚለዉ ቃል በመፅናትና በመንቃት መጠበቅ ማለት እንጂ በመፍዘዝ መጠበቅ ማለት አይደለም ፡፡ “ ሽማግሌ ሰዎች ወደ ቀጣዩ አለም እስኪሄዱ ድረስ በትዕግስት ብቻ የሚጠብቁ ብቻ አይደሉም ፤ የህይወትን ፈተና በንቃት ይታገሳሉ - የሽምግልና እድሜ ፈተናም ቢሆን “ ፡፡

አሮጊቶች በባህሪያቸዉ አምላክን በማወደስ ምሳሌ በመሆን በቤታቸዉ መልካም ምን እንደ ሆነ ለወጣት ሴቶች በመልካምነት መኖርን ያስተምራሉ (ቁጥር 3-4) ፡፡ “ በተመሳሳይ መንገድ “ ማለት ከሽማግሌዎች እና ከአሮጊቶች ይጠበቅ በነበረው መካከል ልዩነት የለም ነበር ማለት ነው ፡፡ “ በአምልኮ ባህሪይ ምሳሌ መሆን “ የሚለዉ ሀረግ ተግባራቸዉን እንደሚፈፅሙ እንደ ካህናት መረዳት ይቻላል ፡፡ አሮጊቶች መላዉ ኑሮአቸዉን እግዚአብሄርን እንደሚያመልክ ማየት ነበረባቸው (ሮሜ 12፡ 1) ፡፡ ለኃሜተኞች የተጠቀመዉ ቃል ለክፉ ከተጠቀመው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ያ ማለት አሮጊቶች ወይም በዚህ ጉዳይ ሌላ ማንኛዉም ሰው - ኃሜት እና አሉባልታ የክፉን ስራ ይሰራሉ ፡፡ በሮም እና በግሪክ ባህል ብዙ ወይነ ጠጅ መጠጣት የአሮጊቶች የተለመደ መዉደቂያ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ትርጉሙ “ ባርነት “ (RSV ይህን “ የመጠጥ ባሪያ “ በማለት ይተረጉመዋል) የሚል በሆነው ዶሎ በሚል ግስ ገልፆታል (ቁጥር 3) ፡፡ ጳዉሎስ ቲቶን ሽማግሌዎችን እና ወጣት ወንዶችን፣ አሮጊቶችን እና ባሪያዎችን እንዲያስተምር ነገረው ነገር ግን ወጣት ሴቶችን አላለዉም ፤ ቲቶ አሮጊቶችን ወጣት ሴቶችን እንዲያስተምሩ እያዘጋጃቸዉ እና እያበረታቸዉ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ጳዉሎስ አሮጊቶችን ባሎቻቸዉን እና ልጆቻቸዉን እንዲወዱ ነገራቸዉ ምክንያቱም እግዚአብሄር ለባሎቻቸዉ እና ለልጆቻቸዉ ተፅዕኖ እና እርዳታ የሚያደርግ ስልጣንን ሰጥቷቸዉ ስለ ነበር ፡፡ ድጋፋቸዉን እና ተፅዕኖአቸዉን እንዲበልጥ ለፍቅር ይፈቅዱ /ይተዉት ነበር ፡፡ አስታዉሉ እዚህ ጋር ያለዉ መታዘዝ የጋራ እና መፅሀፍ ቅዱሳዊ መታዘዝ ነው (ኤፌ 5፡ 21-33) ፡፡ ክርስቲያኖች በመፅሀፍ ቅዱሳዊ መልካም አኗኗር በማይኖሩ ጊዜ ጌታን በማያዉቁት መካከል የእግዚአብሄር ስም ይጠፋል/ይታማል ፡፡

የመልካም ሚስት እና እናት አስፈላጊነት በፍፁም እንደማይቀየር አስተዉሉ ፤ ይሁን እንጂ ይህ ትርጉም የተለዬ ነው፡፡ በቀርጤስ ወጣት ሴቶች ስለ ጋብቻና እናትነት ምንም አማራጭ አልነበራቸዉም፣ ለወጣት ሴቶች በዉጪ ብቸኛዉ ስራ ሴተኛ አዳሪነት ነበር ፡፡ ጳዉሎስ የሴቶችን ስፍራ ለባሎቻቸዉ አገልጋይ እንዲሆኑ ብቻ አልወሰነም በጊዜዉ በነበሩበት ስፍራም በመድረስ ነበር እንጂ ፡፡ ደሞሬስትወደ ክርስቶስ የሚመጡ ሰዎች ራሳቸዉን የአንዱ አካል ሙሉ ክፍል እንደሆኑ እንዳዩ ይገልፃል፡

“ ሴቶችን እንደ በታች እና እንደ ለፍላፊ ከሚታዩበት- እና ባርነት እንደ ቀላል ነገር ከሚታይበት ስፍራ ለተነሱ ሰዎች የክርስቲያን አመለካከት ሙሉ ለሙሉ የተለዬ አመለካከት እና አስተሳሰብ የሚያስተዋዉቅ መንገድ ነበር ፤ ይህ የማህበረሰቡን ዉጫዊ ቅርፅ በመቀየር በታሪቅ የተረጋገጠ ነው ፤ ነገር ግን በዚህ እና በሌላ ስፍራ በሰዎች ግንኙነት በወንጌል የተፈጠረዉን ዉጥረት መረዳት አለብን ….፡፡ የቀድሞ ክርስቲያን በክርስቶስ ያላቸዉን አዲስ ነፃነት በዙሪያቸዉ ካለዉ ከሚያስጨንቀዉ መዋቅር ጋር እንዴት እንደሚያገናኙት ታገሉ “ ፡፡

ቲቶ (2፡ 6-8)፡ ጳዉሎስ ወጣት ወንዶችን ለእነርሱ በሆነዉ መስፈርት “ በተመሳሳይ መንገድ “ ደረሷቸዋል (ቁጥር 6) ፤ ይህ ወጣት ወንዶች ወጣት ሴቶች፣ አሮጊቶች እና ሽማግሌዎች መማር የሚያስፈልጋቸዉን ሊማሩ እንደሚያስፈልጋቸዉ ያሳያል ፡፡ ጳዉሎስ ለወጣት ወንዶች ለአንዳንድ ወጣት ወንዶች ፈተና የሆነዉን (“ በሁሉም ነገር ራሳቸዉን የገዙ እንዲሆኑ) እንዲብራራ አንድ ትዕዛዝን ሰጠ ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ቲቶን ለወጣት ወንዶች በመልካም ስራዉ፣ በሐቀኝነቱና በመልካም ትምህርቱ ምሳሌ እንዲሆናቸው ነገረው (ቁጥር 7) ፡፡ ጌታን በሚገባ እየተከታተለ ካልነበረ ምሪቱን በሚገባ ሊቀበሉት አይችሉም ፡፡

ቲቶ (2፡ 9-10)፡ ጳዉሎስ ባሪያዎች ለእግዚአብሄር ትምህርት መታመናቸዉን ለማሳየት ለጌቶቻቸው የሚታዘዙ፣ የሚያስደስቱ፣ የሚያከብሩ እና ትህትናን ያሳዩ ነበር አለ ፤ ይህ ፅሁፍ በታሪካዊነት ክርስቲያንን ከባርነት ነፃ ለማዉጣት ጥቅም ላይ ቢዉልም ከጳዉሎስ ፍላጎት ተፃራሪ ነው ፡፡ የጳዉሎስ መልዕክት ክርስቲያን ለነበሩ እና እንደ ባሪያ በመጠቀም የተናቁ ቢሆኑም እንኳን የክርስቲያን አኗኗርን ለሚኖሩ ባሪያዎች የታዘዘ ነበር ፡፡ ይህ በራሳቸዉ ባሮች ላይ በግሪክ እና በሮም በሁለቱም የተለመዱ ስፍራዎች በዘመኑ ባህል በክርስቶስ ያለን ነፃነት አቀረበ ፡፡ በቀድሞ አለም ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በማህበራዊ አቀማመጥ ጌቶችን እና አገልጋዮችን በመቀላቀል ታላቁን ባህል አናዉጠዉታል ፡፡ የኔ ስሜት ጳዉሎስ ክርስቶስን በመከተል የመጣዉ ለዉጥ ቀስ በቀስ በአለም ላይ ባርነትን እንደሚያስወግደዉ እንዳመነ ነው ፡፡ ዴሞሬስት “ ይህ ለመታዘዝ መምረጥ የባሪያዎች ስጦታ ነው - ያለ አግባብ ቢሆንም እንኳን -ወንጌል በሚገባ ያጌጠ አድርጎ በመስራት “ በማለት ፅፏል ፡፡

ቲቶ (2፡ 11-14)፡ እነዚህ ጥቅሶች በአንድ አንቀፅ ዉስጥ ወንጌልን ይሰጣሉ ፡፡ እግዚአብሄር ለህዝቦች ሁሉ ድነትን አምጥቷል ፡፡ እግዚአብሄር ለአንዳንዶች የፀጋ ወንጌል ለሌሎች ደግሞ የህግ ወንጌል ወይም የራስን ማፅደቅ ወንጌል የለዉም (ቁጥር 11) ፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ ከቀድሞዉ ኃጢዓተኝነታችን እና አለማዊ ምኞታችን በማስካድ በመተው እና እንድናስወግድ ያስተምረናል (ቁጥር 12) ፡፡ በክርስቶስ ሁለት መልክ መካከል በጊዜአዊነት ስንኖር - በተስፋ እና ዘመናችን የተቆጠረ እንደሆነ እንድናዉቅ እድልን ይሰጠናል (ቁጥር 13) ፡፡ ከቁጥር 14 ጉዚክ “ የኢየሱስ ስራ ሁሉም ይህ መግለጫ አስፈላጊ/ጠቃሚ ነው “ በማለት ፅፏል ፡፡ ኢየሱስ (ፍቃደኛ ስለነበር) ራሱን (መስጠት የቻለዉን ሁሉ) ለእኛ (ለኃጢዓተኛዉ ሰዉ እንደ ምትክ) ሰጠ ፡፡ በዚህ ትርጉምም ምን ያክል ለክርስቶስ የተወደድን እና የከበርን እንደሆንን መማር እንችላለን ምክንያቱም ስለ እኛ በፍቃደኝነት ካደረገዉ ነገር የተነሳ - የራሱ ንብረት ሰዎች ስላደረገን ፡፡ ከሌላዉ ከሁሉም ንብረቶች በላይ የእርሱ ንብረቶች ነን ፡፡ ጳዉሎስ ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር የተመረጡ ንብረቶች አንድ መለያን/ባህሪን ተናግሯል - የእግዚአብሄር ፍቅር እና የማዳን ፀጋ እዉነት የብርሃን ምስክሮች ለመሆን መጓጓት ነው ፡፡

ቲቶ (2፡ 15)፡ አንድ ቀን የእግዚአብሄር የፅድቅ እነ የማዳን አገዛዝ የእምነት ጉዳይ ሳይሆን በሙሉ የሚታይ ይሆናል (ቁጥር 15) ፤ ስለሆነም የቤተ ክርስቲያን የሁል ጊዜ ፀሎት “ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና ! “ (ራዕ 22፡ 20) ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ ተመልሶ የሚመጣ ስለሆነ ተልዕኮ አለን ፡፡ በአገልግሎት እንድንመለከት ሳይሆን እንድንሳተፍ ተጋብዘናል ፡፡ በህይወታችሁ ዉስጥ ኢየሱስ በቅርብ ተመልሶ እንደሚመጣ በእርግጠኝነት ለማወቅ ምን ሲሻሻል ማየት ትፈልጋላችሁ ? ከእግዚአብሄር ፀጋ የተነሳ የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች በቸርነት ኃይለኛ የሆነ ህይወት እንዲኖሩ እና ተመልስ መምጣቱን በሁል ቀን ኑሮአቸዉ በመመልከት እንዲኖሩ ተመርጠዋል (ቲቶ 2፡ 13) ፡፡ አዳኙ ለራሱ የተለዬ ህዝብ አድርጎ እንዳነፃን የታላቅ አምላካችን እና አዳኛችን የከበረ መገለጥን በተቀበልነዉ ጥሪ እንደሚገባ በመጓጓት መጠበቅን በረሳናቸዉ ክስተቶች እና ክርክሮች በመወዛገብ ደንግጠናል ፡፡

7 Guzik.

  1. Gary Demarest, The Communicator’s Commentary: 1, 2 Thessalonians, 1, 2 Timothy, Titus (Waco, TX: Word Books, 1984), p. 311.

  2. Demarest, p. 311.

  3. David Guzik, Enduring Word Bible Commentary; available at https://enduringword.com/bible-commentary/titus-2/.

  4. Demorest, p. 315.

  5. Demorest, pp. 315-316.

  6. Demorest, p. 320.

ጥያቄዎች

  1. ጳዉሎስ ሽማግሌ ወንዶች እና አሮጊት ሴቶች እንዲያደርጉ ምን አዘዛቸው ? በእናንተ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሲሆን ታያላችሁ ?
  2. ጳዉሎስ ቲቶን ወጣት ወንዶች በቤተ ክርስቲያን ስለሚያደርጉት እንዲያበረታቸዉ ምን ጠየቀው ?
  3. ባሪያዎች/አገልጋዮች ማስወገድ የነበረባቸዉ ሰዎስት ኃጢዓቶች ምን ነበሩ (ኤፌ 6፡ 5-8) ? ከልብ ሳይሆን በድርጊት ብቻ መታዘዝ የሚቻል ነው (ኤፌ 6፡ 6) ? አገልጋይ ወይም በነፃ የሚያገለግል የሚለዉ ቃል እንደ አማኝ በእኛ ላይ እንዴት ይተገበራሉ ? (1ቆሮ 7፡ 22)
  4. በቲቶ (2፡ 11-13) ጳዉሎስ የክርስቶስ ምን ሁለት መልክን ጠቀሰ ?
  5. ጳዉሎስ ከድነት በኋላ እንዴት እንደሚኖር ምን ትዕዛዝን ሰጠ ? በዚህ መንገድ መኖርን እንዴት እንፈፅማለን ? (ዮሐ 14፡ 16, 15፡ 5)
  6. በቲቶ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Titus 2:14–15

“He gave Himself for us to redeem us from all lawlessness and to cleanse for Himself a people for His own possession, eager to do good works. Say these things, and encourage and rebuke with all authority. Let no one disregard you.”

ጳውሎስ ቲቶን አስፈላጊ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ትምህርት ላይ ሳያወላውል ጸንቶ በስልጣን ማዘዙን ፣ መምከሩንና መገሰጹን እንዲቀጥል አዘዘው ፡፡ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ቲቶን አስታወሰው ፡- በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው አንተና እኔ ከህግ ሁሉ ተዋጅተን እንደ እግዚአብሔር ህዝብ የጸደቅነው ፡፡ ስለተቀበሉት ጸጋና ምህረት ሌሎች ያዩ ዘንድ በጎ ስራን ለመስራት እንድናፍቁ እንድተጉ መከራቸው ፡፡

እግዚአብሔር ይህን ጽኑ የወንጌል መልዕክት እንድትናገር ፣ ሌሎችን እንድታበረታና በቃሉ እውነት ላይ ቆመህ በስልጣን እንድትገስጽ ያዝሃል ፡፡ ለዚህ ጥሪ እውነተኛ ፣ ንጹህ ፣ ታማኝ ለመሆን ደግሞም ወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ለመምከር ጊዜን የመውሰድ ኃላፊነት አለብህ ፡፡ ኑሮህን ለክርስቶስ ስትኖር በዙሪህ ያሉትን ሰዎች ለማየት አይኖችህን ክፈት ፡፡ ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት አስፈላጊውን እውነት ተናገር ፡፡ ሁልጊዜም ምከር ፡፡ መንፈስም በልብህ ሲመላለስ ተግሳጽ በሚያስፈልግበት ጊዜ እግዚአብሔር የራሱን ሰዓት ያሳውቅህ ዘንድ ጸልይ ፡፡ ከኢየሱስ ቀድመህ ስለተቀበልከው ፍቅር ዛሬ ይህን በጎ ስራ ለመስራት ትጋ ፡፡ በእርሱ ስም ስትወጣ ታላቅ ፍቅሩ ያነቃቃህ ፡፡

“ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል ። ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም ፤ ማንም አይናቅህ ። “

  • ቲቶ 2 ፡14-15

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 28:19–20 — “ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ።

2ኛ ጢሞቲዎስ 4:2 — “ ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም ። “

ቲቶ 2:1 — “ አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር ። “