Paul's Letters Titus

God Our Savior

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Savior Titus 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 570 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ለአንድ ግለሰብ በሜደትራሊያ ባህር ላይ ካለ ደሴት ከቀርጤስ ለሆነ ለቲቶ ለሌኛዉ የጳዉሎስ መልዕክት ነው ፡፡ ቲቶ በአዲስ ኪዳን አስራ ሰዎስት ጊዜ ተጠቅሷል ፡፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን በመቄዶንያ በኩል እየተጓዘ በነበረ ጊዜ በሮም እስራት መካከል ፃፈው (ከክርስቶስ ሞት 62-64 በኋላ) ፡፡ ይህ ምናልባት አራተኛወ የአገልግሎት ጉዞዉ ነበር ነገር ግን ሉቃስ የሐዋሪያት ስራ መፅሀፍን ከጨረሰ በኋላ የተከናወነ ነበር ፤ ስለዚህ ቲቶ ከቆሮንቶስ ወይም ኒኮፖሊስ በ 1 እና በ 2 ጢሞቴዎስ መካከል የተፃፈ ነበር ፡፡ በቲቶ (3፡ 13) መሰረት መልዕክቱ በሕግ አዋቂዉ ዜማስና አጵሎስ የተወሰደ ነበር ፡፡

ምናልባትም ጳዉሎስ ቲቶን በመጀመሪያዉ የአገልግሎት ጉዞ ወይም ከዚያ በፊት ወደ እምነት መራው ፡፡ ጳዉሎስ በመጀመሪያዉ እስራቱ ወደ ሮም በተወሰደ ጊዜ በሚገባ ሰርጤ ላይ አርፈዋል ፤ ቆይቶም ጳዉሎስ ከእስራት ከተለቀቀ በኋላ ወደ ቀርጡስ በመመለስ በሰርጤ ለማገልገል ቲቶን ከእርሱ ጋር ወሰደው ፡፡ ጳወሎስ ከዚያ በተጓዘ ጊዜ በዚያ አገልግሎቱን እንዲቀጥል ቲቶን ተወው ፤ ቆይቶም ጳዉሎስ አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን በዚያ አገልግሎትን እንዲያደርጉ ስለላካቸዉ ቲቶ በክረምት ከጳዉሎስ ጋር በኒክፖሊስ መገናኘት ይችላል (ቲቶ 3፡ 12) ፡፡ በ 2ቆሮንቶስ ጳዉሎስ “ ወንድሜ “ (2ቆሮ 2፡ 13) እና “ ቤተሰቤና የስራ አጋሬ “ (2ቆሮ 8፡ 23) ብሎ በጠራዉ ጊዜ ቲቶ ተጠቅሷል፡፡ ሁልጊዜ ጳዉሎስ ቀይሮ ስለነበረዉ ፀጋ የሚመለከት ስለሚመስል በአገልግሎት በተሸለ የት ስፍራ እንደሚስማሙ ያውቃል ፡፡ ቲቶ የኃሰት ትምህርቶችን አላማ/ትኩረት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስለነበሩ ኃሰተኛ አስተማሬዎች እና ጳዉሎስን እና በርናባስን ወደ ኢየሩሳሌም ሸንጎ የወሰዱትንም እንኳን ያስተዉል ነበር (ሐዋሪያት ስራ 15) ፡፡

ጳዉሎስ ሐዋሪያዊዉ መሪ ጀምሮት የነበረዉን አገልግሎት እንዲቀጥሉ ጢሞቴዎስን እና ቲቶን ሁለቱንም በየስፍራቸዉ ተዋቸው ፡፡ ጳዉሎስ ሁለቱንም ስፍራ ቢተዉም በፀሎቱና በመልዕክቱ በሁለቱም ወጣት ሰዎች ላይ ማስተማሩን/መምከሩን ቀጥሏል ፤ ለአገልግሎት የሚያስደንቅ ምሳሌ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ከቲቶ ወይም ከሌላ ሰዉ በቀርጤስ እየሆነ ስለነበረው ተቀብሎት ስለ ነበረዉ መልዕክት ምላሽን ለቲቶ ፃፈ ፡፡ ማክአርቱር የጳዉሎስ መልዕክት በአስተምሮዉ ላይ ምንም ነገርን እንዳላካተተ ምክንያቱም በቲቶ “ ስነ መለኮታዊ መረዳትና ማሳመን “ ሙሉ እምነት እንደ ነበረዉ ያመለክታል ፤ ከዚያ ይልቅ ጳዉሎስ ቲቶን በሰርጤ ስላሉ ሐሰተኛ አስተማሪዎች አስጠነቀቀው ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ በሰርጤ ገና ልጆች ያልበሰሉ አማኞች ናቸዉ ምክንያቱም በዚያ የነበረዉ አገልግሎት ገና አድስ ስለ ነበር ፡፡ ማክአርቱር በሰርጤ ያለዉን ሁኔታ፡ “ በእንደዚህ አይነት ሰዎች መካከል ስለ ወንጌል መሰማትን ለማግኘት ለወንጌል የአማኞች የመጀመሪያዉ ዝግጅት በእነርሱ መካከል ወራዳነት ከሆነው ከኃሰተኛ አስተማሪዎች ኑሮ (ቲቶ 1፡ 10-16) ጋር በማነፃፀር የማያከራክር በቅድስና፣ በፍቅር፣ በጭምተኛነትና በመልካም ኑሮ ምሳሌነት ይኖሩ እንደ ነበር ( ቲቶ 2፡ 2-14) “ ይገልፃል ፡፡ በሰርጤ የነበረዉ ስራ በተለዬ አስቸጋሪ ነበር ምክንያቱም በዚያ የነበሩ ሰዎች “ ሁልጊዜ ዉሸተኞች፣ ክፉ አዉሬዎች እና ስራ ፈቶች “ ነበሩ (ቲቶ 1፡ 12-13) ፡፡

ሐዋ (2፡ 11) ከቀርጤስ የነበሩት ሰዎች በበዓለ ኃምሳ ቀን ላይ እንደ ነበሩና በመንፈስ ቅዱስ እንደተናገሩ ይናገራል ፡፡ ምናልባትም ይህ የክርስቶስ ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቀርጤስ የመጣበት ነው ፡፡ ጳዉሎስ ቀድሞ መንፈስ ቅዱስ ቀርጤስን ደርሶአት እንደ ነበር ያውቃል ፤ መንፈስ ቅዱስ ከጳዉሎስ በፊት ሄዶ ነበር ፡፡

ትምህርት

ቲቶ (1፡ 1-4)፡ በቁጥር 1-2 ጳዉሎስ ሰላምታን በማምጣት ጥሪዉን በመልካምነት እምነትን ለመገንባት እና እግዚአብሄር ተስፋ ገብቶት በነበረዉ ዘላለማዊ እዉነት እንደ ነበር ይናገራል ፡፡ በዚያ ጥሪ እርግጠኛ መሆን ችሏል ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለማይዋሽ ፤ በእርግጥ በቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሄር ለመቅጣት የወሰደዉ የመጀመሪያዉ ቅጣት በአናንያ እና በሰፒራ የተመዘገበ ነበር (ሐዋ 5፡ 3) ፡፡ በ 1ጢሞ (4፡ 1-2) ጳዉሎስ በሚመጣዉ ጊዜ “ በዉሸት ማስመሰል በኩል “ ከእምነት በመለየት፣ የሚያታልሉ መናፍስቶች እና የሰይጣን አስተምሮዎች ይኖራሉ አለ ፡፡ እግዚአብሄር ሊዋሽ አይችልም ! ጳዉሎስ በአዳኛችን በተገለጠዉ መልዕክት በእግዚአብሄር የታመነ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 3) ፡፡ እንደ አዲስ ኪዳን አማኝ በተለዬ እግዚአብሄርን እንደ አዳኛችን አንናገርም ነገር ግን ያ በመላዉ ብሉይ ኪዳን ዉስጥ ያለ ስር ነው ፤ በዚያም ምክንያት ለቲቶ መፅሀፍ ፍሬ ነገሩ/ጭብጡ አዳኝ የሚል ነው፡፡ እግዚአብሄር በመስቀል ላይ በልጁ ስራ ያዳነን አዳኝ ነው ፤ ድነት ለራሳችን የምናደርገዉ ምንም ነገር ነው ፡፡ በክርስቶስ ፀድቀናል (ጻድቅ ተደርገናል) ፤ ሁላችንም ኃጢዓተኞች ነን በመስቀል ላይ በክርስቶስ ሞት የዳንን ነን ፡፡ ለቲቶ የተላከዉ መልዕክት ስለ እግዚአብሄር አዳኝነት ትልቅ ጭብጥ አለው ፡፡

ቲቶ (1፡ 5-9)፡ በቁጥር 5-9 ጳዉሎስ ለሽማግሌነት የሚያስፈልጉትን ባህሪያት ሰጥቷል ፤ እነዚህ፡ 1) የሚያምኑ ልጆች ያሉት፣ 2) የእግዚአብሄር ባላደራ የሆነ፣ 3) የማይኮራ ወይም የማይጨቃጨቅ፣ 4) የማይበሳጭ፣ 5) መልካም የሆነዉን የሚወድ፣ 6) ፃድቅ የሆነ፣ 7) ቅዱስ የሆነ፣ 8) ራሱን የሚገዛ እና 9) ለክርስቶስ መልዕክት የታመነ የሆነ ፡፡ ይህ ዝርዝር በ 1ጢሞቴዎስ 3 ካለዉ ዝርዝር በጥቂት ይለያል ፡፡

ቲቶ (1፡ 10-16)፡ በቁጥር 10-16 ጳዉሎስ ስለ ኃሰተኛ አስተማሪዎች ምን ይመስሉ እንደ ነበርናለምን በኃሰት ያስተምሩ እንደ ነበር አስጠነቀቀው ፡፡

መግቢያ

ጳዉሎስ ስለ ኃሰተኛ አስተማሪዎች “ እግዚአብሄርን እንዲያዉቁ በግልጥ ይናገራሉ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ስራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ በስራቸዉ ይክዱታል “ በሚል ማስጠንቀቂያ ይዘጋል (ቁጥር 16) ፡፡ ሀሰተኛ አስተምሮን እና ሐሰተኛ አስተማሪዎችን በሚገባ በደንብ መመልከት አለብን ምክንያቱም በአዳኛችን በእግዚአብሄር በመዳን ጻድቅ ስለተደረግን ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ቲቶ አይሁዳዊ ወይስ አሕዛብ ነበር (ገላ 2፡ 3) ? ልክ በጢሞቴዎስ እንዳደረገው ጳዉሎስ ቲቶን በእምነት “ እዉነተኛ ልጄ “ በማለት ጠራው (1ጢሞ 1፡ 2, ቲቶ 1፡ 4) ፤ በዚህ እንዲህ ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  2. በቀርጤስ ጳዉሎስ ቲቶን ለምን ተወው ? በሁሉም ከተማ ሽማግሌን ለመሾም ቲቶ ምን መስፈርቶችን እየተመለከተ ነበር ?
  3. በቀርጤስ የነበሩት ሐሰተኛ አስተማሪዎች ጢሞቴዎስ በኤፌሶን ገልፆአቸዉ ከነበሩት ጋር እንዴት ይመሳሰሉ ነበር (1ጢሞ 1፡ 3-7) ? ቲቶ ለኃሰተኛ አስተማሪዎች እንዴት ምላሽ ይሰጥ ነበር ? (ሮሜ 16፡ 17-18)
  4. ጳዉሎስ ኃሰተኛ አስተማሪዎች የተመረዙ ወይም የረከሱ እንደ ነበሩ እንዴት አለ (ማቴ 15፡ 15-20) ? በህይወት ዘመናችሁ ቲቶ (1፡ 15-16) የሚያረጋግጥ ነገር አይታችኋል ?
  5. እግዚአብሄርን አዉቃለሁ በማለት ነገር ግን በመታዘዝ ያለመኖር አደጋዉ ምንድን ነው ?
  6. በቲቶ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Titus 1:16–17

“They profess to know God, but they deny Him by their works. They are detestable, disobedient, and disqualified for any good work.”

ጳውሎስ ይህን መልዕክት የጻፈው በቀርጤስ እያገለገለ የሚገኘውን ቲቶን ለመምከር ነው ፡፡ ጳውሎስ የቀርጤስን ሰዎች አስጸያፊዎች ፣ የማይታዘዙና ለበጎ ስራ ያልበቁ አድርጎ ይገልጻቸዋል ፡፡ እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ ያውጃሉ ነገር ግን በስራቸው ይክዱታል ፡፡ ጌታ ቲቶን የጠራው እነርሱን ይገስጻቸው ዘንድ ደግሞም በእምነታቸው ይበረቱ ዘንድ እንድመክራቸው ነው ፡፡

እንደ ቲቶ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ኑሯችሁን ለጌታ ስትኖሩ በከንፈራቸው እግዚአብሔርን እንደሚያምኑ በሚናገሩ ነገር ግን በስራቸውና በንግግራቸው ከዚህ የሚቃረን ነገር በሚያሳዩ ሰዎች እንደተከበባችሁ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? እግዚአብሔር እንደዚህ ወዳለ ቦታ ከመራችሁ እርሱ በዙሪያችሁ ያሉትን ሰዎች መርዳት ማገዝ የምትችሉበትን ጥበብ በመስጠት እንደሚያበረታችሁ እርግጠኛ ሁኑ ፡፡ ኃይማኖታችሁንም በእውነት በመኖር ብርሃን ሁኑ ፡፡ በህይወታችሁ ስላለው የጌታ ጸጋና ምህረት ተናገሩ ፡፡ ስለተግዳሮቶቻችሁና ስለፈተናዎቻችሁ ግልጽ ሁኑ ከዚያም ከሞት ስለተናሳው አዳኝ መስክሩ ፡፡ ስጋችሁ ሲደክም የእርሱ ኃይል ብርታትን ይሰጣችኋል ፡፡ መንፈሳችሁም ሲደክም ኃይሉ ተስፋን ይሰጣችኋል ፡፡ ምንም በሌላችሁ ሰዓትም ኃይሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ ለሚናገሩ ነገር ግን ንግግራቸውና ስራቸው ከዚህ ለሚቃረን ሰዎች ጸልዩ ፡፡ በህይወታችሁ ያለው የእግዚአብሔር ኃይል ሌሎች ኑሯቸውን ለእርሱ ይኖሩ ዘንድ ያስተምር ይምከርም ፡፡

“ እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል ። “

  • ቲቶ 1፡16

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 29:13 — “ ጌታም ፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና ፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና ፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና ::

ማቴዎስ 15:8 — “ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው :: “

ቲቶ 1:5 — “ ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም ፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ ፡፡ “