A Well-lived Life
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Righteous Judge 2 Timothy 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለጢሞቴዎስ የጳዉሎስን ሁለተኛ መልዕክት ስንዘጋ ጳዉሎስ ስለ ክርስቶስ ቃል የጳዉሎስን መነሳሳት ጢሞቴዎስ በእርግጠኝነት እንደተረዳዊ ስሜታዊ እንደ ነበር አስባለሁ ፡፡ ጳዉሎስ ተልዕኮዉ እርሱን በተከተሉት እንደተነሳ እና እንደተሸከሙት እርግጠኛ መሆን ፈለገ ፡፡ ይህ መልዕክት የጳዉሎስን የመቸረሻ ንግግር እንዲሁም ደግሞ በሚገባ ስለኖረዉ የህይወቱ ምስክርነት ይይዛል ፡፡ ለእናንተ ፀሎቴ አንድ ቀን ባለፈዉ ህይወታችሁ ላይ ተመልሳችሁ መመልከት በመቻል ኑሮአችሁን ለክርስቶስ በሚገባ መኖራችሁን እንድታዉቁ ነው ፡፡
ሁለተኛ ጢሞቴዎስ ለቤተ ክርስቲያን የተለዮ ቦታን ይዟል ፡፡ (ከእያንዳንዳቸዉ ምዕራፍ) አራት ቃላቶች የጳዉሎስን ትዕዛዝ ለጢሞቴዎስ ያጠቃልላሉ ፤ በምዕራፍ 1 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የእርሱን መልዕክት የማይደግፈዉን በአለማዊ ልማድ የሆነዉን መልዕክት እንዳይወሰድ ፀንቶ እንዲቆም አበረታታው ፡፡ በምዕራፍ 2 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ጳዉሎስ ከማንኛዉም ነገር በላይ ተሸክሞት ስለ ነበረዉ መልዕክት እንዲፀና ነገረው ፡፡ በምዕራፍ 3 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በመጨረሻዉ ዘመን ምን እንደሚመጣ እንዲያስተዉል እና ለመጨረሻዉ ዘመን እንዲዘጋጅ ነገረው ፡፡ በምዕራፍ 4 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ተቀብሎት በነበረዉ ጥሪዉ እንዲቀጥል ነገረው ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እንዲሰራ ተዘጋጅቶበት የነበረዉን ነገር በማድረግ እንዲቀጥል ፈለገ ፡፡
ትምህርት
2-ጢሞቴዎስ (4፡ 1-5)፡ ጳዉሎስ የቤተ ክርስቲያንን ድርጅቶች የመምርመር/የመጠበቅ እና የክርስቶስን መልዕክት የመሸከም ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር ፡፡ በኋላም ሐዋሪያዉ ዮሐንስ የመጨረሻዉ ዘመን መልዕክት ኃላፊነትን ይቀበላል ፡፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ በእምነት የሆነዉን ልጁን እርሱ ፈፅሞት የነበረዉን ተግባር ኃላፊነት ይሰጠዋል ፡፡ ዮሐ (16፡ 7-8) አንብቡ ፤ ኢየሱስ እርሱ በሄደ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በመምጣት (ወደ መካከል መልሶ በመዉሰድ እንደገና ይገልፃል) ኃጢዓትን፣ ፅድቅን እና ፍርድን እንደገና ይገልጣል አለ ፡፡ ቁጥር 2 እንደ እኛ መነሻነት በዮሐንስ 16 ወደ ጥቂት ክፍሎች እንከፋፍለው፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን፡
- እንዲሰብክ (በህዝብ ፊት በመቆም በግልፅ ቃሉን መናገር)
- በወቅቱ የተዘጋጀ እንዲሆን (መቼም ቢሆን የመጣዉን እድል ለመጠቀም የተዘጋጀ እንዲሆን)
- ወቅቱ/ጊዜዉ ሳይመችም (የማይመች ጊዜ እንኳን ቢሆንም)
- እንዲበረታ (በእርሱ ላይ በሚመጣዉ በመንፈስ ቅዱስ ስራ ፓራካልዮ )
- በሁሉም መከራ (በጽናትና በትዕግስት)
- እንዲያስተምር (እንዲያዝ) ነገረው ፡፡
“ ዳግም የተወለድን “ ሁላችንም ከመንፈስ የተወለድን ነን ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ዉስጥ ያለ እና በእኛ የሚሰራ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በፅድቅ መስፈርት መሰረትም ስለ ኃጢዓቴ በመዉቀስ በእኔ ላይ ባሉ ነገሮች ይፈርዳል ፡፡ ሁሉም መንፈስ ቅዱስ የሚያደርገዉ ክርስቶስን የሚያረጋግጥ ነው ፡፡ ወደፊት ወደ አለም በሚመጣው በዉስጤ ባለዉ ተወቅሻለሁ ምክንያቱም በእኔ ዉስጥ ክርስቶስ ስላለ ነው ፡፡ ወደ ቁጥር 2 በመመለስ እንደዚህ እንኳን ባይሰማችሁ ፅኑ ፤ የሚመች እና የማይመች በሚሆን ጊዜም የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ዉስጥ እየሰራ ከሆነ በማበረታታት እና በማስጠንቀቅ ይህን ወደ ሌሎች ለማምጣት ቀላል ይሆናል ፡፡ በትክክል ሰዎችን ከኃጢዓት ፍርድ ወደ ህይወት መንገድ ማምጣት እንጀምራለን ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በመፅናት በቀጥታ እንዲመላለስበት ይነግረዋል ፡፡
ጳዉሎስ ሰዎች ትክክለኛ የሆነዉን ትምህርት የማይታገሱበት ይልቁንም የራሳቸዉን የስጋ ምኞት ላይ በማተኮር በራሳቸዉ መንገድ የሚመላለሱበት ጊዜ ይመጣል አለ (ቁጥር 3) ፡፡ አዲስ ኃሳብን የሚያስተምሯቸዉን እና ሰዎች የሚፈልጉትን እንዲያስተምሯቸው አስተማሪዎችን ይጠብቃሉ (ቁጥር 3-4) ፡፡ ማለትም ያለ ሌላ ቀለም ትክክል ወይም ስህተት፣ ጥቁር ወይም ነጭ የሆነ ነገር ማለት ነው ፤ ነገር ግን ከእዉነት ዞር ማለትን በመምረጥ በዚያም ፋንታ የልብ ወለድ ታሪኮችን ይቀበላሉ ፡፡
ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን፡
ሁሉንም ነገር (
መከራን እንዲታገስ (መከራን ለመቀበል ፍቃደኛ እንዲሆን )
መልዕክቱን በማናገር የወንጌላዊነትን ስራ እንዲሰራ (ማቴ 28፡ 18-20) ፡፡
ስለ አገልግሎቱ ሙሉ ማረጋገጫ እንዲያደርግ እና ወደኋላ እንዳይዝ ፤ በማሳመን እና አሳማኝ እስኪሆን ድረስ እንዲቀጥል አስጠነቀቀዉ ፡፡
የእግዚአብሄር እቅድ የፈጠረዉ ሁሉም ነገር ፍሬ እንዲያፈራ ነው ፡፡ በአገልግሎት ፍሬ የስልጣን ዱላ ማንሳት የሚችሉ ላይ የተገኘ ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዉድድር ደረጃ ይወስዳል - ደቀ መዝሙርነት ይህ ነው ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (4፡ 6-8)፡ ጳዉሎስ የተሰዋ (እንደሚፈስስ መስዋዕት በመፍሰስ እንደሚቃጠል) ለመሆን ዝግጁ እንደ ነበር እና በዚያም የመሞቻዉ/የመጨረሻዉ ጊዜ እንደቀረበ ተናገረ (ቁጥር 6) ፡፡ ጳዉሎስ መልካሙን ገድል ተጋድሎ እንደነበር (ስለ እዉነት ተከራክሮ/ታግሎ እንደነበር)፣ ሩጫዉን እንደጨረሰ (አገልግሎቱን እንደጨረሰ) እና እምነቱን ጠብቆ እንደ ነበር (እዉነትን በሚገባ ጠብቆ እንደ ነበር ) ተናገረ (ቁጥር 7) ፡፡ በመልዕክቱ በዚህ ክፍል ላይ የእንባ ጠብታን አያለሁ ፤ ይህ ለጳዉሎስ እዉነት ነበር ፡፡ ጳዉሎስም ከዚህ የተነሳ በሰማይ ሲደርስ ጌታ ለእርሱ የሚሰጠዉ የጽድቅ አክሊል (የስጢፋኖስ ዘዉድ/አክሊል አይነት -ራዕ 4፡ 10) እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ጳዉሎስ ያን አክሊል የሚቀበል እርሱ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የክርስቶስን መመለስ በመጠበቅ ላይ ያሉ ሁሉም እንደሚቀበሉ አመለከተ (ቁጥር 8) ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (4፡ 9-15)፡ የጳዉሎስ የመጨረሻ ትዕዛዝ በቁጥር 9 ይጀምራል ፡፡ ወደ እርሱ ለመምጣት እንዲተጋ ጢሞቴዎስን ይጠይቀዋል ፤ የጳዉሎስ ጊዜ አጭር ስለ ነበር ከብዙ ምክንያቶች የተነሳ እንደ ገና ጢሞቴዎስን ሊያየዉ ፈለገ (ቁጥር 9) ፡፡ ጳዉሎስ ዴማስ ከክርስቶስ እና ከጳዉሎስ ዞር በማለት ወደ ተሰሎንቄ ሄዷል አለ ፤ በተጨማሪም ጳዉሎስ ቄርቂስን ወደ ገላትያ እና ቲቶን ወደ ድልማጥያ ልኳቸዉ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡ ጳዉሎስ ከሉቃስ ጋር ብቻዉን ስለ ነበር ጢሞቴዎስን ከእርሱ ጋር ማርቆስን እንዲያመጣው ጠየቀው ፤ ጳዉሎስ አገልግሎቱን እንዲረዳዉ ማርቆስን ተመለከተ (ቁጥር 11) ፡፡ ጳዉሎስ ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኮት እንደ ነበር ተናገረ ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በጢሮስ በአክራጳ ዘንድ በርኖስና መፅኀፍት እንዲያመጣለት ጠየቀው (ቁጥር 12-13) ፡፡ ጳዉሎስ የናስ አንጥረኛዉ እስክንድሮስ (1ጢሞ 1፡ 20) በእርሱ ላይ ክፉ አድርጎበት እንደ ነበርና ከሁሉ በኋላ ከእምነት እዉነት ዉጪ እንደነበር ተናገረ (ቁጥር 14-15) ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (4፡ 16-22)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በመጀመሪያዉ ሙግቱ አህዛቦች መስማት እንዲችሉ ቃሉን እንዲሰብክ ካበረታዉ ከጌታ በቀር ብቻዉን ቀርቶ እንደ ነበር ነገረው (ቁጥር 16-17) ፡፡ ከጌታ ኃይል የተነሳ ጳዉሎስ ከአንበሳ አፍ ድኗል ( ከሮም እስራቱ) ፡፡
ጳዉሎስ ጌታ ከሁሉም የክፉ ስራ ነፃ እንዲያወጣዉ እና ለእግዚአብሄር መንግስት እንዲጠብቀዉ ፀለዬ (ቁጥር 18) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ለጵርስቅላ፣ ለአቂላ እና ለሄኔሲፎሩም ቤተሰቦች ሰላምታን ላከ በተጨማሪም ጢሞቴዎስን ስለ ኤርስጦስ እና ስለ ጥሮፊሞስ ወቅታዊ መረጃን ሰጠው (ቁጥር 19-20) ፡፡ ስለ ኤዉግሎስ፣ ስለ ጱዴስ፣ ሊኖስ እና ቅላዉዲያ ማን እንደ ነበሩ መፅሀፍ የሚሰጠዉ መረጃ የለም (ቁጥር 21) ፡፡ በቁጥር 21 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ከክርምት በፊት ወደ እርሱ እንዲመጣ ለመነው ፡፡ ጳዉሎስ “ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመንፈስህ ጋር ይሁን ፤ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን “ በሚለዉ በረከት ያጠቃልላል (ቁጥር 22) ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ መልዕክቱን “ አሜን “ በማለት ለመጨረስ እንደማይፈልግ እርግጠኛ ነኝ ምክንያቱም ልጁን ጢሞቴዎስን የሚያይበት አንድ ቀን በምድር ላይ ወይም በሚመጣዉ በእግዚአብሄር መንግስት እንደሚኖር ስለሚያውቅ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በ 2ጢሞ (4፡ 2) ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እንዲያደርገዉ ምን ኃላፊነትን ሰጠው ? በማን መገኘት ይህንን አደረገ ? “ በሙታን እና በሕያዋን ፊት ሊፈርድ ባለው “ በማለት ኢየሱስ ክርስቶስን መጥራት ምን ማለት ነው ? (ዮሐ 5፡ 28-29, ሐዋ 10፡ 42, 2ቆሮ 5፡ 10, 2ጢሞ 4፡ 1, 1ጴጥ 4፡ 5)
-
ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን መልካም ለሆነዉ ትምህርት ሰዎች የማይቀመጡበት/የማይሰሙበት ጊዜ እንደሚመጣ አስጠነቀቀዉ ፤ በስራዉ ምን ይመልሳቸዋል ? ልክ እንደዚህ አይነት ያያችሁት ሰዉ ምሳሌ ስጡ
-
በ 2ጢሞ (4፡ 5) ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን መከራን እንዲታገስ አበረታው ፤ ጳዉሎስ በዚህ መልዕክት ለጢሞቴዎስ ብዙ ጊዜ ችግሮችን፣ መከራዎችን እና ስደቶችን ጠቀሰ (2ጢሞ 1፡ 8, 12, 2፡ 3, 9፣ 3፡ 11-12፣ 4፡ 5) ፤ በጣም ብዙ ጊዜ ይህን ለምን እንዳመጣዉ ምን ታስባላችሁ ?
-
ጳዉሎስ በናስ አንጥረኛዉ በእስክንድሮስ ከሚደርስበት ጥቃት እየተከላከለ በነበረ ጊዜ ጌታ አበርትቶት ስለ ነበር ለአሕዛቦች መስበክ ችሎ ነበር ፤ በተቃዉሞ እና በጥቃት መካከል ላይ ወንጌልን ለመናገር እድሎችን ተመልክታችኋል ? አዎ ከሆነ ከቡድናችሁ ጋር አንድ ምሳሌን ተነጋገሩ ፡፡
-
በ 2ጢሞቴዎስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Timothy 4:17–18
“But the Lord stood with me and strengthened me, so that the proclamation might be fully made through me and all the Gentiles might hear. So I was rescued from the lion’s mouth. The Lord will rescue me from every evil work and will bring me safely into His heavenly kingdom. To Him be the glory forever and ever! Amen.”
ልክ የጳውሎስ የምድር ላይ ቆይታ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ እርሱ ፈጽሞ ተስፋ አልቆረጠም ይልቁንም ሌሎች ይሰሙ ዘንድ የኢየሱስን ወንጌል ማወጁን ቀጠለ እንጂ ፡፡ ጳውሎስ መልካሙን ገድል ተጋድሏል ፣ ሩጫውን ጨርሷል ደግሞም ኃይማኖትን ጠብቋል ፡፡ ጳውሎስ ስለ ወንጌል ሲል ልክ እንደ መስዋዕት ሕይወቱን ሰውቷል ፡፡ ለደቀ መዝሙሩ ጢሞቲዎስም ከጌታ የተሰጠውን ተስፋ ነገረው ፡፡ ሁሉም በተውኝ ጊዜ ሳይቀር ፣ ጌታ ከጎኔ ቆሞ አበረታኝ ደግሞም አዳነኝ ፡፡
በጠባብዋ መንገድ እየተመላለሳችሁ ወንጌልን በመመስከር እየጸናችሁ ፣ እየተጋችሁና እየቀጠላችሁ ክርስቶስን መከተል ብቸኛ የሚያደርግ ፣ የሚያስፈራና የሚያደክም ሊሆን ይችላል ፡፡ ሆኖም ግን ጓደኞች ጀርባቸውን ሲሰጡ ፣ ክፉው ደግሞም ፈተና በመንገዳችሁ ሲመጣ ፣ መከራና ግራመጋባትም ሲደርስባችሁ ፣ ጌታ ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡ ጌታ ያበረታችኋል ደግሞም ያድናችኋል ፡፡ ጓደኞቼ ለክርስቶስ ኢየሱስ ለመኖር የሚከፈለው መስወዕትነት ዋጋ አለው ፡፡ ስለዚህም ዙሪያችሁን ተመልክታችሁ ከጎናችሁ ማንም እንዳልቆመ ስታዩ ፣ እንዳትፈሩ ፡፡ ጌታ ከጎናችሁ ይቆማል ፡፡ እርሱ አይተዋችሁም በሰላምም ለሰማያዊ መንግስቱ ያበቃችኋል ፡፡ ቀጥሉ…… መልካሙን ገድል ተጋደሉ ፣ ሩጫውን ጨርሱ ፣ ኃይማኖታችሁን ጠብቁ ወንጌልንም መስክሩ !
“ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፥ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ ። ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን ። “
- 2ኛ ጢሞቲዎስ 4፡17-18
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 41:10 — “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
ማርቆስ 16:15 — “ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ። “
2ኛ ጢሞቲዎስ 4:6–7 — “ በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል ። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።