Continue In God's Truth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Righteous Judge 2 Timothy 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በ 2ጢሞቴዎስ ያለዉን ጥናታችንን ስንቀጥል በተለዬ መልኩ የምዕራፉ መጨረሻ የሆኑ የእግዚአብሄር ቃል ላይ እንመለከታለን ፡፡ ወደ ቀጣዩ ትዉልድ ምን እያስተላለፍን እንደሆነ እደነቃለሁ ፡፡ ቶማስ ዳልተን ያለዉ፡
- ለወንጌል ራሱን/ጭንቅላቱን ከማጣቱ በፊት ከጳዉሎስ ያለን ቃል ለሚወዳቸዉ፣ በፀሀፊዉ በራሱ ቀን በራሱ ተስፋ እና አላማ እንዲኖሩ የተወሰኑትን ልጆቹን ተግሳፆች ናቸው ….. የ 2ጢሞቴዎስ መፅሀፍ የዘመኑን ቁጥር መጨረሻ አዉቆ በነበረ ጊዜ የጳዉሎስ መፃፊያ የቆመበት ነው ፤ ብትሮቹ ለጳዉሎስ ህጎች አልነበሩም ለጢሞቴዎስም አይሆኑም ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ወጣት መሪ ስርዓት አስይዞት ነበር፣ ከእርሱ ጋርም ዝም ብሎ በቀላሉ ወንጌልን አልተነጋገረም ወይም ከጢሞቴዎስ ጋር ህይወቱን መጋራትም እንኳን አላቆመም ፡፡ ወንጌልን ለእርሱ አደራ ሰጠ ፤ በቀረዉ በዚህ እድሜ ጌታ እርሱን ከጢሞቴዎስ ህይወት እያስወጣዉ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ ሁላችንም በእግዚአብሄር ለራሳችን ህይወት ተጠያቂ ነን ነገር ግን ጢሞቴዎስ “ የአባቱ “ ያለመኖርን ስሜት እየተሰማዉ ነበር ፤ የሐዋሪያ እድሜ በማርጀት እንደገፋ የመጨረሻዉ መልዕክት እንዴት ይናገራል ምናልባት ባልተጠበቁ ቃላቶች ከኤፌሶን ጳዉሎስ ብላቴና/ወጣት “ ወንጌላዩን “ ፈተነው፡ “ ፡ “ ልጄ ጠንክር/በርታ “ በማለት ፡፡
ትምህርት
2-ጢሞቴዎስ (3፡ 1-5)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ “ ይህን እወቅ “ የሚለዉን ሀረግ የጢሞቴዎስን የረጅም ጊዜ ትኩረት ለማግኘት ተጠቀመ ፡፡ “ አስቸጋሪ ጊዜዎች “ አደገኛ ሁኔታ “ በማለት ሊተረጎም ሲችል ትርጉሙም በትልቁ የሚያስጨንቅ ሁኔታ ማለት ነው ፡፡ ያ ቃል በማቴ (8፡ 28) ኢየሱስ በአትክልት ስፍራዉ ዉስጥ ሁለት ጋኔን የያዘዉን ሰዉዬ ባገኘዉ ጊዜ በአዲስ ኪዳን አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ “ በመጨረሻዉ ጊዜ “ ሰፊ የብሉይ ኪዳን ቃል እና አሁንን የሚያመለክት ነዉ ምክንያቱም ኢየሱስ የመጨረሻውን ጊዜ ስላመጣው ፡፡ ጴጥሮስ በበዓለ ሀምሳ ቀን የጀመረዉ ትንቢት መፈፀም እንደሆነ አሳዉቋል (ሐዋ 2፡ 17) ፤ ስለመጨሻዉ ዘመን ፍርድ ለማዉራት ጥቅም ላይ ዉሏል (ዮሐ 6፡ 39-40, 44, 54, 11፡ 24, 12፡ 48) ፤ ይህ በተለዬ ከኢየሱስ መመለስ በፊት ወዲያዉኑ ስለሚሆን ወቅት የሚመጥን ነው ፤ በአሁኑ ጊዜ በዮናይትድ ስቴት ለአማኞች ስለ ክርስቶስ ተመልሶ መምጣት በብዙ አላስብም ፤ በሌሎች ነገር በማሰብ እና በመሞከር ስለደከምን ይህ ምዕራፍ ይሞገተናል ፡፡
ክርስቲያኖች በችግር እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች የሚሰደዱበት ምክንያቶች በዙሪያ እና በመካከላቸዉ ባሉ ሰዎች በተጣመሙ ዋጋዎች አድጓል ፡፡ በቁጥር (2-5) ጳዉሎስ ብዙ ጊዜ ሳያስቡበት (ባለማስታወላቸዉ) እና አንዳንድ ጊዜ አስበዉበት ኢየሱስን በኃይለኛዉ በተቀበሉ ሰዎች ላይ አስቸጋሪ አየርን ስለሚፈጥሩ ሰዎች 20 ባህሪያትን ይለያል ፡፡ በዚህ ዝርዝር ዉስጥ ጳዉሎስ “ ለፍቅር “ ሁለት ቃላቶችን ተጠቅሟል - አጋፔ ያልሆነ ፊሎስ ፍቅርን ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሰዎችን እና ነገሮችን በተሳሳተ የፍቅር አቅጣጫ ይወዳሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ራሳቸዉን የሚወዱም ናቸው ፡፡ የዚህ ራስን የመዉደድ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስሩ በኤዴን ገነት ሰይጣን አዳምን እና ሔዋንን በማግኘት እንደቀጥሉ እና እግዚአብሄርን እንዲመስሉ እንዲበሉ በነገራቸዉ ጊዜ ይገኛል ፡፡ ራስን መዉደድ ከሚከተሉት ከሁሉም መሰረታዊ የሆነ ኃጢዓት ነው ፡፡ አንድ ሰዉ የራሱን ፍቃድ የህይወቱ ማዕከል በሚያደርግበት ክስተት መለኮታዊ እና ሰዋዊ ግንኙነቶች የጠፉ ናቸዉ በተጨማሪም ለእግዚአብሄር መታዘዝ እና ለሰዎ ቸርነት ማድረግ የማይቻል ይሆናል ፡፡
ገንዘብን መዉደድ አዲስ አይደለም ነገር ግን ፍቅራችንን ገንዘብን ለመከታተል ማድረግ ቀላል ነው (ቁጥር 2) ፡፡ የትምክት፣ የትዕቢት እና ወቀሳ እያንዳንዳቸው ግለሰቦች ራሳቸዉ ከሌሎች እንደሚጠቅሙ እንደሚመለከቱ ያሳያል፡፡ በዝርዝሮቹ ዉስጥ ስታነቡ እያንዳንዱ ባህሪይ ስለ ራስ መዉደድ ያሳያሉ ፡፡ ፓስተር ዳዊት ጉዚክ “ በእግዚአብሄር እና በደስታ መካከል አንመርጥም ፤ እግዚአብሄርን ማገልገል የመጨረሻዉ ደስታ ነው “ (መዝ 16፡ 11)፡፡ በእግዚአብሄር ፍቅር እና ደስታን በመዉደድ መካከል አንመርጥም ፤ ለእግዚአብሄር ፍቃድ መኖር ብዙ ደስታን ይሰጣችኋል ነገር ግን መጀመሪያ እግዚአብሄርን እንደምትወዱት እንጂ ራሱን ደስታን መዉደድ መተዉ ፡፡ በቁጥር 5 ጳዉሎስ “ የአምልኮት መልክ ያላቸዉን ነገር ግን ኃይሉን የካዱትን “ አመለከተ ፡፡ በራሳችን በተያዝንበት አለም ሰዎች ፍሬ የሌለዉ ቅጠል ኃይማኖትን የመሸከም ነፃነት ይኖራቸዋል፣ የሚፈልጉትን ይመርጣሉም ያነሳሉ ፡፡ መንፈሳዊነት እንዲሰማችዉ ይፈልጋሉ ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስለመሆን ግን አይጠነቀቁም ፡፡ በቁጥር 6-8 ጳዉሎስ እነዚህን ሰዎች ለማስወገድ ይገልፃል !
2-ጢሞቴዎስ (3፡ 6-9)፡ በቁጥር 6-7 ጳዉሎስ እነዚህን አደጋዎች ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህ አደጋዎች/ችግሮች በሱ ዘመን በአለም ላይ እንደ ነበሩና አሁንም ከክርስቶስ ተመልሶ መምጣት በፊት እንደሚጨምሩ ያውቃል ፡፡ በተለዬ ወደ ቤተሰብ ዉስጥ እንዳይገቡ/ እንዳይሄዱ ያተኮረ ይመስላል - በአለም ላይ የቀረበ ክፉ ነገር አንድ ነገር ሲሆን ሌሎች ወደ ቤታቸዉ እንዲገባ ይፈቅዱለታል ፡፡ የተሳሳተ ፍቅር ጣዖት ተዉኔት ነው፣ ወንጌል በሆነ ጊዜ ደግሞ ችግሮች ይበዛሉ ፡፡ እንዲሁም ለእኛ ማስጠንቀቂያዎች አሉ፡ በቤታችን፣ በቴሌቪዢናችን እና በኮምፒተራችን ላይ (ዘዳ 6፡ 4-9)፡፡ ቁጥር 7 በተደጋጋሚም እንኳን ሳይቀር መልካምን ዜና ስለሰሙት ነገር ግን በሰሟቸዉ ቃላቶች የማይኖሩና የማያሰላሰላስሉትን ሰዎች ይገልፃል ፡፡ ጉዚክ፡
አንድ ሰው ጳዉሎስ ከጠቀሳቸዉ ከእነዚህ ምርኮኝነት አንዱ እንደሆነ በእርግጠኝነት ካወቀ በመጨሻው ጊዜ በእግዚአብሄር ተቀባይነት ማጣት እና በራስ አከባበር ተፅዕኖ ይያዛል ፤ ለማወቅ አንድ ዉጤታማ መንገድ አለ፡ ማምለጣችሁን አስቸጋሪ ከሚያደርግ ከማንኛዉም ምድራዊ ንጉስ ተፅዕኖ ርቆ በመመላለስ መመልከት ነው ፡፡ በቤታችሁ ዉስጥ በመጨረሻዉ ዘመን በተወሰኑ መናፍስት ማንኛዉም ነገራችሁን ከመያዝ ከመፍቀድ አንድ ሳምንት እረፉ - እንዲሁም ሰንሰለት መልሶ ከእነዚህ ነገሮች ጋር መልሶ እንደሰራችሁ እዩ ፡፡ በማለት ፅፏል ፡፡
ቁጥር 8-9 ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን በመቃወማቸዉ እዉነትን እንደተቃወሙ ይገልፃል ፡፡ እነዚህ ስሞች በፍፁም በዘጸዓት መዝገብ ላይ አልተሰጡም ነበር ነገር ግን የአይሁድ ልምድ የያዘው በፈርዖን ፊት ሙሴን በጊዜዉ ተዓምራቱን በማዛመድ ሙሴ ያደረገዉን ተዓምራት እንኳን በማመሳሰል የተቃወሙ የግብፅ ድግምተኞች እንደ ነበሩ ነበር (ዘጸ 7፡ 8-13, 19-23, 8፡ 5-7, 16-19) ፡፡ የኢያኔስና የኢያንበሬስ ኃይል የተወሰነ ቢሆንም እንኳን ሰይጣንም የተወሰነ ኃይል አለው ፡፡ በመጨረሻዉ ጊዜም እንኳን አሁንም እግዚአብሄር ሁሉም በቁጥጥሩ ስር ነው ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (3፡ 10-12)፡ በቁጥር 10 ጳዉሎስ በክርስቲያን ህይወት ዉስጥ ስላለ ፈተና ማዉራት ጀመረ ፤ “ አንተ ግን “ ጢሞቴዎስ ገልፆአቸዉ የነበሩትን እንደማይመስል በማሳየት ጀመረ ፡፡ ጢሞቴዎስ ተምሮት የነበረዉን ተከተለ ማለትም ምሳሌ ሆነበት እንዲሁም በጳዉሎስ ምሳሌም ኖረ ፤ በመቀጠልም ጳዉሎስ የተወሰኑ መከራዎቸን በአንፆኪያ (ሐዋ 13፡ 50)፣ በሊቃዖንያ (ሐዋ 14፡ 5) እና በልስጥራ (ሐዋ 14፡ 19) ስለታገሰው ጢሞቴዎስን አስታወሰው (ቁጥር 11) ፡፡ ጳዉሎስ በክርስቶስ የሚኖሩ ሁሉ እንደሚሰደዱ አብራራ (ቁጥር 12) ፤ ያን እንደ ገና አንብቡ ፡፡ ኦስዋልድ ቻምበር “ የክርስቲያን ህይወት አማካኝ እይታ ከችግር ነፃ እንደወጡ ማለትም በችግር ነፃ መዉጣት ማለት ሲሆን ይህም የተለዬ ነገር እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡ ሪች ሙሊንስ “ ኢየሱስ ለእናንተ ያደረገላችሁን በፍፁም እንዳትረሱ ፤ የከፈለዉን በፍፁም ቀለል አድርጋችሁ እንዳትወስዱ ፡፡ በተጨማሪም ቀላል ህይወቱን እንደከፈለ እንዳታስቡ ራሳችሁ ለራሳችሁ የማትከፍሉትን “ አለ ፡፡ በአሁኑም ጊዜ ስደት ለክርስቲያን በፍፁም አያቆመም ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (3፡ 13-16)፡ የሚያታልሉ መከራ ያገኛቸዋል ፤ ክፉ ሰዎች የታወቁ ሲሆኑአስመሳዮች ግን አይደሉም (ቁጥር 13) ፡፡ ሄነሪይ ኑዌን “ በአለማችን ዉስጥ ብዙ ጥፋቶች እና በእያንዳንዱ ቀን በሰዎች ላይ የሚሆኑት አስፈሪ ነገሮች በቀላሉ ወደ ተስፋ መቁረጥ በመምራት የሁኔታዎች ተጠቂ እንደሆንን ያሳምነናል ፤ ነገር ግን ኢየሱስ በእነዚህ ክስተቶች ላይ በፍፁም በተለዬ መንገድ ይመለከታል ፡፡ ለምስክርነት እድል ይጠራቸዋል ! “ አለ ፡፡ ለጢሞቴዎስ ልዩነቱን እንዲያዉቅ እና የክርስቶስን የአኗኗር ዘዴ ለመኖር የተማረ ነበር ምንም ይሁን ችግር የለዉም (ቁጥር 14-15) ፡፡ አስፈላጊዉ ነገር ለብቻቸዉ በእነዚህ ነገሮች መቀጠል እና ነገሮቹ እንዲሄዱ አለመፍቀድ ነው ፡፡ ጢሞቴዎስ በእናቱና በአያቱ ብሉይ ኪዳንን ተምሮ ነበር ፤ የክርስቶስን ትምህርት ያውቃል ፤ እነዚያ ነገሮች ይቀጥልባቸዉ የነበሩ ነገሮች ነበሩ ፡፡ ለቁጥር 16 ይህ አዉዱ ነው፡ “ የእግዚአብሄር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሄር መንፈስ ያለበት መፅሀፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለዉ ምክር ደግሞ ይጠቅማል “ ፡፡ በቀጥታ /ቃል በቃል “ በእግዚአብሄር የተነሳሳ “ ማለት “ በእግዚአብሄር የተነገረ “ ማለት ሲሆን ይህ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ጥቅም ላይ የዋለበት ብቸኛዉ ጊዜ ነው (2ጴጥ 1፡ 20-21) ፡፡ “ መፅሀፍ ሁሉ “ ከብሉይ ኪዳን የበለጠን መፅሀፍ ያካትታል ፡፡ እዚህ ጋር ጳዉሎስ ንግግሩን ቀየረ ምክንያቱም በጳዉሎስ ዘመን እግዚአብሄር የእግዚአብሄርን ቃል የተናገረበት ስለ ነበር ከሐዋሪያት እና ከነቢያት ወደፊት እግዚአብሄር ምን እንደሚያመጣ አስተዉሏል ፡፡
መደምደሚያ
በመርህ ደረጃ መፅሀፍ ቅዱስን በመነሳሳት ማመን ቀላል እንደሆነ ነገር ግን በተግባር እንደሚተዉ አስታዉሱ ፡፡ አመለካከታችሁ እና ድርጊታችሁ ክርስቶስን ካልመሰለ ሰፊ የመፅሀፍ ቅዱስ እዉቀት እና ሁልጊዜ ቤተ ክርስቲያን መገኘት ብዙ የተለዬ ነገር አያደርግም ፡፡
Dalton Thomas, Pilgrim Field Journal, vol. II (Frontier Alliance International’s Annual, 2019).
David Guzik, 1–2 Timothy, Titus, Philemon (Santa Barbara, CA: Enduring Word Media, 2013), n.p.
Guzik, n.p.
ጥያቄዎች
-
በመጨረሻዉ ዘመን እንዳለን ታስባላችሁ ? አንዳንድ አመልካቾቹ ምንድን ናቸው ?
-
“ የአምልኮ ልክ አላቸዉ ኃይሉን ግን ክደዋል “ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ምን ኃይል የተካደ ነው ? (ሉቃ 5፡ 17, ሮሜ 15፡ 19, 1ቆሮ 2፡ 5, 4፡ 20)
-
ጳዉሎስ እዉነትን ስለሚቃወሙ ሰዎች ለምን እንደማይከናወንላቸዉ ፃፈ ? (2ጢሞ 3፡ 9)
-
በ 2ጢሞ (3፡ 12) መሰረት በኢየሱስ ክርስቶስ መልክ መኖር የሚፈልጉት ሁለ ምን ይሆናሉ ? ይህ ያስፈራችኋል ወይስ ስለሚመጣዉ ነገር ያዘጋጃችኋል ?
-
ጳዉሎስ በ 2ጢሞ (3፡ 15) ቅዱሱ መፅሀፍ ማድረግ እንደሚችል ምን ተናገረ ? በቁጥር (16-17) ለሁሉም መፅሀፍ እንደ ምንጭ የተነገረዉ ምንድን ነዉ ለእኛስ እንዴት ይጠቅመናል ?
-
በ 2ጢሞቴዎስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Timothy 3:16–17
“All Scripture is inspired by God and is profitable for teaching, for rebuking, for correcting, for training in righteousness, so that the man of God may be complete, equipped for every good work.”
እግዚአብሔር ለጠራህ መንገድ አገልግሎት ብቁ ዝግጁ እንዳልሆንክ ተሰምቶህ ያውቃል ? ምናልባትም የሆነ ሰው እጅህን እንድይዝህና በመንገድህ እንድመራህ ደግሞም እንድያግዝህ ተመኝተህ ይሆናል ? ጢሞቲዎስ እንዲህ ተሰምቶት ስለነበር ነው ጳውሎስ ወደ ፊት ስላለው አስቸጋሪ ዘመን ጢሞቲዎስን ያስጠነቀቀው ይህም ፡- የስህተት ትምህርት እንደሚበዛ ፣ እግዚአብሔርን መምሰል እንደሚጠፋ ደግሞም ስደት እንደሚኖር ነው ፡፡
ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ለእነዚህ ከባድ ቀናት እንደታጠቀ ያስታውሰዋል ፡፡ በተመሳሳይ አንተም ታጥቀሃል ፡፡ አንተም የሚያስፈልግህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አለልህ ምክንያቱም ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀህ ትሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጸሀፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ። ስለዚህም በየቀኑ ቃሉን አንብብ ፡፡ የእግዚአብሔርንም ቃል በምታነብበት ጊዜ ማስተዋልን እንድሰጥህ ጌታን ጠይቅ ፡፡ ከጓደኞችህ ጋር በቃሉ ላይ ተወያይ ፡፡ እግዚአብሔርንም ለማወቅ ስትጸና እርሱ እንድትዘጋጅ ያስታጥቅሃል ያበረታህማል ደግሞም እርሱ እንድትሰራ ለጠራህ ስራ የሚያስፈልገውን ሁሉ ይሰጥሃል ፡፡ ስለዚህም ከባድና አስቸጋሪ ጊዜያትን መፍራት አያስፈልግህም ምክንያቱም አምላክህ የተወደደውም ጠባቂህ ፣ እርሱ ፈጽሞ ላይተውህ ቃል ስለገባ ፡፡ በፊትህ ላለው ጉዞ የተዘጋጀህና የበቃህ ትሆን ዘንድ ዛሬ ቃሉን በማንበብ ጊዜ ውሰድ ፡፡
“ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል ። “
- 2ኛ ጢሞቲዎስ 3፡16-17
ተጨማሪ ጥቅስ
2ኛ ጢሞቲዎስ 3:12–14 — “ በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ ። ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ ። አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና ፡፡ “
ዕብራውያን 13:20–21 — “ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን ፤ አሜን ፡፡ “
2ኛ ጴጥሮስ 1:3 — “ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።