The Process Of Discipleship
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Righteous Judge 2 Timothy 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሁልጊዜ ስለ 2ጢሞቴዎስ 2 ሳስብ በቻርሊቶን ኤንሲ በተሰራዉ ሰሌዳ መጠቀምን አስባለሁ ፡፡ “ ደቀ መዝሙር ደቀ መዝሙር ያደርጋል ….” የሚለዉ ምልክት የተደጋገመ እና በእያንዳንዱ ጊዜ “ ደቀ መዝሙር “ የሚለዉ ቃል የቀረበ ሲሆን በጢቅትም በማነስ የተገኘ ነበር ፡፡ የክርስቲያን ህይወት በአጠቃላይ ደቀ መዛሙርት ማድረግ ፡፡
ጳዉሎስ ከመሞቱ በፊት የመጨረሻዉን መልዕክት እየፃፈ እንደ ነበርና በእምነት ለተወደደ ልጁ ለጢሞቴዎስ መሄዱን እናስታዉሳለን ፡፡ መልዕክቱ ለጢሞቴዎስ እንዴት መልዕክቱን እንደሚቀጥል የመጨረሻ መልዕክቱን እና ማበረታቻዉን ያካትታል ፡፡ ዋይርስቤ በምዕራፍ 2 አገልግሎት ምን እንደሚመስል ሰባት የተለያዩ መልኮችን ይላል፡ “ እንደ ባላደራ፣ እንደ ወታደር፣ እንደ አትሌት፣ እንደ ገበሬ፣ እንደ ሰራተኛ፣ እንደ ሚያገለግል እቃ እና እንደ አገልጋይ “፡፡
ትምህርት
2-ጢሞቴዎስ (2፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ክርስቶስ ለእርሱ አሳይቶት በነበረው ፀጋ እንዲበረታ ነገረው (ቁጥር 1) ፡፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እነዚህን ትምህርቶች ለሌሎች ለሚያስተላልፉ አስተምሮት የነበረዉን እንዲያስተምር አዘዘው (ቁጥር 2) ፤ ይህ በደቀ መዝሙርነት የባለ አደራነት መልክ ነው (1ቆሮ 4፡ 17, 11፡ 1) ፡፡ ማክአርቱር “ ጢሞቴዎስ ከጳዉሎስ ተምሮት የነበረዉን መለኮታዊ መገለጥ በመዉሰድ ለሚታመኑ ለሌሎች ሰዎች ያስተምራል - የተረጋገጠ መንፈሳዊ ባህሪይ እና ስጦታ ያላቸዉ እና በምላሹ በእነዚህ እዉነቶች ላይ ለሌላ ትዉልድ የሚያስተላልፉ ሰዎች “ እንደሆነ ይገልፃል ፡፡ የእግዚአብሄርን መለኮታዊ መገለጦች ለሌሎች ለመናገር የሚቀጥሉ የታመኑ ግለሰቦች ያስፈልጉናል ፤ ጢሞቴዎስ ይህን ትዕዛዝ በመረዳት በአሳሳቢነት ተከተለው ፤ አስፈላጊ እና ጊዜዉን የተበቀ እንደሆነ ያውቃል ፡፡ ይህን ከማድረግ ዉጪ ሃሰተኛ መልዕክቶች በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በተነገሩት ላይ ሰርጎ መግባት ይችላል ፡፡
በሚያናድድ ሁኔታ ብዙ አማኞች እና የሰራተኞች አባላትም በዚህ ሂደት የት ላይ እንደሚጀምሩ እዉቀቱ የላቸዉም ወይም ዉጤቱ ምን እንደሚሆን ስለማያዉቁ ለመጀመር ያመነታሉ ፡፡ ሰዉን ደቀ መዝሙር ማድረግ ጊዜን ይወስዳል ፤ የጳዉሎስ፣ የያዕቆብን እና የዮሐንስን ኑሮ ስንመረምር ለመነቃቃት ጊዜ አስር ቁልፍ ነገሮች ማስረጃዎች ይሆናሉ፡
- ፀሎት፡ ለአንድ ደቀ መዝሙር ጌታን መጠየቅ (ማር 1፡ 35-38) ፡፡
- ጌታ ወዳዘጋጀዉ ደቀ መዝሙር በመመልከት ክፍት/ለመስማት ዝግጁ መሆኑን መለየት (ማር 1፡ 9) ፡፡
- መጥራት ፤ ወደ ደቀ መዝሙር መሄድ፣ የመጀመሪያ ግንኙነት/ቅርርብ ማድረግ (ማር 1፡ 20) ፡፡
- ምላሽ መስጠት ፤ ደቀ መዝሙር በአዎንታዉ ወይም በአሉታዊ በአንዱ ቅርፅ “ ለጥሪዉ “ ምላሽ ይሰጣል (ማር 1፡ 20) ፡፡
- መገናኘት/መተሳሰር፡ “ ህይወትን “ ከደቀ መዝሙሩ ጋር በማድረግ የታሰበበት ግንኙነት ማድረግ (ማር 1፡ 29-31) ፡፡
- መመስረት፡ በህይወታቸዉ የእግዚአብሄርን አላማ እንዲፈልጉ መርዳት (ማር 6፡ 6-13) ፡፡
- ማጋራት/መናገር ፤ በአንድ ላይ ጠንካራ በሆነ መፅሀፍ ቅዱሳዊ እዉነት ማስተማር እና መስራት (ማር 10፡ 35-45) ፡፡
- መታገስ/መቻል፡ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመታገስ ደቀ መዛሙርትን ማገዝ እና ምሳሌ መሆን (ማር 14፡ 32-36, ሐዋ 12፡ 2) ፡፡
- መቆየት/መጠበቅ፡ በጌታ የሚቆይ አንድ ደቀ መዝሙር ፍሬን ያፈራል (ሐዋ 3፡ 1-11) ፡፡
- ማመሳሰል ፤ ሁለቱ በግንኙነት ሲቀጥሉ ደቀ መዝሙሩ ደቀ መዝሙር ለማድግ ሰዉን በማግኘት ታላቁን ተልዕኮ መሸከም ይችላል፣ በተጨማሪምደቀ መዝሙር አድራጊዉ ለአዲሱ ደቀ መዝሙር ይፀልያል (ሐዋ 4፡ 3-4) ፡፡
ቀድሞ እግዚአብሄር ደቀ መዝሙር እንድታደርጓቸዉ ያዘጋጃቸዉ በዚያ ሰዎች አሉ ፤ ያን ሰዉ ወዲያዉኑ ታገኙታላችሁ ፡፡
2-ጢሞቴዎስ (2፡ 3-10)፡ በምዕራፍ 2 ላይ ዋይርስቤ የለየዉን የእረኛን ተግባር ስዕልን/መልክን ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ ፡፡
እንደ ወታደር (ቁጥር 3-4, 8-13) ፡፡
እንደ ሯጭ (ቁጥር 5) ፡፡
እንደ ገበሬ (ቁጥር 6-7) ፡፡
እንደ ሰራተኛ (ቁጥር 14-18) ፡፡
እንደ ሚያገለግል እቃ (ቁጥር 19-22) ፡፡
እንደ አገልጋይ (ቁጥር 23-26) ፡፡
በአገልግሎት እና ደቀ መዝሙር በማድረግ ሁሉም ተግባሮች ወደ ትግበራ ይመጣሉ ፤ በጊዜዉ በእነዚህ ሁሉ ላይ እነልፋለን ፡፡
መደምደሚያ
ደቀ መዝሙር ለማድረግ ለተሰጠን ነገር ባለአደራዎች መሆን አለብን ፡፡ የደቀ መዝሙርነትን መልዕክት ስንሸከም የእግዚአብሄር መንግስት ቀድሞ ተሰጥቶናል ፡፡ ለሁላችንም ፈተናው ማን ደቀ መዝሙር እንደምናደርግ እግዚአብሄርን መጠየቅ ነው ፤ “ የምታስተምሩት ደቀ መዝሙር ለማድረግ እንደሆነ “ ጠይቁት ተስፋዬ ቻርት እንዳላችሁ እና ይህ ቻርት እያደገ እንደ ሆነ ነው ፡፡ ምንም ሰዉ ከሌላችሁ ለመጀመር በፍፁም አትዘግዩ ፤ በፀሎት በመጀመር ዙሪያችሁን መመልከት በመጀመር በህይወታቸዉ ላይ መናገር/ማፍሰስ ትችሉ እንደሆነ በመጠየቅ ለመጥራት የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፡፡ ለዚህ ሞደል ጳዉሎስን በማመስገን ፀሎቴ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እንዲያደርገዉ እንደሞገተው መኖር እንድንችል ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), pp. 244-248.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1806.
Wiersbe, pp.244-248.
ጥያቄዎች
-
አንድ ወታደር እንደምትሆኑ ራሳችሁን ታያላችሁ ? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወታደርነትስ ? በ 2ጢሞ (2፡ 3) ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እንደ ኢየሱስ ወታደር ከእርሱ ጋር ዋጋ እንዲከፍል ነገረው ፤ ራሳችሁን በዚህ ተግባር ታዩታላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታይቱም ?
-
2 ጢሞ (2፡ 11-13) ለማያምን ሰዉ እንዴት ትገልፁለታላችሁ ? እነዚህን ጥቅሶች ለእናንተ ትርጉም የሚሰጡ አድርጓቸዉ ?
-
በግል አስተያየታችሁ 2ጢሞ (2፡ 22) እንዴት ሊፈፀም ይችላል ? አንድ ሰዉ የፅድቅ ኑሮን፣ ፍቅርን፣ እምነትን እና ሰላምን እንዴት ሊከታተል ይችላል ? መልካ አስተሳሰብ ከላቸዉ አማኞች ጋር በምታሳልፉት ጊዜ ትደሰታላችሁ ? የምታደርጉት ያ በቂ እንደሆነ ታስባላችሁ ?
-
በ 2ጢሞቴዎስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 2 Timothy 2:2
“And what you have heard from me in the presence of many witnesses, commit to faithful men who will be able to teach others also.”
ደቀ መዝሙርነት የሚለውን ቃል ስትሰሙ ምንድን ነው ወደ አሳባችሁ የሚመጣው ? አንታ ታስባለህ ፣ እኔጃ ፣ አረ እኔ ይህን ለማሰብ ጊዜ የለኝም ወይም ደግሞ ይህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚያገለግሉ ሰዎች ብቻ ነው ? ልትሉ ትችላላችሁ ፡፡ ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ከእርሱ ለሰማው ትምህርት የታመኑ ሰዎችን ደቀመዝሙር ለማድረግ እንድተጋ አዘዘው ፡፡ ጳውሎስ ጢሞቲዎስ የወንጌሉን እውነት ለሌሎች መናገሩን ማስተላለፉን እንድቀጥል ፈልጎ ነበር ፡፡
እንደ ጢሞቲዎስ ሁሉ ጌታ አናንተንም ደቀመዝሙር እንድታደርጉ ያዛችኋል ፡፡ በጸሎትም እግዚአብሔር የክርስቶስን ፍቅር ያፈስ ዘንድ ጠይቁ ፡፡ ከጌታ ጋር በህይወታቸው ማደግን ለሚሹ ለታመኑ ወንዶችና ሴቶች አደራን ትሰጡ ዘንድ ያዛችኋል ፡፡ ምናልባት ይሄ በሳምንት እንድ ቀን ለቡና ተገናኝታችሁ ከዚያም በቃሉ ምን እንደተማራችሁ መወያየት ፤ መረዳዳት ደግሞም አንዳችሁ ለሌላችሁ መጸለይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ደቀ መዝሙርነት ማለት ለጓደኝነት ለግንኙነት መሰጠት ማለት ነው ፤ ዓላማውም በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ባለው ጉዟችሁ እንድታድጉ አንዳችሁ ሌላችሁን ለማበርታት ነው ፡፡ “ እንድህ ቢሆንስ “ ደግሞም “ አላውቅም “ የሚሉ ንግግሮችን ሁሉ አቁሙ ፡፡ አስታውሱ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ፣ ብርታትና ጥበብ ይሰጣችኋል ፡፡ እርሱ ይሞላችኋል ያስታጥቃችኋልም ፡፡ ዛሬ የሆነን ሰው ደቀመዝሙር ለማድረግ ጌታ ይመራችሁ ዘንድ ጸልዩ ፡፡
“ ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ ። “ - 2ኛ ጢሞቲዎስ 2፡2
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማቴዎስ 28:19-20 — “ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ ። “
- ዮሐንስ 1:45 — “ ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ ። ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው ። “
- ቲቶ 2:3 — “ እንዲሁም አሮጊቶች ሴቶች አካሄዳቸው ለቅዱስ አገልግሎት የሚገባ፥ የማያሙ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።