Paul's Letters 2 Timothy

Be Not Ashamed Of The Gospel

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Righteous Judge 2 Timothy 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 566 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ ጥናታችንን ለጢሞቴዎስ የጳዉሎስን ሁለተኛ መልዕክትን እንጀምራለን ፤ በ 1ጢሞቴዎስ ኢየሱስ እንዴት አስታራቂአችን/መካከለኛችን እንደሆነ አይተናል ፡፡ በ 2ጢሞቴዎስ ኢየሱስ እንደ ፃድቅ ፈራጅ ቀርቦአል (2ጢሞ 4፡ 8) ፤ ከኢየሱስ ሞት እና ትንሳኤ የተነሳ አሸናፊዎች ነን ፡፡ በእርሱ በኩል የጽድቅን አክሊል/ዘዉድ መቀበል ችለናል ፡፡ በ 1ጢሞቴዎስ ጥናታችን ላይ የጢሞቴዎስ ስም “ እግዚአብሄርን የሚያከብር “ ማለት እንደሆነ ተምረናል ፡፡ በእናቱ በኤዉንቄ እና በአያቱ በሎይድ በእግዚአብሄር ቃል ያደገ ነበር ፤ አባቱ ግሪካዊ እና ምናልባትም የማያምን ነበር (ሐዋ 16፡ 1) ፡፡ ጢሞቴዎስ በገላቲያ የሮም ከተማ ከነበረችው ከልስጥራ ከተማ ነበር (በአሁኑ ጊዜ ቱርክ የሆነችዉ) ፡፡ ጳዉሎስ በመጀመሪያዉ በአገልግሎት ጉዞዉ በልስጥራ ዉስጥ በመጓዝ (ሐዋ 16፡ 1) በዚያ ጢሞቴዎስን በማግኘት ጢሞቴዎስን መራዉ እርሱም የጳዉሎስ “ የተወደደ ልጅ ሆነ “ ፡፡ በሁለተኛዉ ጉዞዉ ላይ ጳዉሎስ እንደ ገና ልስጥራን በመጎብኘት በቀረዉ የአገልግሎት ጉዞዉ ላይ ጢሞቴዎስን ለመዉሰድ ወሰነ (ሐዋ 16፡ 1-3) ፡፡

ማክአርቱር የጳዉሎስን እና የጢሞቴዎስን ግንኙነት “ ጢሞቴዎስ የጳዉሎስ ደቀ መዝሙር፣ ጓደኛ እና በቀረዉ በጳዉሎስ ህይወት በቤሪያ፣ በአቴና እና በቆሮንቶስ ከእርሱ ጋር በማገልገል የስራ አጋሩ ነበር በተጨማሪም ወደ ኢየሩሳሌም በነበረዉ ጉዞ ላይ የጉዞ ጓደኛዉ ነበር “ ብሎ በመናገር ያስቀምጣል ፡፡ በሮም በጳዉሎስ በመጀመሪያዉ እስራት ጊዜ ጢሞቴዎስ ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ጳዉሎስ እስኪለቀቅም ድረስ በዚያ ከእርሱ ጋር ነበር ፤ ከዚያ ጢሞቴዎስ ወደ ሄደ ፡፡ ጢሞቴዎስ የጳዉሎስ ተወካይ በመሆን በማገልገል ጳዉሎስ የጀመራቸዉን ብዙ ቤተ ክርስቲያኖችን ጎበኘ ፡፡ በ 1ጢሞቴዎስ ጊዜ ጢሞቴዎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን እንደ እረኛ እያገለገለ ነበር (1ጢሞ 1፡ 3) ፡፡ ዕብ (13፡ 23) የሆነ ጊዜ ላይ ጢሞቴዎስ በእስር ቤት እንደ ነበር እና እንደተለቀቀ ይናገራል ፡፡

ጳዉሎስ 1ጢሞቴዎስን እና ቲቶን በሮም ከክርስቶስ ሞት (62-64 ) በኋላ ከመጀመሪያዉ እስራት እንደተለቀቀ ወዲያዉኑ ፃፋቸው ፤ ጳዉሎስ 2ጢሞቴዎስን ከክርስቶስ ሞት (66-67) በኋላ በሁለተኛ እስራቱ ጊዜ በአጭሩ ከመሞቱ በፊት ፃፈ ፡፡ በሁለተኛዉ እስራቱ ጊዜ ጳዉሎስ እንደሚለቀቅ ጥቂት ተስፋ ስለ ነበረው (2ጢሞ 2፡ 9, 4፡ 6-8, 13) እና የመጨረሻዉን ምክር ቃሉን እና ምክሩን ለመስጠት ጢሞቴዎስን ፃፈ ፡፡ ማክአርቱር በጳዉሎስ ላይ እነዚህን ሁለት እስራቶች ያወዳድራል፡

“ በመጀመሪያዉ እስራቱ ጳዉሎስ እንደሚለቀቅ ካለዉ ተስፋ በተቃራኒ በዚህ ጊዜ እንደዚያ አይነት ተስፋ አልነበረውም ፡፡ ኒሮ ክርስቲያኖችን ማሳደድ ከመጀመሩ ከክርስቶስ ሞት 64 በኋላ በፊት በሮም በመጀመሪያዉ እስራቱ በቤት ስር በመታሰር ከሰዎች እና ከአገልግሎት ጋር የመገናኘት ብዙ እድሎች ነበሩት (ሐዋ 28፡ 16-31) ፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ አምስት ወይም ስድስት አመት ቆይቶ (ከክርስቶስ ሞት 66-67 በኋላ) በቀዝቃዛ ስፍራ ነበር (2ጢሞ 4፡ 13)፣ በሰንሰለት (2ጢሞ 1፡ 2-9) እና ነፃ የመዉጣት ተስፋ በማጣት ዉስጥ ነበር (2ጢሞ 4፡ 6) “ ፡፡

በመልዕክቱ ዉስጥ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ስድስት ምክሮችን ሰጠው፡ 1) በስራዉ የታመነ በመሆን እንዲቀመጥ (2ጢሞ 1፡ 6)፣ 2) በጠንካራ አስተምሮ እንዲያስተምር እና እንዲኖር (2ጢሞ 1፡ 13-14)፣ 3) ስህተትን እንዲያስወግድ (2ጢሞ 2፡ 15-18)፣ 4) ስለ እምነቱ መከራ/መሰደድ እንደሚገጥመዉ እንዲቀበል (2ጢሞ 2፡ 3-4, 3፡ 10-12)፣ 5) በእግዚአብሄር ቃል የተደገፈ በመሆን እንዲቀመጥ እና 6) ያለማቋረጥ የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያስተምር (2ጢሞ 3፡ 15-4፡ 5) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ በእምነቱና በመጠራቱ የበረታ እንዲሆን ፈለገ ፡፡

ትምህርት

2-ጢሞቴዎስ (1፡ 1-12)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ንግግሮች የጀግንነት ስሜት በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ ጥሪዉን ለአገልግሎት እንደሆነ(ቁጥር 1)፣ ፍቅሩ ለጢሞቴዎስ (ቁጥር 2)፣ ጸሎቱ ጢሞቴዎስን መደገፍ እንደሆነ (ቁጥር 3)፣ ደስታዉ ከጢሞቴዎስ ጋር ባለዉ ግንኙነት (ቁጥር 4, 5) እና ፍላጎቱ ጢሞቴዎስን ማየት እንደሆነ ገለፀ ፡፡ ጳዉሎስ ሁለተኛ በታሰረ ጊዜ ያ ደስታ እየገጠመዉ ስላልነበር እያሳወቀ/እየተናገረ እና በክርስቶስ ከተወደደዉ ልጁ ጋር መሆንን እንደናፈቀ የሚናገር ይመስላል ፡፡

ደስታ መኖር በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ አስፈላጊ ነው ፡፡ ሮበርት ድርስኬል ስለ ደስታ ማወቅ የሚያስፈልጉ ሰባት ነገሮችን ይሰጣል፡ “ የአለም ደስታ ጊዜአዊና ተለዋዋጭ ነው “ (ኢዮ 20፡ 5, 18)፣ “ በብሉይ ኪዳን ደስታ እዉነተኛ ከሆነ እግዚአብሄርን ማምለክ ጋር የተገናኘ ነበር “ (1ዜና 15፡ 16, ዕዝ 3፡ 12, 6፡ 16)፣ “ ደስታ ከእግዚአብሄር የሚሰጥ ነው “ (ገላ 5፡ 22)፣ “ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ማድረግ ደስታችንን ይጨምረዋል “ (2ቆሮ 1፡ 24, 2፡ 3, ፊል 1፡ 4, 2፡ 2)፣ “ ሁኔታዎች ደስታችንን ሊወስዱት አይችሉም “ (2ቆሮ 6፡ 10, 1ጴጥ 4፡ 13)፣ “ ደስታችንን መንጠቅ የሚችለዉ ብቸኛዉ ነገር ኃጢዓት ብቻ ነው “ እና “ ክርስቲያን ሁል ጊዜ ደስ ይላቸዋል “ (1ተሰ 5፡ 16-18) ፡፡ ሲ. ኤስ. ሊዊስ “ ደስታ የሰማይ የማያቋርጥ ስራ ነው “ ፡፡ ጳዉሎስ ያን ደስታ ከጢሞቴዎስ ጋር ለማጣጣም ናፈቀ ፡፡

በቁጥር 6 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ከእግዚአብሄር ተቀብሎት የነበረዉን ስጦታ መጠቀም እንዲቀጥል አበረታታው ፡፡ ጳዉሎስ ያደረገዉ ስዕል በቡድኑ ዉስጥ እያስቀመጠው ነበር፣ አገልግሎቱን እየዳሰሰዉ ነበር እንዲሁም ለአገልግሎት ለመለየት እሱና ሌሎች በጳዉሎስ ላይ እጃቸዉን የጫኑበትን ቅዱሱን ጊዜ ለማስታወስ ነበር (ቁጥር 6) ፡፡ የድነት ሰራዊት ጠቅላይ ቡዝ “ የእሳት ዝንባሌ ወደ ዉጪ ለመዉጣት ነው፣ በልባችሁ መሰዊያ ላይ እሳትን ተመልከቱ ፤ እሳት ምድጃን የቀረበ ማንኛዉም ሰው አልፎ አልፎ ለማስነሳት/ለመደገፍ የሚያስፈልግ እሳት ይታወቃል “ አለ ፡፡ እጅ ን መጫን በመፅሀፍ ቅዱስ ለመባረከ፣ ለመፈወስ እና ለመቀደስ ሲሆን የሚታይ ነው (ዘኁ 27፡ 18, ማር 10፡ 16, ሉቃ 4፡ 40, ሐዋ 8፡ 17, 1ጢሞ 5፡ 22, ራዕ 1፡ 17) ፡፡

ጳዉሎስ በመቀጠልም ጢሞቴዎስን ኃይል፣ ፍቅር እና ራስን መግዛት እንጂ ፍርኃት ከእግዚአብሄር እንዳልመጣ አሳሰበው (ቁጥር 7) ፡፡ ጳዉሎስ የራሱን ሁኔታ በመግለፅ ጢሞቴዎስን በእስርቤት በመሆኑ በእርሱ እንዳያፍር እና ጢሞቴዎስ በክርስቶስ በመሆኑ (ቁጥር 8)፣ ክርስቶስ እኛን ከሞት እና ከቅጣት (በማፅደቅ ሂደት) በማዳን ለእርሱ የተለዬን እንድንሆን ስለ መጠራታችን እንዳያፍር ይነግረዋል (ቁጥር 9-10) ፡፡ ጳዉሎስ እንደገና ጥሪዉን እንደ እረኛ፣ እንደ ሐዋሪያ እና እንደ አስተማሪ በመመልከት ከእነዚህ ጥሪዎች የተነሳ መከራ እንደደረሰበት ጢሞቴዎስን አሳሰበው (ቁጥር 11-12) ፡፡

2-ጢሞቴዎስ (1፡ 13-18)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን መንፈሳዊ ስልጣን ተሰጥቶት እንደ ነበርና ተቀብሎት በነበረዉ ጠንካራ አስተምሮ ላይ እንዲፀና እንዲሆን አሳሰበው (ቁጥር 13) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ከተቀየሩት ብዙዎች ጋር ለሁለት አመታት ወንጌልን አጋርተዉ እንደ ነበር ያስታዉሰዋል ፤ ይሁን እንጂ በእስያ ያሉት ሁሉ ፊሎግስና ሄርዋጌኔስ ጨምሮ ተመልሰዉ ነበር (ቁጥር 13-15) ፡፡ ይሁን እንጂ ልሄኔሲፎሩ በመራቅ አልወደቀም ነበር፣ ብዙ ጊዜም ጳዉሎስን በእስራት ጎብኝቶት እንደ ነበርና በእስራቱም አላፈረም ነበር (ቁጥር 13-15) ፡፡ ጳዉሎስ ልሄኔሲፎርና ቤተ ሰቦቹ የእግዚአብሄርን ምህረት እንዲቀበሉ ፀለየላቸው (ቁጥር 18) ፡፡

መደምደሚያ

ይህ 2ጢሞቴዎስ 1 ነው ፡፡ ታሪኩን ነገ እንቀጥላለን ፡፡

11 Ralph Earle. "2 Timothy." In Ephesians-Philemon. Vol. 11 of The Expositor's Bible Commentary. 12 vols. Edited by Frank E. Gaebelein and J. D. Douglas. Grand Rapids: Zondervan Publishing House, 1978, p. 395; quoted in Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): 2 Timothy, p. 14; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2timothy.pdf.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1772.

  2. MacArthur, p. 1772.

  3. MacArthur, p. 1772.

  4. MacArthur, p. 1772.

  5. MacArthur, p. 1801

  6. MacArthur, p. 1801.

  7. MacArthur, p. 1801.

  8. MacArthur, p. 1801.

  9. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 240.

  10. Robert Driskell, “Bible Study on Joy: 7 Things You Need to Know,” What Christians Want to Know; available at https://www.whatchristianswanttoknow.com/bible-study-on-joy-7-things- you-need-to-know/.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ጢሞ (1፡ 6) ጳዉሎስ እግዚአብሄርን የሰጠው ስጦታን “ እንዲያቀጣጥለው “ ነገረው ፤ ተመሳሳይ ልምድ አላችሁ ? የማን ኃላፊነት የሚያቀጣጥል ነው ? በስጦታችሁ እየተመላለሳችሁ ነው ? አይደለም ከሆነ ለምን ?
  2. የፍርሀት መንፈስ (2ጢሞ 1፡ 7) ከጠላት እንደሆነ ካወቅን እና እግዚአብሄር የፍቅርን፣ የኃይልን መንፈስ ስለሰጠን ፍራትን እንዋጋዉ ፡፡ በላያችሁ ላይ የፍራት መንፈስ መጥቶባችሁ ያውቅ ነበር ? እንዴት አድርጋችሁ አስተናገዳችሁት/ያዛችሁት ? እግዚአብሄርን ለኃይል፣ ለፍቅር እና ራስን ለመግዛት ፈልጋችሁታል?
  3. በ 2ጢሞ (1፡ 14) ጳዉሎስ ቲሞቴዎስን “ በእርሱ ያለዉን መልካሙን አደራ “ እንዲጠብቅ ነገረው ከማን ወይም ከምንድን ነዉ የሚጠብቀው ?
  4. በ 2ጢሞቴዎስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Timothy 1:8

“So don’t be ashamed of the testimony about our Lord, or of me His prisoner. Instead, share in suffering for the gospel, relying on the power of God.”

በጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በተጻፈ የመጨረሻ ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ ጢሞቲዎስን በኃይል ፣ በፍቅር እና ራስን በመግዛት የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መመስከሩን እንድቀጥል ደግሞም ከጌታ በሆነው ምስክርነቱ እንዳያፍር መከረው ፡፡ በእግዚአብሔርም ኃይል ላይ እንድደገፍ አዘዘው ፡፡

ወንጌልን ለመናገር ፣ ህይወትህን ለክርስቶስ ለመኖር ፣ በእምነትህም ለመጠንከር ስታስብ ፍርኃት ይሰማህ ይሆናል እንድሁም መሸማቀቅ ፣ ማፈር ወይም አለመመቸትም እንድሁ ፡፡ እስኪ እንዲህ ብለህ ራስህን ጠይቅ ፡- በራሴ አቅምና እውቀት ላይ ነው የምደገፈው ወይስ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ኃይል ላይ ነው የምደገፈው ? እስኪ አስብ የውሃ ላይ ተንሸራታቹ በውሃው ላይ ለመቆም ሲሞክር ፡፡ ይህ የውሃ ላይ ተንሸራታች በራሱ ኃይልና ብርታት ከውሃው ውስጥ ራሱን ለማውጣት ቢጥር ፣ ፈጽሞ ሊቆም አይችልም ፡፡ ነገር ግን ተንሸራታቹ አካሉን የት ጋር ማስቀመጥ እንዳለበት ትኩረት ሲያደርግና ፣ አይኖቹን በጀልባው ላይ እንድያነጣጥሩ አድርጎ ሲያስተካክል ደግሞም የጀልባው ኃይል እንድረዳው ሲያደርግ ፣ ያኔ ነው ተሳክቶለት በውኃው ላይ መቆም የሚችለው ፡፡

በተመሳሳይ ምስክርነትህን ስትናገር አይኖችህንና ልብህን ከእግዚአብሔር ባገኘኸው ኃይል አድርግ ፡፡ የራስህን ጉዳይና ስርዓት ተወው ፡፡ ራስህን ከጌታ ጋር ስታደርግ ፣ በእግዚአብሔርም ኃይል ላይ ስትደገፍ መለኮታዊ በሆነ መንገድ የወንጌል ምስክርነት ከአንተ ይፈሳል ፡፡ ፍርኃት ይጠፋል ኃይልንም ትለብሳለህ !

“ እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል ፡፡ “

  • 2ኛ ጢሞቲዎስ 1፡8

ተጨማሪ ጥቅስ

ዮሐንስ 14:26 — “ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል ። “

ፊልጵስዩስ 4:13 — “ ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ ። “

2ኛ ጢሞቲዎስ 1:7 — “ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና ። “