Paul's Proverbs Of Ministry
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የጳዉሎስ የመጀመሪያ መልዕክት ለጢሞቴዎስ የዉትድርና ሀሳብ ባለዉ ምዕራፍ በምዕራፍ 6 ያጠቃልላል (1ጢሞ 6፡ 12) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በኤፌሶን ላለች ቤተ ክርስቲያን ስለሚጠቅሙ ነገሮች እንዲዋጋ/እንዲታገል በማሳሰብ የኤፌሶንን ቤተ ክርስቲያን እየጎዱ በነበሩ የሀሰት ትምህርቶች እና በሀሰት አስተማሪዎች ላይ እንዲነሳ ጠራው ፡፡ መልዕክቱ አሁንም ለቤተ ክርስቲያን መልካም/ተገቢ የሆነ ነው ፤ ወደኃላ ሳንመልስ እዉነት እንደሆን በምናዉቀዉ ነገር ላይ መዋጋት ያስፈልገናል ፡፡
1-ጢሞቴዎስ 6 እንደ ምሳሌ ምርጫ ይነበባል ፤ ጳዉሎስ መልዕክቱን ከመዝጋቱ በፊት ከጢሞቴዎስ ጋር ስለተነጋገራቸዉ ነገሮች እርግጠኛ መሆን የፈለገባቸዉ ብዙ ትምህርቶች ነበሩት ፡፡
ትምህርት
1-ጢሞቴዎስ (6፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ባሮች ከእግዚአብሄር ጋር ካላቸዉ ግንኙነት የተነሳ እንዴት ጌቶቻቸዉን መመልከት እንዳለባቸዉ ትዕዛዞችን ይሰጣል ፡፡ ከባሪያነት አገባብ የተነሳ እነዚህን ጥቅሶች እንዴት እንደምደርስ አላውቅም ፤ ስለዚህም መፅሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ብቻ በማንበብ በዚያ ዉስጥ እንጓዛለን ፡፡ ዋይርስቤ ይህን ለአሁኑ ዘመን እንደ አማኝ አለቆቻቸዉ ያ ክብር ቢገባቸዉም ባይገባቸውም ለአለቆቻቸዉ የሚደግ ክብር በማለት ይተረጉመዋል ፡፡ ስለዚህም ባሪያ የነበሩ በኃላፊነት ለነበሩት አማኞች ይሁኑም አይሁኑም ከማያምኑት ይልቅ ለወንድሞቻቸዉ ጠንክረዉ በመስራት አክብሮትን ሊያሷያቸዉ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
ኮንስታብል “ ጳዉሎስ ወደ ሌሎች ተገቢ ድርጊትን ለማድረግ ቀላል የሚያደርገዉን ተገቢ የሆነን ጠባይ እንዲቀበሉ እንዳሳሰበ ፤ ጌቶቻቸዉን በእነርሱ ላይ ስልጣን እንዲኖራቸዉ እግዚአብሄር አስቀምጧቸዉ ከነበረዉ በላይ ሌላ ምክንያት ከሌለ ክርስቲያን አገልጋዮች ጌቶቻቸዉ የሚገባቸዉን ክብር ሁሉ ማድረግ/መስጠት ነበረባቸው “ በማለት ይገልፃል ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (6፡ 3-10)፡ ከክርስቶስ አስተምሮ ጋር የማይስማማ የሐሰት ትምህርት የሚያስተምር ማንኛዉም ትዕቢተኞች የነበሩ እና ባለመስማማት እና በቃላት ዉጊያ “ የታመመ ፍላጎት ነበራቸው “ (ቁጥር 3-4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ እነዚህ ሐሰተኛ አስተማሪዎች እዉነታን ወደ ተግባር ከማስቀመጥ ይልቅ የቲዎሪይ እና የክርክር ፍላጎት ነበራቸው ፡፡ በቃላቶች ላይ ለመከራከር በሽተኛ/ልክ ያልሆነ ፍላጎት እንደ ነበራቸው “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ሐሰተኛ አስተማሪዎች በትምህርታቸው በፋይናንስ/በገንዘብ ጥቅም የሚነዱ እንደ ነበሩ ገልፆአቸዋል (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስ “ እዉነትን የከለከሉ “ በማለት ገለፃቸዉ ትርጉሙም ንግግራቸው ጥቅም የለዉም ነበር ፡፡
በቁጥር 6-7 ጳዉሎስ በቁስ በሚገኘዉን ሳይሆን በክርስቶስ የሚገኘዉን እርካታን አጥብቆ ይናገራል ፡፡ ቁጥር 7 ጢሞቴዎስን የሰዉ ልጅ ያለምንም ነገር እንደተወለደ በሚሞቱም ጊዜ በክርስቶስ ከሚያገኘዉ የዘላለም ህይወት ዉጪ ምንም ነገር ይዞ እንደማይሄድ የሚያስታዉሰዉን ኢዮብ (1፡ 21) ይጠቅሳል ፤ ሌላ ምንም በቋሚነት አይቆይም ፡፡ በምድር ላይ የሚያስፈልገዉ ሁሉ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚደረግ ይዘት አለዉ - ምግብን እና ልብስን (ቁጥር 8) (ማቴ 6፡ 25-28, 34, ሉቃ 12፡ 25, ዮሐ 14፡ 27, ፊል 4፡ 11-12) ፤ ይሁን እንጂ ብልፅግናን/ሀብትን ለማግኘት ትኩረት የሚያደርጉ ለፈታና፣ ለወጥመድ እና ሞኝነት ለሆነ ፍላጎት ክፍት ናቸው (ቁጥር 9) ፡፡ ይህ ትኩረት ወደ ዉርደት/መፍረስ እና ጥፋት ዉስጥ ይዘፈቃሉ (ቁጥር 9) ፤ ጊዜአዊ ነዉ ወይስ ዘላለማዊ ? የኔልሰን ማብራሪያ መፍረስን እና መጥፋትን “ እንደ መፍረስ እና እንደ ማይመለስ ኪሳራ “ ይገልፀዋል ፤ “ ይህ ኪሳራ ለመኖር ስህተት በሆነ አላማ በዚህኛዉ ህይወት ሊደርስ እንደሚችል ወይም የቁስ ፍላጎት ሰዉዬዉን ከክርስቶስ አርቆ ከመራው ከህይወት በኋላም የሚገጥም እንደሚሆን “ ይቀጥላል ፡፡
ጳዉሎስ አብዛኛዉን ጊዜ በእነዚህ ቃለምልልሶች ቃል ላይ ችግሩ ገልፆአል፡ “ ገንዘብን መዉደድ የጥፋት ሁሉ ስር ነው “ (ቁጥር 10) ፡፡ ጳዉሎስ ገንዘብን መዉደድ ስር እንደሆነ እንጂ የክፋ ስር አይደለም አለ ፡፡ ገንዘብ መጥፎ አይደለም ነገር ግን የገንዘብ ፍቅር፣ ፍላጎት እና ጉጉት ችግር ነው ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (6፡ 11-16)፡ ገንዘብን መጓጓት ሰዎችን ከክርስቶስ በማራቅ ሊመራ ይችላል ምክንያቱም ትኩረታቸዉን ከእርሱ ላይ በመዉሰድ ኃብትን ማሳደድ ስለሚሆን ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን “ እንደ እግዚአብሄር ሰው “ ከገንዘብ እና ከኃብት ፈተናና ወጥመድ በማምለጥ/በመሸሽ የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንዲከተል አዘዘው (ቁጥር 11) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን “ ስለ እምነት መልካሙን ገድል እንዲታገል “ እና በእግዚአብሄር ነገር ላይ እንዲፀና አዘዘው (ቁጥር 12) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ከምኞት እንዲሸሽ (1ዮሐ 2፡ 15-17)፣ የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንዲከተል (ሮሜ 7፡ 18-25) እና ክርስቶስ እስኪመለስ ድረስ መልካሙን ገድል እንዲጋደል ነገረው (ቁጥር 14) (2ጴጥ 3፡ 10-16, 1ዮሐ 2፡ 28) ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እግዚአብሄር እግዚአብሄር ስለሆነ ነገሮችን በጊዜዉ እንደሚያደርጋቸዉ አሳሰበው (ቁጥር 15) ፤ እሱ ሉዓላዊ፣ ዘላለማዊ እና ህያዉ/የማይሞት ስለሆነ (ቁጥር 16) ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (6፡ 17-19)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ባለፀጋ የነበሩትን ከኃብታቸዉ የተነሳ ትዕቢተኞች እንዳይሆኑ ወይም በጣም የሚጠቅም ለማድረግ ከዚያ ይልቅ በእግዚአብሄር ላይ እንዲያተኩሩ እንዲያዛቸዉ ነገረው (ቁጥር 17) ፡፡ ጢሞቴዎስ መልካም የሆነዉን እንዲያደርጉ፣ ለጋስ/ቸርነትን እንዲያደርጉ እና እግዚአብሄር ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ነገር እንዲያካፍሉ (ቁጥር 18) እና የማይደረገዉን የህይወት ነገር የሆነዉን የእግዚአብሄርን ነገር እንዲያከማቹ ይነግራቸዋል (ቁጥር 19) ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (6፡ 20-21)፡ ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ በግል በምዕራፉ መጨረሻ ላይ መለሰለት ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ለእርሱ ተሰጥቶት የነበረውን እንዲጠብቅ እና ከሀሰት ትምህርት የመጣውን ባዶ ንግግር እና ክርክር ከንቱ ቃልን ከመናገር ራሱን እንዲጠብቅ አበረታታው (ቁጥር 20) ፡፡ ጳዉሎስ የሐሰት ትምህርት ሰዎችን ከእግዚአብሄር ለይቶ የነበረ እና በጣም አደገኛ እንደነበር አብራርቷል ፡፡ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ያሉትን ሁሉ በመባረክ ዘጋ “ ፀጋ ከእናንተ ጋር ይሁን “ (ቁጥር 21) ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲከተል ደረጃን ለመስጠት በ እ የሚጀምሩ አራት ቃላቶችን ተጠቅሟል፡
- ከምኞት እንዲሸሽ
- የእግዚአብሄርን ፅድቅ እንዲከተል
- መልካሙን ገድል እንዲጋደል
- ለትምህርቱና ለእግዚአብሄር የታመነ ሆኖ እንዲቀመጥ
ኢየሱስ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ሁላችንም እነዚህን ሁሉ እናደርጋለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 224.
Thomas Constable, Constable’s Expository (Bible Study Notes): 1 Timothy, p. 117; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1timothy.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1605.
Nelson’s Commentary, p. 1606.
Nelson’s Commentary, p. 1606.
ጥያቄዎች
-
በ 1ጢሞ (6፡ 1-2) በባሮች እና በጌቶቻቸዉ መካከል ስላለዉ ግንኙነት ተናገረ ፤ በአሁኑ ጊዜ በምን ግንኙነት የሚወዳደር ሊሆን ይችላል ? በእኛ ላይ ስልጣን ያላቸዉን ማክበር ለምን ጠቃሚ/አስፈላጊ ነው ? (ዘጸ 22፡ 28, ሐዋ 23፡ 5, ሮሜ 13፡ 1, ቲቶ 2፡ 9)
-
በ 1ጢሞ (6፡ 3-5) ላይ አማኞችን የጳዉሎስ ማስጠንቀቂያ ምን ነበር ? (ሮሜ 16፡ 17-18, 2ጢሞ 3፡ 8)
-
1ጢሞ (6፡ 6) “ ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለዉ ግን እግዚአብሄርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነዉ “ ይላል ፤ እግዚአብሄር በሰጣችሁ እንዴት ታተርፋላችሁ ? ከነገሮች በኋላ ብዙ ትፈልጋላችሁ ወይስ እግዚአብሄርን ይበልጥ ትፈልጋላችሁ ?
-
በጳዉሎስ ንግግር መሰረት ገንዘብ መኖር መጥፎ ነገር ነው ? በ 1ጢሞ (6፡ 7-10) አገባብ ስለዚህ ነገር አስቡ ፤ ጳዉሎስ ገንዘብ በራሱ መጥፎ ነገር ነዉ እያለ ነበርን ? ለባለፀጋ ሰዎች ጳዉሎስ ምን ትዕዛዝ ሰጠ ? (1ጢሞ 6፡ 17-19)
-
በ 1ጢሞ (6፡ 12) “ ስለ እምነት መልካሙን ገድል ተጋደል “ ሲል ምን ማለቱ ነው (2ጢሞ 2፡ 2-4, 4፡ 7-8, ዕብ 12፡ 1-2)
-
በ 1ጢሞቴዎስ 6 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Timothy 6:11–12
“But you, man of God, run from these things, and pursue righteousness, godliness, faith, love, endurance, and gentleness. Fight the good fight for the faith; take hold of eternal life that you were called to and have made a good confession about in the presence of many witnesses.”
በጣም ብዙ የዓለም ነገሮች የእናንተን አሳብ ፣ ፍቅርና ትኩረት ለመስረቅ ይታገላሉ እነርሱም ፡- ውበት ፣ ስፓርት ፣ ፣ ገንዘብ ፣ ስኬት ፣ እውቀት ፣ ልማድ ፣ የማህበራዊ ሚድያ ተፅዕኖ ….. ብዙ መጥቀስ ትችላላችሁ ፡፡ እነዚህ እየጨመሩ ይሄዳሉ ነገር ግን እናንተን ገና ብዙ እንደሚቀራችሁ ምንም እንዳልያዛችሁ እንድሰማችሁ ያደርጋሉ ፡፡ እናም ከዚያ በቂ እንዳልሆናችሁ በምታስቡበት በዚያ ውሸት ቀስ ብሎ ይገባል ፡፡
እግዚአብሔር ከእነዚህ ክፉ መሻቶች ፣ ፍላጎቶች ፣ የዚህ ዓለም ነገሮችን ከመውደድ መራቅ እንደሚገባ ይናገራል ፡፡ እነዚህ ነገሮች አሳባችሁን ደግሞም እናንተን ከእግዚአብሔር ያርቃሉ ፡፡ ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ከእነዚህ ነገሮች እንድርቅ እናም ጽድቅን ፣ እግዚአብሔርን መምሰል ፣ እምነትን ፣ ፍቅርን ፣ መጽናትን ፣ የዋህነትንም በማድረግ እግዚአብሄርን እንድከተል አዘዘው ። በየቀኑ ከልባችሁ በመሆን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ስትኖሩ እርሱን ለማወቅ ትራባላችሁ ፣ እርሱን ለመምሰል ትፈልጋላችሁ እንድሁም አለም ከሚያቀርብላችሁ ነገሮች ይልቅ ከእዚአብሔር በሆኑት ነገሮች ደስ ይላችኋል ፡፡ በእርሱ ደስ ይላችኋል ደግሞም በየቀኑ ለምታደርጉት መንፈሳዊ ውጊያ ብርታትን ታገኛላችሁ ፡፡ ጠላት የመጀመሪያ ምርጫችሁ ለመሆን ይታገላል ፡፡ ሆኖም ግን በርቱ በጌታም ላይ ባላችሁ እምነት ጸንታችሁ ቁሙ ፡፡ ከዚህ ዓለም ነገሮች ሽሹ ፣ እግዚአብሔርንም ተከተሉ ፡፡ ስለእምነት መልካሙን ገድል ስትጋደሉ በእናንተ በኩል በኢየሱስ አማካኝነት ድልን ታገኛላችሁ ፡፡ ዛሬ በዚህ ተስፋ ተራመዱ ፡፡
“ አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ፥ ከዚህ ሽሽ ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል ። መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ ። “
- 1ኛ ጢሞቲዎስ 6፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
ኤርምያስ 29:13 — “ እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ ። “
1ኛ ጢሞቲዎስ 6:6 — “ ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው ፡፡ “
ያዕቆብ 4:7 — “ እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።