Paul's Letters 1 Timothy

The Widows And Elderly

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 564 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በጳዉሎስ መልዕክት ጥናታችን ይህ 78ተኛ ክፍል ነው ፡፡ ለእኛ ቃሉ በጥበብ እና በተግባረዊ ምክር የሚንጠባጠብ ነው ፡፡ በ 1ጢሞቴዎስ ጳዉሎስ እንደ ታላቅ አገልጋይ ወደ ወጣት ተተኪዉ ጢሞቴዎስ ላይ አፈሰሰ ፡፡ በምዕራፍ 5 በትክክል ትኩረት የሚያስፈልጋቸዉን የቤተ ክርስቲያንን ተግባራዊ ጉዳዮችን ያቀርባል ፡፡

ትምህርት

1-ጢሞቴዎስ (5፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን “ ከእድሜአቸዉ አንፃር ለመዉደድ እና ሁሉንም ለማገልገል ታላላቅ የሆኑትን አባላት ችላ እንዳይላቸው “ በማዘዝ ጀመረ ፡፡ በቁጥር 1-2 ከእድሜአቸዉ አኳያ ትኩረት የሚገባቸዉን ያክል ጢሞቴዎስን በማስታወስ አራት ግላዊ የሆኑ ቡድኖችን ይዘረዝራል ፡፡ መገሰፅ ማለት ለሰዉ በኃይለኛዉ መናገር ማለት ነው (ቁጥር 1) ፡፡ ወጣቶች/ብላቴና ሰዎች ከማክበር ዉጪ ለታላቅ/ለትልልቅ ሰዎች የሚናገሩት ጉዳይ አልነበራቸው ፤ ይህ ከእኛ የሚበልጡትን በማክበር እንድንናገር የእግዚአብሄር ስርዓት አካል ነው ፡፡ ጳዉሎስ ትልቅ የሆኑ ሴቶች ለእነርሱም ማክበር እንዲደረግላቸዉ እና ለወጣት ሴቶች ደግሞ እህቶቹ እንደ ሆኑ አድርጎ እንዲመለከት ያካትታቸዋል (ቁጥር 2) ፡፡

1-ጢሞቴዎስ (5፡ 3-16)፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ባልቴቶችን ሁሉ የተከበሩ መሆን እንዳለባቸው እና “ በእዉነት ባልቴቶች የሆኑ “ ማለትም የሚያግዛቸዉ ቤተሰብ ያልነበራቸው በሚያስፈላጋቸዉ የገንዘብ እርዳታ የተከበሩ እና የተረዱ እንዲሆኑ አዘዘ (ቁጥር 3) ፤ ይሁን እንጂ ባልቴቶቹ ቤተሰብ ከነበራቸው በእግዚአብሄር ፊት መልካም የሆነዉን በመምሰል ያከብሯቸዉ እና ይረዷቸው ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቤተሰባችንን ማክበር እንዲያድጉ በአካላዊና በፋይናንስ መርዳትን እንደሚያካትት “ ይናገራል ፤ ይህ ጌታን ያስደስተዋል ፡፡ ከቤተሰብ ድጋፍ ዉጭ በልመናና በፀሎት ራሳቸዉን የሰጡ ከሆነ ይህ ኃላፊነቱ የቤተ ክርስቲያን ነው (ቁጥር 5) ፤ ራሳቸዉን የሚሞላቀቁ ወይም እንደ እግዚአብሄር በማይኖሩት ቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት የለባትም (ቁጥር 6) ፡፡

ትክክል የነበረዉን በማድረግ አማኞች በጉባኤዉ ዉስጥ በማህበረሰቡ መልካም ዝናቸዉን ይጠብቃሉ ቤተ ክርስቲያንም ያለ ነቀፋ ትሆናለች (ቁጥር 7) ፡፡ የጳዉሎስ በቤተሰባቸዉ ዉስጥ ለባልቴቶች ትኩረት ለማይሰጡት ነቀፋዉ/ፍርዱ ጠንካራ ነበር ፤ እምነታቸዉን በመካድ ከማያምኑት ይልቅ የከፉ እንደሆኑ ገለፃቸው (ቁጥር 8) ፡፡

ጳዉሎስ ለባልቴቶች ከቤተ ክርስቲያን ድጋፍን ለመቀበል መስፈርቶችን ሰጥቷል ፡፡ ቢያንስ 60 አመት የነበራቸዉ የአንዲት ሴት ባል የሆኑት በመልካም ስራዎች የታወቁ ነበሩ - ልጆቿን በማምጣት፣ እንግዳ ተቀባይነትን በማሳየት፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የታመሙትን በመርዳት እና ሌሎች መልካም ስራዎችን አድርገዋል (ቁጥር 9-10) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የእድሜ ገደቡ ለምን ተቀምጦ እንደ ነበር ይገልፃል “ ለዚህ ክልከላ ምክንያቱ (ከ60 አመት በታች) ያሉት ወጣት ባልቴቶች የማይረባ ፍላጎት በማሳደግ ጋብቻቸዉ ከመጀመሪያዉ እምነታቸዉ ዉጪ ይሆናል ይህ ማለት ወሲባዊ ፍላጎትን ለማግኘት/ለመለማመድ ምናልባትም የማያምኑትን ለማግባት ስለሚፈልጉ “ (ቁጥር 11-13) ፡፡

ጳዉሎስ ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ እና ልጆች እንዲኖሯቸዉ ይፈልጋል ይህ ከሆነ ሰይጣን ሊጠቀምባቸዉ አይችልም (ቁጥር 14-15) ፡፡ በቁጥር 16 ለቤተሰብም ሴት አማኞችን በማካተት በቤተሰባቸዉ ዉስጥ ባልቴቶችን በመደገፍ እንዲረዱ እና ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን እዉነተኛ የሆኑትን ባልቴቶች መርዳት እንደምትችል ጳዉሎስ ግሳፄዉን ደገመው (ቁጥር 16) ፡፡

1-ጢሞቴዎስ (5፡ 17-25)፡ በቁጥር 17 ጳዉሎስ ለሽማግሌዎች ላይ በሚደረግ እርዳታ ላይ ቀጠለ ፡፡ በስብከት እና በማስተማር ጠንክረዉ ለሚሰሩ እና መልካም መሪዎች ለነበሩ “ ለሰራተኛ ደሞዙ ስለሚገባዉ “ (ቁጥር 18) መክፈል መልካም እንደ ነበር ተናገ ፡፡ በቁጥር 19 ጳዉሎስ በአንድ ሽማግሌ ላይ ያለ ክስ ከሁለት ወይም ከሰዎስት ምስክር ዉጪ እንዳይመጣ ገለፀ ፤ ይህ አሁንም ክብርን ስለማሳየት ነው ፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰዉ ጥፋተኝነት በተገኘበት ጊዜ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ሌሎች በኃጢዓታቸዉ ዉጤት ምክንያት እንዲፈሩ በአደባባይ እንዲገስፃቸው አዘዘው (ቁጥር 20) ፡፡ ጳዉሎስ “ ቅጣት በቤተ ክርስቲያን እንደሚተገበር ያውቃል ፤ ነገር ግን ያለ ምንም አድሎ ወይም ወገንተኝነት መሆን የሌበትም (ቁጥር 21-22) “ ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ጊዜዉን ሽማግሌን በመሾም እና በሌሎች ኃጢዓት እንዳልተባበረ እርግጠኛ እንዲሆን አስጠነቀቀው (ቁጥር 22) ፡፡

ጳዉሎስ በቁጥር 23 ለጢሞቴዎስ በግል መልዕክት በመፃፍ የንግግሩን ሰንሰለት ተርጉሟል ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የሆድ ህመሙን ለማስታገስ እና ቶሎ ቶሎ ለሚያመዉ እንዲረዳው በዉሃዉ ላይ ጥቂት ወይን እንዲጨምር ነገረው፡፡

በመጨረሻም ጢሞቴዎስን አንዳንድ ኃጢዓት ከመጀመሪያዉ የተገለጠ እንደሆነ ነገር ግን ሌሎች ቆይተዉም ላዩን እንደማያየው አሳሰበው (ቁጥር 24) ፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ መልካም ስራዎች ከተፈፀሙበት ጊዜ ጀምሮ የታወቁ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ብዙ ቆይተዉም የማይታወቁ እንደሆኑ አመለከተ (ቁጥር 25) ፡፡

መደምደሚያ

የጳዉሎስ ምክር ለጢሞቴዎስ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ስርዓትን/ደም ተከተልን እንዴት እንደሚያመጣ፣ መሪዎችን እንዴት እንደሚመለምል እና የቤተ ክርስቲያንን መበለቶች እንዴት ማየት እንደሚገባው ነበር ፡፡ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በቤተ ክርስቲያ ዉስጥ ያሉ ሰዎችን መቀጣት የሚያስፈልጋቸዉንም እንኳን በማክበር እንዲመለከታቸዉ አሳሰበው ፡፡ በፃፈዉ ሁሉ የጳዉሎስ ዋና ትኩረት ለጉባኤዉ አባላት እና እንደ እረኛ ለጢሞቴዎስ ነበር ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 228.

  2. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1604.

  3. Nelson’s Commentary, p. 1604.

  4. Nelson’s Commentary, p. 1604.

  5. Nelson’s Commentary, p. 1604.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ጢሞቴዎስ 5 መሰረት በቤተሰባቸዉ ዉስጥ ለባልቴቶች እንክብካቤ ማድረግ ለልጆች እና ለልጅ ልጆች እንዴት ጠቃሚ ነው ? እንደ ማህበረሰብ ዛሬ በዚህ ላይ ስለምናደርገዉ መልካም ስራ እንዴት እንደምናደርግ ታስባላችሁ ? ቤተሰብ ለሌላቸዉ ባልቴቶች የማን ስራ ጥንቃቄ ያደርግላቸዋል ?
  2. ለወጣት መበለቴቶች ጳዉሎስ ያለዉ ምኑ ነበር ምርጥ ለምንስ ?
  3. በ 1ጢሞ (5፡ 17) ጳዉሎስ “ በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት እጥፍ ክብር ይገባቸዋል “ አለ ፤ እዚህ ላይ ጳዉሎስ እያወራ የነበረዉ ማንን ነበር ? እንደ ቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችን የሚጠብቅ/የሚንከባከብ መልካም ስራዎችን እናደርጋለን ? ለተለያዩ ቤተ ክርስቲያኖች በጳዉሎስ መልዕክቶች ዉስጥ ብዙ የተለያዩ ጊዜ ለመሪዎቻችን እንድንጠነቅቅ ጠቅሷል (ገላ 6፡ 6, 1ተሰ 5፡ 12) ፡፡ ይህን ማድረጉን ለምን ታምናላችሁ ?
  4. በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ላይ ያለን ክስ ለመቀበል ግዴታዎቹ ምንድን ናቸው ? ይህ ለምን አስፈላጊ ነው (ማቴ 18፡ 16) ? በግል አስተያየታችሁ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ለተሳሳተ ድርጊታቸዉ መሪዎቻችንን በሚገባ በተጠያቂነት እንይዛቸዋለን ? ብዙ ፀጋን እንሰጣቸዋለን ወይስ በቂ ፀጋ አይደለም ?
  5. በ 1ጢሞቴዎስ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Timothy 5:3

“Support widows who are genuinely widows.”

ጳውሎስ ልክ ሽማግሌ ወጣትን በአገልግሎቱ እንደሚመክር ሁሉ አብሮት የሚያገለግለውን ጢሞቲዎስን መከረው ፤ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ልትሆን እንደሚገባ ደግሞም ባልቴቶችን እና ሽማግሌዎችን ለመርዳት ቤተ ክርስቲያን ስላለባት ኃላፊነት መመሪያን ሰጠው ፡፡

የሰማዩ አባታችን ልብ ልጆቹን በመመልከት ላይ ነው ፡፡ በተለይም ደግሞ በዚህ ክፍል ውስጥ ጳውሎስ ስለ ባልቴቶች ያወራል ፡፡ እግዚአብሔር አብ የሚረዳና የሚንከባከብ ልብ አለው ፡፡ አናንተም እንደ እግዚአብሔር አምባሳደርነት ባልቴቶችን ልትረዱ ልትንከባከቡ ተጠርታችኋል ፡፡ ስለ ማሀበረሰብህ ፣ ጎረቤቶችህ ፣ ቤተሰብህ ወይም ስለ ስራ ቦታህ ለማሰብ ትንስ ደቂቃ ውሰድ እስኪ ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታይ እንዴት አድርጋችሁ ባልቴቶችን መርዳት እንደምትችሉ ጌታን ጠይቁ ፡፡ በየጊዜው ጎብኙዋቸው ፡፡ እራት ጋብዙዋቸው ፡፡ ሳራቸውን ወይም አዝመራቸውን ሰብስቡላቸው ፡፡ ለህክምና ቀጠሮ ይዛችሁዋቸው ሂዱ ፡፡ በርግጥ ይህ የሆነን ሰው ለመርዳት ለመንከባከብ ከራሳችሁ ፕሮግራም እንደ መውጣት ነው ፡፡ አዎን ይህ ለሆነ ሰው ብላችሁ የራሳችሁን አጀንዳ ወደ ጎን እንደ ማለት ነው ፡፡ ነገር ግን ይህ ነው የሰማዩ አባታችን ልብ ! እርሱ ወዷችኋልና ስለዚህም እናንተ ሌሎችን ያለ ስስት መውደድና እነርሱን መርዳት መንከባከብ ትችላላችሁ ፡፡ ልክ እናንተ ባልቴቶችን ለመንከባከብ በመታዘዝ በእርሱ ላይ ስትታመኑ እርሱ ደግሞ ብርታት ፣ ጥበብና ደስታን ይሰጣችኋል ፡፡ በህይወታችሁ በዙሪያችሁ ያሉትን ባልቴቶች ለማየት አይኖቻችሁን ክፈቱ ፡፡ ልታደርጉ የተጠራችሁት ይህን ነው ፡፡

“ በእውነት ባልቴቶች የሆኑትን ባልቴቶች አክብር ። “ - 1ኛ ጢሞቲዎሰ 5፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 68:5 — “ እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው ። “
  • ኤፌሶን 6:20 — “ ስለ ወንጌልም በሰንሰለት መልእክተኛ የሆንሁ፥ መናገር እንደሚገባኝ ስለ እርሱ በግልጥ እናገር ዘንድ ለምኑ ። “
  • ያዕቆብ 1:27 — “ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው ። “