The Characteristics Of Godly Ministers
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ጳዉሎስ ይህን መልዕክት መፃፉን በመቀጠል ለጢሞቴዎስ እንደ ቀደምት እረኛ ለወጣት እረኛ ከሚናዉ መናገርን ጀመረ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ በምዕራፍ 4 ስለ ጢሞቴዎስ የጳዉሎስን ተስፋ ማድረግ ይዘረዝራል/ያስቀምጣል - ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የእግዚአብሄር ቃል ጥሩ አስተማሪ እንደሚሆን ጠርቶታል (ቁጥር 1-6), ቃሉን በመፈፀም /ተግባራዊ በማድረግ እግዚአብሄራዊ አገልጋይ እንደሚሆን (ቁጥር 7-12) እና በቃሉ ሂደት ዉስጥ የሚያድግ አገልጋይ (ቁጥር 13-16) በማለት እንደጠራው ያስቀምጣል ፡፡
ትምህርት
1-ጢሞቴዎስ (4፡ 1-6)፡ በቁጥር 1-2 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን መንፈስ ቅዱስ አንዳንዶች በሚመጣዉ ጊዜ እምነትን በመጣል የኃሰት መንፈስን እና የክፉን ትምህርት የሚከተሉ እንደሚሆኑ እንዳለ ነገረው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ጳዉሎስ ከእግዚአብሄር እዉነት መኮብለልን በተመለከተ በመንፈስ ቅዱስ የተነሳሳ ወይም መንፈስ ለእርሱ ሰጥቶት ስለ ነበረዉ ራዕይ በመናገር ስለተለያዩ ትንቢቶች እያመለከተ እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ የጳዉሎስ ንግግር በትክክል እነዚህ ሰዎች ከእምነት ፈቀቅ በማለት ይመላለሳሉ ማለት አይደለም ፤ ለእግዚአብሄር በመታዘዝ በእምነታቸዉ መመላለስ አቁመዋል ማለት ነው ፡፡ ጋኔኖች/ክፉዎች/መናፍስት የሰይጣን ተላላኪዎች የሆኑ የወደቁ መላዕክት ናቸው ፤ የሚያታልሉ መንፈሶች እና የትዕቢት መንፈስን ወይም የፍርሀት መንፈስ አይነትን በመጠቀም ከእግዚአብሄር አርቀዉ ሊስቡን የሚሰሩ ናቸው ፡፡ እንደ አማኝም እንኳን አሁንም በመናፍስት እንፈተናለን ( ማቴ 16፡ 21-23) ፤ ለኢየሱስ የቀረቡት ደቀ መዛሙርትም እንኳን (ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ) በማቴዎስ 16 እንዳለዉ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ ሂድ ከእኔ ራቅ አንተ ሰይጣን ! “ ብሎ እንደ ነገረው ከመናፍስት/ከክፉዉ ጋር ይዋጉ ነበር ፡፡ የሰይጣን ዉጠየት ሌላ ምሳሌ በሐዋ (5፡ 1-10) በአናንያ እና በሰጲራ ኑሮ ላይ የሚገኝ ነው ፤ ከሸጡት ጥቂት መሬት ተቀብለዉ ስለ ነበረው መንፈስ ቅዱስን በመዋሸት የእግዚአብሄርን መንፈስ ፈተኑ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በማሳወቅ ስለ ጠላቷ ታወራለች ፡፡
አንዳንድ የስህተት አስተምሮዎቹ በቁጥር 3 ላይ ተዘርዝረዋል - እግዚአብሄር የፈጠረውን ትዳርን/ጋብቻን መከልከል እና እግዚአብሄር ፈጥሮት እና ባርኮት ከነበረዉ አንዳንድ ምግቦች መጠበቅ/መቆጠብ መፈለግ ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር የፈጠረዉ ሁሉም ነገር መልካም እና በእግዚአብሄር ቃል እና በፀሎት (ቁጥር 5) የተቀደሰ እንደሆነና በማመስገን በማመስገን የተቀበለ ከሆነ የሚጣል/የሚተዉመሆን እንደሌለበት አብራርቷል (ቁጥር 4) ፡፡ በቁጥር 6 ጳዉሎስ እንደ በጎ የእግዚአብሄር አገልጋይ ጢሞቴዎስ በእግዚአብሄር ቃል ራሱን ማሳደግ እንደሚያስፈልገዉ ያሳያል/ይለያል ፡፡ የክርስቶስ መልካም/በጎ አገልጋይ የመሆን አንዱ መንገድ የኃሸት ትምህርቶችን መለየት ሲሆን ይህ ሲሆን አማኞች ላይ ተፅዕኖ አያደርጉም ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (4፡ 7-12)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የእግዚአብሄርን ቃል እንዲኖርበት እና እንዲሁም ደግሞ እንዲሰብከዉ ያበረታታዋል ፤ ጳዉሎስ አክብሮት የሌለዉን ነገር እና የማይረባ ተረተረት የሆነ ነገር እንዳይኖረዉ ነገር ግን በቅድስና ራሱን እንዲያስለምድ (እንዲኖር) ነገረው (ቁጥር 7) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ማስለመድ ወይም መለማመድ የሚለዉ ቃል “ ለግሪክ አትሌቶች ለአካላዊ ልምምድ ጥቅም ላይ የዋለ እንደ ነበር ፤ እዉነተኛ መንፈሳዊነት አንድ ሰዉ በጌታ ባለዉ ምልልስ በእግዚአብሄራዊ አኗኗር መለማመድን የሚጠይቅ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ሰዉነትን ማስለመድ የጊዜአዊ ዉጤት ሲኖረዉ በእግዚአብሄር አኗኗር ማስለመድ ደግሞ ለዘላለም ነው (ቁጥር 8) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥር 9 ፅፎላቸዉ የነበረውን “ ማንም መካድ እንደማይችል “ እንደ ጳዉሎስ ግሳፄ ይገልፀዋል ፡፡ ጳዉሎስ አማኞችን በሁሉን አዳኝ በእግዚአብሄር ተስፋ ስለ ነበራቸው ይሰሩ እና ይተጉ እንደ ነበር ነገራቸው (ቁጥር 10) ፡፡ “ ይልቁንም የሚያምኑት “ የሚለዉ ንግግር ለሁሉም የሆነዉን የእግዚአብሄርን ፀጋ እና እንደ አዳኛቸዉ እርሱን በሚያምኑት ላይ ካለዉ የተለዬ ፀጋ ጋር ያለዉን ንፅፅር ይስላል “ ፤ ስለሆነም ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በቁጥር 10 ላይ ዘርዝሯቸዉ የነበሩትን ነገሮች እንዲያስተምር አበረታው (ቁጥር 11) ፡፡ ጢሞቴዎስ ምንም ታናሽ ቢሆን እንደ እግዚአብሄር ምሳሌ የሚሆን ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እዚህ ጋር ጥቅም ላይ የዋለዉ ታናሽ የሚለዉ ቃል ብዙ ጊዜ እስከ 40 አመት ድረስ ያሉትን የሚያካትት ሲሆን ምናልባትም በዘያን ጊዜ ጢሞቴዎስም በ35 እና በ40 መካከል አመት ነበር ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለእርሱ ወጣጦች ማርከሻዉ ህይወቱ እንደ ነበር “ ይቀጥላል ፡፡ ጢሞቴዎስ በሚናገረዉ ቃል (ኤፌ 4፡ 15)፣ በባህሪዉ በኩል (ገላ 5፡ 16, ቲቶ 1፡ 16, 1ዮሐ 2፡ 6)፣ በእግዚአብሄር ፍቅር (1ዮሐ 4፡ 18-21)፣ በመንፈስ ቅዱስ ሁኔታ፣ በእምነት (በእግዚአብሄር ላይ ባለ እምነት)(1ጢሞ 1፡ 14, 2፡ 15, 6፡ 11) እና በንፁህነት ( በወሲባዊ ጉዳይ እና ሀሳብ) (ፊል 4፡ 8, ቆላ 3፡ 25) ምሳሌ እንዲሆን ተነግሮታል ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (4፡ 13-16)፡ በመጨረሻም ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በጌታ መዳጉን እንዲቀጥል ያዝዘዋል ፡፡ ጳዉሎስ ወደ ኤፌሶን መምጣት እንደሚፈልግ ተናገረ ነገር ግን መምጣት እስከሚችል ድረስ ጢሞቴዎስን መፅኀፍን በህዝብ ፊት እንዲያነብ (ሐዋ 13፡ 15)፣ ቃሉን እንዲታዘዙ አማኞችን እንዲያበረታታ እና የእግዚአብሄርን ቃል እንዲያስተምር (ቁጥር 13) አዘዘው ፡፡ በመቀጠለም ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በትንቢት እና በሽማግሌዎች እጅ መጫን ተቀብሎት የነበረዉን የፀጋ ስጦታን ችላ እንዳይል አዘዘው (ቁጥር 14) ፤ ለጢሞቴዎስ ይህ የአለፈ ልምምድ እንዲያደርገዉ ተጠርቶበት ለነበረዉ ስራ የታዘዘ የመሆኑ አካል እና ምናልባትም በልስጥራ ሳለ የሆነ ነበር (ሐዋ 16፡ 1) ፡፡ በተጨማሪ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን የተሰጠዉን ስጦታ እንዲለማመደዉ ያዝዘዋል ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እነዚህን ስጦታዎች የሚፈፅማቸዉ እንዲሆን ፈለገ (ቁጥር 15) ፡፡ ጳዉሎስ ይህን ክፍል ጢሞቴዎስን ለራሱ ህይወት እና እግዚአብሄር እንዲያደርግ ጠርቶት የነበረዉን በእርግጠኝነት እያደረገ እንደሆነ ለትምህርቱም ትኩረትን እንዲሰጥ በማዘዝ ዘጋ ፡፡ በዚህ ሁሉ ጢሞቴዎስ እየተጋ የነበረ እና ተሰጥቶት በነበረው አገልግሎቱ ይቀጥላል (ቁጥር 16) ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ በኤፌሶን የአማኞች መሪ ቢሆንም እንኳን በጌታ ማደግ እንዴት አስፈላጊ እንደ ነበር ተረድቷል፡፡ የጳዉሎስ ትዕዛዞች ዛሬም ለእኛ ተገቢዎች ናቸው ፤ ለእርሱ ስራ የተጠራን እና በተለዬ ስራዉን ለመስራት የተሰጠን ነን ፡፡ በእኛ ዉስጥ ባለዉ መንፈስ ቅዱስ ብቻ በመንፈሳዊ ነገር በማደግ ላይ ስናተኩር ብቻ የተሳካልን ነን፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), pp. 224–226.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
Nelson’s Commentary, p. 1602.
ጥያቄዎች
-
በ 1ጢሞ (4፡ 1) መሰረት ከእምነት አርቀዉ የሚጥሉ ጥቂት ምክንያቶች ምን ይሆናሉ ? “ የሰይጣን/የክፉዉ አንዳንድ አስተምሮዎች “ ምንድን ናቸው ? (ኤፌ 6፡ 12, ያዕ 3፡ 14-15, 2ዮሐ 7-11)
-
እግዚአብሄራዊ ከሆነ አኗኗር የሚመጡ ጥቅሞች ምንድን ናቸው ? (1ጢሞ 4፡ 8, 6፡ 6)
-
በ 1ጢሞ (4፡ 10) ጳዉሎስ ህያዉ እግዚአብሄር የሁሉም አዳኝ ነዉ በተለይም የአማኞች ባለ ጊዜ ምን ማለቱ እንደ ሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በምን ጥቂት መንገዶች ጢሞቴዎስ ለአማኞች ምሳሌ እንዲሆን የተነገረው (1ጢሞ 4፡ 12) ? በእነዚህ አምስት ነገሮች/ስፍራዎች ለሌሎች ምሳሌነታችሁ እንዴት ነው ?
-
1ጢሞ (4፡ 16) አንብቡ ፤ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እንዴት እንደሚያስተምር እና እንዴት እንደሚኖር እንዲጠነቀቅ ለምን አዘዘው ?
-
በ 1ጢሞቴዎስ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Timothy 4:11–12
“Command and teach these things. Let no one despise your youth; instead, you should be an example to the believers in speech, in conduct, in love, in faith, in purity.”
ጢሞቲዎስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚኖረው የአገልግሎት ህይወት እንዳንዶች ከእምነት ርቀው እንደሚሄዱ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በግልጽ መከረው ፡፡ እነዚህም በግብዝነት እንደሚስቱና እንደሚታለሉ ነገረው ፡፡ ምንም እንኳ ጢሞቲዎስ ወጣት የነበረ ቢሆንም ፣ ይህ የርሱን መሰጠትና በጌታ ላይ ያለውን ጥንካሬ ስለሚያሳይ ለአማኞች በቃል ፣ በኑሮ ፣ በፍቅር ፣ በእምነትና በንጽህና ምሳሌ ሆኖ በመኖር መትጋት ይጠበቅበት ነበር ፡፡
ልክ እንደ ጢሞቲዎስ ሁሉ ምንም ያህል ገና ልጅ ወይም ትልቅ ሰው ሁን በቃል ፣ በኑሮ ፣ በፍቅር ፣ በእምነት እና በንጽህና ለሌሎች ምሳሌ በመሆን እንድትኖር ጌታ ጥሪ ያቀርብልሃል ፡፡ ፍጹም መሆን አለብህ ? የለብህም ! እግዚአብሔር ፍጹም እንድትሆን አይጠይቅም ፡፡ ይልቁንም በየቀኑ መገኘቱንና ቃሉን ስትፈልግ የእግዚአብሔር ጸጋ ቃልህን ፣ ኑሮህን ፣ ፍቅርህን ፣ እምነትህንና ንጽህናህን ይለውጣል ፡፡ በትዕግስት ስትናገርና ራስህን ስትገዛ ፤ ያልተገደበ መልካምነትን ስታሳይ ፤ ከርኩሰት ይልቅ ንጽህናን ስትመርጥ የአንተ የተለወጠ ህይወትህ ለሌሎች ከእግዚአብሔር የሆነ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል ፡፡ አንተ በህይወት ስትመላለስ የእግዚአብሔርን ፍቅር ትወክላለህ ፡፡ አሁን ከኢየሱስ ጋር ጊዜ ውሰድ ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ ጊዜን ማሳለፍ ህይወትህን ይለውጠዋል እንድሁም ለሌሎች እንደ ምሳሌ ሁኖ ያገለግላል ይህም እነርሱን በጌታ ላይ ባላቸው እምነት ያበረታቸዋል ፡፡
“ ይህን እዘዝና አስተምር ። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው ። “
- 1ኛ ጢሞቲዎስ 4፡11-12
ተጨማሪ ጥቅስ
ዮሐንስ 13:35 — “ እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ ። “
ሮሜ 12:2 — “ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ። “
1ኛ ጢሞቲዎስ 4:1–2 — “ መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል ፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።