Requirements For The Overseer
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ጢሞቴዎስ እንዴት እረኛ እንደሚሆን ለጢሞቴዎስ በጳዉሎስ የመጀመሪያ መልዕክት ዉስጥ መስራታችንን እንቀጥላለን ፡፡ እረኝነት ጠንካራ ሰራተኝነት ነው ፡፡ የ 1ጢሞቴዎስ ቃላችን መካከለኛችን/አስታራቂአችን የሚል ነው ፡፡ መካከለኛችን ክርስቶስ በሞቱና በትንሳኤዉ በፀሎት ወደ አባቱ እንድንመጣ ይፈቅድልናል (1ጢሞ 2፡ 5-6) ፡፡ በምዕራፍ 3 ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ እንደ ተጣለበት መሪነት ማገልገል ለሚችሉ ትዕዛዛትን ይሰጠዋል ፤ ጢሞቴዎስ እንደ ቤተ ክርስቲያን እረኛ ከተተካ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ጥሪያዋን እንድትፈፅም የዳቆን እና የሽማግሎዎች መሪነት አስፈላጊ ነው ፡፡ በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ስንሰራ /ስንነጋገር በራሳችሁ ጉባኤ ላይ በመመለስ ገፍታችሁ እንድትመለከቱ እፈልጋለሁ ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችሁ ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ ያስቀመጠለትን መስፈርቶች እንደምታሟላ ራሳችሁን ጠይቁ ፡፡ ጳዉሎስ ሽማግሌዎች እና ዳቆኖች የተመሰረቱ/የቆሙ እንዲሆኑ ፈለገ ያከሆነ ስራዉ አይበላሽም (1ጢሞቴዎስ 3) ፤ ጳዉሎስ ጉባኤዉን ከሐሰተኛ አስተማሪዎች ለመከላከል እንዲረዳዉ ሌላ የሰዎች መዋቅር ቡድን እየመሰረተ ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ጢሞቴዎስ (3፡ 1-7)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ መጋቢ/እረኛ ወይም ጳጳስ ከሚለዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ በሆነዉ ተቆጣጣሪ በሚል ቃል ስልጣን ይሰይማል ( በቲቶ 1 እንደ ሽማግሎዎች ተጠቅሰዋል ) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ተቆጣጣሪን “ ጎባኤዉን የሚቆጣጠር ሰዉሰ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ በመቀጠልም ዳቆኖችን በመገለፅ (ቁጥር 8-13) “ የቤተ ክርስቲያንን የዉስጥ ጉዳይ ለመጠበቅ “ ኃላፊነት የተሰጣቸዉ ናቸው ፤ ይህ የሐዋ (6፡ 4) ቅርፅ/መልክ አይነት ነው ፡፡ ጳዉሎስ አንድ ጠቆጣጣሪን “ መልካም ስራን የሚፈልግ “ (ቁጥር 1) እንደ ነበር በማብራራት ለአንድ ተቆጣጣሪ/እረኛ/መጋቢ 15 መስፈርቶችን ሰጥቷል (ቁጥር 2-7) ፤ እነዚህ በጥቂቱ መንፈሳዊ ስርዓት መምሰል ይችላሉ እንዲሁም በእነርሱ ለመኖር በፍፁም አስቸጋሪ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሁሉ ከኮንስታብል የሚስማማቸዉን ትርጉም ተገልፆአላቸዋል ፡፡
- የማይነቀፍ/እንከን የሌለበት፡ ኮንስታብል ኢጲስቆጶስን/ተቆጣጣሪን/አገልጋይን “ በኑሮዉ ወይም በባህሪዉ ምንም የሚታይ እንከን የሌለበት ፤ ያም አሁን እና ቀድሞ ማንም ሰዉ እሱን ዋጋ ለማሳጣት ሊጠቀሙበት የሚችሉት እና በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ዘለፋን ሊያመጣ የሚችል ተገቢ ለሆነ ትችት ምክንያት መሆን የሌለበት ነው “ በማለት ይገልፃል ፡፡
- የአንዲት ሚስት ባል፡ ይህ መስፈርት በአራት መንገድ ተተርጉሟል፡- ማግባት ይጠበቅበታል፣ ማግባት የሚችለዉ አንድ ብቻ እንደሆነ፣ አንድ ሚስት ብቻ ያገባ መሆን አለበት ስለዚህም በአንድ ጊዜ አንድ ሰዉ የጋባ ብቻ እና “ ስርዓ ያለዉ ባል መሆን አለበት “ ፡፡ ጳዉሎስ ስለ ቀድሞ ሳይሆን በስዓቱ ስላለ ስለ ሰዎች ሁኔታ እየፃፈ እንደሆነ ይመስላል ፡፡
- የተረጋጋ፡ “ የማይሰክር፣ ንቁ የሆነ፣ ልከኛ እና በሚገበ የሚያስተዉል “ ፡፡
- ራሱን የሚገዛ/ጠንቃቃ፡ “ ራሱን የሚቆጣጠር ….ሰዎችን፣ አገልጋዮችን የሚያስተዉል፣ በኃይል/በክፋት የማይናገር፣ ተገቢ ፍርድን የሚሰጥ፣ የራሱ እና የሁኔታዎቹ ተቆጣጣሪ የሚሆን “ ፡፡
- የተከበረ፡ “ ጥሩ ፀባይ ያለዉ፣ የመልካም ባህሪይ ባለቤት የሆነ እና በኑሮዉ መልካም የሆነ ሰው “ ፡፡
- እንግዳ ተቀባይ የሆነ፡ “ ለቀድሞ ቤተ ክርስቲያን በሩን የከፈተ ፤ ይህ ለሚጓዙት አገልጋዮች እና ብዙ ፍላጎቶችን በጊዜአዊነት ለተቸገሩት ክርስቲያኖች ለመዉሰድ ትንሽ ምቾት/አቅርቦት ስለ ነበር በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን የተለዬ አስፈላጊ ጥራት ነበር “ ፡፡ ይህ “ እንግዶችን መዉደድ “ የሚል ትርጉም ከግሪክ የመጣ ቃል ነው ፡፡
- ማስተማር የሚችል፡ “ ንቁ፣ ጥራት ያለዉ እና የእግዚአብሄርን ቃል ለመግለፅ እና ለመከላከል ብቁ የሆነ “ ፡፡
- የማይሰክር፡ “ የማይረብሽ፣ ራሱን የማይገዛ/የሚያዝናና ፣ የመጠጥ ሱሰኛ ወይ ሰካራም መሆን የለበትም “ ፡፡
- አምባጓሮ የመይፈጥር/የማይጨቃጨቅ፡ “ ብስጭቱን ለመወጣት ወይም ግጭቶችን ለመፍታት በአካል ወይም በንግግር ሁከትን የማይፈጥር ሰዉ የሆነ “ ፡፡
- ደግ/ገር፡ “ ትዕግስተኛ እና ይቅር ባይ የሆነ “ ፡፡
- የማይከራከር፡ “ ተዋጊ ወይም የሚጣላ …. ጠበኛ ያልሆነ ሰው “ ፡፡
- ገንዘብን የማይወድ፡ ብቁ የማይሆነው ለገናዘብ ባለቤትነት ፍቅር ያለዉን አይደለም ፤ “ ይህ ማለት የተመራጩ አመለካከት ከገለልተኛ ጤነኝነት አንዱ ለመሆን ቁሳዊ ነገር ላይ ያደርጋል ማለት ነው “ ፡፡
- ቤቱን በሚገባ የሚያስተዳድር፡ “ ቤተ ሰቡን በሚገባ የሚቆጣጠር “ (ምሳ 24፡ 3-4, 27፡ 23, ኤፌ 6፡ 4, ቲቶ 1፡ 6) ፡፡
- አዲስ ክርስቲያን ያልሆነ፡ “ የበሰለ/የጠነከረ ሳይሆን….እንደ ሽማግሌዎች/እንደሚበልጡት መስራት እንደሚችል በማስረደት …የታወረ እና በትዕቢት የተነፋ ይሆናል “ ፡፡
- ከቤተ ክርስቲያን ዉጪ መልካም ስም ያለዉ፡ በአማኞች ፊት እና ከአማኞችም ዉጪ ነቀፋ የሌለበት መሆን አለበት ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (3፡ 8-13)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ለዳቆንነት የተዘረዘሩ ሌሎች 12 መስፈርቶች አሉ ፡፡ ዳቆኖች አገልጋጶች/እረኞች በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ነገሮችን እንደቆጣጠሩ የሚፈቅድን ስራ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የሚፈፅሙ ሰራተኞች ናቸው ፡፡
መደምደሚያ
በዚህ ምዕራፍ ላይ የቀሩትን ለመመልከት ጊዜ የለንም ነገር ግን በፀሎት በዚህ ዉስጥ በማጥናት በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስለ እያንዳንዱ ስራ አስፈላጊነት እንዲያሳያችሁ እንድትጠይቁት አበረታታችኋለሁ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1600.
Nelson’s Commentary, p. 1600.
David A. Mappes, "Moral Virtues Associated with Eldership," Bibliotheca Sacra 160:638 (April-June 2003):pp. 202-218 quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes, pp. 64-75; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1timothy.pdf.
Guy H. King, A Leader Led (London: Marshall, Morgan & Scott, 1962), p. 59; quoted in Constable, p. 66.
Philip H. Towner, 1–2 Timothy & Titus, The IVP New Testament Commentary Series (Downers Grove, Ill, and Leicester, England: InterVarsity Press, 1994), p. 87; quoted in Constable, p. 68.
ጥያቄዎች
-
አንድ ሰዉ አገልጋይ/እረኛ መሆን ቢፈልግ ማሟላት ያለበት 15 መስፈርቶች/መመዘኛዎች ምንድን ናቸው ? ሁሉም ክርስቲያኖች እነዚህን ባህሪያቶች ማሳየት እንዳለባቸው ትስማማላችሁ ?
-
እንደ ዳቆን ለሚያገለግል ሰዉ 12 መስፈርቶቹ/መመዘኛዎቹ ምንድን ናቸው ? በዳቆን እና በእረኛ/በታስተር መካከል ያለዉ ልዩነት እና ተመሳሳይነት ምንድን ናቸው ?
-
ለአንድ ሰዉ ቤቱን በሚገባ ማስተዳደር መቻል በቤተ ክርስቲያን መሪ ለመሆን ለምን አስፈላጊ ነው ?
-
በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በሚገባ ለሚያገለግሉ ዳቆናት የተሰጣቸዉ መባረታታት ምንድን ነው ?
-
የአምላክነት ሚስጥር መሰረታዊ እዉነታዎች ምንድን ናቸው ? በሌሎች መፅኀፍ እነዚህን ጥያቄዎች መልሱ (ማቴ 3፡ 16, 28፡ 2, ሉቃ 24፡ 51, ዮሐ 1፡ 14, ሐዋ 10፡ 34, ሮሜ 10፡ 18, 16፡ 26, 1ጴጥ 1፡ 20, 1ዮሐ 1፡ 2, 3፡ 5)
-
በ1-ጢሞቴዎስ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Timothy 3:14–15
“I write these things to you, hoping to come to you soon. But if I should be delayed, I have written so that you will know how people ought to act in God’s household, which is the church of the living God, the pillar and foundation of the truth.”
እግዚአብሔር የስርዓትና የሰላም አምላክ ነው ፡፡ ስለዚህም ጳውሎስ ለቤተ ክርስቲያን መሪነት ማለትም ሽማግሌ እና ድያቆን ለመሆን መከተል የሚያስፈልገውን መንገድና ከአማኞች የሚጠበቀውን ለቤተ ክርስቲያን አዘዘ ፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያን መሪ ለመሆን ቀድማችሁ እንዴት ልትኖሩና ልትመላለሱ እንደሚገባ የሚገልጽ መመሪያ ነው ፡፡ የራሳቸውን ቤት ማስተዳደር የማይችሉ የእግዚአብሔርን ቤት ያስተዳድራሉ ተብሎ እንደማይጠበቅ ጳውሎስ በግልጽ ተናግሯል ፡፡ የጳውሎስ አሳብ የእግዚአብሔርን አሳብ ነው የሚያንጸባርቀው እርሱም ፡- በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት ፣ በህያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ፣ በእውነት ዓምድና መሠረት ሰላምን ለማስጠበቅ ነው ፡፡
ህይወታችሁ ጳውሎስ ለቤተ ክርስቲያን መሪነት ያስፈልጋሉ ብሎ የዘረዘራቸውን ባህሪያት ከያዘ ይህ ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ውስጣዊ ግንኙነት የሚያሳይ ወደ ውጪ የሚታይ ምልክት ነው ፡፡ ህይወታችሁ ለእርሱ ያላችሁን ፍቅርና ክርስቶስን ለመከተል ያላችሁን ቁርተኝነት ያሳያል ፡፡ ይህ ለቤተ ክርስቲያን መሪነት አስፈላጊ ነው ምክንቱም የሰላምና የስርዓት አምላክ የሆነው እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን መሪ በጌታ እና የራሱን ቤት በመምራት ብርቱ ሊሆን እንደሚገባ ስለሚያዝ ነው ፡፡ ባላችሁ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ስትከተሉ እርሱ የቅድስና ህይወትን ለመምራት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል ፡፡ የእናንተ ቤት በእውነቱ የእግዚአብሔርን ሰላምና ስርዓት ያሳያልን ፡፡ ዛሬ ራሳችሁን እንዲህ በማለት ጠይቁ ፡- ህይወቴ ፣ ባህሪዬ ደግሞም ቤቴ ለጌታ ያለኝን ፍቅር ያሳያልን ?
“ ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ ። ብዘገይ ግን፥ በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ ፤ ቤቱም የእውነት ዓምድና መሠረት፥ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነው ። “
- 1ኛ ጢሞቲዎስ 3፡14-15
ተጨማሪ ጥቅስ
1ኛ ቆሮንቶስ 14:33 — “ እግዚአብሔርስ የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና፤ በቅዱሳንም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲህ ነው ። “
1ኛ ጢሞቲዎስ 3:5 — “ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል ? “
2ኛ ጴጥሮስ 1:3 — “ የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።