Instructions For Praying For Men and Women
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምዕራፍ 2 ጳዉሎስ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ስላለ ስነ ስርዓት ጉዳይ ይዳስሳል ( 1ቆሮ 14፡ 40) ፡፡ ጳዉሎስ በኤፌሶን በቤተ ክርስቲያን እረኛ በነበረዉ እንዴት እንደ ሚያደርግ በማዘዝ ወጣት በሆነዉ ተማሪዉ ጢሞቴዎስ ላይ እያፈሰሰ ነበር ፡፡
ትምህርት
1-ጢሞቴዎስ (2፡ 1-4)፡ በቁጥር 1 ጳዉሎስ የፀሎትን ቀዳሚነት መሰረተ፡ “ ከሁሉ አስቀድሜ የማሳስባችሁ….” በመቀጠልም አራት አይነት ፀሎቶችን አስቀምጧል - ለራሳቸዉ ሳይሆን ለሁሉም የልመና (የተማፅዕኖ)፣ ፀሎቶች፣ የምልጃ እና የምሳጋ ፀሎቶች ናቸው ፡፡ ዋይርስቤ በእነዚህ በአራቱ መካከል ልዩነትታቸዉን ያሳያል፡
- ልመናን “ ለሚያስፈልግ ነገር እንደ ሚቀርብ ጥያቄ “ ፡፡
- ፀሎቶች “ የአምልኮ ድርጊት እንጂ የፍላጎታችን እና የሚያስፈልጉን ነገሮች መግለጫ አይደለም …. ወደ እግዚአብሄር ስንፀልይ በልብ እንዳለ አምልኮ “
- ምልጃ ስለሌሎች በመሳብ ወደ እግዚአብሄር መቅረብ ነው ፤ “ ይህ ከእግዚአብሄር ጋር ባለ ህብረት እንድንደሰት እና ስንፀልይ በእርሱም ሙሉ እምነት እንደሚኖረን ይመክራል “ ፡፡
- የማመስገን/ምስጋና የመስጠት “ ለፀሎት መልስ ምስጋና መስጠት ብቻ ማለት ሳይሆን እግዚአብሄር አምላክ ስለሆነና በፀጋዉ ስላደረገልንም ነገር የሚሰጥ ነው “ ፡፡
ጳዉሎስ በፀሎት የተካተቱ የሆኑትን “ ሁሉም “ (ቁጥር 1) በማለት ይገልፃል - ነገስታትን እና ባለስልጣናትን ይጠቅሳል (ቁጥር 2) ፤ ያ ማለትለፕሬዜዳንት ትራምፕ እና በመንግስት ዉስጥ እኛን ለሚወክሉት ባለስልጣናት እንፀልያለን ማለት ነው ፡፡ ፀሎታችን ወደ አንድ ጎን ያደላ ወይም ለምንስማማቸዉ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም መሆን አለበት ፡፡ ባለስልጣናት በጳዉሎስ ላይ ስላደረጉት አስቡ - እስራትን፣ ግድያን - ይሁን እንጂ እርሱ ስለ እነርሱ ፀለዬ ! ለምንድን ነዉ የምንፀልየው ? ምክንያቱም ይህ እግዚአብሄራዊ የሆነ የፀጥታ ኑሮን ስለሚፈቅድልን ፡፡ ስለ ሰዎች መጥፎ ነገርን ማዉራት እንድታቆሙ ይልቁንም ስለ እነርሱ እንድትፀልዩላቸዉ እሞግታችኋለሁ ፤ በቤተ ክርስቲያናችሁ ዉስጥ ለዳቆኖች እና ለአገልጋዮች ከእነርሱ ጋር ባትስማሙም እንኳን እንድትፀልዩላቸዉ እሞግታችኋለሁ ፡፡ ጳዉሎስ እንዲህ አይነቱን ፀሎት እግዚአብሄርን ደስ እንደሚያሰኝ እና እንደ መልካም ይገልፃል (ቁጥር 3) ፤ የእግዚአብሄር ፍቃድ ለሁሉም የሆነዉን (ዮሐ 3፡ 16) እና በመስቀል ላይ ስለሆነዉ የክርስቶስ ሞት እዉነት መረዳት (1ዮሐ 2፡ 2, 4፡ 14) እንዲፈፀም እንፀልያለን ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (2፡ 5-7)፡ ጳዉሎስ ከአብ ጋር ለምን ማዉራት እንደምንችል ይገልፃል - ምክንያቱም ክርስቶስ መካከለኛችን ስለሆነ ነው ፡፡ ስለ እኛ በእኛና በእግዚአብሄር መካከል አለፈ (ቁጥር 5) ፤ መካከለኛችን በእግዚአብሄር ትክክለኛ ጊዜ ላይ ምስክርነት የነበረዉን እንደ ቤዛነት ራሱን ሰጠን ፡፡ በብሉይ ኪዳን ኢዮብ ስለ እርሱ በእግዚአብሄር ሊማልድለት/ጣልቃ ሊገባለት የሚችል ማንም እንዳልነበር ፅፏል (ኢዮ 9፡ 33) ፤ በሆነ መጠን ያክል ሙሴ ስለ እስራኤላዊያን ያን ሚና ወስዷል (ገላ 3፡ 19) ፡፡ በቁጥር 6 ኢየሱስ ያን ለእኛ ማድረግ ችሏል ምክንያቱም በህይወቱ ያን ዋጋ ስለከፈለ - “ ለሁላችንም ቤዛ ሆነ “ (ማቴ 20፡ 28) ፡፡ ጳዉሎስ ስለ እነዚህ አላማ ለአሕዛብ እንደ ሰባኪ፣ እንደ ሐዋሪያ እና አስተማሪን የተመረጠ/የተሸመ እንደ ነበር ገልፆአል (ቁጥር 7) ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (2፡ 8-15)፡ በ 1ቆሮ (11፡ 4-5) ጳዉሎስ ሴቶች እና ወንዶች ሁለቱም መፀለይ እንዳለባቸዉ ተናገረ፡፡ ሴቶች እና ወንዶች ሁለቱም በቀድሞ ቤተ ክርስቲያን ፀልየዋል ፤ ቁጥር 10 ከ 1ቆሮንቶስ 11 ፅሁፍ ጋር አይጣረስም ፡፡ በይበልጥም ጳዉሎስ በቤተ ክርስቲያን ለጸሎት ስርዓትን እየመሰረተ ነበር ፤ በፀለዩት በሁሉም ፀሎት ወንዶች ያለ ቁጣና ያለ ክፉ ሀሳብ “ የተቀደሱ እጆቻቸዉን “ ያነሱ ነበር (ቁጥር 8) ፡፡ በመፅሀፍ ዉስጥ ሰዎች በተለያዩ ስፍራዎች/ስልጣኖች ታይተዋል - እጆቻቸዉን በመዘርጋት (1ነገ 8፡ 22)፣ በመነሳት (ሉቃ 18፡ 11)፣ በመንበርከክ (ዳን 6፡ 10), በመቀመጥ (2ሳሙ 7፡ 18)፣ ራሳቸዉን ዝቅ በማድረግ (ዘፍ 24፡ 26)፣ በመሬት ላይ በመዉደቅ (ዘፍ 17፡ 3) እና አይኖቻቸዉን በማንሳት (ዮሐ 17፡ 1) ፡፡ እነዚህ ቁመናዎች ሰዉ/ሰዎቹ ምን እንደተሰማዉ/እንደተሰማቸዉ የሚገልፁ ናቸው ፡፡ በጣም አስፈላጊዉ ነገር የአካል አቋቋም/ኁኔታ ሳይሆን የልብ አቋቋም ሁኔታ ነው ፡፡
ጳዉሎስ ለፀሎት ሰዎስት መስፈርቶችን ያስቀምጣል፡ “ የተቀደሱ እጆች “ ማለትም በቅድስና ህይወት መኖርን፣ “ ያለ ቁጣ “ ማለትም “ አንዱ ለሌላው በመልካም ንግግር መሆን “ ማለት ሲሆን በተጨማሪም “ ያለ ክርክር “ ማለትም “ ያለ ግጭት “ ወይም “ ከሌሎች ጋር በሆነ ቀላል አለመግባባት “ ማለት ነው ፡፡
በቁጥር 9-10 ለሴቶች የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ይገልፃል - የፀጉር ስታይላቸዉን ሳያጋንኑ፣ ጌጥ ሳያበዙ ወይም ወድ ልብሶችን ሳይለብሱ በመጠነኝነት እና በእርጋታ እንዲለብሱ ነው ፡፡ በዚያ ፋንታ “ እግዚአብሄራዊ የሆነን እዉነተኛ ዋጋን እና ክርስቲያናዊ አገልግሎትን “ የሚያሳይ የመልካም ስራ የሆነን ይለብሳሉ ፤ በተጨማሪም ሴቶች በሙሉ መታዘዝ በፀትታ/በዝምታ ይማራሉ (ቁጥር 11) ፡፡ ዋይርስቤ በፀጥታ የሚለዉን ቃል በደንብ የማይገልፅ የግሪክ ቃል ትርጓሜ እንደሆነ ይገልፃል፡ በ 1ጢሞ ( 2፡ 2) ተመሳሳይ የግሪክ ቃል “ በሰላም “ የሚል ተተርጉሟል ፡፡ የጳዉሎስ ትዕዛዝ “ አንዳንድ ሴቶች በክርስቶስ ያገኙትን አዲስ ነፃነት ጣልቃ በመግባት አገልግሎትን መረበሽ ስለፈጠሩ “ ነበር ፡፡ በይበልጥ “ መታዘዝ “ በደንብ በሚገባ “ በቤት እና በቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ/ስርዓት በማስተዋል በደስታ መፈፀም/ማድረግ “ በማለት መረዳት ይቻላል ፡፡ መታዘዝ በስልጣን እና በቅደም ተከተል/በስርዓት ስላለ ደረጃ እንጂ ስለ ዋጋ ወይም ጥቅም አይደለም ፡፡ ልጆች ለቤተሰቦቻቸዉ የሚታዘዙበት፣ ተቀጣሪዎች ለአለቆቻቸዉ የሚታዘዙበት እና ዜጎች ለመንግስት የሚታዘዙበት ወቅቶች አሉ ኢየሱስ ለአባቱ እንደታዘዘው ፤ ይህ እግዚአብሄር ሁሉንም በስፍራዉ ሲያስቀምጥ ከሌሎች ሰዎች እናንሳለን ማለት አይደለም በክርስቶስ አካል ዉስጥ ቅደም ተከተልን/ስርዓትን ለመፍቀድ ነዉ እንጂ ፡፡
በቁጥር 12 ላይ ከመመልከታችን በፊት በሪቫይቭ ት/ቤት ዉስጥ ጥቂት አወዛጋቢ ፅሁፎች እንደ ነበሩ ላስታዉሳችሁ እፈልጋለሁ ፡፡ ካልተስማማችሁ ሪቫይቭ ት/ቤት አትተዉም ፤ መፅሀፍ ቅዱስ ከሚለዉ ከልምዴ ለማመጋገር እየሞከርኩኝ ነው ፤ ካልተስማማችሁ ችግር የለዉም !
በቁጥር 12 ጳዉሎስ ሴት ወንድን እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ እንድትሰለጥን እንደማይፈቅድ ተናገረ ፤ ጳዉሎስ ትልቅ ሴት እንዴት ትንሽ ሴትን እንዴት ማስተማር እንዳለባት (ቲቶ 2፡ 3-4) እና እንዴት ጢሞቴዎስ በቤቱ በሴት ተምሮ እንደ ነበር ተናገረ (2ጢሞ 1፡ 5, 3፡ 15) ፡፡ ሴቶች በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የማይታመን ታሪክ ነበራቸው ፤ መስቀሉ ጋር ስለ ነበሩት ሴቶች እና በባዶዉ መቃብር ጋር ስለ ነበሩት አስቡ ፤ ስለ ሊድያ፣ ስለ ጵርስቅላ እና ዶርቃ አስቡ ፡፡ በሮሜ 16 ጳዉሎስ ቢያንስ ስድስት ሴቶችን በስማቸዉ ሰላምታን ሲሰጥ ፌበን መለኮታዉ መልዕክቱን አድርሳለች ፤ ሴቶች በግልፅ ቤተ ክርስቲያንን በማነጋገር / በመቅረብ ሚና አላቸው ፡፡
በቁጥር 13-14 ጳዉሎስ ይህን ትዕዛዝ ለምን እንደሰጠ ምክንያቱን ሰጥቷል ፤ የመጀመሪያው አዳም ከሂዋን በፊት ተፈጠረ ሂዋን ተሳሳተች እንጂ አዳም የተታለለ ስላልነበር ፤ እግዚአብሄር የሰጠዉን ቅደም ተከተል/ስርዓት መጣስ ስለ ነበር መታለል ነበር ፤ ይሁን እንጂ ሴት በመዉለድ እና በመልካም ፍርድ በእምነት፣ በፍቅር እና በቅድስና ትድናለች (ቁጥር 15) ፡፡ አዳኙ “ ከሴት የተወለደ ነበር “ (ማቴ 1፡ 18, ሉቃ 1፡ 34-35, ገላ 4፡ 4) ፡፡
መደምደሚያ
ቀስ በማለት እዚህ ጋር ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ ምን እያለዉን እንደሆነ አሰላስሉ ፡፡ በፀሎት፣ በልመና፣ በምልጃ እና በምስጋና አረፊፍ/ደህና ከሆናችሁ ቀጣዩ ፁሁፍ ምንድን ይስልላችኋል ፡፡ በማንኛዉም መንገድ ሴቶች ሊኖራቸዉ የሚችለዉን ሚና አላጠፋም ፤ የሚስቴ ጥራቶች አሉ፣ በጌታ በማይታመን መልኩ ጠንካራ መሪ ነች ፤ እግዚአብሄር ማንኛዉንም ሴት መጠቀም እንደሚችለው በሚያስደንቅ ሁኔታ እየተጠቀመባት ነው ፡፡ ይህ እንደ መፅሀፍ እና በስርዓቱ አድርጉት ፤ ይህ ለመመላለስ ከባድ/ጠንካራ መስመር ነው ነገር ግን ፀሎቴ ይህ ፅሁፍ ምን እያለ እንደሆነ እንዲያሳያችሁ መንፈስ ቅዱስን እንድትጠይቁት ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 215.
Wiersbe, p. 216.
Wiersbe, p. 216-217.
Wiersbe, p. 218.
Wiersbe, p. 218.
Wiersbe, p. 217
ጥያቄዎች
-
እንደ 1ጢሞቴዎስ 2 ገለፃ የፀሎት ባለቤቶች እነማን ናቸው ? ይህ በስልጣን ላይ ላሉ ለምንስማማባቸዉ ብቻ መፀለይ ማለት ነው ? ዛሬ ጊዜ ዉሰዱና በስልጣን ላይ ላሉት እና መንፈስ ቅዱስ ወደ ሀሳባችሁ ላመጣቸዉ ፀልዩ
-
መልካም የሚለው ቃልበጳዉሎስ የእረኝነት መልዕክት ዉስጥ ቁልፍ ቃል ነው ፤ ጳዉሎስ 1ጢሞ (2፡ 3) በመጀመር መልካም ያላቸዉ አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው ? (1ጢሞ 1፡ 8, 19፣ 3፡ 7, 4፡ 4, 2ጢሞ 1፡ 14, ቲቶ 2፡ 7)
-
ስላልነበረዉ ኢዮብ ቅሬታ ለእግዚአብሄር ያቀረበበት (ኢዮ 9፡ 33) ዛሬ እንደአማኝ ያለን መልካም ዜና ምንድን ነው ? መካከለኛችን ስለ እኛ ምን አደረገ ? (ማቴ 20፡ 28)
-
እግዚአብሄር በወንድ እና በሴት መካከል በቤተ ክርስቲያን ሚና ላይ ለምን ልዩነት ያደረገ ይመስላል ? (1ቆሮ 14፡ 40)
-
ጳዉሎስ ሴቶች እንዲያደርጉት ምንን አልፈቀደም ? ጥያቄዎን ለማሳመን/ለመመለስ የተጠቀማቸዉ ሁለት ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
-
በ 1ጢሞቴዎስ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Timothy 2:1
“First of all, then, I urge that petitions, prayers, intercessions, and thanksgivings be made for everyone.”
ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ቤተክርስቲያን ክርስቶስን ስትከተል የሚያጋጥሟትን መንፈሳዊ ፈተናዎች እንዴት መዋጋት እንደሚጋባው አዘዘው ፡፡ ለጢሞቲዎስም እነዚህን ጸሎቶች እንድጸልይ ነገረው ፡- ልመና ፣ ጸሎት ፣ ምልጃና ምስጋና ፡፡ ጳውሎስ ሁሉም አይነት ጸሎቶች እንድጸለዩ ተናገረ ፡፡ ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ለሁሉም ማለትም ፡- ለባለስልጣናት ፣ በውጪ ላሉት ፣ ለቤተሰብ ፣ ለጓደኞች ፣ ወዳጅ ላልሆኑ ደግሞም ሌሎችን ለሚያሳድዱ ጭምር ጸሎትን እንድታደርግ አስገነዘበ ፡፡ ለሁሉም የመጸለይ ኃላፊነት አለባችሁ፡፡ ለምን ? ምክንያቱም ይህ መልካም ስለሆነና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ስለሆነ ፡፡
ዛሬ ለሌሎች ለመጸለይ ጊዜ ውሰዱ ፡፡ አስር ደቂቃ ያዙና በዚያች ሰዓት ለመጸለይ ቁርጠኛ ሁኑ ፡፡ ጌታ ጸሎታችሁ ያሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ስም ወደ ልባችሁ እንድያመጣ ጠይቁ ከዚያም ስማቸውን ጻፉ ፡፡ ከዚያም ሁሉንም አይነት ጸሎቶች ጸልዩ ፡፡
- ልመና ፡- እንደ እግዚአብሔር ቃል በሆነ ድፍረት መጠየቅ መለመን ፡፡
- ጸሎት ፡- ከአምላካችሁ ከሰማዩ አባታችሁ ጋር መነጋገር ፡፡
- ምልጃ ፡- በእግዚአብሔር ፊት የሌሎችን ችግር ይዞ መቅረብ ፡፡
- ምስጋና ፡- እግዚአብሔርን ስለ እያንዳንዱ ሰው እንድሁም የእርሱን ኃይለኛ ችሎታዎች በማንሳት ደግሞም ስለተመለሱ ጸሎቶች ማመስገን ፡፡
በመንፈሳዊ ውጊያ ውስጥ ስለምትኖሩ ስለሌሎች ጸልዩ ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉም ይድኑ ዘንድና እውነቱን ያውቁ ዘንድ ስለሚሻ ጸሎት እርሱን ደስ ያሰኘዋል ፡፡
“ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ ። “
1ኛ ጢሞቲዎስ 2፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎሰ 5:44 — “ እኔ ግን እላችኋለሁ ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ ፡፡ “
ኤፌሶን 6:18 — “ በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ ፡፡ “
1ኛ ጢሞቲዎስ 2:3–4 — “ ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።