Advice To Timothy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Our Mediator 1 Timothy 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ “ ለተወደደ ልጁ “ የጳዉሎስን የመጀመሪያዉን መልዕክት ጥናታችንን እንጀምራለን ፡፡ ማክአርቱር የጢሞቲዎስ የስሙ ትርጉም “ እግዚአብሄርን የሚያከብር “ ማለት እንደ ሆነ መዝግቧል ፡፡ ጢሞቲዎስ የክርስቶስ ተከታዮች የሆኑት የተሰጡ አይሁዶች በነበሩት በአያቱ በሎይድ እና በእናቱ በኤዉንቄ በሁለቱም በእምነት ያደገ ነበር (2ጢሞ 1፡ 5) ፡፡ አባቱ ግሪካዊ እና ምናልባትም የማያምን ነበር ፤ ጢሞቴዎስ በአሁኑ ቱርክ በቀድሞዉ በገላትያ የሮም ከተማ ከነበረች ከልስጥራ ነበር (ሐዋ 16፡ 1) ፡፡ ጳዉሎስ በመጀመሪያ ጉዞዉ በልስጥራ በኩል ሲያልፍ በዚያ ጢሞቴዎስን በማግኘት ጢሞቴዎስን ወደ ክርስቶስ በመምራት “ የተወደደ ልጁ “ አደረገው (ሐዋ 14፡ 6-23) ፤ በሁለተኛው ጉዞዉ ላይ ጳዉሎስ እንደ ገና ልስጥራን በመጎብኘት በቀረዉ ጉዞዉ ላይ ጢሞቴዎስን መዉሰድን መረጠ (ሐዋ 16፡ 1-3) ፡፡ ጢሞቴዎስ ገና ልጅ ምናልባት እድሜዎ አስራዎቹ ዉስጥ ወይም ሀያዎቹ መጀመሪያዎች ዉስጥ ነበር (1ጢሞ 4፡ 12) ፤ በተጨማሪም ሐዋ (16፡ 2) ጢሞቴዎስ እግዚአብሄርን የመፍራት ዝና ነበረው ፡፡ ማክአርቱር የጳዉሎስን እና የጢሞቴዎስን ግንኙነት “ ጢሞቴዎስ የጳዉሎስ ደቀ መዝሙር፣ ጓደኛ እና በቀረዉ በጳዉሎስ ህይወት በቤሪያ፣ በአቴና እና በቆሮንቶስ ከእርሱ ጋር በማገልገል የስራ አጋሩ ነበር በተጨማሪም ወደ ኢየሩሳሌም በነበረዉ ጉዞ ላይ የጉዞ ጓደኛዉ ነበር “ ብሎ በመናገር ያስቀምጣል ፡፡ በሮም በጳዉሎስ በመጀመሪያዉ እስራት ጊዜ ጢሞቴዎስ ከእርሱ ጋር ስለ ነበር ጳዉሎስ እስኪለቀቅም ድረስ በዚያ ከእርሱ ጋር ነበር ፤ ከዚያ ጢሞቴዎስ ወደ ፊልጵስዮስ ሄደ ፡፡ በተጨማሪም ጢሞቴዎስ ጳዉሎስ ጀምሯቸዉ የነበሩትን ቤተ ክርስቲያናት በመጎብኘት ጢሞቴዎስ እንደ ጳዉሎስ ተወካይ አገልግሏል ፡፡ በጳዉሎስ የመጀመሪያዉ መልዕክት ጊዜ ጢሞቴዎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን እንደ ፓስተር እያገለገለ ነበር (1ጢሞ 1፡ 3) ፡፡
የጳዉሎስ ግንኙነት ከጢሞቴዎስ ጋር በተከታይነት እንደ ተቆጣጣሪ ነበር ፡፡ ሁሉም አማኝ እግዚአብሄር በጠራቸዉ ተግባር ላይ እንዲሳተፉ በማዘጋጀት ለመርዳት ተቆጣጣሪ/አጋዥ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ ጳዉሎስ በጢሞቴዎስ ላይ ትምህርትን ብቻ አላፈሰሰም የአገልግሎትን ስራም ጢሞቴዎስን ወደ ራሱ ስፍራ በመላክም እንኳን አመነዉም እንጂ ፡፡ ደቀ መዝሙርነት እንዴት መስራት እንዳለበት የሚያስደንቅ ምሳሌ እና ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ ያደረገዉ ያሳያል ፡፡ በ 1ጢሞቴዎስ ኢየሱስ የቀረበበት ቃላችን/ዓ.ነገራችን አስታራቂያችን/መካከለኛችን የሚል ነው (1ጢሞ 2፡ 5-6) ፡፡ የደቀ መዝሙርነት ቋሚ ማስታወሻ/አስታዋሽ ነው ፡፡ ዕብ (13፡ 23) የሆነ ስፍራ/ጊዜ ላይ ጢሞቴዎስ በእስር ቤት እንደ ነበርና እንደተለቀቀ ይናገራል ፡፡
ጳዉሎስ በቁጥር 1 የመፅሀፊ ፀሀፊነትን ተናገረ የቀድሞዋም ቤተ ክርስቲያን ተስማማች ፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ የዘመኑ ምሁራን ጳዉሎስ በእዉነት 1 እና 2 ጢሞቴዎስን እና ቲቶን ስለመፃፉ ይጠይቃሉ ፡፡ እነዚህ ምሁራን አምስት መከራከሪያ ሀሳቦችን ያቀርባሉ፡
- በእረኝነት መልዕክት የተሰጠዉ ታሪካዊ ማስረጃ በጳዉሎስ ህይወት ላይ በሐዋሪያት ስራ አቀራረብ አይስማማም ፤ ይሁን እንጂ የእስራት መልዕክት በመባል በሐዋሪያት ስራ የተጠቀሰ ምንም የለም ፡፡ ለአንዳንድ ምሁራን ይህ ታሪካዊ ድጋፍን ያጣ/ያልያዘ ነው ፡፡ ሐዋሪያት ስራ ከጳዉሎስ መጨረሻ የእስራት ቀን ወይም የሞት ፍርድ በፊት ያበቃል፣ ከእርሱ መጨረሻ መልዕክቶች ማንኛዉም አልጠቀሰውም ፡፡
- ጳዉሎስ በራሳቸዉ ሀሳብ የሚሄዱ/የማይሰሙ በማለት ጠቅሷቸዉ የነበሩት ሀሰተኛ አስተማሪዎች በሁለተኛዉ ክፍለ ዘመን አሉ ፡፡
በእስራት መልዕክቶች ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችበት መንገድ የሁለተኛዉ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ያንፀባርቃል ፤ ይሁን እንጂ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ጳዉሎስ በሐዋሪያት ስራ 14 እና በፊልጵስዮስ ከመሰረታቸዉ ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡
የጳዉሎስ የሌሎች መልዕክት ጭብጥ/ፍሬ ነገር በእስራት መልዕክቶች ዉስጥ የተጠቀሱ አይደሉም ፡፡ አሁንም ጳዉሎስ ስለ እግዚአብሄር ቃል፣ ስለ ድነት፣ ስለ ምርጫ አስፈላጊነት እና ቤተ ክርስቲያን ምን መሆን እንዳለበት አወራ ፡፡ የጳዉሎስ ድምፅ በ 1 እና 2 ጢሞቴዎስ እና ቲቶ መሰማት የሚችል ነው ፡፡
በእስራት ልዕክቶች ላይ የተጠቀማቸዉ የግሪክ ቃላቶች በሌላ በጳዉሎስ ፅሁፎች ወይም በሌላ በአዲስ ኪዳን መፅሀፍ ዉስጥ አይገኝም ፡፡
ይህን አጋራችኋለሁ ምክንያቱም ሁልጊዜ ተገቢ/ትክክለኛ የሆነ አመለካከት እና በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የማንኛዉም ፅሁፍ የተለያዬ አተረጓጎሞች እንዳሉ ማወቅ አስፈላጊ ስለሆነ ፡፡ መፅሀፍን የማጥናት አካል ሰዎች በተለያዬ መልኩ እንደሚያነቡት ማወቅ እና የተለያዩ አመለካከቶች ማስተዋል ጤነኝነት እንደሚሆን ማወቅ ነው ፡፡ ልክ እናንተ እንደምታዉቁት ጳዉሎስ እነዚህን ሰዎስት መፅሀፎች ከክርስቶስ ሞት 62-64 መካከል ፅፏል ከሚለዉ ከማክአርቱር ጋር እስማማለሁ - 1ጢሞቴዎስ እና ቲቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእስራት ከተለቀቀ በኋላ ሲሆን 2ጢሞቴዎስ ደግሞ ከመገደሉ ሩቅ ባልነበረዉ በሁለተኛ እስራቱ ጊዜ የተፃፈ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ከእስራት ለመጀመሪያ ጊዜ በተለቀቀ ጊዜ ጀምሯቸዉ የነበሩትን ብዙ ቤተ ክርስቲያናት ኤፌሶንን ጨምሮ እንደ ገና ጎበኘ ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ቀድሞ በኤፌሶን አራት ችግሮችን እንዲፈታ ትቶት ነበር፡ “ የሐሰት አስተምሮን፣ በአምልኮ ያለን ስርዓት ማጣት፣ ለመሪነት ብቃት የሚያስፈልጉ ነገሮችን እና ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ ስለማተኮር “ ፡፡ ከመቄዶኒያ በጢሞቴዎስ በኩል እነዚህን ጉዳዩች እርስ በእርሳቸዉ እንዴት እንደያዟቸው ተከታተላቸው ፡፡
ትምህርት
1-ጢሞቴዎስ(1፡ 1-11)፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ መጀመሪያ ጢሞቴዎስ ትክክለኛ አስተምሮ እንደሚያስተምር ማብራራት እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ስለ እግዚአብሄር ባዶ ግምትን የያዘ ማንኛዉንም ነገር እንዳይሰማ (ቁጥር 1-4, 6-7) ነገር ግን በንፁህ ልብ እዉነተኛዉን እምነት እንዲያስተምር ነገረው (ቁጥር 5) ፡፡ ጳዉሎስም ህጉ ለፃድቃን ሳይሆን ፃድቃን ላልሆኑት እንደሆነ መናገሩን በመቀጠል 14 ምሳሌዎችን ይዘረዝራል፡ “ ለማይታዘዙ፣ ለዓመፀኞችና፣ ለኃጢዓተኞች፣ ቅድስና ለሌላቸዉ ለርኩሳን፣ አባትና እናትን ለሚገድሉ፣ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፣ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፣ በሰዎችም ለሚነግዱ፣ ለዉሸተኞችም በዉሸትም ለሚምሉ እና ደህና የሆነዉን ትምህርት ለሚቃወሙ ሁሉ “ (ቁጥር 8-10) ፡፡ ጳዉሎስ ይህ ሁሉ ከእግዚአብሄር መጥቶ በነበረው ወንጌል ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አብራራ (ቁጥር 11) ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (1፡ 12-17)፡ በመቀጠልም ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን ወንጌልን እንዲሰብክ አዘዘው ፡፡ በቁጥር (12-17) ጳዉሎስ የክርስቶስን ወንጌል ከማካፈል ዉጪ ለማድረግ የማይቻሉ የነበሩ ነገሮችን እና ለህይወቱ ምን ማለት እንደ ነበሩ የግል ምስክርነቱን አጋራ/ተናገረ ፡፡ ጳዉሎስ ኢየሱስን ከማግኘቱ በፊት ማን እንደ ነበር(ቁጥር 13) እና በክርስቶስ ገጥሞት የነበረዉን ነገር (ቁጥር 14) ገለፀ ፤ ጳዉሎስ የምንጊዜም አንደኛ/ትልቅ ኃጢዓተኛ እንደ ነበር ራሱን ገለፀ (ቁጥር 15) ፤ ይሁን እንጂ ጳዉሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ተቀብሎት ስለ ነበረዉ ምህረት እና ፀጋ እዉቅና በመስጠት ሁሉንም ክብር ሰጠ (ቁጥር 16-17) ፡፡
1-ጢሞቴዎስ (1፡ 18-20)፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን እምነትን እንዲጠብቅ አዘዘው ፡፡ ጳዉሎስ ጢሞቴዎስን በእርሱ ላይ ተነግሮ የነበረዉን ትንቢታዊ ቃል ስላስታወሰው ጢሞቴዎስ በዚያ እዉቀት ላይ መያዝ በመቻል በዉጊያ፣ በእምነት እና በበጎ ህሊና ብርታትን መያዝ ቻለ (ቁጥር 18-19) ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ በቁጥር 18 ከሰራዊት መልክ በቁጥር 19 ወደ ባህር ሰራዊት መልክ በመሄድ የእግዚአብሄርን ያለመቀበል መከራ “ እንደ እምነታቸዉ የመርከብ አደጋ “ በመግለፅ አመለከተ ፡፡ ጳዉሎስም መርከበኞች የነበሩትን እነዚህ ሁለቱን መጥቀስን ቀጠለ - ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ - ወደ ሰይጣን መልሷቸዉ እንደ ነበር ተናገረ (ቁጥር 20) ፡፡
መደምደሚያ
ለአሁኑ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ምን እያደረግን እንደ ሆነ ለመመርመር መንፈሳዊ ጥናቶችን ከእነዚህ ጥቅሶች የሚወሰዱትን እነዚህን እንወስዳለን፡
በቤተ ክርስቲያን እዉነተኛ የሆነ አስተምሮ እያስተማርን ነው ?
ወንጌል እየተናገርን ነዉ ?
እምነትንስ እየጠበቅን ነው ?
ጳዉሎስ ጢሞቴዎስ እነዚህን ነገሮች ተግባራዊ ካደረገ በኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን እዉነተኛ የእምነት እንቅስቃሴ እንደሚሆን ያውቃል ፡፡ ክርስቶስ አስታራቂያችን ስለሆነ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን በተመሳሳይ እዉነት ነው ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1772.
MacArthur, p. 1772.
MacArthur, p. 1772.
MacArthur, p. 1772.
MacArthur, p. 1772-1773.
MacArthur, p. 1773.
MacArthur, p. 1773.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, David C. Cook, 1989), p. 210.
Wiersbe, p. 212.
Wiersbe, p. 213.
Wiersbe, p. 213.
ጥያቄዎች
-
በ 1ጢሞ (1፡ 2) ጳዉሎስ ለጢሞቴዎስ እንዴት ጠቀሰው ? ለሰዉ መንፈሳዊ አባት ወይም መንፈሳዊ እናት ናችሁ ? ስለ መንፈሳዊ ወንድ እና ሴት ልጅስ ? አዎ ከሆነ ይህ ግንኙነት በእምነት እንዴት እንድታድጉ እና እንድትበስሉ ይረዳችኋል ?
-
ጳዉሎስ እንግዳ የሆነዉን አስተምሮ እያስተማራቸዉ ለነበሩ ሰዎች የትዕዛዙን አላማ ከጢሞቴዎስ ጋር ተነጋገረ ፤ አላማዉ ምን ነበር (1ጢሞ 1፡ 5) ? ይህን ነገር አለመያዝ ወደ ምን ይመራል (1ጢሞ 1፡ 6-7) ? አማኝ የሚመስል ነገር ግን እንግዳ የሆነ ትምህርት እያስተማረ የነበረ ሰዉ ታውቃላችሁ ?
-
ጳዉሎስ አንዳንድ የግል ምስክርነቶቹን ተናግሯል ፤ ታሪኩን በመናገር ዉስጥ ምን እንደሚሆን ምንን ተስፋ አደረገ ? ((1ጢሞ 1፡ 12-16)
-
ጢሞቴዎስ “ መልካሙን ነገር እንዲጋደል “ ተነገረው (1ጢሞ 1፡ 18) ፤ ይህ ማለት ነው ? መልካሙን ገድል እንድትጋደሉ ሌሎች እንዴት ያበረቷችሁ ይሆናል ? ሌሎችን እንዴት ታበረታቱአቸዋላችሁ ?
-
በ 1ጢሞቴዎስ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Timothy 1:12–13
“I give thanks to Christ Jesus our Lord who has strengthened me, because He considered me faithful, appointing me to the ministry—one who was formerly a blasphemer, a persecutor, and an arrogant man. But I received mercy because I acted out of ignorance in unbelief.”
በዚህ ለጢሞቲዎስ በተጻፈ የምክር ደብዳቤ ጳውሎስ በክርስቶስ ፊት ቀድሞ የነበረውን ህይወቱን አስታወሰ ፡፡ ተሳዳቢ ፣ አሳዳጅ እና አንገላች የነበረባቸውን ዘመናት አስታወሰ ፡፡ ከአምላኩ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለውን ጸጋና ምህረት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ጳውሎስ ምስክርነቱን አካፈለ ፡፡ ጳውሎስ ለሌሎች ስለእግዚአብሔር ምህረት
ስለመሰከረ ምስክርነቱ የብዙዎችን ህይወት ለዘላለም ለወጠ ለእግዚአብሔርም ክብርንና ምስጋናን አስገኘ ፡፡
ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ከተቀበልክ አንተም ልክ እንደ ጳውሎስ ምስክርነት አለህ ፡፡ የምትናገረው ታሪክ አለህ ክርስቶስን ከመቀበለህ በፊት ማን እንደነበርክና አሁን ከክርስቶስ በኋላ ማን እንደሆንክ ፡፡ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ታሪክ የለውም ፡፡ ምናልባት የኔ ታሪክ እንደ ጳውሎስ ድራማዊ አይደለም ብልህ ታስብ ይሆናል ፡፡ አታወዳድር ! እስኪ ታሪክህን ማን እንደጻፈው ገምት ? ኢየሱስ ነው ፡፡ እርሱ የእምነትህ ባለቤትና ፈጻሚ ነው ፡፡ ምስክርነትህን የምትጠራጠር ከሆነ እግዚአብሔር በህይወትህ የሰራውን ታሪክ እየተጠራጠርክ ነው ፡፡ ቀድሞ የነበረህን ማንነት በዳሹ ላይ በማስገባት እንድህ በማለት ጀምር ፡- “ ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ ፤ አስቀድሞ ……………… ፣ …………………. ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ ፡፡ “ በል አሁን ሂድና ቢያንስ ለአንድ ሰው ታሪክህን ተናገር ! እግዚአብሔር የጻፈውን ታሪክህንና እርሱ በህይወትህ ላይ ያሳያውን ምህረት ከልብህ ለሌሎች አካፍል ፡፡
“ ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ ፤ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ ፡፡ “
- 1ኛ ጢሞቲዎስ 1፡12-13
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 66:16 — “ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ ። “
ማርቆስ 5:19 — “ ኢየሱስም አልፈቀደለትም፥ ነገር ግን፦ ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደ ማረህ አውራላቸው አለው ። “
1ኛ ጢሞቲዎስ 1:16 — “ ስለዚህ ግን ፥ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።