Paul's Letters 2 Thessalonians

Church Discipline

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Faithful Lord 2 Thessalonians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 559 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ማቴ (5፡ 17) ለሪቫይቭ ት/ቤት ዋና ጥቅስ ነው፡ “ እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ ፡፡ ኢየሱስ በህጉ እና በነቢያት ሁሉም አካል ላይ ነው ፤ በመፅሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ማየት እንችላለን ፡፡ ሁለቱም መልዕክቶች ለተሰሎንቄ ስለ ጌታ ተመልሶ መምጣት በማዉራት ወደ ኢየሱስ በማመልከት የዳንኤል 9 ትንቢትን ተፈፀመ ፡፡ ለ 2ተሰሎንቄ ቃላችን የታመነ ጌታ ነዉ የሚለው ፡፡

ትምህርት

2-ተሰሎንቄ (3፡ 1-2)፡ ለተሰሎንቄያዊያን በሁለተኛዉ መልዕክት መደምደሚያ ላይ ጳዉሎስ ለአገልግሎቱ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፀሎት ጠየቀ ፡፡ ጳዉሎስ በተለዬ ሁኔታ በተሰሎንቄያዊያን መካከል ተሰራጭቶ በነበረዉ ተመሳሳይ መንገድ የጌታ መልዕክት ወደ አዲስ ስፍራ እንዲሰራጭ እንድትፀልይ ቤተ ክርስቲያንን ጠየቀ ፡፡ ጳዉሎስ ስለ ፀሎት በ 1ጢሞ (2፡ 1-2) በተመሳሳይ መስመር ጠይቋል፡ “ እንግዲህ እግዚአብሄርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገስታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ “ ፡፡ ጳዉሎስ ቀድሞ አድርጎት በነበረዉ ስራ የበቃዉ መሆን አልፈለገም ፤ ይልቁንም ወንጌል ወደ ሌላ አዲስ ስፍራ ሲሰራጭ ማየት ፈለገ ፡፡

በተጨማሪም ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያን “ ከዓመፀኞች እና ከክፉ ሰዎች እንዲድኑ “ እንድትፀልይ ጠየቀ (ቁጥር 2) ፡፡ ኮንስታብል ጳዉሎስ በቆሮንቶስ እንደገጠመዉ እነዚህ የማያምኑትን አይሁዶች የሚመስሉ እንደ ነበሩ አቅርቧል ፡፡

2-ተሰሎንቄ (3፡ 3-5)፡ በዳግም ምፅዓት/ንጥቀት ላይ ያላችሁ አመለካከት ምንም ቢሆን ጌታ የእርሱን ተመልሶ መምጣት በምትጠብቁ ጊዜ እናንተን ለማበርታት እና ለመጠበቅ የታመነ ይሆናል ፡፡ ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን በኢየሱስ ላይ እንዲያተኩሩ በተለይም “ ወደ እግዚአብሄር ፍቅር እና ወደ ክርስቶስ ትዕግስት “ (ቁጥር 5) የተሳቡ እንዲሆኑ አበረታታቸው ፡፡

2-ተሰሎንቄ (3፡ 6-13)፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያን በቅድስና እንድትመላለስ ፀለዬ ፡፡ ይህ ተግሳፅ ምን ያክል ከባድ/ጥብቅ እንደ ነበር ለማሳየት ጳዉሎስ ኢየሱስን በሚከተሉበት መንገድ ላይ ከሚያገኟቸው ማንኛዉም ሰዉ በመራቅ እንድትቀመጥ ለማስጠንቀቅ በኢየሱስ ስም ለመናቸው ፡፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስታኗን እርሱን እና አገልግሎት አጋሮቹን በተለይም ራሳቸዉን በመደገፍ እንዴት እንደሰሩ እንዲመስሏቸው አበረታታቸው ፡፡ ኮንስታብል ይህን ግሳፄ/ማስጠንቀቂያ ምናልባትም አንዳንድ ተሰሎንቄዋዊያንን ስራቸዉን በማቆም በቤተ ክርስቲያን እርዳታ እንዲኖሩ ከመራቸው በቤተ ክርስቲያን ሰርጎ ከገባዉ ካልተለዬ የሀሰት ትምህርት ጋር አገናኝቶታል ፡፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ የፊልጵስዮስን ቤተ ክርስቲያን እርሱን እንድትመስል አበረታታቸው፡ “ ወንድሞች ሆይ እኔን የምትመስሉ ሁኑ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ “ (ፊል 3፡ 17) ፡፡ ይህ በጳዉሎስ በኩል ትዕቢት ሳይሆን ክርስቶስን በመከተሉ ያለ ሙሉ መተማመን ነበር ፡፡ በሚገባ ለክርስቶስ ተመልሶ መምጣት የተዘጋጀ መሆን ማለት ያለምንም ስራ በመቀመጥ በጠበቅ ማለት አይደለም ፤ ይልቁንም ሁል ጊዜ ወንጌልን በመያዝ ክርስቶስን በመከታተል መስራት ማለት ነው ፡፡ በመጨረሻም ከ 1ቆሮ (11፡ 1)፡ “ እኔ ክርስቶስ እንደምመስል እኔን ምሰሉ “ በማለቱ ሌሎች እርሱን እንዲመስሉት ማዘዙን ቻለ ፡፡

ጳዉሎስ እና የስራ ባልደረቦቹ/አጋሮቹ በተሰሎንቄ እንደነበር ከቤተ ክርስቲያን ድጋፍን ማግኘት መብቱ ቢሆንም እንኳን እየሰሩ አገለገሉ ፡፡ ለሚከተሏቸው አማኞች የስራን ምሳሌ ለማስቀመጥ የቤተ ክርስቲያንን ድጋፍ የማግኘት መብታቸዉን ተዉ ፤ በእርግጥበተሰሎንቄ እንደ ነበሩ የመልዕክታቸዉ አካል ያልሰራ አይብላ የሚል ነበር ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ሰዎች የክርስቶስን ተመልሶ መምጣት ሲጠብቁ “ መልካም ስራን ለመስራት ባለመታከት ስራቸዉን እንዲቀጥሉ “ መከራቸው (ቁጥር 13) ፡፡

2-ተሰሎንቄ (3፡ 14-15)፡ ከተቃዋሚ ወንድሞች ዉስጥ የጳዉሎስን መልዕክት ለመቀበል እምቢ የሚል ካለ ጳዉሎስ እፍረትን እና ተስፋ የተሞላን ንስኃን ለማምጣት እንዲያሳፍሩት ቤተ ክርስቲያንን አበረታታ ፡፡ ኮንስታብል በዚህ ምሳሌ ዉስጥ ወደ ወንድሞች ንስኃ በመራ ጊዜ ማህበራዊ ግፊቶች መልካምን ለማስቀመጥ እንደሚጠቅም አስቀምጧል ፡፡ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያን እንድታሳፍረዉ የነገራቸዉን ሰዉ በኃሰተኛ ትምህርት የተነሳ በኃጢዓት ዉስጥ እንደሚሆን ማስተዋል አስፈላጊ ነው ፤ ይህ ቀላላ አይደለም ምክንያቱም ሌላ ሰው የማይወደዉን ነገር ሌላ አማኝ ስላደረገው ፡፡ ጳዉሎስ ይህንን ሂደት መካከለኛ መንፈሳዊነት እንዲሆን አልፈለገም ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን “ እንደ ወንድም እንድትገስፅ እንጂ እንደ ጠላት እንዳያዩት “ (ቁጥር 15) አበረታታቸው ፡፡

2-ተሰሎንቄ (3፡ 16-18)፡ ጳዉሎስ መልዕክቱን ወደ እግዚአብሄር ለቤተ ክርስቲያን ሰላምን እንዲሰጣት በመፀለይ እና ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን ፀጋ መለማመድን እንድትቀጥል በመመኘት አጠቃለለ ፡፡

መደምደሚያ

የኔልሰን ማብራሪያ የቤተ ክርስቲያንን ተግሳፅ/ቅጣት ለመተግበር አራት ቅደም ተከተሎችን ያስቀምጣል ወይም “ በተገለጠ እና በታወቀ ኃጢዓት ዉስጥ ካሉ አማኞች ጋር ህብረት እንዴት እንደሚተው “፡

  1. አንድ ለአንድ ከእነርሱ ጋር መገናኘት ፤ የህብረቱን አማኝ ስለኃጢዓቱ/ኃጢዓቷ በግለ መቃወም/መጋፈጥ ፡፡
  2. ሌላ የቤተ ክርስቲያን አባል መዉሰድ ፤ ንስኃ ካልገቡ ሌሎችን ከእናንተ ጋር መዉሰድ ፡፡
  3. ለቤተ ክርስቲያን ማሳወቅ ፤ አሁንም ንስኃ ካልገቡ የሰዎቹን ንስኃ ያለመግባት አመለካከት ቤተ ክርስቲያንን ማሳወቅ ፡፡
  4. ሰዎቹን ቤተ ክርትያኗን እንዲለቁ መጠየቅ ፤ ሰዎቹ አሁንም ንስኃ ባለመግባት የሚቀመጡ ከሆነ ይህ ቤተ ክርስቲያንን እንዲለቁ ለመጠየቅ የሚፈቅድ ጊዜ ነው ፡፡

የዚህ ሂደት አላማ ሰዎች ወደ ንስኃ ሲመጡ ለማየት ነው፡ “ ወንድሞች ሆይ ሰው በማናቸዉም በደል ስንኳ ቢገኝ መንፈሳዊያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለዉን ሰው በየዉሃት መንፈስ አቅኑት ፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ “ (ገላ 6፡ 1) ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ተግሳፅ/ቅጣት ለክርስቶስ ተመልሶ መምጣት አካሉን ለመዘጋጀት ያደርጋል ፡፡

  1. Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: 2 Thessalonians, p. 39. Available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/2thessalonians.pdf.

  2. Constable, pp. 42.

  3. Constable, pp. 45.

  4. Earl Radmacher, et. al. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999) p. 1590.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ተሰ (3፡ 4) ጳዉሎስ በተሰሎንቄ ያሉት ወንድሞችን አዟቸዉ የነበረዉን ማድረግ እንደሚቀጥሉ በጌታ መሉ እምነት እንደ ነበረዉ ተናገረ ፤ እንዲከተሉት ትዕዛዝን ማን ሰጣቸዉ ትዕዛዞቹስ ምን ነበሩ ? (1ተሰ 4፡ 1-12)
  2. 2 ተሰ (3፡ 6) በማንበብ ጳዉሎስ ወንድሞችን ስራ ፈትነት ህይወትን እንዲኖሩ ከሚመሩ ሁሉም ወንድሞች እንዲርቁ ለምን እያስጠነቀቃቸዉ እንደ ነበር ግለፁ (2ተሰ 3፡ 7-12)
  3. መልካምን ነገር ከማድረግ ታክታችሁ/ደክማችሁ ታውቃላችሁ (2ተሰ 3፡ 13) ? አዎ ከሆነ እንዴት ተቋቋማችሁት ?
  4. ጳዉሎስ በ 2ተሰ (3፡ 14-15) መልዕክት ላይ የተሰጠዉን ትዕዛዝ የማይታዘዝን ማንኛዉም ሰዉ ላይ ተሰሎንቄያዊያን በጽናት ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው ? ጳዉሎስ አለመታዘዘ እንደ እፍረት እንዲሰማ ለምን ፈለገ ? (መዝ 51፡ 17, 2ቆሮ 7፡ 9-10)
  5. በ 2ተሰሎንቄ 3 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Thessalonians 3:3a

“But the Lord is faithful.”

“ ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ፡፡ “ ክፉ ሰዎች ምንም ቢያደርጉ ፤ ህይወት ምንም ነገር ብታስከትል ፤ ጌታ ሲመጣም ቢሆን ምንም ይፈጠር ፣ ነገር ግን ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች ይህንን ነገር አረጋገጠ ፡- ጌታ የታመነ ነው ፡፡ ያበረታችሁ ዘንድና ልባችሁን ከክፉው ይጠብቅ ዘንድ ጌታ የታመነ ነው ፡፡

ምናልባት ዛሬ ይህን ቀላል ነገር ግን ኃይለኛ እውነት ማስታወስ ያስፈልጋችሁ ይሆናል ፡- ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ፡፡ ምናልባት ዛሬ መክፈል የማትችሉት የህክምና ክፍያ ተጠይቃችሁ ይሆናል ፣ ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ፡፡ ምናልባትም ልቡ በባህል በልማድ ደግሞም በጠላት ውሽት የተወሰደ ልጅ ይኖራችሁ ይሆናል ፣ ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ፡፡ ምናልባትም ሊወድቅ ሊያበቃለት ከሚመስል ትዳር ፣ ጓደኝነት ፣ ስራ ወይም ህልም ጋር እየታገላችሁ ይሆናል ፣ ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ፡፡ ስትጸኑ እናም ደግሞ በመንገዳችሁ ሁሉ ጌታን ስትሹ ፣ እርሱ ይታመንላችኋል ፡፡ እርሱ ለሺህ ትውልድ እንደሚታመን ተናግሯል ! የተሸከማችሁት ሸክም ምንም ያህል ከባድ ይሁን ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አስታውሱ ፣ እርሱ የታመነ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል ፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣችኋል ፡፡ ስትሄዱም ይጠብቃችኋል ፡፡ እግዚአብሔር ልባችሁን ወደ ፍቅር ያቀናል ደግሞም ትጸኑ ዘንድ ብርታትን ይሰጣችኋል ፡፡ በዚህ ሁሉ በእርሱ ታማኝነት ላይ ተጣበቁ ፡፡ እርሱ የታመነ ነው ፡፡

“ ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው ። “ - 2ኛ ተሰሎንቄ 3፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዘዳግም 7:9 — “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ ፡፡ “
  • 1ኛ ቆሮንቶስ 1:9 — ” ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው ። “
  • 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3b–5 — “ የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ፡፡ የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል ። ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው ። “