Paul's Letters 2 Thessalonians

Stand Firm

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Faithful Lord 2 Thessalonians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 558 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለ 1ተሰሎንቄ ቃላችን የሚመጣዉ ጌታ ሲሆን ለ 2ተሰሎንቄ የታመነ ጌታ የሚል ነው ፡፡ እዉነታዉ ክርስቶስ የተዘጋጀን ሆንም ወይም ደግሞ ያልተዘጋጀን ብንሆንም ክርስቶስ እንደ ሚመጣ ነው፣ ያ መቼ እንደሚሆንም አናዉቅም (ማቴ 24፡ 36) ፡፡ በምዕራፍ 2 ጳዉሎስ በሐሰተኛዉ ክርስቶስ ላይ በማተኮር ስለ መጨረሻዉ ጊዜ መናገሩን ቀጠለ ፡፡

ትምህርት

2-ተሰሎንቄ (2፡ 1-7)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ጳዉሎስ ስለ ቤተ ክርስቲያን መነጠቅ ያወራል ፡፡ ሐሰተኛ አስተማሪዎች ተሰሎንቄያዊያን በመጨረሻዉ ጊዜ ላይ እንደ ነበሩ ስለተናገሯቸው ስራቸዉን በመተው ተመልሶ መምጣቱን እእየተጠባበቁ ነበር ፡፡ ይሁን እንጂ ማቴ (24፡ 36) ተመልሶ መምጫዉን ማንም እንደማያዉቀዉ ራሱ ኢየሱስም እንኳን እንደማያዉቀዉ አብ ብቻ እንደሚያዉቀዉ ይናገራል ፡፡ በጥንቃቄ እና የተዘጋጀን በመሆን መጠበቅ አለብን (ማቴ 24፡ 42) ፡፡ ቁጥር 1 የክርስቶስ መምጣት አላማን ይናገራል ፤ ቁጥር 6 አሁን ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ተቆጥቦ/ተገቶ እንዳለ እና በትክክለኛዉ ጊዜ እንደሚገለጥ ይናገራል ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስን የገታዉ ማነው ? ምናልባትም መንፈስ ቅዱስ ነው ፡፡ ለአቃቢዉ/ለገቺዉ የመጀመሪያዉ ማጣቀሻው ፆታ የሌለዉ እንደ ሆነ አስታዉሉ፡፡

ቁጥር 2 ተሰሎንቃዊያን በቀላሉ የጌታ ቀን እንደሚመጣ በሚያወራዉ ከጳዉሎስ በሆነ መልዕክት፣ መንፈስ ወይም የሚበሳጩ መሆን እንደ ሌለባቸው ይናገራል ፡፡ በግልፅ ኢየሱስ ተመልሶ እንደ ነበር የሐሰት ትምህርት በተሰሎንቄያዊያን ዉስጥ አልፏል ፤ ጳዉሎስ የጌታን ቀን ከሚያስታችሁ በሀሰት ትምህርት እንዳትያዙ ይላል ፡፡ ክርስቶስ ሲመለስ ሁላችንም እናዉቀዋለን ፤ ዛሬ አንድ ሰዉ እኔ ክርስቶስ ነኝ ብሎ ቢናገር ያ የሀሰት መንፈስ እና ሀሰተኛ የክርስቶስ መንፈስ ነው ፡፡

ቁጥር 3 ስለ ዳግም ምፅዓት በመከራዉ መካከል እና ከመከራዉ በኋላ የሚለዉን ሀሳብ የሚደግፍ ይመስላል ፤ ከመነጠቃቸዉ በፊት አማኞች ቢያን ሰዎስት አመት ከግማሹን በመከራዉ ዉስጥ እንደሚቆዩ በመምከር ሐሰተኛዉ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ የጌታ ቀን እንደማይሆን ይናገራል ፡፡ “ የክፋት ሰዉ “ እና “ የጥፋት ልጅ “ ሁለቱም ሀሰተኛዉ ክርስቶስን ያመለክታሉ ፤ ቁጥር 4 ሐሰተኛዉ ክርስቶስ አምልኮ እንደሚገባዉ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግ በእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ራሱን በማስቀመጥ አምላክ እንደሆነ ይናገራል ፡፡

እነዚህ የመጨሻው ጊዜ ትንቢታዊ ክስተቶች ሂደቶች ናቸው፡

  1. የቤተ ክርስቲያን መነጠቅ የሆነ ጊዜ ላይ ይሆናል ፤ በማንኛዉም ጊዜ የተዘጋጀን መሆን አለብን ፡፡
  2. የአስር የአዉሮፓዊያን መሪ ከእስራኤል ጋር የሰባት አመት የሰላም ስምምነት ያደርጋል ፤ ያ መሪ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ይሆናል (ዳን 9፡ 26-27) ፤ ያ ሲሆን ሁላችንም የተዘጋጀን መሆን አለብን ፡፡
  3. ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ስምምነቱን ያፈርሳል (ዳን 9፡ 27) ፡፡
  4. ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ በቤተ መቅደሱ ዉስጥ ስዕሉን በማስቀመጥ አምላክ እንደሆነ ያውጃል (2ተሰ 2፡ 3-4) ፤ ያ ማለት ይህ እንዲሆን ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ መገንባት አለበት ማለት ነው ፡፡
  5. ሐሰተኛዉ ክርስቶስ አለምን በመቆጣጠር ለእርሱ እንዲሰግዱለት ማስገደድን ይጀምራል ፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ታላቅ መከራን ይልካል (ማቴ 24፡ 21-22) ፡፡
  6. አሕዛቦች በአርማጌድዮን ላይ በመሰባሰብ ሐሰተኛ ክርስቶስን ይዋጉታል (ራዕ 16፡ 16) ፤ የሆነ ስፍራ/ጊዜ ላይ በእስራኤል ሐሰተኛ ክርስቶስን ለመዋጋት የኢየሱስ ክርስቶስ የመምጣት ምልክትን እናያለን ፡፡
  7. ንጉሱ ኢየሱስ ወደ ምድር በመመለስ ጠላቱን በማሸነፍ በአይሁዶች የተቀበለ ይሆናል መንግስቱንም ይመሰርታል (ራዕ 19፡ 11) ፡፡
  8. ኢየሱስ ለ 1,000 አመት ያስተዳድራል (ራዕ 20፡ 4-6) ፡፡

ለኔ እነዚህ ሁሉ ወደ አንድ ጥያቄ ያመለክቱኛል ፤ ጌታ በእነዚህ ሁሉ እኛ እንደ ምስክሮች እንዴት ሊጠቀምብን ይችላል ?

በቁጥር 5 ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን ምን እንደሚሆን ቀድሞ ነግሯቸዉ ስለ ነበር ለሐሰተኛ አስተማሪዎች እና ለሐሰት ትምህርት ተስበዉ እንዳይወድቁ አሳሰባቸው ፡፡ ዋይርስቤ በኤደን ገነት የሰይጣንን እና ከአዳምና ከሒዋን ጋር የነበረዉን እና እግዚአብሄር በእርሱ ቤተስብና በሰይጣን መካከል ጦርነት እንዳለ ያወጀበትን ምሳሌ በመስጠት ሰይጣን የእግዚአብሄርን ዙፋን ለራሱ ለመዉሰድ ከሞከረበት ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሄር ጋር በዉጊያ እንደሆነ አመለከተ (ዘፍ 3፡ 15) ፡፡ ዋይርስቤ “ ሁል ጊዜ ሰይጣን የተመለከ እና እንደ እግዚአብሄር የተገለገለ መሆን ይፈልጋል ፤ አንድም ቀን የፈጠራ ዉጤቱን በማመንጨት አለም ሰይጣንን እንድታገለግል ምክንያት በመሆን የሰይጣንን ዉሸት በማመን የሆነዉ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ አንድ ቀን ፈጠራዉን ያመነጫል “ በማለት ያብራራል ፡፡

2-ተሰሎንቄ (2፡ 8-12)፡ ኢየሱስ ሐሰተኛ ክርስቶስን በአንድ እስትንፋስ እና በመምጣቱ ብርኃን ወደ ምንም ያመጣዋል (ቁጥር 8) ፤ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ መምጣት በሐሰተኛ ክርስቲያኖች (13፡ 38)፣ በሐሰተኛ አገልጋዮች (2ቆሮ 11፡ 13) እና በሐሰተኛ ወንጌል ተደግፎ ይመጣል (ገላ 1፡ 6-9፣ 2ተሰ 2፡ 9) ፡፡ በመሰረቱ ኃሰተኛዉ ክርስቶስ የሰይጣን አሸንጉላሊት ይሆናል ፡፡ እነዚህሁሉምይጠፋሉ ምክንያቱም እነርሱን የተቤዠዉን የኢየሱስን እዉነት ስላልተቀበሉ (ቁጥር 10) ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ፃድቅ ያልሆኑትን “ በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሄር የስህተትን አሰራር ይልክባቸዋል “ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ዋይርስቤ ብዙዎች እንደሚሞቱ ይገልፃል ፤ እነዚህ ሰዎች ለማመን እና ለመዳን እድል የላቸውም ፡፡ እግዚአብሄር በፍርድ በጠፉት ደስተኛ አይደለም (ሕዝ 33፡ 11) ፡፡ እግዚአብሄር “ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሳል “ (2ጴጥ 3፡ 9) ፡፡ እነዚህ ሰዎች ይፈረድባቸዉ እና ለዘላለም መከራ ይደርስባቸዋል ምክንያቱም እዉነቱን ስላልተቀበሉ እና ስላላመኑበት ፡፡ በእርግጥ ልባቸው ክፉ ስለሚሆን ለእዉነት ምንም አይነት ፍቅር አይኖራቸዉም ፡፡

መደምደሚያ

እስካሁን ያልመጣዉን ሐሰተኛ ክርስቶሱን እንዴት ልትገልፁት ትችላላችሁ ? ዋይርስቤ በሚመጣ ጊዜ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ምን እንደሚመስል እነዚህንመገለጫዎች ያስቀምጣል፡

የሰላም ሰዉ/አስታራቂ ይሆናል (ራዕ 6፡ 1-2) ፤ ስልጣናቸዉን ሙሉ በሙሉ የሚሰጡትን አስር ሕዝቦችን በአንድ ላይ ወደ አንድ ጎራ በመሳብ የሚያስተዳድር ፖለቲካዊ መሪ ይሆናል (ራዕ 17፡ 12-13) ፡፡

የሚከላከል/የሚጠብቅ ይሆናል (ዳን 9፡ 24-27) ፤ ይህ ለእስራኤል፣ ለኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ይተገበራል እንጂ ለቤተ ክርስቲያን አይደለም ፡፡

ሰላምን አፍራሽ ይሆናል (ዳን 9፡ 27) ፤ ከሰዎስት አመት ከግማሽ በኋላ ከቤተ መቅደስ ዉስጥ አምላክ ለመሆን የተናገረዉን ሰላም ያፈርሳል ፡፡

አሳዳጅ ይሆናል (ራዕ 13፡ 15-17) ፤ የአስሩ ሕዝቦች ስምምነት ከፈረሰ በኋላ ኃይለኛ ስደትን እና መከራን ያመጣል (ማቴ 24፡ 21) ፤ ዜጎች ማንኛዉንም ነገር ለመግዛት እና ለመሸጥ የአዉሮዉን ምልክት መሸከም ይጠበቅባቸዋል (ራዕ 13፡ 16-17) ፡፡

እስረኛ ይሆናል (ራዕ 19፡ 11-21) ፤ ክርስቶስ ተመልሶ በመጣ ጊዜ የእግዚአብሄር እስረኛ ይሆናል ፡፡

የኢየሱስ መመለስ ስትመለከቱ ግራ እንዲያጋባችሁ ለማንኛዉም የሐሰት ትምህርት አትፍቀዱ ፡፡ ኢየሱስ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አምላክ ነኝ ብሎ እስከሚናገር ድረስ ተመልሶ አይመጣም ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 196-197.

  2. 2 Wiersbe, p. 199.

  3. 3 Wiersbe, p. 199

ጥያቄዎች

  1. በጳዉሎስም ጊዜ እንኳን ሰዎች የጌታ ተመልሶ መምጣት በእነርሱ ላይ የሚሆን እንደ ነበር አምነዋል ፤ ከሁለት ሺህ አመት በፊት ጳዉሎስ በ 2ተሰ (2፡ 2-12) የተናገራቸዉ ነገሮች ለማለፍ እንደመጡ ታዩአቸዋላችሁ ? የጌታ ተመልሶ መምጣት በቅርብ እንደሆነ ይሰማችኋል ? ለምን ወይስ ለምን በቅርብ እንደሆነ አይሰማችሁም ?
  2. በ 2ተሰ (2፡ 11) ጳዉሎስ እግዚአብሄር “ ጠንካራን ዉዥንብር ስለላከባቸው ሀሰት የሆነዉን ያምናሉ “ ይላል ፤ የጠላታቸዉን ዉሸት ያመኑ ወይም በዉሸቱ የተሸዱ ሰዎችን ታዉቃላችሁ ? ለእነርሱ እዉነትን ተናግራችኋል ? ፀልያችሁላቸዋል ? አልፀለይንም ከሆነ አይኖቻቸዉ እና ጆሮቻቸዉ እንዲከፈቱ ጥቂት ጊዜን በመዉሰድ በፀሎት አንሱአቸዉ
  3. በተሰሎንቄ እንዳሉ አማኞች እንዳደረገዉ እግዚአብሄር ለመዳን/ለድነት እንደጠራችሁ ታስታዉላላችሁ/ታዉቃላችሁ ? በ 2ተሰ (2፡ 13) ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን ስለ ድነት ለእኛ እንዳደረገው እግዚአብሄር እንደመረጣቸዉ ነገራቸው ፤ ጥቂት ደቂቃ በመዉሰድ ስለ አዳኙ ፀጋው፣ ስለ ማይደበዝዘዉ ፍቅር እና እንደራሱ ስለ መረጣችሁ ለእግዚአብሄር ምስጋናን አንሱ ፡፡
  4. በ 2-ተሰሎንቄ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Thessalonians 2:7–9

“For the mystery of lawlessness is already at work, but the one now restraining will do so until he is out of the way, and then the lawless one will be revealed. The Lord Jesus will destroy him with the breath of His mouth and will bring him to nothing with the brightness of His coming. The coming of the lawless one is based on Satan’s working, with all kinds of false miracles, signs, and wonders.”

ጳውሎስ አማኞችን ስለመጨረሻው ዘመን ማስጠንቀቁን ቀጠለ ፡፡ በተለይም ደግሞ ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ፣ የአመጽ ሰው ፣ በሰይጣን አሰራር ስለሚሰራው ፤ በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም ስለሚመጣው አስጠነቀቃቸው ፡፡ ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ፣ የአመጽ ሰው ፣ አሳቹ ፣ የውሸት ተአምራት ፣ ምልክቶችና ድንቆችንም ስትሰሙ እንዳትፈሩ ፡፡ አንዳትጨነቁ ፡፡ ስለ ኢየሱስ ከሞት ስለተነሳው አዳኝ ኃይልና አሰራር ምንም እንዳትጠራጠሩ ፡፡ ፍርሃት ሰይጣን እንድኖራችሁ የሚፈልገው ስሜት ነው ፤ ፍርሃት ሰይጣን እናንተን ለማሳት ያመቸው ዘንድ እንድትቆዩበት የሚፈልገው ቦታ ነው ፡፡

እንደ አማኝ ስለ መጨረሻው ዘመን ፣ ስለ ስህተት ትምህርቶች ፣ ስለ አመጽ ሰውና ስለ ክፉው ከፍ ከፍ ማለት እወቁ ፣ ራሳችሁንም አንቁ ፡፡ ነገር ግን እንዳትፈሩ ፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር ለእናንተ ስላለው ፍቅር ማመስጋናችሁን ቀጥሉ ፡፡ ጸንታችሁ ቁሙ ደግሞም በተማራችሁት እውነት ላይ ተጣበቁ ፡፡ እግዚአብሔር እናንተን በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለማዳን መርጧችኋል ፡፡ ጥሪያችሁን ፈጽሙ ፡፡ ከእርሱ ጋር ስትራመዱ የእግዚአብሔር መገኘት እና ኃይል ፈጽሞ አይተዋችሁም ፡፡ አሳቹ ለሚመጣበት ቀን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል ፡፡ በእግዚአብሔር ብቻ ድልን ትቀዳጃላችሁ ! ስለዚህም በዚያ ድል አሸናፊነት ተመላለሱ !

“ የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና ፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ ። በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው ፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል ፤ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም እንደ ሰይጣን አሠራር ነው ። “

  • 2ኛ ተሰሎንቄ 2፡7-9

ተጨማሪ ጥቅስ

ሉቃስ 12:25 — “ ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው ? “

ሮሜ 8:38–39 — “ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን ፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ ፥ ከፍታም ቢሆን ፥ ዝቅታም ቢሆን ፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ ። “

2ኛ ተሰሎንቄ 2:13–15 — “ እኛ ግን ፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና ፤ ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ ። እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ ፥ ጸንታችሁ ቁሙ ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ ። “