Paul's Letters 2 Thessalonians

Eternity In The Presence Of God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Faithful Lord 2 Thessalonians 1 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 557 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እስካሁን ከ730 ክፍል 556 ክፍሎችን ጨርሰናል በመዝለል በዚህ ጥናት ለመጀመር በፍፁም የዘገዬ አይደለም ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ህያዉ እና በአሁኑ ጊዜም በመስራት ትዕዛዝን እንዲሁም ደግሞ በኑሮአችን ዉስጥ ማበረታታትን ያመጣል ፡፡ ሁለተኛ ተሰሎንቄ ተመልሶ በአንዳንድ ነገሮች በ 1ተሰሎንቄ ባሉ ነገሮች ላይ ይመለከታል ነገር ግን በተለዬ መንገድ ፡፡ ጳዉሎስ የመፅሀፉ ፀሀፊነቱን ሁለት ጊዜ ተናግሯል (2ተሰ 1፡ 1, 3፡ 17) ፡፡ ጢሞቲዎስ እና ሲላስ ጳዉሎስ መልዕክቱን በፃፈ ጊዜ ከእርሱ ጋር ነበሩ ፤ 1 ተሰሎንቄ ከተፃፈ ጥቂት ወራት በኋላ ሁለተኛ ተሰሎንቄ ከክርስቶስ ሞት 51 በኋላ ወይም ከክርስቶስ ሞት 52 በኋላ ቀደም ብሎ የተፃፈ ነበር፣ ሁለቱም ከቆሮንቶስ ከተማ የተፃፉ ነበሩ ፡፡ ለ 1ተሰሎንቄ ቃላችን የሚመጣዉ ጌታ የሚል ነበር ሲሆን ለ 2ተሰሎንቄ የታመነ ጌታ የሚል ነው (2ተሰ 3፡ 3) ፤ ጌታ ላለዉ ነገር የታመነ ስለሆነ ተመልሶ ይመጣል ፡፡

ጳዉሎስ በሁለተኛዉ የአገልግሎት ጉዞዉ በ ተሰሎንቄ ሰዎስት ሰንበትን በዚያ አሳለፈ ፤ በዚህ ያለዉ የጳዉሎስ ጊዜ በሐዋሪያት ስራ 17 የተመዘገበ ነው ፤ መድረሱ (ቁጥር 1-2)፣ ስለ ኢየሱስ አስተምሮዉን (ቁጥር 2-3)፣ የአዲስ አማኞች ምላሽን (ቁጥር 4)፣ የአይሁዶች ምላሽ (ቁጥር 5-9) እና በክርስቲያን ወንድሞቹ ወደ ቤርያ ከተማ የተላኩ ሆኑ (ቁጥር 10) ፡፡ ከቤርያ ጢሞቲዎስ እና ሲላስ በዚያ እንዳሉ ወደ ጳዉሎስ ብቻዉን ወደ አቴንስ ሄደ ፤ ቆይተዉም እንደ ገና በአቴና ከጳዉሎስ ጋር ተገናኙ (ቁጥር 15) ፡፡ ከአቴና ጳዉሎስ ጢሞቲዎስን መልሶ ወደ ተሰሎንቄ ላከዉ ሲላስን ደግሞ ወደ ፊልጵስዮስ ፡፡ በሐዋ (18፡ 1) ጳዉሎስ አተናን/አቴንስን በመተው ወደ ቆሮንቶስ ሲሄድ ጢሞቲዎስ እና ሲላስ በዚያ እንደ ገነ ተቀላቀሉት ፡፡

ጢሞቲዎስ በቆሮንቶስ በደረሰ ጊዜ በተሰሎንቄ ምን እየሆነ እንደ ነበር ለጳዉሎስ ሪፖርትን አደረገ ጳዉሎስም ለጢሞቲዎስ ምላሽ እንዲሆን የመጀመሪያ መልዕክቱን ፃፈ ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ አስራ ስምንት ወራትን በመቆየት ከዚያ ብዙ መልዕክቶችን ፃፈ ፡፡ ማክአርቱር “ ምናልባት የመጀመሪያዉ መልዕክት ተሸካሚ ጳዉሎስን የበሰለዉ እና ተስፋፍቶ የነበረው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ መልሶ ወሰደው (1፡ 3)፣ ነገር ግን ግፊቱ እና መሰደዱ ጨምሯል ፡፡ ጌታ በተመለከተ የሐሰት አስተምሮ ዘር ተዘርቶ ስለ ነበር የሰዎቹ ባህሪይ የተዛባ ነበር “ ፡፡ የጳዉሎስ ሁለተኛ መልዕክት ለተሰሎንቄያዊያን “ ስለ ጌታ ተዘርቶ ስለ ነበረዉ የኃሰት አስተምሮ ምላሽን በተመለከተ ነበር “፣ በተጨማሪም “ በመከራ ተስፋ በመቁረጥ ለመጠንከር ማበረታቻ ፈልገዉ ለነበሩ፣ 2) ስለ ጌታ ተመልሶ መምጣት ግራ ባጋቧቸዉ ኃሰተኛ አስተማሪዎች ተታለዉ ለነበሩት እና 3) በተግባር ለመስራት መለኮታዊ የሆነን ትዕዛዝ እምቢ በለዉ ለነበር “ ፡፡ የጳዉሎስ ፍላጎት ስደት/መከራ ደርሶባቸዉ ለነበሩት መፅናናትን ማቅረብ እና የሐሰት ትምህርትን ተቀብለዉ የነበሩትን ማስተካከያ ለመስጠት እና የማይታዘዙ ለነበሩት ለጋፈጥ ነበር ፡፡ ጳዉሎስ እነዚህን ጉዳዮች ብቻ አልደረሰም መፍትሄዉንም አቀረበ እንጂ ፡፡

ትምህርት

2-ተሰሎንቄ (1፡ 1-4)፡ ቁጥር 1-2 የጳዉሎስን ሰላምታ ሲይዝ ቁጥር 3 እምነታቸዉ ፍሬ እያፈራ ለነበረት እና እርስ በእርስ ፍቅራቸዉ እየጨመረ ለነበረዉ ለተሰሎንቃዊያን ምስጋናን ይገልፃል ፡፡ በእርግጥ ጳዉሎስ ስለ ተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ለሌሎች ተሰሎንቄያዊያን እየደረሰባቸዉ ስለ ነበረዉ መከራ በእምነታቸዉ የታገሱ እንደ ነበሩ ተናገረ (ቁጥር 4) ፡፡

2-ተሰሎንቄ (1፡ 5-8)፡ ጳዉሎስ ስለ ከፈሉት ዋጋ/ስለ መከራቸዉ የእግዚአብሄር ፀጋ እና የመንግስቱን የሚገባቸዉን ዋጋ እንደሚቆጥርላቸው (ቁጥር 5) እና እነርሱን ያሳደዷቸዉንም እግዚአብሄር ዋጋቸዉን እንደሚከፍላቸው አመለከተ (ቁጥር 6 -8) ፡፡ አንዳንድ ምሁራን ቁጥር 7 መከራዉ ከመጀመሩ በፊት ቅዱሳን ይመጣሉ የሚለዉን ሀሳብ እንደ መደገፊያነት ይጠቅሳሉ ፡፡ ኢየሱስ ከመለዓክቱ ጋር በተገለጠ ጊዜ መሰደድ እና መከራ ደርሶባቸው የነበሩት ረፍትን ይቀበላሉ ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍራት አይኖርም “ እግዚአብሄርን የማያዉቁትን ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል “ (ቁጥር 8) ፡፡ መከራዉ ለሰባት አመታት ይቆያል እናም እነዚህ ምሁራን ተሰ (1፡ 7) ኢየሱስ አማኞቹን መከራዉ ከመሆኑ በፊት እንደሚያወጣቸዉ ያሳያል ይላሉ ፡፡

ሌሎች ምሁራን 1ተሰ (4፡ 13-18) አማኞች ከመከራዉ እንደሚድኑ እንደሚያብራራ እና 2ተሰ (1፡ 7-8) እግዚአብሄርን በማያዉቁት ላይ ስለሚመጣዉ በቅል እንደሚናገር ያምናሉ ፤ ይህን ትርጉም የያዙት ዳግም ምፅዓት ከመከራዉ መጨረሻ ላይ እንደሚመጣ ያምናሉ ፡፡

2-ተሰሎንቄ (1፡ 9-12)፡ ቁጥር (9-10) ክርስቶስን የማያዉቁት የዘላለም ጥፋት እነደሚገጥማቸዉ በግልፅ ያመለክታል ፤ ከዚህ የዘላለም ጥፋት የተነሳ ጳዉሎስ ለተሰሎንቄያዊያን በእግዚአብሄር መብቃትን እንዲያገኙ ፀለየላቸው (ቁጥር 11-12) ፡፡ ጳዉሎስ ለክርስቶስ እንደ ምስክር የእምነት ስራቸዉን በመቀጠል የክርስቶስ ስም የከበረ እንዲሆን ፀለዬ ፡፡

መደምደሚያ

ጳዉሎስ በክርስቶስ የማመን አስፈላጊነትን ጠበቅ አድርጎ ተናግሯል ፤ የሚያደርጉት በእግዚአብሄር ፊት ዘላለማዊነትን ሲቀበሉ የማያደርጉት ደግሞ ዘላለማዊ ጥፋትን ይቀበላሉ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1762.

  2. MacArthur, p. 1763.

  3. MacArthur, p. 1763.

  4. MacArthur, p. 1763.

ጥያቄዎች

  1. በ 2ተሰሎንቄ 1 በተሰሎንቄ ያለች ቤተ ክርስቲያን በችኮላ እና በፍጥነት እያደጉ ነበር ፤ ጳዉሎስ እምነታቸዉ እንዳደገ እና በ 2ተሰ (1፡ 3) ፍቅራቸዉ ስለመትረፍረፉ ይናገራል ፡፡ በዚህ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን የሚታይ ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይታይም ?
  2. 2 ተሰ (1፡ 6) ክፉ በአደረገብን ሰዉ ላይ በቀልን እንዳንፈልግ ነገር ግን እግዚአብሄር እንዲሰራ እንድንተዉ ይናገራል ፤ በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ እግዚአብሄርን ስለ እኛ እንደሚዋጋ ይናገራል ? (ዘጸ 14፡ 14, ዘዳ 3፡ 22, 20፡ 4, ኢያ 23፡ 10, ሮሜ 12፡ 19)
  3. ስለ እምነት የእናንተ ትርጓሜ ምንድን ነው ? በተሰሎንቄ ያለች ቤተ ክርስቲያን ሳታይ ጳዉሎስ የተናገረው አምናለች ፤ ከእናንተ የተለዬ ነገር አለ ? ከእናንተ የተለዬ እምነት አለ ? እምነታችሁን ሁሉ በኢየሱስ እና በመስቀሉ መልዕክት ላይ ታስቀምጣላችሁ ? አይደለም ከሆነ ምንድን አስቆማችሁ ?
  4. በ 2ተሰሎንቄ 1 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 2 Thessalonians 1:3–4

“We must always thank God for you, brothers. This is right, since your faith is flourishing and the love each one of you has for one another is increasing. Therefore, we ourselves boast about you among God’s churches—about your endurance and faith in all the persecutions and afflictions you endure.”

ጳውሎስ ስለ ተሰሎንቄ ሰዎች ስለ እምነታቸው ደግሞም ስለተቀበሉት ስደትና መከራ አረጋገጠ ፡፡ ልቡንም ነፍቶ ለሌሎች ስለ እምነታቸው መሰከረ ፡፡ ጳውሎስም ስለ እነርሱ መጸለዩን ቀጠለ ደግሞም ከፊታቸው ዘላለማዊ ህይወት ስላለ የጌታን ስራ መስራታቸውን እንድቀጥሉ መከራቸው ፡፡

ምናልባት አሁን ለምን በእምነት እንደምትመላለሱና ክርስቶስን እንደምትከተሉ ባልተረዳ የቤተሰብ አባል ስደት እየደረሰባችሁ ሊሆን ይችላል ፡፡ ምናልባትም ደግሞ ብዙሃኑን እንድትቀላቀሉ ፣ ኃጢአትን ርኩሰትን እንድታደርጉ በሚፈልጉ ጓደኞች ልትሰደቡ ትችላላችሁ ፡፡ ነገር ግን እናንተ በስጋችሁም ሆነ በአሳባችሁ ንጹህ ሆናችሁ መቀጠልን ምረጡ ፡፡ ይህን ቃል ከጌታ መስማት ያስፈልጋችኋል …….. መልካም አደረጋችሁ ! ጓደኞቼ በዚህ ልማድ ባህል ውስጥ እንኳ ሳላችሁ በርቱ ፡፡ ለተቀበላችሁት ጥሪ በቂ እንደሆናችሁ ይህን አስቡ ፡፡ ጌታ በኃይሉ ያበረታችኋል ስለዚህም በእምነትና የምስራቹን በዙሪያችሁ ላሉት በማብሰር ትቀጥላላችሁ ፡፡ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እና በእናንተ ይከብራል ፡፡ ተስፋ እንዳትቆርጡ ፡፡ የእግዚአብሔር ፍርድ ቀርቧል ስለዚህም በርቱ ፣ ቀጥሉ ደግሞም በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል የእርሱን ፍቅር ለሌሎች አካፍሉ ፡፡

“ ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን ፤ ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን ። “

  • 2ኛ ተሰሎንቄ 1፡3-4

ተጨማሪ ጥቅስ

ማቴዎስ 5:11–12 — “ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና ። “

ሐዋርያት ሥራ 1:8 — “ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ ። “

2ኛ ተሰሎንቄ 1:11–12 — “ ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን ። “