Paul's Letters 1 Thessalonians
The Day Of The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Lord 1 Thessalonians 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ስለ ዳግም ምፅዓት ከላይ ከላይ አዉርተናል ፤ ዛሬ በትንሹ በጥልቀት እንመለከታለን ፡፡ ዳግም ምፅዓት ከመከራዉ በፊት፣ መከራዉ መካከል ላይ እና ከመከራዊ በኋላ ነዉ ለማለት አዋቂ አይደለሁም ፡፡ ዳግም ምፅዓት በ 1ተሰ (4፡ 16-17) ተገልፆአል ፡፡ በአየር ላይ ኢየሱስን ለመገናኘት በምንነሳ/በምናርግ ጊዜ የማይታመን ሰማያዊ ድግስ ይኖራል - አሁንም በምድር አየር ክልል ዉስጥ ስለምንሆን በመጀመሪያዉ ሰማይ የሚሆን ይመስላል ፡፡ ይህ ዳግም ምፅዓት ነው ፡፡ ያ መቼ ነዉ የሚሆነው ? ጌታ በተሰጠዉ በማንያዉም ክስተት ላይ ተመልሶ መምጣት ይችላል ፡፡ ይህ አያስፈራንም ተስፋን በመስጠት ስለ ክርስቶስ ለሌሎች እንድናገር ያፈጥነናል እንጂ ፡፡ ለ 1ተሰሎንቄ ጭብጣችን የሚመጣዉ ጌታ እንደሆነ አስታዉሱ ፤ ተዘጋጁ፣ ጌታ ተመልሶ ይመጣል ፡፡
ትምህርት
1-ተሰሎንቄ (5፡ 1)፡ ጳዉሎስ ስለ ጊዜዉ እና ስለ ወቅቱ ለእነርሱ የተፃፈ ማንኛዉም ነገር አያስፈልጋቸዉም በማለት ለምን ይህን ስነ መለኮታዊ ማመሳሰል ለምን ፈጠረ ? ጳዉሎስ ስለ ዳግም ምፅዓት አወራ ምክንያቱም የተዘጋጁ መሆን ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ግን ኢየሱስ መቼ ተመልሶ ይመጣ እንደ ነበር ስለማያዉቁ በቅድስናቸዉ መመላለስ አስፈለጋቸው ፡፡ በሐዋ (1፡ 7) ኢየሱስ ተከታዮቹን “ አብ በገዛ ስልጣኑ ያደረገዉን ወራትንና ዘመናትን ታዉቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም “ በማለት ነገራቸው ፡፡ ኢየሱስ ተመልሶ መቼ እንደሚመጣ ትክክለኛ ጊዜዉን ማወቅ ስላልቻሉ የመንፈስ ቅዱስን ኃይል ሰጣቸዉ(ሰጠንም) (ሐዋ 1፡ 8) ፡፡ መፅሀፍ ሁሉም አሕዛቦች ወንጌልን የመስማት እድል እስኪያገኙ ድረስ ኢየሱስ ተመልሶ እንደማይመጣ ይናገራል ፤ ስለዚህ እንድናደርግ ያዘዘንን በሚገባ ስላላደረግን ተመልሶ መምጣቱን ይዘነዋል/አዘግይተነዋል ፡፡
1-ተሰሎንቄ (5፡ 2)፡ ስለ ጌታ ቀን በምታስቡ ጊዜ ስለ ምን ታስባላችሁ ? በዘፍጥረት አንዳንድ ጊዜ አንድ ቀን ሀያ አራት ስዓት እንደ ሆነ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጠቅላላ ሳምኑቱ ማለት እንደሆነ ዉይይት ነበር ፡፡ ይህ ሁሉም ነገር በሀያ አራት ስዓት ዉስጥ ይከናወናል ይታወቃል ማለት አይደለም ፡፡ የእግዚአብሄር የጊዜ ቅደም ተከተል ሙሉ በሙሉ በእኛ አቆጣጠር ዉስጥ እንዳልሆነ ማስተዋል አለብን - ያ ምን ማለት እንደሆነም እንኳን መያዝ አንችልም ፤ ነገር ግን ስለ ዚህ ቀን ስለ እግዚአብሄር ሀሳብ እናዉራ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የሚተገበሩ ሁለተ ነገሮች አሉ ይላል፡ 1) በኃጢዓተኞች ሰዎች ላይ የእግዚአብሄርን ፍርድ እናያለን፣ 2) በህዝቦቹ ላይ የእግዚአብሄርን ዘላለማዊ አገዛዝ እናያለን ፡፡ የጌታ ቀን “ እግዚአብሄር አለምን የሚዳኝበት እና አሕዛቦችን የሚቀጣበት ነዉ ፤ በተመሳሳይ ጊዜ እግዚአብሄር መንግስቱን ለመመስረት በምድር ላይ እስራኤልን ወደ ክርስቶስ ለመመለስ የሚያዘጋጅበት ጊዜ ነው “ ፡፡ በአጭሩ የጌታ ቀን የኢየሱሱ ሁለተኛ መምጣት ነው ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የጌታ ቀን ለመጥቀስ/ለማመልከት ኤር (30፡ 7) በመሄድ ይህን ቀን የያዕቆብ የመከራ ጊዜ በማለት ይጠሩታል ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የጌታን ቀን መከራ በማለት ይጠሩታል ምክንያቱም ወዲያዉኑ ኢየሱስ ስለሚመጣ ፡፡ የጌታ ቀን በተከሰተ ጊዜ የመንግስቱ መሆን ዉልደትን መጠበቅ ትችላላችሁ ፡፡ “ የጌታ ቀን ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ እንዲሁ ይመጣል “ የሚለዉ ስዕል በማቴ (24፡ 42-44) በኢየሱስም “ ጌታችሁ በምን ስዓት እንዲመጣ አታዉቁምና እንግዲህ ንቁ “ በማለት ተጠቅሞበታል ፡፡
1-ተሰሎንቄ (5፡ 3-7)፡ በዚህ ጥቅስ ላይ “ እነርሱ ባሉ ጊዜ “ ያልዳኑትን እና ያላመኑትን ያመለክታል ፡፡ በክርስቶስ ባላመኑት ላይ ፍርድ ይመጣል (ቁጥር 3) ፤ ነገር ግን አማኞች ስለመምጣቱ ስለሚያዉቁ አይደነግጡም/አዲስ አይሆንባቸውም (ቁጥር 4) ፡፡ አማኞች “ ነቅተዉ እና ተጠንቅቀዉ የሚጠብቁ “ (ቁጥር 6) “ የቀንና የብርሃን ልጆች ናቸው “ (ቁጥር 5) ፡፡ በጨለማ እየተመላለሳችሁ ከሆነ ተመልሶ ለመምጣቱ የተዘጋጃችሁ አይደላችሁም (ቁጥር 7) ፡፡ ለ ሀያ ክፍለ ዘመናት ጌታ በማንኛዉም ስዓት/ጊዜ ተመልሶ እንደሚመጣ የሚል ተስፋ ተሰጥቶናል ፡፡ ጴጥሮስ “ እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት ሺህ አመትም እንደ አንድ ቀን እንደ ሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ “ በማለት ፅፏል (2ጴጥ 3፡ 8) ፡፡ እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ በተለዬ ቀን አቆጣጠር ላይ ስለሆነ ኢየሱስ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል መኖር አለብን ፡፡ በኢሳያስ ብዙ ፅሁፎች ስለ ዉልደት ህመም ያወራሉ ፤ በማቴ (24፡ 8) የዉልደት ህመም የመዉለድ ህመም መጀመሪያ እንደ ሆነ ነግሮናል ፡፡
1-ተሰሎንቄ (5፡ 8-11)፡ ያለማቋረጥ በእምነት፣ በተስፋ እና በፍቅር ልንሰራ/ልንኖር ይገባናል (ቁጥር 8) ፡፡ እግዚአብሄር እንደሚገለጥ እና ኢየሱስ መሲህ እንደሆነ በማመን የእምነትን እቃ ጦር እንለብሳለን ፤ ክርስቶስን ምሳሌ ሆኖ በመግለጥ እና ኑሮአችንን ለሌሎች በመስጠት ፍቅርን በደረታችን ላይ እንለብሰዋለን ፤ በዚህ ሂደት ዉስጥ ለእኛ ተመልሶ እንደሚመጣ በማወቅ የድነትን ተስፋ ኮፍያን እንለብሰዋለን ፡፡ ዋይርስቤ “ ለመንቃት፣ ለመንፃት እና ለመልበስ ጊዜዉ ነው “ ብሏል ፡፡ ዳግም ምፅዓት መቼም ቢሆን በዳመና ላይ እርሱን ባገኘነዉ ጊዜ “ ከእርሱ ጋር በአንድ ላይ እንኖራለን “ (ቁጥር 10) ፡፡ ከመከራዉ በፊት፣ በመከራዉ ጊዜ እና ከመከራዉ በኋላ ቢሆንም ችግር የለዉም - ከክርስቶስ ጋር እንሆናለን ፡፡ በመከራዉ ዉስጥ የማለፍ እድል የሚኖረን ከሆነ ለመከራዉ የተዘጋጀን መሆን ያስፈልገናል ፡፡
1-ተሰሎንቄ (5፡ 12-28)፡ እነዚህ ጥቅሶች ቤተሰባችሁን እንዴት እንደምትመሩት፣ ቤተሰቦቻችሁን ከቤተሰባችሁ ጋር እንዴት እንደ ምታጣምሩት እና ይህን በክርስቶስ አካል ዉስጥ እንዴት እንደምታደርጉት ያወራል ፡፡
ስለ መከራዉ አንዳንድ መረጃዎችን እንከልስ/እንመልከት ፤ ብዙ ሰዎች መከራዉን ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ወደ ጨዋታዉ በመምጣት ሰላምን የሚያስጀምር የሰባት አመት ጊዜ በማለት ይገልፁታል ፡፡ በመጀመሪያዉ ሰዎስት አመት ከግማሽ የተረጋጋ እና መልካም የሆነ ቤተ መቅደሱ ተመልሶ የሚገነባበት ነው ፤ በሰባቱ አመት መካከል ላይ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ አምላክ ነኝ ይላል ፤ ቀጣዮቹ ሰዎስት አመት ከግማሽ ስለመከራዉ እና ስለ ቁጣ ነው ፡፡
ዳግም ምፅዓት ከሰባት አመቱ የመከራ ጊዜ በፊት እንደሚመጣ የሚያምኑ ሰዎች ኢየሱስ ከሚመጣዉ ቁጣ እንደሚታደግን የሚናገረው 1ተሰ (1፡ 10) ከተማ እና 1ተሰ (5፡ 9) እግዚአብሄር ለቁጣ አልመረጠንም ስለሚል ፡፡ ይህ ከመከራዊ በፊት የሚለዉ እይታ እግዚአብሄር ለቁጣ ካልመረጠን በሰባቱ የመከራ አመታት ዉስጥ አናልፍም ይላል ፡፡ ዋይርስቤ ይህን እይታ/አመለካከት ይወስዳል ምክንያቱም 1) የእግዚአብሄርን ቁጣ መቅመስ የቤተ ክርስቲያን ተፈጥሮ ስላልሆነ (ዮሐ 5፡ 24) እና 2) ያልታወቀ ጊዜ ከመሆኑ ይልቅ ግልፅ የሆነዉ የክርስቶስ የመመለስ ተስፋ የሰላምን ስምምነትን በመፈረም የተመሰረተ ጊዜ ስለሚኖር ፡፡ በዚህ ላይ እዉነት የሀነዉ አንድ ክርክር ክርስቶስ መከራን እንደተቀበለ በእርሱ በማመን ስለ እርሱ መከራን በመቀበል እግዚአብሄር እንዲያከብሩ አማኞችን ፈቅዶላቸዋል የሚል ነው ፡፡
2ተሰሎ (2፡ 3) “ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ አይደርስምና “ ይላል ፤ ይህ ጥቅስ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ወደ ተግባር ሲገባ እናየዋለን ይላል ፡፡ ስለዚህ ይህ ጥቅስ የመከራዉ መካከልን ወይም ከመከራዉ በፊት ወይም ከመከራዉ በኋላ ያለን የዳግም ምፅዓት እይታን ያረጋግጣል ፡፡ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ ራሱን በመግለጥ አምላክ ነኝ ብሎ በሚያዉጅ ጊዜ የክፋት ጥላቻ ይሆናል (ማቴ 24፡ 15) ፡፡
ራዕ (6፡ 16-17) በመከራዉ ዉስጥ የሚያልፉ አማኞች እንዳሉ ያመለክታል ምክንያቱም ከእግዚአብሄር ፊት እና ከበጉ ቁጣ የተደበቁ መሆን ስለሚፈልጉ ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ከመከራዉ መካከል ላይ እና ከመከራዉ በኋላ የሚለዉን አመለካከት ይደግፋሉ ፡፡ ራዕይ ኢየሱስ ስለፈታቸዉ ሰባት ማህተሞች እና የእግዚአብሄር ቁጣ ሰባተኛዉ ማህተም እስኪፈታ ድረስ እንደማይፈስስ ያወራል ፡፡
ራዕ(7፡ 9 እና 14) በዙፉኑ ፊት እና በበጉ ፊት ስለሚቆመዉ ታላቅ ህዝብ ይገልፃል (ቁጥር 7) ፤ “ ከታላቁ መከራ የመጡ “ በመባል ተለይተዋል (ቁጥር 14) ፡፡ ይህ ከራዕይ ስድስት እና የቁጣዉ ቀን መጥቶ እንደ ነበር ከሚናገረው ስድስተኛዉ ማህተም የተከፈተ/የተፈታ ከሆነ በኋላ ይመጣል ፡፡ ራዕይ 7 በመዓት/በቁጣ እና በዳግም ምፅዓት በኩል እንዲያልፉ ታትመዉ የነበሩትን 144,000 ይገልፃል ፡፡ “ ታላቅ መከራ “ የሚለዉ ቃል ከክፉዉ ጥፋት በኋላ ስለ ሚመጣዉን የመከራዉን ክፍል በማቴ (24፡ 15) ኢየሱስ የተጠቀመበት ቋንቋ ነበር ፡፡ ይህ ዳግም ምፅዓት በመከራዉ መካከል ላይ ወይም ከመከራዉ በኋላ የሚለዉን ሀሳብ ይደግፋል ፡፡
ማቴ (24፡ 29-31) “ ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ…..የሰዉም ልጅን በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል….ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፍሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ “ ፡፡ ቁጥር (30-31) ዳግም ምፅዓቱ ከመከራዉ በኋላ እንደሚመጣ ይገልፃሉ ፤ ይህ ከመከራ በኋላ ወይም ከመኣት በፊት ላለ ታላቅ ሀሳብ/ክርክር ነው ፡፡
መደምደሚያ
ክርስቶስ ቅድመ መከራ፣ የመከራዉ መካከል ወይም ከመከራዉ በኋላ እንደምናገኘዉ አናዉቅም ነገር ግን ሁላችንም የተዘጋጀን እንድንሆን ለሁሉም ምክንያት ይሆናል ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1580.
Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), p. 723.
Wiersbe, p. 723.
Wiersbe, p. 723.
Wiersbe, p. 724.
Wiersbe, p. 725.
ጥያቄዎች
-
የጌታ ቀን እንዴት ነዉ የሚመጣው ? በብሉይ ኪዳን የጌታ ቀን በምን ሁለት መንገዶች የተመሰለ ነበር ? (ኢሳ 2፡ 1-3, 11፡ 1-9, 30፡ 23-26, ኢዩ 2፡ 1-2, አሞ 5፡ 18-20, ሰፎ 1፡ 14-17, ዘካ 14፡ 1, 7-11)
-
ክርስቶስ እንዴት አንድ ሆነ ተከፈለስ ? (ዮሐ 7፡ 43, 9፡ 16, 10፡ 19, 1ቆሮ 1፡ 10, ገላ 3፡ 28, 1ተሰ 4፡ 17)
-
በ 1ተሰ (5፡ 6) ጳዉሎስ አንቀላፉ በሚለዉ ቃል ምን ማለቱ ነው ? በክርስቶስ ያሉ አማኞች ምን ያደርጋሉ ? (ሮሜ 14፡ 10-11, 1ቆሮ 3፡ 11-15, 9፡ 24-27, 2ቆሮ 5፡ 10)
-
እግዚአብሄር ለአማኞች ያላዘጋጀዉ/ያልመረጠው ምንድን ነው (ራዕ 6፡ 12-17) ? ምንድን ነዉ ያዘጋጀላቸው(1ተሰ 1፡ 10) ? በእነዚህ እዉነቶች ብርሃን እምነታችሁን ከሌሎች ጋር እንድትነጋገሩ/እንድትጋሩ ያበረታታችኋል ?
-
ለእናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሄር ፍቃድ የሆኑት ጳዉሎስ የተናገራቸዉ ሰዎስት ነገሮች ምንድን ናቸው ? ከመንፈስ እና ከትንቢት ጋር በተገናኘ ጳዉሎስ የሰጣቸዉ አምስት ተግሳፆች ምንድን ናቸው ?
-
በ 1ተሰሎንቄ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Thessalonians 5:5–8
“For you are all sons of light and sons of the day. We do not belong to the night or the darkness. So then, we must not sleep, like the rest, but we must stay awake and be serious. For those who sleep, sleep at night, and those who get drunk are drunk at night. But since we belong to the day, we must be serious and put the armor of faith and love on our chests, and put on a helmet of the hope of salvation.”
ኢየሱስ ይመጣል ፡፡ ይህ እውነት ነው ፡፡ የማታውቁት ጊዜው መቼ እንደሆነ ብቻ ነው ፡፡ ጳውሎስ በራሱ ዘመን እንደሚሆን ያስብ ነበር ፡፡ እናንተም ደግሞ በእናንተ ዘመን እንደሚሆን ታስቡ ይሆናል ፡፡ መጠየቅ የሚያስፈልገው ጥያቄ ግን ፡- ኢየሱስ ዛሬ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል አድርጋችሁ ነወይ የምትኖሩት ነው ? ለዳግም ምጽዓቱ ተዘጋጅታችሁ እንድትኖሩ ተጠርታችኋል ፡፡ በብርሃን ወይስ በጨለማ ነው የምትመላለሱት ? እንደ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ነቅታችኋል ወይስ እያንቀላፋችሁ ነው ? በመንፈስ ተሞልታችኋል ወይስ በወይን ጠጅ ሰክራችሁ እያንቀላፋችሁ ነው ? በዙሪያችሁ ጦርነት ለሚቀሰቅሰው ትግል ታጥቃችኋል ? ጳውሎስ በደንብ ግልጽ አድርጎታል ፡- በብርሃን ተመላለሱ ፤ ንቁ ስለ ኢየሱስም በመጠን ኑሩ ፡፡ የእምነትንም ጋሻ ጦር ልበሱ ፡፡ ጦር ሜዳ ውስጥ ነው ያላችሁት ፡፡ ይህ እውነት ነው ደግሞም እየሆነ ነው ፡፡ ዛሬ ማታ ወደ ቤታችሁ የሚመጣ እንግዳ ቢኖር አትዘጋጁምን ? የክርስቶስ ዳግም ምጽዓትም እንዲሁ ነው ፡፡ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ !
እንዴት ነው ተዘጋጅታችሁ የምትኖሩት ? እግዚአብሔር አንዳችሁ ለሌላችሁ በጎ የሆነውን ማድረግን ትከተሉ ዘንድ ይሻል ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቃድ ለእናንተ ሁልጊዜ ደስ እንድላችሁ ፤ ሳታቋርጡ እንድትጸልዩና በነገር ሁሉ እንድታመሰግኑ ነው ፡፡ ለክርስቶስ መምጣት ራሳችሁን ስታዘጋጁ በእነዚህ ነገሮች ላይ አትኩሩ ፡- ደስ መሰኘት ፣ መጸለይና ማመስገን ፡፡ በየቀኑ ይህንን በማድረግ ለመጽዓቱ ትዘጋጃላችሁ ሌሎችም የክርስቶስን ብርሃን በእናንተ ውስጥ ያያሉ ፡፡ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ !
“ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና ። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም ፤ እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ ። የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና ፤ እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር ፡፡ “
- 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡5-8
ተጨማሪ ጥቅስ
ማቴዎስ 24:27 — “ መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና “
ሮሜ 13:12 — “ ሌሊቱ አልፎአል ፥ ቀኑም ቀርቦአል ። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ ። “
1ኛ ተሰሎንቄ 5:16–18 — “ ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።