Paul's Letters 1 Thessalonians

Call To Sanctification And Comfort Of Christ's Coming

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Lord 1 Thessalonians 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 555 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የሆኑ ሰዎችን በማጣታችሁ በምታዝኑ ጊዜ የት እንዳሉ ለማወቅ ትፈልጋላችሁ ፡፡ በጌታ እየተመላለሳችሁ ከሆነ 1 ተሰሎንቄ 4 በኃዘን ሂደት ዉስጥ ተስፋ ማግኘት ስለምትችሉ እንደ ቀብር ስነስርዓት ምዕራፍ የሚታይ ነው ፡፡ በ 1ተሰሎንቄ 3 ጳዉሎስ በተሰሎንቄ አማኞችን ለማፅናናት ጢሞቲዎስን ላከላቸዉ ምክንያቱም እየተሰደዱ/መከራ እየደረሰባቸዉ ስለ ነበር ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ለሚመጣዉ ጌታ የተዘጋጁ እንዲሆኑ ማሳሰቡን ይቀጥላል ፡፡ ዛሬ በሚመጣ ጊዜ ምን ሊመስል እንደሚችል እናወራለን ፡፡

ትምህርት

1-ተሰሎንቄ (4፡ 1-8)፡ ጳዉሎስ ተሰሎንቄያዊያን በቅድስና እንዲመላለሱ ፈለገ ፤ በጌታ በኢየሱስ በጳዉሎስ በኩል ለእነርሱ የተሰጣቸዉን ትዕዛዞች በመከተል እግዚአብሄርን ያስደስቱታል (ቁጥር 1-2) ፡፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ ትዕዛዝ “ የሚለዉ ቃል “ ከላይ ሰራተኛ የሚወርድን ትዕዛዝ “ የሚያመለክት ሚሊታርይ ቃል ነበር ፡፡ በቅድስና ለመመላለስ እግዚአብሄር እንድናደርግ የጠየቀንን ማድረግ አለብን ፡፡ ታላቁ ተልዕኮ ስለ እርሱ ማዉራት ማለት ሳይሆን ስለ ተልእኮዉ ስዕልን ማስቀመጥ፣ የራዕይ ንግግር መፃፍ ወይም የተልዕኮ ንግግራችሁን መቀየር ማለት ነው፡፡ በሚገባ እናደርገዋለን ፡፡

ቀጥሎም ጳዉሎስ የተለዩ/ዝርዝር ትዕዛዞችን ሰጠ ፡፡ ተሰሎንቄ ብዙ ልማድ/ባህል ያላቸዉ ብዙ ሰዎች በዉስጧ የሚያልፉባት ከተማ እና የወሲባዉ ስርዓት አልበኝነት የነበረባት ከተማ ነበረች ፡፡ ጳዉሎስ “ ከወሲባዉ ስርዓት አልበኝነት ስለሚታቀቡ/ስለሚቀደሱ “ (ቁጥር 3) እግዚአብሄርን የሚያስደስት ንፁህነትማድረገ ይችላሉ ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄርን በማያዉቁት በአሕዛብ የዝሙት ምኞት ከመሳተፍ ይልቅ ሰዉነታቸዉን እንዲገዙ ጠራቸው (ቁጥር 4-5) ፡፡ በቅድስና በምንመላለስ ጊዜ እግዚአብሄርን ለማስደሰት፣ እግዚአብሄርን ለመታዘዝ እና ለእግዚአብሄር ክብርን ለማምጣት አድርጉት ፤ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ልጆቹ ኃጢዓት ሲያደርጉ እንደሚቀጣ አሳሰባቸው (ቁጥር 6) ፡፡ እግዚአብሄር አማኞችን ለቅድስና ስለጠራቸው ይህን ትዕዛዝ የማይቀበሉ እግዚአብሄርን አይቀበሉም (ቁጥር 7-8) ፡፡ ቅድስና/መቀደስ የተቀደሰ ለመሆን ወይም ቅዱስ ለመሆን ያለ ሂደት ነው ፤ ያ ሊሆንበት የሚችለዉ ብቸኛዉ መንገድ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባደረገዉ ስራ ብቻ ነው - ያ ስራ የነፃን፣ ይቅርታ የተደረገልን እና ነፃ የወጣን እንድንሆን ይፈቅድልናል - የቀድሞዉን ኃጢዓት ስላስወገደው ወደ ንፁህ ገበታ መምጣት እንችላለን ፡፡ ቅድስና ማለት የተለዬ መሆን ማለት ነው ፤ መቀደስ፣ ቅድስና ፅድቅ ሁሉም ተመሳሳይ ዋና መርሆች ናቸው ፡፡ እግዚአብሄር ቀድሞ በምናደርጋቸዉ ነገሮች እንድንመላለስ አልጠራንም ፤ የተለዮን በመሆን በክርስቶስ አዲስ እንድንሆን ጠርቶናል ፡፡ ጴጥሮስ “ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ “ (1ጴጥ 1፡ 15) በማለት ፅፏል ፡፡ ከአለም የተለዬን በመሆን በብርኃን መመላለስ ያስፈልገናል ፡፡

1-ተሰሎንቄ (4፡ 9-10)፡ ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን በስምምነት/በመዋሀድ እንዲመላለሱ ፈለገ ፡፡ ጳዉሎስ በተሰሎንቄ እና በመላዉ መቄዶኒያ አካባቢ ስለ ሌሎች ስላላቸዉ የፍቅር እንክብካቤ መልካም ነገሮች ሰማ (ቁጥር 9-10) ፤ ከዚህ የበለጠ እንዲሰሩም አበረታታቸው ፡፡ ስለ ፍቅር አራት ቃላቶች አሉ፡ ለወሲብ የሚያነሳሳ አካላዉ የፍቅር አይነት ኢሮስ፣ ቤተሰቦች ለልጆቻቸዉ እንዳላቸዉ ፍቅር አይነት የሆነ ቤተሰባዊ ፍቅር ስቶርጋ፣ “ በጓደኝነት እና በትዳር ዉስጥ ያለ ጥልቅ ፍቅር የሆነው “ ፊሊያ እና “ እግዚአብሄር ለእኛ ያሳየዉ ፍቅር አጋፔ ፤ በስሜት ላይ የተመሰረተ ፍቅር አይደለም፣ በራሳችን ፍላጎት የተገለፀ ነው ፡፡ አጋፔ ፍቅር እግዚአብሄር እኛን እንዳየበት ሌሎችን ይመለከታል “ ፡፡

1-ተሰሎንቄ (4፡ 11-12)፡ ጳዉሎስ ተሰሎንቄያዊያን በታማኝነት እንዲመላለሱ ፈለገ ፤ ኮንስታብል ፀጥ ያለ ህይወት በመኖር ሌሎችን አትረብሹም፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ በማዘንበል የሌላ ሰዉ ስራን አትረብሹም እንዲሁም ለራሳችሁ ቤተሰብ በመመገብ ለሌሎች ሸክም አትሆኑም ፡፡

1-ተሰሎንቄ (4፡ 13-18)፡ የሚመጣዉን ጌታ ተስፋ እያደረግን ከሆነ የተዘጋጀን መሆን አለብን ፡፡ ቤታችን በስርዓት መሆን አለበት ፡፡ ስለ ዳግም ምፅዓት በምናወራ ጊዜ ኢየሱስ መቼ እንደሚመጣ ማንም አያዉቅም ፡፡ ሰዎች ተመልሶ መምጣቱን ገምተዋል ፤ ሰዎች ተመልሶ ስለ መምጣቱ ተንብየዋል ፤ ነገር ግን ማንም ሰዉ መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ ስለማያውቅ ማድረግ የምንችለዉ ምርጥ ነገር በእምነታችን በመመላለስ ሁልጊዜ የተዘጋጀን መሆን ነው ፡፡

እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ በቁጥር 13 እና 15 መገለጥ አለን፣ የእግዚአብሄር እዉነት አለን ፡፡ የእግዚአብሄር እዉነት ስላለን ተስፋ አለን ፡፡ “ ያንቀላፉት “ የሚለዉ ሀረግ የሞቱትን ያመለክታል ፡፡ በምላሹም ጳዉሎስ ቀጥታ ከጌታ የመጣዉን ለተሰሎንቄያዊያን እንደገለጠ ተናገረ (ቁጥር 15) ፡፡ ጳዉሎስ ክርስቶስ ተመልሶ እንደ ገና እንደሚመጣ አብራራ ፤ በተግባር በሰማይ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ እንደሆነ እየተናገረ ነው ፡፡ ጳዉሎስ ኢየሱስ የሞቱትን ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋል ሲል በኢየሱስ ያመኑት እና የሞቱት አሁን ከእርሱ ጋር እንደሆኑ እየገለፀ ነው (ቁጥር 14) ፡፡ ስለዚህ የሞቱትን አማኞች እንደ ገና ለማየት ተስፋ ሊኖረን ይችላል ፤ ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ህያዋን የሆኑ በሞቱት ላይ ምንም የተሸል እድልን አይኖራቸውም (ቁጥር 15) ፡፡ ሁላችንም ከጌታ ጋር የምንሆን ከሆነ ጊዜዉ ችግር/ልዩነት የለዉም ፡፡ መገለጡ ክርስቶስ እንደ ገና ተመልሶ እንደሚመጣ ነው ፡፡ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ ከእኛ በፊት የሞቱትን ይዞአቸዉ ይመጣል ፤ የሞቱትን ያስነሳቸዋል ፡፡ ይህ ፅሁፍ እምነታቸዉን በኢየሱስ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ ላይ በማስቀመጥ የሞቱትን እንደ ገና እንደምናያቸዉ ተስፋን ስለሚሰጠን በቀብር ስነስርዓት ላይ ጥቅም ላይ የዋለ ነው ፡፡ መቼ እንደ ሆነ አናዉቅም ፡፡

ጌታ በሰዎስት ድምፅ ከሰማይ ይወርዳል (ቁጥር 16) ፤ በጩኸት ይወርዳል ፤ ምን ማለት እንደሆነ አናዉቅም ሁሉም ሰዉ እንደሚሰማዉ ግን መገመት እንችላለን ፡፡ በመለዓክት ድምፅ/መለከት ይወርዳል እንሰማዋለንም ፡፡ ብዙ ጊዜ ለጦርነት የሆነ ድምፅ የመለከት ድምፅ ይኖራል ፤ ዉጊያዉ መጥቷል የተዘጋጀን መሆን የተሻለ ነበር ፡፡

በመቀጠልም ምፅዓቱን እናያለን ፤ በህይወት ያሉ አማኞች ከሞቱት ጋር በአንድ ላይ በመሆን ጌታን በአየር ለመገናኘት በደመና ላይ እንነጠቃለን (ቁጥር 17) ፡፡ ዳግም ምፃት የሚለዉ ቃል ብዙ ሰዎችን አስደንግጧል ፤ ስለ ዳግም ምፅዓት የተፃፉ መፅኀፍቶች አሉን ፡፡ ቃሉ ለመያዝ ወይም ለመሸከም መነጠቅ ማለት ነው ፤ ዶር. ኬኔንዝዉስቴ ለዚህ ቃል የተለያዩ ትርጎሞችን ይገልፃል ፤ ልክ ኢትዮጲያዊዉን ወደ ክርስቶስ ከመራዉ በኋላ ፊልጶስን መንፈስ እንዳንቀሳቀሰው “ በፍጥነት ሌላ ጋር መወሰድ “ ሊሆን ይችላል ፤ ምናልባትም ሰይጣን ከምድር ሊያጠፋን እንደሚጠብቀው የሚያመለክተው “ በጉልበት/በኃይል መንጠቅ “ ሊሆን ይችላል ፡፡ ክርስቶስ ሙሽራዉን እንደሚወስደው “ ለራስ መዉሰድ “ ማለት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሌሎቹ ትርጉሞች “ ወደ አዲስ ስፍራ መጓዝ “ ወይም “ ከአደጋ መታደግ “ ማለት ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህ የመጨረሻውን አመለካከት የሚወስዱ ይህንን ጥቅስ አማኞች ከመከራዉ በፊት እንደሚወሰዱ ይጠቀሙበታል ፡፡

ክርስቲያን አማኞች ለዘላለም ከጌታ ጋር ይሆናል ፡፡ የሚመጣዉ ጌታ ሁሉም አማኞች የሞቱትም በህይወትም ያሉትም በሚመጣበት ጊዜ በአንድ ላይ እንዲሆኑ ይፈቅድላቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

ክርስቶስ በማንኛዉም በተሰጠዉ ክስተት ስለሚመጣ የተዘጋጃችሁ ሁኑ ፡፡ ይህ ዳግም ምፃት መቼ ይሆናል ? ይህ ከሰባቱ የመከራ አመታት በፊት ይሆናል፣ ከሰዎስት አመት ከግማሽ በመካከል ላይ ይሆናልንስ፣ ከሰባቱ አመት መከራ በኋላ ይሆናልን ? መቼም ቢሆን ችግር የለዉም ፡፡ አመለካከታችን ምንም ቢሆን ያለ ጥበቃ የተጠበቅን አንሆንም ፤ አመለካከታችን ክርስቶስ ተመልሶ እንደሚመጣ እና የተዘጋጀን መሆን እንዳለብን መሆን አለበት ፡፡ በቅድስና፣ በስምምነት እና በታማኝነት እንጓዝ ምክንያቱም ልጆቹ እርሱን ይመስሉ እንደሆነ መለየት ስለሚችል ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 717.

  2. Wiersbe, p. 717.

  3. Wiersbe, p. 718.

  4. Wiersbe, p. 718.

  5. Wiersbe, p. 19.

  6. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: 1 Thessalonians, p. 46-47; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/1thessalonians.pdf.

  7. Wiersbe, p. 720.

  8. Wiersbe, p. 721.

  9. Wiersbe, p. 721.

  10. Wiersbe, p. 722.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ተሰ (4፡ 3) ጳዉሎስ ተሰሎንቄያዊያንን ከክፉ/መጥፎ ወሲባዊ ነገር የታቀቡ/የተቀደሱ እንዲሆኑ ለምን እንደ ነገራቸዉ ምን ታስባላችሁ ? በመፅሀፍ መሰረት የወሲብ ኃጢዓት ከሌሎች ኃጢዓቶች እንደሚበልጥ ታስባላችሁ ( 1ቆሮ 6፡ 13, 18-19, ገላ 5፡ 17) ? ለምን ወይስ ለምን አይበልጥም ?
  2. በ 1ተሰ (4፡ 9-10) ጳዉሎስ ባለዉ መሰረት የተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን በሚገባ እርስ በእርስ ይዋደዳሉ ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ይህን ታዩታላችሁ ?
  3. 1 ተሰ (4፡ 16-17) አንብቡ ፤ ጳዉሎስ ይህን እንዴት እንዳወቀዉ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በ 1 ተሰሎንቄ 4 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Thessalonians 4:3–5

“For this is God’s will, your sanctification: that you abstain from sexual immorality, so that each of you knows how to control his own body in sanctification and honor, not with lustful desires, like the Gentiles who don’t know God.”

ጳውሎስ ለቤተክርሰቲያን አጥብቆ ስለተጨነቀ እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት በቅድስና ይመላለሱ ዘንድ መከራቸው ፡፡ ጳውሎስ ይህን ምክር የመከራቸው ኢየሱስ ተመልሶ ለሚመጣበት ለዚያ ቀን ቤተክርስቲያኑዋ ተዘጋጅታ ትኖር ዘንድ በመናፈቅ ነው ፡፡

ዛሬም እንዲሁ ነው ! ለኢየሱስ ዳግም ምጽአት ተዘጋጅታችሁ እየኖራችሁ ነው ? እንደ አማኝ እግዚአብሔር የጠራችሁ በቅድስና ህይወት በእርሱ ውስጥ እንድታድጉ ነው ፡፡ እንደ አማኝ እናንተ ተለይታችኋል ፣ ጸድቃችኋል ፣ ተቀድሳችኋል ፣ ይቅርታን አግኝታችኋል ደግሞም ኃጢአታችሁ ተሰርዮላችኋል ፡፡ ሆኖም ግን እንደ ክርስቶስ ደቀመዝሙር ፈተና በመንገዳችሁ ይመጣል ፡፡ ልክ በጳውሎስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ዝሙትና ፍትወት ፈተና ነው ፡፡ አሁንም እርኩሰትን እንድትቃወሙና ከዚህ እንድትሸሹ ፤ ጸንታችሁ እንድትቆሙና በክርስቶስ ወደ ማደግ እንድትሮጡ ተጠርታችኋል ፡፡ በስጋ ነገር አትጠመዱ ፡፡ በጊዜያዊ ደስታ አትጠመዱ ፡፡ ከዝሙት ራቁ ፡፡ ተቀደሱ ፡፡ ለህይወታችሁ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነው ፡፡ ይህን እያደረጋችሁ ለክርስቶስ ምጽአት ትዘጋጃላችሁ ፡፡ ዛሬ ከእርኩሰት ራሳችሁን በመጠበቅ ለመንግስቱ ስራ ግድ ስጡ ፡፡ ምጽአቱ ቀርቧል ፡፡ ተዘጋጁ ፡፡

“ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና ፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ ፡፡ “

  • 1ኛ ተሰሎንቄ 3፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

ሉቃስ 12:40 — “ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና ። “

1ኛ ተሰሎንቄ 4:7 — “ ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና ። “

1ኛ ተሰሎንቄ 4:15–17 — “ በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም ፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን ። “