Paul's Letters 1 Thessalonians

Encouraging And Praying For The Church

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Lord 1 Thessalonians 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 554 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የጳዉሎስ አንዱ ተግባር በከተሞች ዉስጥ በሚገባ በማፍሰስ/በማስተማር ህዝቡ የተጠበቁ እና በቃሉ ስር እንደሰደዱ እርግጠኛ ማድረግ ነበር ፡፡ በተሰሎንቄ ያሉ ሰዎች ጥንቃቄ ስለማድረጋቸዉ እርግጠኛ ለመሆን ጳዉሎስ እንዲረዳቸዉ ጢሞቲዎስን ላከላቸው ፡፡ በዚህ መፅሀፍ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች ዉስጥ ጳዉሎስ እንዴት ቤተ ክርስታኗ እንደ ተወለደች/እንደ ተመሰረተች እና እንዴት አድገዉ እንደነበር ገልፆአል ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ስለ ደረሱበት ብስለት ያወራል ፤ ለዚህ መፅሀፍ ቃላችን ከ 1ተሰ (4፡ 16-17) የመጣው የሚመጣው ጌታ የሚል ነው ፡፡ ጳዉሎስ የዚህ የአማኞች ቡድን ለክርስቶስ መልሶ መምጣት የተዘጋጁ ስለ መሆናቸዉ እርግጠኛ መሆን ፈለገ ፡፡

ትምህርት

1-ተሰሎንቄ (3፡ 1-2)፡ ጳዉሎስ ጢሞቲዎስን በተሰሎንቄ ያሉትን አማኞች እንዲያጠነክር እና እንዲያበረታታቸው ላከው (ቁጥር 1-2) ፡፡ እርስ በእርስ መተያየት በምትችሉበት ስፍራ በአካል ፊት ለፊት ከሚደረግ ደቀ መዝሙርነት የተሻለ ነገር የለም ፡፡ ጳዉሎስ መመለስ ስላልቻለ ለመስራት የማይፈራዉን የህብረቱ ሰራተኛ፣ አማኝ፣ አገልጋይ እና ዳቆን የነበረውን ጢሞቲዎስን ላከላቸው ፡፡ ለሚመጣዉ ጌታ ስንዘጋጅ ያስተማርናቸዉን ሰዎች ልናጠነክራቸዉ እና ልናበረታቸዉ ይገባናል ፡፡ ጳዉሎስ በእምነታቸዉ እንዲያድጉ እንዲረዳቸዉ ጢሞቲዎስን - በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ በመጀመሪያዎቹ አስር ጥቅሶች ዉስጥ የሚጠቅሳቸዉን ፡፡ በእምነት የማደግ አስፈላጊነት ምንድን ነው ?

1-ተሰሎንቄ (3፡ 3፡ 3-5)፡ ጳዉሎስ በእምነታቸዉ እንዲያድጉ እና “ በእነዚህ መከራዎ/ስደቶች የማይናወጡ እንዲሆኑ ፈለገ “ (ቁጥር 3) ፡፡ “ ለዚህ ተመርጠናል “ በማለት ጳዉሎስ እግዚአብሄር ተከታዮቹ መከራን እንደሚቀበሉ እንደሚያውቅ አመለከተ ፡፡ በመከራና በችግር ጊዜ ዉስጥ በምናልፍ ጊዜ ሊያጠራን እና ሊያጠነክረን ነው ፤ እንደ ማክአርቱር ገለፃ “ ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን ስለዚህ መለኮታዊ ምርጫ ስላስታወሳቸው፡ 1) የእግዚአብሄር እቅድ በጳዉሎስ መከራዎች እንደ ማስረጃነት እንደማይሰራ ወይም 2) የጳዉሎስ ፍቅር በእርሱ የእግዚአብሄርን ደስ አለመሰኘት ያሳያል “ ፡፡ ኢየሱስ በዚህ ዉስጥ ከሄደ ጳዉሎስም በዚህ ዉስጥ ከሄደ ለምን ተሰሎንቄያዊያን የተለዬ ይሆናሉ ? በማቴ (5፡ 10-12) ኢየሱስ “ ስለ ፅድቅየሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው….. በእኔ ምክንያት ሲነቅፋአችሁና ሲያሳድዳችሁ ብፁዓን ናችሁ…. ፤ ….ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትም እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና “ አለ ፡፡ ጳዉሎስ በጠንካራ ጊዜ ሲያልፉ ክንዱን በዙሪያቸዉ ለማስቀመጥ ጢሞቲዎስን ስለላከላቸው በዚህ ሂደት ዉስጥ የጠነከሩ ይሆናሉ ፡፡ በዚያ እንደ ነበር ጳዉሎስ መከራ/ስደት እንደሚመጣ አስጠንቅቋቸዋል (ቁጥር 4) ፤ አሁን “ ፈታኝ ምናልባት ፈትኞአቸዋል ድካማችንም ከንቱ ሆኖአል ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ “ (ቁጥር 5) ጢሞቲዎስን ላከ ፡፡

1-ተሰሎንቄ (3፡ 6-8)፡ ጳዉሎስ ረዳት ላከላቸዉ ምክንያቱም ስለ መከራዉ እና ስለስደቱ ፈርቶ ስለ ነበርና ይመለሳሉ/ከጌታ መንገድ ዞር ይላሉ በማለት እየፈራ ስለ ነበር ፡፡ ጢሞቲዎስ ወደ ጳዉሎስ በመልካም ዜናዎች ተመለሰ፡ እምነታቸዉ እና ፍቅራቸው ጠንካራ እንደ ነበር፣ ስለ ጳዉሎስ መልካም ትዉስታ እንደ ነበራቸዉ እና እንደገና ሊያዩት እንደሚፈልጉ (ቁጥር 6) ፡፡ ጳዉሎስ በጌታ ፀንቶ እንዲቆሙ እያበረታታቸዉ ነበር (ቁጥር 7-8) ፡፡ ማክአርቱር “ እዚህ ጋር አንድ ሰራዊት በጠላት የተጠቃ ቢሆንም እንኳን ማፈግፈግን እንደማይቀበል ስሏል “ አለ ፡፡ ጳዉሎስ ይህን መልዕክት በእነርሱ ደስተኛ እንደ ነበር ላከላቸው ፡፡ ዋይርስቤ ይህ መልዕክት “ የእግዚአብሄር ቃል እኛን የሚመግበን ምግብ እንደሆነ (ማቴ 4፡ 4), እኛን ለመምራት ብርኃን እንደ ሆነ (መዝ 119፡ 105) እና እኛን ለመከላከል መሳሪያ እንደሆነ ያሳያል (ኤፌ 6፡ 17) “ አለ ፡፡

1-ተሰሎንቄ (3፡ 9-13)፡ ጳዉሎስ ረዳትን ብቻ እና መልዕክቱን ብቻ አላከላቸዉም ነገር ግን ጳዉሎስ ስለ እነርሱም ፀለዬ ፤ ጳዉሎስ በእነርሱ ባየዉ ለዉጥ ደስተኛ ነበር (ቁጥር 9) እና በይበልጥ እንደ ገና ብዙ ለማስተማር እንዲያያቸዉ ቀን እና ሌሊት ፀለዬ (ቁጥር 10) ፡፡ ጳዉሎስ እየተቻቸዉ ነበር፣ በኑሮአቸዉ የእግዚአብሄር ሙሉነት እንዲቀምሱ ፈለጋቸው ፡፡ ጳዉሎስ በደንብ እነርሱን በመዉደድ በሁሉን ቻይ አምላኪ ፊት በመሄድ ፍቅራቸው እንዲበዛ ፀለዬ ተሰሎንቃዊያን ላይ ፈጣን ተፅዕኖ እንዲያመጡ እና በስፍራው ወደ ሌላ ከተሞች እንዲስፋፋ በተጨማሪም ለሁሉም (ቁጥር 11-12) ፡፡ ጳዉሎስ እግዚአብሄር ልባቸዉን “ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ “ (ቁጥር 13) ፤ በፀሎቱ ጳዉሎስ “ ኢየሱስ ስለሚመጣ ልባችሁን የተዘጋጀ እንዲሆን እፈልጋለሁ ፤ በቅድስና እንድትኖሩ እፈልጋለሁ ስለዚህም እርሱን ታንፀባርቃላችሁ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያ ሊሆን የሚችልበት ብቸኛዉ መንገድ በህይወታችሁ ለዚያ ነገር ስፀልይ ነው “ አለ ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ ተመልሶ ስለሚመጣ ጳዉሎስ የተዘጋጁ እንዲሆኑ ፈለገ ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 1754.

  2. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: New Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1989), pp. 714-715.

  3. MacArthur, p. 1754.

  4. Wiersbe, p. 715.

  5. Wiersbe, p. 715.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ተሰሎንቄ 3 ጳዉሎስ እሱና የእርሱ የጉዞ አጋሮቹ ስለ እምነታቸዉ ደርሶባቸዉ ስለ ነበረዉ መከራ አዉርቷል ፤ ጳዉሎስ ስለ ወንጌል እንደደረሰበት መከራ አይነት ለመቀበል ፈቃደኞች እንሆናለን ብለን ታስባላችሁ ? ጳዉሎስ ምን ያክል በሆነ ነገር ዉስጥ እንዳለፈ አሰላስሉት
  2. ለቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ፍቅር ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ያለዉን ፍቅር እንዴት ታወዳድሩታላችሁ ? ከራስ ያለፈ እዉነተኛ ፍቅር ነው ? አይደለም ከሆነ ያን እንዴት ልትቀይሩት ትችላላችሁ ?
  3. 1ተሰ (3፡ 13) “ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸናል “ ይላል ፤ ልባችሁን ያለነቀፋ እንዴት ታደርጉታላችሁ ?
  4. በ 1-ተሰሎንቄ በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Thessalonians 3:6–7

“But now Timothy has come to us from you and brought us good news about your faith and love and reported that you always have good memories of us, wanting to see us, as we also want to see you. Therefore, brothers, in all our distress and persecution, we were encouraged about you through your faith.”

ጳውሎስና ሲላስ ተሰሎንቄ ስላሉት አማኞችና ስለ እምነታቸው ተጨንቀው ያጸናቸውና ይመክራቸው ዘንድ ጢሞቲዎስን ልከውት ነበር ፡፡ ጢሞቲዎስም በስደት ውስጥ እንኳ ሳሉ ስለነበራቸው ብርቱ እምነት የምስራች ይዞ ተመለሰ ፡፡ ጳውሎስም ስለ እነርሱ መጸለዩን ቀጠለ ደግሞም በጌታ ጸንተው ይቆሙ ዘንድ መከራቸው ፡፡

እንደ አማኝ የምክር ቃልን መናገር አስፈላጊ ነው ፡፡ ወንጌላዊን ፣ መጋቢን ፣ የትዳር አጋርን ፣ ልጅን ፣ ጓደኛን ወይም የስራ ባልደረባን ለመምከር ለማበረታታት ምን ያህል ፕሮግራም ትይዛላችሁ ? ምክር ለእንድ ሰው ነፍስ ህይወትን ይሰጣል ፡፡ እንደ አማን ጸንታችሁ ቁሙ ለሌሎችም ህይወትን ፣ ተስፋን ደግሞም ምክርን ተናገሩ ፡፡ ዛሬ ጌታ ወደ ልባችሁ ያመጣውን ሰው ለመምከርና ስለ እርሱ ለመጸለይ ጊዜ ውሰዱ ፡፡ ደውሉላቸው ወይም መልዕክት ጻፉላቸው ፡፡ እንደ ምሳሌ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች የጸለየውን ጸሎት ተመልከቱ ፡- “ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም ። “ በማለት ስማቸውን በመጥቀስ ጸልዩላቸው ፡፡

“ አሁን ግን ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ወደ እኛ መጥቶ ስለ እምነታችሁና ስለ ፍቅራችሁ የምስራች ብሎ በነገረን ጊዜ፥ እኛም እናያችሁ ዘንድ እንደምንናፍቅ ታዩን ዘንድ እየናፈቃችሁ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስቡን በነገረን ጊዜ ፥ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በእምነታችሁ በኩል በችግራችንና በመከራችን ሁሉ ስለ እናንተ ተጽናናን ፡፡ “

  • 1ኛ ተሰሎንቄ 3፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

1ኛ ተሰሎንቄ 3:12–13 — “ ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ይጨምርም ። “

ዕብራውያን 3:13 — “ ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ ፡፡ “

ዕብራውያን 10:24–25 — “ ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ ፤ በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ ። “