Paul's Letters 1 Thessalonians
Paul Modeled Discipleship
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Coming Lord 1 Thessalonians 2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በተሰሎንቄ ያለችዉ ቤተ ክርስቲያን ገና ያልጠነከረች ስለ ነበረች ጳዉሎስ ወደ እነርሱ ጋር በመምጣት እንዲያድጉ ሊረዳቸዉ ፈለገ ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ጳዉሎስ በዉጣ ዉረድ ዉስጥ ስለ ተግቶ መስራት ያወራቸዋል ፡፡ በምዕራፍ 1 ጳዉሎስ እንደ አንድ ወንጌል ሰባኪ ወደ ቤተ ክርስታኗ መጣ ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ ጳዉሎስለሚመጣዉ ጌታ የሚያዘጋጃቸዉ እረኛ እንደሆነ ራሱን ይገልጣል ፡፡
ትምህርት
1-ተሰሎንቄ (2፡ 1-6)፡ ዋረን ዋይርስቤ ጳዉሎስ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ራሱን እንደ ታማኝ ባለ አደራ ገለፀ ብሏል፡፡ በግልፅ ወደተሰሎንቄ የመምጣት የጳዉሎስ ፍላጎት ጳዉሎስ ከተማዋን ለቆ ከሄደ በኋላ ምናልባትም በአይሁዶች እና አምላክ በሌላቸዉ አሕዛቦች የሆነን ለመጠየቅ እና ለመሞገት ነበር ፡፡ ጳዉሎስ ጉብኝቱ ከንቱ እንዳልነበር በመናገር ምላሽ ሰጠ (ቁጥር 1) ፡፡ ምንም እንኳን ጳዉሎስ በፊልጵስዮስ አስደንጋጭ ችግር ቢደርስበትም በተሰሎንቄ ወንጌልን በድፍረት ሰበከ (ቁጥር 2) ፤ ይህ የሚያናድድ ድርጊት በሐዋ (16፡ 22-24) የተገለፀ ነበር ፡፡ የጳዉሎስ ምክር ( ተግሳፅ እና ማበረታታት) ለዚች ቤተ ክርስቲያን የማፅናነት እና የሚያጠነክር መገኘት ነበር (ቁጥር 3) ፡፡ ጳዉሎስ ከስህተቱ (ሰዉን ወደ ሚያሳስት መንገድ ከሚመራ ነገር ማለት ነው) ወይም ከርኩሰት (ሞራሊ ተገቢ ካልሆነ ነገር ወይም በማይሆን ጉጉት ወይም በተሳሳተ ፍላጎት ማለት ነው) ወይም ደግሞ ከተንኮል (ይህ ቃል ማባበልን ልክ አሳን ለመያዝ እንደ ሚደረግ ማባበል ወይም መሸወድ ማለት ነው ) አልተናገረም ፡፡
ጳዉሎስ እነዚህ ሁሉ መጀመሪያ “ በወንጌል አደራ የተቀበለ ለመሆን በእግዚአብሄር እንደተረጋገጠ “ ተናገረ (ቁጥር 4) ፤ “ ተረጋገጠ “ ማለት ነገሮችን በሚገባ ትክክል ናቸዉ ወይም አይደሉም ብሎ ለማየት የተመረመረ፣ የተፈተነ ወይም ደግሞአጥብቆ የሚመረምር የሚል ዶኪማዞ የሚል የግሪክ ቃል ነው ፡፡ ጳዉሎስ ከደረሰበት ነገር የተነሳ እንደተረጋገጠ፣ ፈተናዉን አልፎ እንደ ነበር እና በወንጌል አደራን ለመቀበል የበቃ እንደ ነበር ተሰምቶታል ፡፡ እንደ ክርስቶስ ተከታዮች በወንጌል አደራ የተቀበልን እና ይህን መልዕክት ወደፊት ለመሸከም ተረጋግጦልናል/ተመርጠናል ፡፡ በ 2ቆሮ (5፡ 17-21) ጳዉሎስ አማኞች የማስታረቅን መልዕክት ለአለም ለማድረስ የክርስቶስ አምባሳደሮች የሆኑ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረቶች ናቸዉ ብሏል ፡፡ ጳዉሎስ ለራሱ ተከታዮችን ለማግኘት ሰዎችን ለማስደሰት የሽንገላ ንግግርን በመጠቀመ ወንጌልን አልሰበከም (ቁጥር 5) ፤ እግዚአብሄር ልብን እንደሚመረምር ያውቃል ፡፡ ለጳዉሎስ የሚያስጨንቀዉ ብቸኛዉ ነገር ጌታን ማስደሰት ነበር ፤ ከአንደበቱ የሚወጣዉ ቃል እዉነት እንዲሆን ፈለገ እንጂ ሰዎች እንዴት አድርገዉ ለሚመልሱለት አልተጨነቀም ፡፡ ንጉስ ዳዊትም በመዝ (12፡ 2) እንደገለፀው የሽንገላ ኃጢዓትን ይጠላል፡ “ እርስ በእርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነዉ ይናገራሉ “ ፡፡ በ 2ጢሞ (4፡ 3-4) ጳዉሎስ ጢሞቲዎስን “ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል…… እዉነትንም ከመስማት ጆሮቻቸዉን ይመልሳሉ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ “ በማለት አስጠነቀቀው ፡፡ ጴጥሮስ አማኞችን ኢየሱስን በመካድ ራሳቸዉን በአሳች ቃላት ከሚስቡ ኃሰተኛ አስተማሪዎች እንዲጠነቀቁ ያስጠነቅቃቸዋል ( 2ጴጥ 2፡ 1-3) ፡፡ ጳዉሎስም ልክ እንደ ኢየሱስ በእዉነት ወደፊት በመቀጠል ያን እዉነት ለመከተል እንደሚፈልጉ ወይም ላለመከተል እንዲወስኑ ለሰዎቹ ተወላቸዉ/ፈቀደላቸው ፡፡ መመኘት የሚለዉ ቃል ብዙ እንዲኖር የስስት ፍላጎት ማለት ነው ፡፡
1-ተሰሎንቄ (2፡ 7-8)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ዉስጥ ጳዉሎስ ራሱን የምታፈቅር እናት ባህሪይ እንዳለዉ በማድረግ ያቀርባል ፡፡ በመሰረቱ ጳዉሎስ የደቀ መዝሙርነትን ሞደል ሆኗል ፤ ወንጌልን ወደ እነርሱ በማምጣት በኑሮአቸዉ ላይ ብዙ ነገርን አስተምሯል/ አድርጓል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አንድ ሞግዚት ባለሙያ ለአንድ ህፃን በአካል የሚያስፈልገዉን እንዴት መስጠት እንዳለባት እንደምታዉቅ አንድ እናት በእናታዊ ፍቅር ልጇን እንደምትንከባከበው ፤ ጳዉሎስ የፍቅሩን ልክ፡ አስፈላጊ ከሆነ ህይወቱንም ለእነርሱ አሳልፎ እንደሚሰጣቸዉ አብራራ “ ይላል ፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ፈተና ነው፡ ላልጠነከሩ/ለአዲስ አማኞች በዚያ ልክ እንጠነቀቃለን/እናስባለን ? ምንም ነገር ቢወስድ ኑሮአችንን ወደ እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ፍቃደኞች እንሆናለን ? ዋይርስቤ “ በክርስቶስ ህፃናት የሆኑ እንደ ሚከባከባቸው የመዉደድ ፍቅር እንክብካቤዉን ይሰማቸዋል “ አለ ፡፡ ህፃን ልጅን ለመንከባከብ/ለማሳደግ ጉልበትን እና ጊዜን ይወስዳል፣ ጳዉሎስም በእነርሱ ታላቅ ትዕግስት አሳዬ ፡፡
1-ተሰሎንቄ (2፡ 9-12)፡ በተጨማሪም ጳዉሎስ ራሱን እንደሚያስብ/እንደሚጨነቅ አባት አሳይቷል ፡፡ ጳዉሎስ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እንደ ነበረው (1ቆሮ 4፡ 15-16) ለዚች ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት ነበር ፤ ጳዉሎስ ለዚች የቀደመች ቤተ ክርስቲያን የአባት ልብ እንደሚመስለዉ /እንደሚሆነዉ ሞደል ሆኗል ፡፡ ጳዉሎስ ቀን እና ሌሊት በመድከም ስለሰራ ከእነርሱ ጋር ወንጌልን ሲጋራ/ሲነጋገር በእነርሱ ላይ ሸክም አይሆንባቸዉም (ቁጥር 9) ፡፡ የጳዉሎስ ስራ እንደ አባት ምሳሌ የሚሆን ነበር ፤ በዕብ (12፡ 14) ከሁሉም ጋር በሰላም ለመኖር ሁሉንም ጥረት እንድናደርግ ተነግሮናል ፡፡ በ 2ጴጥ (1፡ 5) ጴጥሮስ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ለመጨመር ሁሉንም ጥረት አድርጉ ብሏል ፡፡ ኤፌ (4፡ 3) “ በሰላም ማሰሪይ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ “ ፡፡
ጳዉሎስ እንደ መንፈሳዊ አባት ሞደል የሆነበት ሁለተኛዉ ነገር ምልልሱ ነበር ፤ ጳዉሎስ መልዕክቱን ብቻ ሳይሆን ያጋራዉ በተናገረዉ መልዕክትም ኖሯል (ቁጥር 10) ፡፡ ተሰሎንቄያዊያን ጳዉሎስን በጊዜው ከፍተኛ ዉጥረት መነሳቱን እንዴት እንደሚመልስ በማየት ተመልክተዋል ፡፡ ሰዎስተኛው ጳዉሎስእንዴት በቃሉ መንፈሳዊ አባት በመሆን ነው ፡፡ ጳዉሎስ በኑሮአቸዉ ላይ የሚያጠነክራቸዉን እና የሚያበረታቸዉን ቃል ተናገረ ፤ ጳዉሎስ እንደ ራሱ ልጆች ለእግዚአብሄር ጥሪ እንደሚገባ እንደ አባት እንዲመላለሱ መከራቸው፣ አፅናናቸዉም እንዲሁም ኃላፊነት ጣለባቸው (ቁጥር 11-12) ፡፡ በታላቁ ተልዕኮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አለም በመሄድ ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ እና ያዘዘዉን ሁሉ እንዲጠብቁ እንዲያስተምሩአቸዉ ነገራቸው (ማቴ 28፡ 19-20) ፡፡
1-ተሰሎንቄ (2፡ 13-20)፡ ጳዉሎስ በሚገባ/በተገቢዉ የእግዚአብሄርን ቃል በመቀበላቸው አመስግኗል (ቁጥር 13) ፤ “ በሚገባ “ የሚለዉ ቃልበስራ፣ በኃይል እና በአቅም የሚለዉን ይወክላል ፡፡ በቁጥር (14-16) ይቺ ቤተ ክርስቲያን በዚያን ጊዜ በመከራ ዉስጥ አልፋለች ፡፡ ጳዉሎስ ወደፊት እንዲቀጥሉ በማፅናናት አበረታቸው ፡፡ ምናልባትም ተመሳሳይ ነገር ገጥሟችኋል ፤ በጌታ እያደጋችሁ እንደሆነ ይሰማችኋል ነገር ግን ሁሉም ያልታሰበ ነገር ጭንቀትን መጋፈጥ እየጀመራችሁ ነው ፡፡ ምናልባትም የራሳችሁ ቤተሰቦች ወደ ጎን እየገፏችሁ ይሆናል ምክንያቱም በእምነት መመላለስ ስለጀመራችሁ እና በጌታ እያደጋችሁ ስለሆነ ፡፡ የጳዉሎስ መልዕክት ለእናንተ፡ በእምነት መመላለሳችሁን ቀጥሉ ማደጋችሁንም ቀጥሉ የሚል ነው ፡፡ የአንድ የአካባቢ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ዋጋ በሚያስቸግር ጊዜ በአንድ ላይ መቆም እና አንዱ ሌላዉን ማበረታታት ነው ፡፡ ዋይርስቤ እንዳለው፡ “ ብቸኛ ቅዱሳን በኃይለኛው ለሰይጣን ጥቃት የተጋለጡ ናቸው ፤ በህይወት ዉጊያ ዉስጥ እርስ በእርስ እናስፈልጋለን “ ፡፡ በ 2ቆሮ (4፡ 16-18) ጳዉሎስ አማኞችን በዘላለም ላይ እንዲያተኩሩ እንጂ ልባቸዉን እንዳያጡ ያበረታታቸዋል ፡፡
በቁጥር (19-20) ጳዉሎስ ተሰሎንቄዋዊያንን ክብሩ እና ደስታዉ እንደ ነበሩ ነገራቸው ፤ የጳዉሎስ ደስታ እነርሱን በክርስቶስ መገኘት ዉስጥ በማየት በእርሱ መሄዳቸዉን ቀጥለዉ በማየት ይመጣል ፡፡ ጉዞአቸዉን እንዲቀጥሉ አበረታታቸው ምክንያቱም ኢየሱስ ተመልሶ ስለሚመጣ እና ሁሉም የሚገባ ስለሆነ ፡፡
መደምደሚያ
ጳዉሎስ ደቀ መዝሙርነትን እንደ አንድ የእምነት ባላደራ፣ እንደ አንድ የምትወድድ እናት እና እንደ አንድ የሚያስብ/የሚጨነቅ አባት ሞደል ሆኗል ፡፡ ጳዉሎስ ደቀ መዝሙርነትን በስራዉ፣ በምልልሱ እና በቃሉ ምሳሌ ሆኗል ፡፡ ዋይርስቤ ጳዉሎስ “ በኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸዉን መንፈሳዊ ምንጮቻቸዉን አስቀምጠዉ እንዲይዙ አበረታቸው ፤ በዉስጣችሁ የእግዚአብሄር ቃል አላችሁ፣ በዙሪያችሁ የእግዚአብሄር ሰዎች እና ከፊታችሁ ደግሞ የእግዚአብሄር ክብር አላችሁ ፤ ተስፋ መቁረጥ አይሰፈልግም “ አለ ፡፡ ጴጥሮስም አማኞችን ስለ ወንጌል መከራ በሚደርስባቸው ጊዜ በክብሩ መገለጥ እንዲደሰቱ እንጂ እንዳይሸበሩ/አዲስ እንዳይሆንባቸው አበረታታቸው (1ጴጥ 4፡ 12-14) ፡፡ ዛሬም ጌታ እያበረታን ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቀላል አይደለም ነገር ግን ከሚመጣዉ ከኢየሱስ ክርስቶስ ሽልማት አለው !
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ephesians (Colorado Springs: David C. Cook, 1989), p. 708.
Wiersbe, p. 709.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 1574.
Wiersbe, p. 709.
Wiersbe, p. 709.
Wiersbe, p. 709.
Wiersbe, p. 710.
Wiersbe, p. 710.
Wiersbe, p. 713.
Wiersbe, p. 713.
ጥያቄዎች
-
የጳዉሎስ ተሰሎንቄን ጉብኝት ለምን ለከንቱነት እንዳልነበር ግለፅ ፤ (1ተሰ 1፡ 5-8)
-
ጳዉሎስ ወንጌልን ወደ ተሰሎንቄ ለምን አመጣው ? የጳዉሎስ ክርክር በምን የእርሱ አላማ አልነበረም ? ወንጌልን የመናገር/የማጋራት አንድ መልካም ባላደራ መሆን የሚጠበቅባቸዉ ለምንድን ነው ? (ሉቃ 16፡ 1-2, 1ቆሮ 4፡ 1-2)
-
ጳዉሎስ ተሰሎንቂያዊያንን በወንጌል ለማሳመን የማታለያ ቃል እንዳልተጠቀመ ለማሳየት ይህን አደረገ ፤ የሽንገላ ንግግር ለምን መጥፎ አቀራረብ ይሆናል ? (መዝ 12፡ 2, 36፡ 2, 78፡ 36, ማር 7፡ 6)
-
ጳዉሎስ በትምህርቱ በመጨረሻ ማስደሰት የሚፈልገዉ ማንን ነበር ? ከእግዚአብሄር ይልቅ ሰዉን ማስደሰት የመፈለግ ዝንባሌ አላችሁ ? በዚህ ስፍራ ላይ ከጳዉሎስ እንዴት ልትማሩ ትችላላችሁ ?
-
በ 1ተሰ (2፡ 10-11) ጳዉሎስ አገልግሎቱን ለመግለፅ ምን ማሳያ ተጠቀመ ? ያን ጥቅስ ከ 1 ተሰ (2፡ 7) ጋር አወዳድሩ
-
በ 1ተሰሎንቄ 2 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Thessalonians 2:3–4
“For our exhortation didn’t come from error or impurity or an intent to deceive. Instead, just as we have been approved by God to be entrusted with the gospel, so we speak, not to please men, but rather God, who examines our hearts.”
ልክ ጳውሎስን ለሌሎች ወንጌልን እንድናገር እንደመራው ሁሉ ጌታ እናንተንም ለሌሎች እንድትናገሩ ይመራችኋል ፡፡ እናም ለመናገር ስትሄዱ ለጌታ በመታዘዝ መራመድ እንዳለባችሁ እንዳትዘነጉ ፡፡ ሌሎችን ደስ ለማሰኘት አታስቡ ፡፡ ሌሎችም ስለእናንተ ሊያስቡ ስለሚችሉት ነገር አትጨነቁ ፡፡ ይልቁንም የጌታን ድምጽ ስሙ ፡፡ እርሱ እውነትን እንድትናገሩ ከቀሰቀሳችሁ ፤ በፍቅሩ ሌሎችን እንድትወዱ ፤ በተለየ መንገድ የእርሱ አገልጋዮች እንድትሆኑ ካሳሰባችሁ በቃ ያንን ድምጽ ታዘዙ ፡፡ ሌሎችን ሳይሆን ጌታን ፍሩ ፡፡
ብዙ ጊዜ የሆነ ነገርን ለመናገር ለመስራት ትነሳሱና ነገር ግን ወዲያውኑ በአሳባችሁ “ እንዲህ ቢሆንስ “ አረ “ እኔጃ “ የሚል ድምጽ ይመጣና ያሰንፋችኋል ፡፡ ጽና ደግሞም ሁልጊዜ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር የሚስማማውን የጌታን ድምጽ ስማ ፡፡ በንጹህ ልቦና በመታዘዝ ተራመድ ከዚያም ጌታን ታየዋለህ ፡፡ እግዚአብሔር ልታስበው ከምትችለው በላይ በአንተና በሌሎች ህይወት ውስጥ መስራት ይፈልጋል ! ሌሎች ለእግዚአብሔር ድምጽ በመታዘዝ ይመላለሱ ዘንድ በደንብ አድርጎ የሚጨነቅ ልብ ይኑራችሁ !
“ ልመናችን ከስሕተት ወይም ከርኵሰት ወይም ከተንኰል አልነበረምና ፤ ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን ፥ እንዲሁ እንናገራለን ፥ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም ። “
- 1ኛ ተሰሎንቄ 2፡3-4
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 29:25 – “ ሰውን መፍራት ወጥመድ ያመጣል ፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን እርሱ ይጠበቃል ። “
ኢሳይያስ 30:21 – “ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ ። “
1ኛ ተሰሎንቄ 2:8, 11–12 – “ እንዲሁም እያፈቀርናችሁ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለማካፈል ብቻ ሳይሆን የገዛ ነፍሳችንን ደግሞ እናካፍላችሁ ዘንድ በጎ ፈቃዳችን ነበረ፥ ለእኛ የተወደዳችሁ ሆናችሁ ነበርና……… ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እየመከርንና እያጸናን እየመሰከርንላችሁም ፥ አባት ለልጆቹ እንደሚሆን ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን ታውቃላችሁና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።